“ጉልቻ ቢለውጥ ወጥ አያጣፍጥም” የኢትዮጵያን ሪቪው ወቅታዊ ርዕሰ አንቀጽ
በኢትዮጵያ ላይ እንደ አልቅት ተጣብቆ የህዝቡን ደም እየመጠጠ፣ እየገደለ፣ እያሰቃየና የፈለገውን እያደረገ ለሃያ አንድ ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ቅጥረኛው፣ ጎሰኛው፣ አምባገነኑና ዘራፊው የህወሃት አገዘዝ ቁንጮ መለስ ዜናዊ በስልጣን ላይ ቢቆይም ወይም በትረ ስልጣኑን ለሌላ ወያኔ ቢያስተላልፈው፣ አጠቃላዩ የአፈናውና የግፈኛው ሥርዓት ተገርስሶ እስካልወደቀ ደረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያመጣው አንዳችም ለውጥ አይኖርም። ሕወሃቶች ከደደቢት በረሃ ተማምለው የመጡበትን ታላቁንና ለብዙ ዘመናት የኖረውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነቷንና አገራዊ አንድነቷን የማፈራረስና የማዳከም የጥፋት ዓላማቸውን ከሥልጣን እስካልተነቀሉ ድረስ እንደሚቀጥሉበት በሥልጣን ኮርቻ ላይ ከተፈናጠጡበት ጊዜ አንስቶ እየታየ ነው። “ከዝንጅሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ” እንደሚባለው መለስ ዜናዊ በሌላ ወያኔ ቢተካ ለኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያመጣው ምንም ዓይነት ለውጥ አይኖርም።
የህወሃት ቡድን ከመነሻው አንስቶ እስከአሁን ድረስ ከአርባ ዓመታት በላይ የሰራበትን ወደፊትም ለመቀጠል በዕቅድ ይዞ የሚንቀሳቀስበትን መሠረታዊ የኢትዮጵያን ብሔራዊና አገራዊ አንድነት የማፈራረስና የማላላት እኩይ ዓላማ ኢትዮጵያዊያን እስካላስቆሙት ድረስ እንደሚቀጥልበት ምንም ዓይነት ብዥታ ሊኖር አይገባም። አንዳንድ የዋሆች የእባቡን የወያኔን ባሕርይ ካለመረዳት እንደሚሉት “መለስ በሌላ ወያኔ ቢተካ የተሻለ ጊዜ ሊመጣ ይችላል” ብለው ሲናገሩ ይደመጣሉ። የወያኔ ድርጅት እንደ ድርጅት አምባገነን፣ ጸረ-ዲምክራሲ፣ አፋኝ፣ ጎሰኛ፣የንጹሃን ደም አፍሳሽና ከሁሉም በላይ ጸረ ኢትዮጵያዊ ነው። ስለሆነም የወያኔን ድርጅት እንደ ድርጅትና ሥርዓት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጭንቃ ላይ አወርዶ በማፈራረስ በምትኩ ኢትዮጵያዊ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት መተካት እንጅ ወያኔዎችን አንዱን ወያኔ ከሌላው ወያኔ ጋር በማነጻጸር “እከሌ ከእከሌ” ይሻላል እያሉ ከእውነታው የተለየ ጉንጭ አልፋ ወሬ ማናፈስ፣ ወያኔዎችን መጥቀም እንጅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ምንም ማለት አይደለም።
በቅርቡ ወያኔመውደቂያው እንደተቃረበ ስላወቀ እንዳበደ ውሻ በመልከፍከፍ ከፍተኛ ትኩረቱን ያደረገው የሃይማኖት ተቋማትን ማጋየትና ማፈራረስ እንዲሁም ምዕመናንን ማበጣበጥ ላይ ነው። ታሪካዊዎቹን የአሰቦትና የዝቋላ ገዳማት ላይ እሳት በመለኮስ እንዲሁም ጥንታዊውንና ተደፍሮ የማያውቀውን የዋልድባ ገዳምን በመድፈር የመንኮሳትን መካነመቃብር በትራክተር በማረስና ቤተመቅደሶችን በማፈራረስ እኩይ ተገባር ላይ ተሰማርቶ ይገኛል። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያንን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ስር ለማስገባት ወያኔ እንደ ሸቀጥ ከውጭ ባስመጣው “አህባሽ” በሚባለው የተጭበረበር አስትምህሮት ሐይማታቸውን ለመበረዝና ለመከለስ እንዲሁም የሀገር ፍቅራቸውንና አንድነታቸውን ለማናጋት የሚያደርግባቸውን ደባ ለማክሸፍ ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የሕይወት መስዋዕትነት ጭምር እየከፈሉ ይገኛል። ወያኔ ይህ ብቻ ሳይበቃው ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የሃይማኖታቸውን አስተዳዳሪዎችን እራሳቸው በመስጊዶቻቸው መምረጥ ሲገባቸው ሰርጎ ገብ ካድሬዎችን በማሰማራት ሐይማኖታቸውን በሰላም እንዳያካሂዱ እንቅፋት በመፍጠር ላይ ይገኛል። ሆኖም ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በአንድ ቃልና ድምጽ በሙስሊምነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ወያኔ የሚያደርስባቸውን ግፍና በደል ተጋፍጠው በመመከት ላይ ይገኛሉ። ይህ ሙስሊሞች መብታቸውን ለማስከበር በሰላማዊና ህጋዊ ሁኔታ በማድረግ ላይ ያሉት እንቅስቃሴ ወያኔን በከፍተኛ ሁኔታ ፍርሃትና መርበትበት ውስጥ ጥሎታል። የሙስሊሞች ጥያቄ ወያኔን እንዲህ ሊያንዘፈዝፈውና ሊያወራጨው የቻለው ሙስሊሞች እንደ ሙስሊምነታቸውንና እንደ ኢትዮጵያዊነታቸው አንድ ሆነው በመነሳታቸውና የወያኔን የጎሳ አጥር ሰበረው በመውጣታቸው ነው። ሙስሊሞች እንደ ኢትዮጵያዊ ሆነው ጥያቄያቸውን በአንድነት ባያቅርቡና በተበታተነ ሁኔታ ቆመው ቢሆን ኖሮ ወያኔ “የኦሮሞ ሙሲሞች እንዲህ አሉ” ወይም “የአፋር ሙስሊሞች እንዲያ አሉ” ወይም የጉራጌ ሙስሊሞች ይህንን ጠየቁ ወዘተ” እያለ እንደለመደው ከፋፍሎ ለመግዛት በሚችልበት ህኔታ ሊያላግጥበትና ለራሱ መጠቀሚያ ሊያደርገው በቻለ ነበር። ሙስሊም ኢትዮጵያዊያን በዚህ ተጋድሏቸው የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድነትና በጎሳ አለመለያየት ለወያኔ ብቻ ላይሆን ለመላው ዓለምም አረጋገጠዋል።ይህም የትግል ሥልት ለወደፊቱ በተጠናከረና በተቀላጠፈ ሁኔታ ሊቀጠልበት የሚገባ በፍጥነት ውጤት የሚያመጣ የትግል ዘዴ ነው።
ኢትዮጵያውያኖች በሙሉ በአሁኑ ሰዓት ጎሳና ሃይማኖት ሳይለዩ ከወያኔ ጋር ከፍተኛ ትንንቅና ፍልሚያ የገቡበትና የሚደርሳባቸውን ጭቆናና የግፍ አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የህይወት መሰዋዕትነትን ጭምር እየከፈሉ የሚገኙበት ወሳኝ ወቅት ነው። ስለሆነም ኢትዮጵያዊያን ይህንን በኢትዮጵያዊነት የጀመሩትን አንድነት አጠናክረው በመቀጠል ይህንን የበሰበሰ አምባገነንና ፈላጭ ቆራጭ፤ ከላይ እስከ ታች ድረስ ድረስ በምዝበራ፣ በጉቦና በዝርፊያ የተጨማለቀ የባዕዳን ተላላኪ የወያኔን አገዛዝ አሽቀጥረው የሚጥሉበት ጊዜ ቅርብ እንጅ እሩቅ እንደማይሆን ሳይታለም የተፈታ ነው።

እግዚአብሔር ይባርክሀ:: ወያኔ ሙሉ በሙሉ መወገድ አለበት!!! አለበለዚያ በኢትዮጵያ የነገሰው ግፍና መከራ ሊቆም አይችልም::
ሞት ለወያኔ እና ቡችሎቹ!!
This is nonsense and very far from truth. EPRDF has displayed a quality world-class leadership in the country and will cotinue to lead the country with its wise, brilliant and smart leaders for many more years. You guys don’t know anything excpet insulting people like ‘Duriye’. Elias – Duriyew!!!
ምን ወጥ አያጣፍጥም ብቻ በተዳከመው ደደብ ወራሪው መንግስት አዲስ ደደብ ይቀየርና ወጡ ይጎመዝዛል በነገራችን እሚጣበቀው መዥገር ነው አልቅት ግን የውኅ ውስጥ ነፍሳት ሆኖ ከብቶች ይገድላል ነገር ግን ወያኔ ሁለቱም ነው
አሁንስ በቃን
21 ዓመታት ብዙ ነው የኢትዮጲያ ሕዝቦች ጭቆናው ብዝበዛው ውሸቱ ይብቃን ። በዘርና በጎጥ መከፋፈሉ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠሩ
በፍርሀትና በመሸማቀቅ መኖር ይብቃ ። ወያኔ የዘረኞችና የአምባገነኖች ጥርቅም ስለሆነች መለስ ዜናዊ ቢያልፍም ብዙም ለውጥ ይኖራል ብዬ
ተስፋ አላደርግም ሌላ አምባገነን ይተካል እንጂ ። ወያኔዎች ምንም ዐይነት ሞራል እይኖራቸውም ኢትዮጵያን ማስተዳደርም ሆነ ስለ ኢትዮጲያ ማውራት አይችሉም። ባብዛኛው ወያኔዎች በሙስና በሰብአዊ መብት ረገጣዎች መጠየቅ አለባቸው።
The Woyane’s worest fear is happening, i.e. the unity of all Ethiopians. Woyanes failed in their attemp to divide the people along ethnic lines. And now they failed to divide Ethiopian people along religious affiliation. Woyane will be be out of power very soon. Long live Ethiopia.
nakupenda Reply:
July 30th, 2012 at 8:02 am
dear denkoro Reta
things are much more complicated than you illiterate guys ever immagine. politics is not a tale, you should use your mind to see all aspects of a single term before you start stretching your stupid toungue. but the best thing is leave everything to the polititians and hear from them until you get experienced for it.
Can any one here tell us who has the heavenly power to lebel this Ethipian and the other anti-Ethiopia? If Woyane are not Ethiopians, where are they from? The mambo jambo article above talks about the longstanding Ethiopian history. Without the Woyane and without the people where they come from, what is Ethiopian history?
Where did the Ethiopian language, religion, culture, alphabet, kingdoms, etc come from? This kind of blind hate and opposition needs radical liberation!!!
Today’s so called Eritrea and today’s Tigray/Tigrans made most of Ethiopian history. But those with fascist views in Ethiopia pushed Ertireans to the limit and unlike their fathers who wanted to stay under a federal Ethiopia, the new generation Eritreans rather became victims of EPLF’s sessationist ageda!
Stil now we see the same fascist views reflected by some Ethiopians over woyane or Tigreans, but the time has changed. It is too late editors of Ethiopian Review!!!
You balme the Government in power for checking some non-sense journalists, and hope you will not sendor this. If you do, message gone and no damage!!!
A.. ha, you mederate what people write? good sensorship then!!!
Well articulated and timely framed editorial. Elias keep up the good work.
በትክክል ብሀል:: ሃገሪቱን ሽባ ያደረገ ገዥ ነው መለስ ዘንናዊ::
እኒ ምንም ችግር አይታይኝም:: ግን ስላም ለህዝቡ ያድርግልት ባይ ነኝ:: መለስን በስላም ያቆይልን ብቻ;; አሱ ኢትዮጵያ ታላቅ ልጅ ነው::
የኢትዮጵያ መከራ ሊያከትም እየተቃረበ ነው::ሁላችንም በትግሉ መቀላቀል አለብን: የመለስን መሞት አበበ ጀመረው የዋልድባ አምላክ እና የሁላችን አምላክ ገሀነም ወስዶታል ስለዚህ ሁላችንም ለትግል እንነሳ: የኢትዮጵያ ታላቅ ልጆች የሚመሩትን ታላቅ የፖለቲካ ድርጅቶችን እንቀላቀል እትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች ::