በመቀሌ “ቤታችንን አናስፈርስም” ያሉ ሰልፎኞች ድብድባና አስራት ተፈጸመ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ባለፈው ጊዜ በመቀሌ ከተማ መንግስት ቤታቸው አንዲፈርስ በወሰኑ ምክንያት ሰልፍ ወጥተው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሰልፈኞቹ ከክልሉ ፕሬዳንት ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ለመነጋገር ተወካዮቻቸው እንዲመርጡ ተደርጎ ለጊዜው ሰልፉ እንዲበተን ተደርጎ ነበር፡፡

ከዚያ በኋላ የመንግስት አካላት ከህዝቡ ጋር ለመነጋገር ቀጠሮ ከተያዘ ኋላ ባልታወቀ ምክንያት በቀጠሮው ቀን ሳይገኙ ይቀራሉ፡፡ ትናንት ሚያዚያ 24 ግን ማስክ ባጠለቁና ከባባድ መሳሪያ የታጠቁ ፌደራል ፖሊሶች በመኪኖች ተጭነው በአከባቢው እንዲራገፉ ከተደረገ በኋላ በሚፈርሱ ቤቶች ላይ የቀለም ምልክት ማድረግ ይጀምራሉ፡፡ ህዝቡ ደግሞ ይህን አታደርጉም በማለት ሲቃወም፤ ህፃናት፣ ሴቶችና ሽማግሌዎች ላይ ሳይቀር በጣም የሚያስለቅስና የሚያቃጥል ጭሽ በመተኮስ ህዝቡን ለመበተን ሲሞክሩ አካበባው ወደ ዋይታና ግርግር አፍታም ሳይቆይ ተቀየረ፡፡

አስለቃሽ ጋዝ ከአሁን በፊት ህዝቡ Aይቶ ሰለማያውቅ የሚገድል መርዝ መስሎት ብዙ ሰው በድንጋጤ ባለበት ወድቀዋል፡፡ በሁኔታው ተደናግጠው ልጆቻቸውን ይዘው ከዘመዳቸው ቤት የተጠለሉ አንዲት እናት ስለዚህ ጉዳይ ሲናገሩ “እኛ አይጥ ነን ወይስ ምንድነን መርዝ የሚረጭቡን” በማለት በለቅሶ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ አስለቃሹ ጭስ መሆኑ ነው መርዝ የሚሉት፡፡

ይህ ግርግር ሙሉ ቀን ከዋለ ኋላ ህዝቡ ተደናግጦ በመበታተኑ ምክንያት ፌደራል ፖሊሶቹ ማታ አስራ ሁለት ሰዓት አከባቢውን ለቆ ይወጣል፡፡ ህዝቡ እንደገና ተመካክሮ እንደ አዲስ ተደራጅቶ በሌሊት ወደ መቀሌ መሀል ከተማ ገብቶ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አካባቢ አንድ ላይ ተሰባስቦ አደረ፡፡ ጧት ለአባይ ግድብ ድጋፍ ተብሎ ሰልፍ ተጠርቶ ስለነበረ የእነዚህን እንቅስቀሴ ልብ ሳይባል በመቀሌ እንምርት ላይ ሰልፎኞቹ መታየት ጀመሩ! በዚህ ጊዜ ፖሊሶች ሰልፎኛቹን የሚያነጋግራችሁ ሰው አለ በማለት አግባብተው ወደ አንድ ሰው ብዙ የማያልፍበት ቦታ ከወሰዷቸው በኋላ ፀሐይ ላይ ለሰዓታት ቁጭ አድርገው የስድብና የእርግማን መዓት አወረዱባጭው፡፡ ከኋላችሁ ማን እንዳለ እማናውቅ እንዳይመስላችሁ። ባለፈው በዓለም ዙሪያ የእናንተ ጉዳይ ሲያራግቡት የነበሩት አቃጣሪዎች ሁሉ የሚያድናችሁ እንዳይምስላችሁ። ከዚህ ኋላ ቀልድ የለም። ነገ ቤቶቹን መጥተን እናፈርሳለን። እስከዚያ ግን ንብረታችሁን አስወጡ” የሚል አጭር መልስ ነው የተሰጠው፡፡ በዚህ ጊዜ ህዝቡ መጮህና ማልቀስ ሲጀምር በዱላ እየመቱ ዋና ዋና ያሏቸውን አፍሰው ወስዷል፡፡

በተጨማሪም በትናንትናው እለት የአካባቢው ምልሻዎች ከህዝቡ ጋር ስላደሙ ትጥቃቸውን እንዲፈቱ ሲደረጉ፤ ሰልፉ ያስተባብራሉ ያሏቸውን ሁሉ እንዲታሰሩ አድርገዋል፡፡

በባለፈው ሰልፍ ጊዜ ከፊት ሆኖ የኢትዮጵያ ሰንድቅ ዓላማ ይዞ ሲመራ የነበረው አንዶም አራያ የተባለው ወጣትም በትናንትናው እለት ከፍተኛ ድብደባ የደረሰበት ሲሆን በፖሊስ ተይዞ ወደ አልታወቀ ቦታ ተወሰዷል፡፡