የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር ሁለተኛ ክብረ በዓል/ ፌስቲቫል በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር ሁለተኛ ክብረ በዓል/ፌስቲቫል  በደማቅ ሁኔታ ተጠናቀቀ

የኢትዮጵያ ውርስና ቅርስ ማሕበር ከጁላይ 27 እስከ ጁላይ 29, 2012 ድረስ በጆርጅ ታውን ዩኒቨርስቲ ውስጥ ሁለተኛውን ክብረ በዓል በደማቅና በተሳካ ሁኔታ አካሄዷል። በዚህ ዝግጅት ላይ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን የተሳተፉ ከመሆኑም በላይ በተላይ የልጆች ተሳትፎ እጅግ የጎላ ነበር። በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ ዝግጅቶች የቀረቡ ከመሆናቸው በላይ ከብዙ በጥቂቱ የእግር ኳስ ጨዋታ፣ የሩጫ ውድድር፣ የባህል ሙዚቃ፣የመጽሃፍ ምረቃ፣ ይገኙበታል።

የዘንድሮ የክብር እንግዳ ብጹዕ አቡነ መልክጻዲቅ ሲሆኑ አባታዊ የሆነ ምክራቸውንና አበረታች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በተለይም በመዝጊያው ዝግጅት ላይ ታዋቂውና ጀግናው ጋዜጠኛ አበበ ገላው ተገኝቶ ታዳሚውን በሙሉ ያነቃነቀ በአፈና አገዛዝ በመማቀቅ ላይ ለሚገኘው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነት እንደሚያስፈልገው ጥሪውን በድጋሚ አቅርቧል። ከዚህም በላይ ታዋቂና አገር ወዳድ ከሆኑት ድምጻዊያን መካከል ሻምበል በላይነህ፣ ጸሃዬ ዮሐንስና አብዱ ኪያር ተገኝተው የአገር ፍቅርና ብሔራዊ ኩራትን የሚያንጸባርቁ ታላቅ መልዕክት ያላቸውን ዘፈኖቻቸውን ተጫውተዋል። አርቲስት ታማኝ በየነም ተገኝቶ ቀስቃሽ መልዕክት አስተላልፏል። 

በዚህ ክብረ በዓል ላይ ኢትዮጵያዊያን እንደዚህ በነቂስ በመውጣት የአገርና የወገን ፍቅር እንጅ አላፊ ጠፊ ገንዘብ እንደማይገዛቸው ለወያኔ/አላሙዲ ተላላኪዎች አስፈላጊ መልዕክት አስተላልፈዋል። በዲሲው የአላሙዲ ፌስቲቫል ላይ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ የተረጨ ቢሆንም ዝግጅቱ  በተመልካች ድርቅ ተመቶ እንደነበርና ወያኔዎች ለአሳሳች ፖሮፓጋንዳ እንዲያመቻቸው እስቴዲዮሙ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ ሰዎችን ሰንደቅ አላማ አስይዘው፣ አለክፍያ አስገብተው ሲያስተናግዱና ሲያሽሞነሙኑ እንደነበር ይታወሳል። እዚህ ክብረ በዓል ላይ ግን በዋናነት የተገኙት ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ጥቂት ጥሪ የተደረገላቸው ኢትዮጵያዊ ያልሆኑ እንግዶችም ተገኝተዋል። “ብዙ ከመስማት አንዴ ማየት ይሻላል” እንደሚባለው እራሳቸው አስረጅ የሆኑትን ከዚህ በታች የተለጠፉትን ፎቶግራፎች ይመልከቱ።