በምኒያፖሊስ-ሴንትፖል ከተማዎች ለምትኖሩ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያኖች በሙሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ኢትዮጵያውያን በሁሉም ቦታዎች በከፍተኛ ደረጃ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው። እኛም በምንያፖልስና- ሴንትፖል ከተማዎችና በአካባቢው የምንገኝ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ አገራዊ ስሜት ተነስተን ይህን ዓይን ያወጣ የወያኔ ዘመቻ ማጋለጥ አለብን። ለምን ብለን አንዴ ሕሊናችንን እንጠይቅ። ለናሙና ያህል ብንጠቅስ፤ አገራችን ን ኢትዮጵያ ዘረኛውና ፀረ-ኢ ትዮጵያ የሆናዉ ወያኔ በጎሳና በሃይማኖት በማከፋፈል፣ አሁንም ይህ አምባገነኑና ዘረኛው የወያኔ ገዢ ቡድን እንደተለመደው ሕሊናቸውን ሽጠው ለሆዳቸው ያደሩ ቱባ ቱባ ካድሬዎቹን አደራጅቶ በተለያዩ የሰሜን አሜሪካ ከተሞች በማሰማራት አገራችን በኢኮኖሚ አድጋለች፣ ንግድ ተስፋፍቷል፤ ሰላምና ዲሞከራሲ ሰፍኗል ብለው በሃሰት የተሞላ ዜናቸውን ሊሰብኩንና በውጭ አገር የምንገኘውን ኢትዮጵያውያን ለመከፋፈል ከምን ጊዜ በላይ ከፍተኛ ዘመቻ ለማካሄድ በመራወጥ ላይ ይገኛሉ። ይህን ፀረ-ኢትዮጵያ ዘመቻ ለማጋለጥ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ትዮጵያውያን በመንቀሰቀስ ላይ ናቸዉ።አገራችን ወያኔ አገዛዝ መዳፍ ሥር ከወደቀች ወዲህ፥

* በኢኮኖሚና ማሕበራዊ እድገት በዓለም ከሚገኙት ድሃ አገሮች የመጨረሻውን ደረጃ ይዛ ትገኛለች፤ እንዲሁም ወያኔ ከ400 ቢሊዮን በላይ ብር ከአባዳሪ ሀገሮች በኢትዮጵያ ስም ወስዶ ገንዘቡን በልቶ ትዉልዱ የእዳዉ ተሸካሚ እንድትሆን አድርጝል።

* ንጹሃን ወገኖቻችን በፀራራ ፀሐይ በአረመኔው የወያኔ አግአዚ ና በሌሎች ጦሮች በጎንደር፣ በጋምቤላ፣ በአዲስ አበባ፣ በአዋሳ፣ በሐረር፣ በአርሲ፣ በጅማ ፣ በሃድያ፣ ወዘተ…ተጨፍጭፈዋል፤ ህዝቡ መጠነ ሰፊ ስቃይ እንድቀበል አድርገዋል፤

* ፖለቲካዉን ለብቻው በመያዝ፣ ነፃ ሚዲያ በማጥፋት ፣ የሕግ የበላይነትን በማጥፋት፣ ኢትዮጵያን የሕዝቦችዋ እስር ቤት አድርገዋል፤

* በሺዎች የሚቆጠሩ የኢትዮጵያ ልጆች በወያኔ አስከፊና ድብቅ እስር ቤቶች ተወርውረው የምድር ሲኦል በማየት ላይ ይገኛሉ፤

* በመቶ ሺህዎች የሚሆኑት ወገኖቻችን በዘረኛው ወያኔ አገዛዝ ምክንያት ሰባዊ መብታቸው ተረግጦና ተገፎ የመኖር ዋስትናቸው አደጋ ላይ ስለወደቀ ከአገር ተሰደዋል፤

* ሴት እሀቶቻችን ወደ ዉጭ እንድሰደዱ በማድረግ ገንዘብ እየሰበሰበ እህቶቻችንን ለበርነትና ህይወታቸዉን እንድያጡ አድርጎል፤

* በሚሊዮን የሚቆጠሩት ወገኖቻችን ለከፍተኛ ርሃብ በተደጋጋሚ ተጋልጠው ይገኛሉ። በከተሞች የሚኖሩት በርካታ ወጣቶችና አዛውንቶች ደግሞ የሚበሉት አጥተው ቆሻሻ መጠያ ሜዳ ላይ የተጣለውን የምግብ ቤቶች ትርፍራፊ ከውሾች ጋር እየተሻሙ ይለቅማሉ፤

* በደቡብ ኢትዮጵያ በተለይም በጋምቤላ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የእርሻ ማሳቸውን በጎልበት እየተቀሙ ተወልደው ካደጉበትና እትብታቸው ከተቀበረበት ቀያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጭ አገር ከበርቴዎች በርካሽ ዋጋ ይቸበቸባል፤ የአገራችን መሬቶች ለእነዚሁ ከበርቴዎች እየተሸጡ ብርቅዬ ደኖቻችን እየተመነጠሩ አካባቢው ለከፍተኛ የተፈጥሮና አየር ማዛባት ተጋልጧል፤ ከሺያጭ ያገኛዉን ገንዘብ የወያኔ በለስልጣኖች ከኪሳቸዉ አስገተዋል፡፡

* ወጣቶች ትምህርታቸውን ጨርሰው ሥራ ሲፈልጉ የወያኔ አባል ካልሆናችሁ የሥራ እድል የላችሁም እየተባሉ በሺዎች የሚቆጠሩት ሥራ አጥተው የወላጅ ሸክም ሁነዋል፤ ክፍተኛ ትምህርት ለመማር የወያኔ አባል የግድ ሆኖል።

* በአሁኑ ውቅት በሺህ የሚቆጠሩ ሠራተኞች ከሥራ ገበታቸው ተባረዋል፤ መሠረታዊ የፍጆታ እቃዎች ዋጋ ከመጠን በላይ ንሯል፤ አንዳንዶቹ እቃዎች ከገቢያ ጠፍተዋል፤ አስከፊውን የኑሮ ውድነት ለመግለጽ ቃላት ያጥራል፤

ኢትዮጵያ በአንድነቷ ለዘላለም ትኑር!

በምኒያፖሊስ- ሴንትፖውል የሰልፍ አስተባበሪ ኮሚቴ

Date: April 10, 2011
Time: 1:00 PM
Place፡ Hilton Hotel at downtown MPLS, 1001 Marquette Avenue, South