ለጦር ወንጀለኛው ሮዶልፎ ግራዚያኒ ሃውልት መቆሙን የሚቃወም ታላቅ አለማቀፋዊ ትዕይንተ-ሕዝብ በዲሲ ተጠራ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


 ለጦር ወንጀለኛው ሮዶልፎ ግራዚያኒ ሃውልት መቆሙን የሚቃወም ታላቅ አለማቀፋዊ ትዕይንተ-ሕዝብ በዲሲ ተጠራ

እ.አ.አ. በ1930ዎቹ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንጹሃን ወገኖቻችን ላይ  አረመኔያዊ ጭፍጨፋ ለፈጸመው ሮዶልፎ ግራዚያኒ የመታሰሰቢያ ቤተመዘክርና የመናፈሻ ቦታ መሰየሙን የሚቃወም ዓለም ኣቀፍ ሰልፍ ተጠርቷል።

ግራዚያኒ በዓለም አቀፍ ስምምነት የተከለከሉና የተወገዙ የመርዝ ጋዝና ፈሳሽ በኢትዮጵያውያን ላይ ከአውሮፕላን ላይ በማዝነብ ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ላይ የጅምላ እልቂት ፈጽሟል። ግራዚያኒ ከዚህም በተጨማሪ ሊቢያ ውስጥም ከፍተኛ እልቂት እ.አ.አ. በ1920ዎችም ውስጥ ፈጽሟል። በዚህም መሠረት ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ ለፈጸማቸው የጦር ወንጀሎች 19 ዓመት እስር ተበይኖበት እንደነበር ይታወቃል።

ለዚህ ዓለም በአለም ዓቀፍ ደረጃ “አራጅ” በመባል ለሚጠራው የቢኒቶ ሙሶሊኒ የቀኝ እጅ በመሆን በጦር ሚኒስትርነት ተመድቦ እጅግ ዘግናኝና የሰው ልጅ ይፈጽማቸዋል ተብሎ ለመናገር የሚዘገንኑ ማሳቃያዎችን ለፈጸመው የጦር ወንጀለኛ  ለአዶልፎ ግራዚያኒ በደቡባዊ የሮም ከተማ በሚገኝ ቦታ በአገሪቱ ግብር ከፋዮች ወጭ መታሰቢያ ተሰርቶለታል። ይህም የሚያሳየው በአሁን ሰዓት ጣሊያንን በማስተዳደር ላይ ያለው መንግስት ለኢትዮጵያውናንና ለሊቢያውያን ያለውን ንቀትና ጥላቻ ነው። ለምሳሌ ያህል ጀርመን ውስጥ ለአዶልፍ ሂትለርና ለተካታዮቹ መዘክር መስራት ይቅርና ስለናዚዎች በበጎ ሁኔታ ማንሳት እንኳ በህግ የተከለከለና “ውግዝ ከማሪዎስ” የሆነ ተግባር ነው። ይህ ሊደረግ ቢሞከር እንኳ ምን ያህል ዓለማቀፋዊ ትኩረትና ውግዘት በተለይም ከይሁዳዊያን እንደሚያስከትል መገመት አያዳግትም። ለነገሩ ጀርመኖች እንኳን ይህንን ሊያደርጉና ሊያስቡት የሚችሉት ነገር እንኳን አይደለም። ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንደሚባለው ጣሊያኖች ይህንን እጅግ የሚያስቆጣ ወንጀል በኢትዮጵያዊያን ላይ የፈጸሙት ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው አገዛዝ ባንዳና ለአገሪቱ የማይቆረቆር መሆኑ ስለሚያውቁ ነው።

ይህ ዓለማቀፋዊ ሰልፍ የሚካሄደው እ.አ.አ. ማክሰኞ፣ ፌብሪዋሪ 19, 2013 ከጠዋቱ 10 ኤ.ም. ሲሆን ቦታው ዋሽንግተን ዲሲ 3000 Whitehaven Street, N.W. Washington D.C. 20008 በሚገኘው የኢጣሊያ ኢምባሲ ፊትለፊት ነው። ስለዚህ ስልፍ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 301-202-4579 ይደውሉ ወይንም በድረገጽ አድራሻ www.globalallianceforethiopia.org ይጎብኙ። ይህንን ታላቅ ዓለማቀፋዊ ትዕይንተ ህዝብ በተመለከተ የተዘጋጀውን እራሱ አስረጅ የሆነውን በራሪ ወረቀት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። ታላቅ አለማቀፋዊ ትዕይንተ ሕዝብ