በሳን ዲያጎና አካባቢዋ ለሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሁሉ!


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ወያኔ ኢትዮጵያ አገራችንን በጎሳና በሐይማኖት ከፋፍሎን ለ20 ዓመታት በጉልበት እየገዛ ነው። ለመብታቸው የሚታገሉ ኢትዮጵያውያን ወደ እሥር ቤት እየተወረወሩና ለሞትና ለስደትም እየተዳረጉ ይገኛሉ።

በየትም ዓለም ያልታየውን የኢኮኖሚ እድገት አሳይተናል፣ “14 በመቶ ኢኮኖሚያችን አድጋጓል” በማለት እየሸፈጠ 2.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በእራብ እያለቁ ናቸው። ወገኖቻችን ከቦታቸው እየተፈናቀሉ ለሙ የእርሻ መሬታቸው በኢንቨስትመንት ስም ለውጭ ዜጋ እየታደለ ይገኛል።

በቅርቡ በሰሜን አፍሪቃና በአረቡ ዓለም የተነሳው የነፃነት ሰደድ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይደርስና ለማዳፈንም “የኢትዮጵያ ሕዳሴ” በሚል ፕሮፓጋንዳና በ2010 ዓ/ም በተደረገው የይስሙላ ምርጫ 99.6% የውሸት አሽናፊነት፤ ኢትዮጵያን ለማስተዳደር መብት አግኝቻለሁ በማለት ዲያስፖራውንም በኢንቨስትመንት ስም ለመስበክና ድጋፍን ለማሰባሰብ የመለስ ዜናዊ ተላላኪዎች በ14 የአሜሪካና የካናዳ ከተማዎች እንደተሰማሩ ታውቋል። ስለዚህ በሎስ አንጄለስ ከተማ April 10, 2011 Los Angeles Convention Center ወያኔ ስብሰባ የጠራ ስለሆነ፡ በአንፃሩ ሎስ አንጄለስ ከሚገኙ የሕዝባችን ስቃይና መከራ የተሰማቸው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ጎን በመቆም ወያኔ የሚያራምደውን ዲክታተራዊ ሥርዓት ለመቃወም ሎስ አንጄለስ እድንገኝ ታላቅ ጥሪ እናቀርባለን።

ቀኑ፡ April 10, 2011
ቦታው፡ Los Angeles Convention Center
1201 South Figueroa Street
Los Angeles, CA 90015
ሰዓት፡ 1:00 P.M.