Posts Tagged ‘addis ababa’

Not Breaking News: Abune Mathias Has won

Thursday, February 28th, 2013

የ6ኛ ፓትርያርክ ምርጫው ወደ መጠናቀቁ ነው

Thursday, February 28th, 2013

  •     ደጀ ሰላም እያካሄደች ባለችው “የድረገጽ” ድምጽ አሰጣጥ አቡነ ማቴዎስ ቅድሚያውን ይዘዋል፤
(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 21/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 28/2013/ PDF)፦ አምስቱን እጩ ፓትርያርኮች ያካተተው የ6ኛው ፓትርያርክ መርጫ ይህንን ዜና በሠራንበት ወቅት እየተካሄደ ሲሆን ከመራጮች አብዛኛዎቹ ድምጻቸውን ከኮሮጆው ውስጥ እንደጨመሩና የቀረው የመራጭ ቁጥር ከ100 እንደማይበልጥ ታውቋል። የአኃት አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችን ጨምሮ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ በየደረጃው ድምጽ መስጠት የሚችሉት መራጮች ያለ ምንም ግርግርና ወከባ ድምጻቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ከዚህ አስቀድሞ ዛሬ ጠዋት በተደረገላቸው ገለጻ “ምርጫው ነጻ እና መራጮችም ያለ ምንም ችግር የራሳቸውን እጩ ብቻ እንዲመርጡ” ምክር ተለግሷቸዋል። በቀሩት ሰዓታት ቀሪ መራጮች ካርዳቸውን ከኮሮጆው ከጨመሩ በኋላ  አሸናፊውን መለየት ወደሚያስችለው ሥርዓት ይሸጋገራሉ።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ደጀ ሰላም በምታካሂደው “ኢ-ቀጥተኛ” የምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ከመረጡት መካከል ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በከፍተኛ ድምጽ በመምራት ላይ ሲሆኑ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ በሁለተኛነት ይከተላሉ። ዜናው በተጠናቀረበት ሰዓት ያለው ዝርዝር ይህንን ይመስላል።
1)     ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ፣   328 ድምጽ  (33%)
2)    ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ፣   185 ድምጽ (18%)
3)    ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣   160 ድምጽ  (16%)  
4)      ብፁዕ አቡነ ማትያስ፣ 159 ድምጽ  (16%)
5)      ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ፣ 81 ድምጽ (8%)

አንባብያን ድምጽ ሰመስጫው እስከሚዘጋበት ድረስ ድምጻቸውን በድረገጻችን መስጠት የሚችሉ ሲሆን የሁሉንም ጠቅልለን በመጨረሻ እናሳውቃለን።
         


ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

የሕወሐት ፍጥጫ ቀጥሏል « አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው » እነ ስብሃት « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን » እነ አባይና አዜብ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

Wednesday, February 27th, 2013

ሁለት ቦታ የተከፈለው የሕወሐት አመራር ልዩነቱን በማስፋት እየተወዛገበ መሆኑን ከመቀሌ ታማኝ ምንጮች ገለፁ። ስብሃት እና አዜብ የሚመሩት ሁለቱ ቡድን አነጋጋሪ አቋም ይዞ መውጣቱን ምንጮቹ ጠቁመዋል። በስብሃት ነጋ የሚመራው ቡድን ባስቀመጠው አቋም « መለስ ሕወሐትን ገድሎ ነው የሔደው! አሁን ያለው ሕወሐት ቆዳ ነው። ጥያቄው ግልፅ ነው፤ ሕወሐት መቀጠል አለበት.. ወይስ የለበትም?» ሲሉ በድርጅቱ ቀጣይ ሕልውና ላይ ጥያቄ አሳርፈዋል። ከዚህ በተቃራኒ የቆመውና አባይ ወልዱ፣ አዜብና ከጀርባ በረከት ስምኦን ያሉበት ቡድን በበኩሉ « የሕወሐት ወራሾች እኛ ነን፤» ሲል ለነስብሃት ምላሽ መስጠቱ ታውቋል። በተጨማሪ በሁለቱም ቡድኖች በልዩነት ነጥብ ተደርጎ የተወሰደው በ1993ዓ.ም ከፓርቲው የተባረሩት አመራሮች « ይመለሱ» ፣ « አይመለሱም» የሚለው እንደሚገኝበት ተጠቁሟል። የሁለቱም ጐራ ፖለቲካዊ ግብ አንዱ ሌላኛውን ገፍትሮ ከሜዳው ማስወጣትና ፓርቲውን ብሎም አገሪቱን በፈላጭ ቆራጭነት ለመቆጣጠር ያለመ እንደሆነ አንድ የፓርቲው ቅርብ ሰው ጠቁመዋል።

በፓርቲው በተለኮሰው ስር የሰደደ ፖለቲካዊ ፍጥጫ ካድሬው ለሁለት ተከፍሎ ሲነታረክ መሰንበቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በፓርቲው አባላት « አደገኛ» የተባለውን ይህን ፍጥጫ መሰረት በማድረግ በቴውድሮስ አድሃኖምና ብርሃነ ገ/ክርስቶስ የሚመራ ቡድን ራሱን « የአስታራቂ ሽማግሌዎች ቡድን» በሚል ሰይሞ ባለፉት ቀናት ሲነቀሳቀስ መቆየቱን ገልፀዋል። ሆኖም ሁለቱን ጎራዎች አቀራርቦ ለማነጋገርና ለማስማማት የተጀመረው ጥረት በሁለቱም በኩል በሚታየው አክራሪ አቋም ምክንያት ተስፋ ሰጪ ሁኔታ እንደማይታይ ምንጮቹ አስታውቀዋል። አሁንም ድርድሩ መቀጠሉን ምንጮቹ አልሸሸጉም።

የሕወሐት ሕልውና አጣብቂኝ ውስጥ በገባበት በአሁኑ ወቅት በሌላ ጐራ የተነሱ ወጣት የፓርቲው ካድሬዎች ባነሱት ጥያቄ ፥ ሁሉም አንጋፋ አመራሮች ከድርጅቱ እንዲለቁ ጥያቄ ማቅረባቸውንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆኑ ግን ሕወሐት ሊፈርስ እንደሚችል ማስጠንቀቂያ ጭምር መስጠታቸውን ምንጮቹ አያይዘው ገልፀዋል።

በተያያዘም « ጉባኤ ይጠራ» በሚል በካድሬዎች የቀረበውን ጥሪ እነ አባይ ወልዱና አዜብ ያሉበት ቡድን ውድቅ እንዳደረገው ታውቋል። አባይና አዜብ የሚመሩት እንዲሁም ትርፉ ኪዳነማሪያም፣ ሃድሽ ዘነበ፣ አለም ገ/ዋህድ፣ በየነ ምክሩ፣ ተክለወይኒ አሰፋና ሳሞራ የኑስ የተካተቱበት ቡድን በጉባኤው አሸናፊ ሆነው እንደማይወጡ ከወዲሁ በማመናቸውና በነስብሃት በኩል ከፍተኛ ሃይል እንደተደራጀባቸው ጠንቅቀው ስለተረዱ ነው ሲሉ የጠቆሙት ምንጮቹ አክለውም ሳሞራ በመከላከያ እጣ ፈንታቸው ተመሳሳይ መሆኑን በማመናቸው ከነአዜብ ጋር ተሰልፈው እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የበላይነትን እየያዘ ነው የሚባለውና በስብሃት የተደራጀው እንዲሁም በደብረፂዮን የሚመራው ቡድን አብዛኛውን የማ/ኮሚቴ አመራር በዙሪያው ያሰባሰበ ሲሆን ከነዚህም፥ አዲስአለም ባሌማ፣ አርከበ እቁባይ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ፈትለወርቅ፣ ፀጋዬ በርሄ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሃ/ኪሮስ ገሰሰ፣ ተ/ብርሃን…በዋንኛነት እንደሚገኙበት ምንጮቹ አመልክተዋል። የሽማግሌው ቡድን ስብስባ እንደቀጠለ ተጠቁሞዋል።

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 27, 2013

Wednesday, February 27th, 2013
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family

ንቅሳትና መዘዙ

Wednesday, February 27th, 2013
«የጥርሷ ንቅሳት ያንገቷ ሙስና ረቡዕ ያስገድፋል እንኳን ሐሙስና!» ቆንጆ ወጣት ፤ በመነቀስ ፣ በውበት ላይ ውበት ጨምራ ፣ እጅግ ታማልላለች እንደማለት ነው ፣ የእነዚህ ሁለት ስንኞች ፍሬ ሐሳብ!፤ የአንገት ፤ የእጅ ንቅሳት ፣የጥርስ፤ ውቅራትና

የቤኔዲክት 16ኛ ሥንብት

Wednesday, February 27th, 2013
ከሥምንት ዓመት በፊት የርዕሠ ሊቀነ-ጳጳሳትነቱን ሥልጣን የተረከቡት ቤኔዲክት አስራ-ስድሰተኛ ሥልጣናቸዉን በፈቃዳቸዉ መልቀቃቸዉን ባስታወቁት መሠረት ነገ-መንበራቸዉን በይፋ ይለቃሉ

የምርጫ ክርክር በኬንያ

Wednesday, February 27th, 2013
የፊታችን ሰኞ ኬንያ ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ታካሂዳለች። ለዚህ ዝግጅትም በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕሬዝደንታዊ እጩዎችን በምርጫ ክርክር ፊት ለፊት አሟግታለች። ከሁለት ሳምንታት በፊት የመጀመሪያዉ ዙር ሰኞ ምሽት ደግሞ የመጨረሻዉ እና ሁለተኛዉ ክርክር ተካሂዷል።

ኢጋድና የታሰበው የሽብርተኝነት መቋቋሚያ ማዕከል

Wednesday, February 27th, 2013
የምሥራቅ አፍሪቃ በይነ መንግሥታት የልማት ባለሥልጣን፤ ሽብርተኝነትን መቋቋም የሚቻልበት ማዕከል ለማቋቋም አቅድ ያለው መሆኑን የኢጋድ የሰላምና ፀጥታ ክፍል ዋና ኀላፊ ፤ ኮማንደር አበበ ሙሉነህ አስታውቁ። እስከ መጪው ዓመት ታኅሳስ ወር ማለቂያ ሊቋቋም

UTC 16:00 የአለም ዜና 270213

Wednesday, February 27th, 2013
የእለቱ ዜና

የዕዳ ምሕረት ትናንትና ዛሬ

Wednesday, February 27th, 2013
በገንዘብ ችግር ላይ ለወደቀ አገር የዕዳ ምሕረት ማድረጉ ከ80ኛዎቹ ዓመታት ወይም ከቅርቡ ዓለምአቀፍ የፊናንስ ቀውስ ወዲህ የተለመደ ነገር አይደለም።

የ5ቱ እጩ ፓትርያርኮች አጭር የሕይወት ታሪክ

Tuesday, February 26th, 2013

(MK Website/  PDF http://bit.ly/YwKqd1):-የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በዝግጅት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሠረት ቅዱስ ሲኖዶስ አስመራጭ ኮሚቴ በመሠየም እጩ ፓትርያርኮችን ለመምረጥ ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከካህናት፤ ከሰንበት ትምህርት ቤቶች፤ ከማኅበረ ቅዱሳን፤ እንዲሁም ከምእመናን ጥቆማ እንዲያካሔዱ ተደርጓል፡፡ በተካሔደው ጥቆማ መሠረት አስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማውን በግብአትነት በመጠቀም አምስት ሊቃነ ጳጳሳትን በእጩነት በማቅረብ የካቲት 16 ቀን 2005 ዓ.ም. ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ አቅርቧል፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤም ከየካቲት 16 – 18 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ውይይት በማካሔድ አምስቱም ሊቃነ ጳጳሳት በእጩነት እንዲቀርቡ አጽድቋል፡፡


የካቲት 21 ቀን 2005 ዓ.ም. ለሚካሔደው የ6ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የፓትርያርክ ምርጫ የቀረቡት ብፁዐን ሊቃነ ጳጳሳት፡-  ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዪጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት ሊቀ ጳጳስ፤ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ  የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የምዕራብና የደቡብ አዲስ አበባ፤ የከፋ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡ በዚህም መሠረት አጭር የሕይወት ታሪካቸውን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡:

ብፁዕ አቡነ ማትያስ


የቀድሞው የአባ ተክለማርያም ዐሥራት የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በ1934 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ቅዳሴ፣ ዜማ፣ ቅኔ፣ ባሕረ ሐሳብ፣ የመጻሕፍተ ሐዲሳት ትርጓሜ ተምረዋል፡፡ በ1948 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ማርቆስ ዲቁናን ጮኸ ገዳም ተቀብለዋል፡፡ ከመ/ር ዐሥራተ ጽዮን ኰኲሐ ሃይማኖት መአረገ ምንኩስናን አግኝተዋል፡፡ በ1955 ዓ.ም በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ መአረገ ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡

በጮኸ ገዳም በቄሰ ገበዝነት፣ በመጋቢነት በልዩ ልዩ ገዳማዊ ሥራ አገልግለዋል፡፡ በገዳሙ ውስጥ በነበራቸው ቆይታ ሐዲስ ኪዳንን አስተምረዋል፡፡ ከ1964 -- 68 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በቅዳሴና በልዩ ልዩ አገልግሎቶች ተመድበው አገልግለዋል፡፡ ከ1968 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ዓመታት የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አቡነ ቀሲስና ምክትል ልዩ ጸሐፊ በመሆን ሠርተዋል፡፡ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ኤጲስ ቆጶስ ሆነው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ገዳም ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ

 የቀድሞው አባ ኅሩይ ወልደ ሰንበት የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ በ1930 ዓ.ም ተወለዱ ጸዋትዎ ዜማ፣ ቅኔ፣ ትርጓሜ መጻሕፍት፣ ፍትሐ ነገሥት፣ ባሕረ ሐሳብና ሐዲስ ኪዳንን ተምረዋል፡፡ በ1945 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ዲቁና በ1964 ዓ.ም ምንኩስናን በደብረ ሊባኖስ ገዳም ተቀብለዋል፡፡ በ1965 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሚካኤል ቅስና በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ሰላማ ቁምስናን ተቀብለዋል፡፡ በደብረ ጽጌ ገዳም በመዘምርነትና በቅዳሴ አገልግለዋል፡፡ ጥር 13 ቀን 1971 ዓ.ም  በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ የከፋ ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የሰሜን ጎንደር  ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
ነሐሴ  16  ቀን  1944  ዓ.ም  በሰሜን  ሸዋ  ክፍለ  ሀገር  በሸኖ አውራጃ  ልዩ  ስሙ  ጨቴ  ጊዮርጊስ  በተባለው  ቦታ ተወለዱ፡፡ የቀድሞ ስማቸው  ቆሞስ  አባ ኀይለጊዮርጊስ ኀይለ ሚካኤል ይባላል፡፡ ፊደል የቆጠሩት ዜማን የተማሩት ቅኔን የተቀኙት በሀፋፍ ማርያም በኢቲሳ ደብረ ጽላልሽ ገዳም ነው፡፡ ቅዳሴን በዳግማዊ ምኒሊክ መታሰቢያ የቀሳውስት ማሠልጠኛ ት/ቤት ተምረዋል፡፡ በሰዋሰወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ት/ቤት ለ4 ዓመታት ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀው ዘመናዊ ት/ርታቸውን እስከ 12ኛ ክፍል በማጠናቀቅ በምዕራብ ጀርመን እሸት ኬርከሌ መንፈሳዊ ት/ቤት ስለ ገዳማት አስተዳዳር አጥንተዋል፡፡ ሐምሌ 5 ቀን 1991 ዓ.ም. በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የምዕራብ ሐረርጌ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት የባሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡
ምንጭ፡- ዜና ቤተ ክርስቲያን 31ኛ የዓመት ቁ.3፣ ጥር 4 ቀን 1971 32ኛ ዓ.ም ቁ.4


ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል


የቀድሞ ስማቸው መልአከ ምሕረት አባ ሀብተ ማርያም ይባላል፡፡ ግንቦት 7 ቀን 1946 ዓ.ም በደቡብ ወሎ አማራ  ሳይንት ልዩ ስሙ ደብረ ብርሃን ለንጓጥ ሥላሴ ተወለዱ፡፡ አባታቸው ግራ ጌታ መኮንን ኀይሉ እናታቸው ወ/ሮ አታላይ ደርሰህ ይባላል፡፡ ዜማ፣ አቋቋም፣ ቅኔ፣ ፍትሐ ነገሥት ትርጓሜ ተምረዋል፤ የቅኔ መንገድ ከነአገባቡ ተምረው በመምህርነት ተመርቀዋል በ1956 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ ገብርኤል ዲቁና ተቀብለዋል፡፡

ጳጉሜን 3 ቀን 1981 ዓ.ም በደብረ ሊባኖስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስና ፈጽመዋል፡፡ ኅዳር 12 ቅን 1982 ዓ.ም የቅስና ማዕረግ ከብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፤ ከብፁዕ አቡነ ቄርሎስ መዓርገ ቁምስና ተቀብለዋል፡፡  ከ1982 – 87 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በደብረ ሰላም ቅዱስ እስጢፋኖስ በጽርሐ ጽዮን ጎላ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የመጽሐፍ መምህር ሆነው አገልግለዋል፡፡ ከሠኔ 20 ቀን 1987-1990 ዓ.ም በምሥራቅ ሐረርጌ ሐደሬ ጤቆ መካነ ሥላሴ ደብር፣

ከየካቲት 1990-93 ዓ.ም የድሬዳዋ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን፣ ከሠኔ 1 ቀን 1993 ዓ.ም - ሐምሌ 1 ቀን 1994 ዓ.ም ጀምሮ ለጵጵስና መአርግ እስከ በቁበት ዘመን በአዲስ አበባ ቦሌ ደብረ ምጽላል እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን አገልግለዋል፡፡ ከሐምሌ 1 ቀን 1994 ዓ.ም የሰሜን ወሎ ደብረ ሮሐ ቅዱስ ላሊበላ ገዳም አስተዳዳሪ ሆነው አገልግለዋል፡፡ ነሐሴ 22 ቀን 1997 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የከፋ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ተብለው ተሹመዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የምዕራብና ደቡብ አዲስ አበባ ፤ የከፋ ሸካ ቤንች ማጂ አህጉረ ስብከት  ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ
በ1955 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ልዩ ስሙ ምንታምር ቀበሌ ከአቶ ጌታነህ የኋላሸትና ከወ/ሮ አምሳለ ወርቅ
ማሞ ተወለዱ፡፡


አቋቋም፣ ቅኔ ከነአገባቡ ቅዳሴ ኪዳን አንድምታ፣ ዜማ፣ ሠለስት፣ አርያም፣ ጾመ ድጓ፣ ቁም ዜማ ተምረዋል፡፡ በ1969 ዓ.ም ከብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ዲቁና ተቀብለው ቅስና ከብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ተቀብለዋል፡፡ በ1975 ዓ.ም በደብረ ዝቋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ሥርዓተ ምንኩስና ፈጽመዋል፡፡ በሰዋሰው ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ትምህርት ቤት ለ4 ዓመታት ያህል ተምረው በዲፕሎማ ተመርቀዋል፡፡ በሆላንድ ሆህ እስኩለ የቲዎሎዲ ትምህርት ቤት ገብተው ለ4 ዓመታት ተምረው በቲኦሎጂ የመጀመሪያ ዲግሪ ተቀብለዋል፡፡

በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በሰበካ ጉባኤ አደራጅነት፣ በሰ/ት ቤት ሓላፊነት፣ አ/አ ሀገረ ስብከት ሸሮ ሜዳ መንበረ ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በሰባኪነት፣ በሐረር ደብረ ገነት መድኀኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በአ/አ ሀገረ ስብከት በአቃቂ መድኀኔዓለም በአስተዳዳሪነት በቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል በሳሎ ደብረ ፀሐይ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በመካነ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ ደብርና በሐረር ደብረ ገነት መድኀኔዓለም አብያተ ክርስቲያናት በአስሪተዳዳሪነት አገልግለዋል፡፡ በውጭ ሀገር በአሜሪካ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል በአውሮፓ ሲውዘርላንድ በጀኔሻ፣ በሎዛን፣ በዙሪክና በበርንባዝል ከተሞች ባሉ አድባራት በቀዳሽነትና በሰባኪነት አገልግለዋል፡፡

ነሐሌ 22 ቀን 1997 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የዋግ ሕምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው ተሾሙ፡፡ በአሁኑ ሰዓት የየወላይታና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው፡፡

በዲ/ን ኅሩይ ባየ
http://www.eotcmk.org/site/index.php/-mainmenu-24/--mainmenu-26/1217-5

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 26, 2013

Tuesday, February 26th, 2013
News, Ask the Doctor, Agriculture and Business

የኬሪና የጀርመን ባለሥልጣናት ዉይይት

Tuesday, February 26th, 2013
ኬሪ እዚያዉ በርሊን ዉስጥ ከሩሲያዉ አቻቸዉ ከሰርጌይ ላቫሮቭ ጋርም በተለይ የሶሪያዉን ጦርነት አስተዉ ተነጋግረዋል።ከአሜሪካዊ ዲፕሎማት የሚወለዱት ጆን ኬሪ በ1950ዎቹ የልጅነት ጊዚያቸዉን በርሊን ነዉ ያሳለፉት።የያኔ ትዝታቸዉን ዛሬ ለበርሊን ወጣቶች ተርከዉላቸዋል።

ሶማሊያ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወታደሮች

Tuesday, February 26th, 2013
ባለፉት ጥቂት ወራት ከሶማሊያ ከደርሱን አጫጭር የስልክ መልዕክቶች መካከል አብዛኞቹ ፣ በሶማሊያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል መች ወደ ሀገር እንደሚመለስ የሚጠይቁ ሲሆኑ፣ ወታደሮቹ ላይ ደረሰ ስለተባለ እሮሮም ያወሳሉ።

የአንጎላ የነዳጅ ዘይት ሃብት

Tuesday, February 26th, 2013
በአንጎላ ሰሜናዊ የባህር ዳርቻ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ክምችት ይገኛል። አንጎላ የነዳጅ ዘይት ክምችትዋን ለመጀመርያ ግዜ ያገኘችዉ በ1960ዎቹ ዓመታት መጨረሻ ላይ ነዉ። ከጎርጎረሳዉያኑ 1975 እስከ 2002 ዓ,ም ድረስ በአንጎላ የነበረዉ የእርስ በርስ ጦርነት ካበቃ በኋላ ሀገሪቱ ያላትን የነዳጅ ዘይት ለማዉጣት የተሻለ ዘዴ ተፈጠረላት።

ኢትዮ-ጀርመናዊዉ የአቶም ሳይንቲስት

Tuesday, February 26th, 2013
ፈረንሳይና ብሪታኒያን የመሳሰሉ ሃገሮች ግን የአቶም ኃይል ጣቢያዎቻቸውን የመዝጋትም ሆነ የመቀነሰ ሃሳብ የላቸውም ። አንዳንድ የአፍሪቃ ሃገሮች ደግሞ የአቶም ቴክኖሎጂን የመጠቀም ፍላጎት እያሳዩ ነው ። ዶክተር ጌድዮን ግን የአቶም ቴክኖሎጂን መጠቀምን ለአፍሪቃ አገራት አይመክሩም ።

የፓትሪያርክ ምርጫ ዝግጅት

Tuesday, February 26th, 2013
የፊታችን ሐሙስ ለሚካሄደዉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ምርጫ በእጩነት የቀረቡት አምስት ሊቃነጳጳሳት ማንነት ትናንት ይፋ ሆኗል።

የሳዑዲ አረቢያ ምህረት

Tuesday, February 26th, 2013
ያለመኖሪያ እና ስራ ፈቃድ ሳዉዲ የሚገኙ ወገኖች ያለምንም ቅጣትና እስራት ወደሀገራቸዉ እንዲመለሱ መወሰኑን የጄዳዉ ወኪላችን በላከዉ ዘገባ ጠቅሷል።

ዜና 250213 16:00 UTC

Tuesday, February 26th, 2013

ሞት ለአስራ አንደኛው ቃል!!! በታሪኩ አባዳማ

Tuesday, February 26th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሽክሙ ለሃምሳ ሰው ግን ጌጡ ነው በሙኒክ የአንድነት ደጋፊ ማህበር

Monday, February 25th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት ከተስፋዬ ዘነበ (ኖርዌይ በርገን)

Monday, February 25th, 2013

የዘረኛው የህውሃት ስርዓት በነፃ አውጪ ስም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ እንዲሁም ከዛም በፊት የሚከተለው የተሳሳተ ሃገር መገነጣጠሉንና ቤሄራዊ ጥቅምን አሳልፎ መስጠቱን መመልከት የተለመደና የቀን ከሌት ክንውናቸው መሆኑ በሃይል ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ የሚታይ እውነታ ነው፡፡

ከምስረታው ጀምሮ ይዞት የተነሳው የኢትዮጲያን ሉዋላዊነት የማፍረስና የመበተን አላማውን መተግበር የጀመረው የሻቢያ አሽከር በመሆን ለሃገር አንድነትና ክብር ዘብ የቆመውን የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊት በመውጋት ሃገራችን ያለ ባህር በር እንድትቀርና በኢትዮጲያዊነት የታነፀውን ዘመናዊ የወታደር ሃይል በትኖ በምትኩ የአንድ ብሄር የበላይነት የሚታይበት፣ ቤሄራዊ ስሜት የሌለው፣ በአለቆቹ ከመታዘዝ ውጪ የወታደራዊ ሳይንስ እውቀት ያልዘለቀው ጀሌዎቻቸውን በህዝብ ላይ አንግሰው ያሻቸውን ሲገሉ፣ የሻቸውን ሲያስሩ እንሆ አሁን ያለንበት ደርሰናል፡፡
በመሰረቱ ይህ እኩይ ስርዓት(ቡድን) በኢትዮጲያዊነት ላይ ካለው የመረረ ጥላቻ የተነሳ አብረው የመሰረቱትን ግን በኢትዮጲያዊነት ላይ ፅኑ አቋም የነበራቸውን ባልንጀሮቻቸውን ሳይቀር እያስወገዱና እያባረሩ በምግባር የሚመቻቸውን በተለይ በህዝብና በሃገር ላይ የጠለቀ ጥላቻ ያላቸውን አስከትለው የጥፋት ዘመናቸውን ቀጥለውበታል፡፡

በተለይ የመንግስት ስልጣን ከያዙ በሗላ ከስልጣን በተጨማሪ በገቢ እራሳቸውን ለማጠናከር ከኢትዮጲያ ህዝብ በዘረፉት ሃብትና ንብረት በትግራይ ህዝብ ስም ባቋቋሙት ኢፈርት ሃገሪቱን ጫፍ እስከ ጫፍ በመቆጣጠር የንግዱን መስክ በበላይነት በመያዝ ገቢና ወጪው የማይታወቅ ትልቅ የሃብት ምንጭ በመፍጠር የአገሪቱን የትኛውም የንግድ እንቅስቃሴ በበላይነት ይዘው ነግሰውበታል፡፡

በተለያየ መስክ ከሚፈፀመው የሰብዓዊ መብት እረገጣ በተጨማሪ የሃገርን ቤሄራዊ ጥቅም አሳልፈው በመስጠት ወይም ገንዘብ የሚይስገኝላቸውን ሁሉ በመዝረፍና በማሸሽ፣ ምስኪኑ ህዝብ በዜግነቱ ሊያገኝ የሚገባውን ብቻ ሳይሆን በስሙ ተለምኖ የመጣውን ሁሉ በመንጠቅ ብዙሃን በርሃብ በሚሰቃይበት ሃገር ለአራት ለአምስት ትውልድ የሚበቃ ሃብት አሽሽተዋል፡፡
ከምርጫ 1997 ዓ.ም በፊት በተወሰነ መጠን እራሳቸው ላወጡት ህገ-መንግስት ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ቢያስቸግራቸውም ህጋዊ መስሎ ለመታየት የሚሞክሩበት ሁኔታዎች ይስተዋሉ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ፍርድ ቤት መመላለስ የእለት ከእለት ስራቸው ቢሆንም ከአሁን በተሻለ የህትመት ውጤቶች በቁጥርም በይዘትም የተሻሉ ነበሩ፡፡ በሌላም በኩል ይህው እኩይ ስርዓት ህግን ከመሻሩ በፊት የፓርላማ ጀሌዎቹንን ሰብስቦ ሊሽር ባስበው ህግ ላይ ሌላ ህግ ሲያወጣ ታይቷል ለምሳሌ የቀድሞ የህውሃት አባል የነበሩት አቶ ስዬ አብረሃ በተከሰሱበት ወንጀል ህጉ የሚፈቅድላቸውን የዋስትና መብት ለመከልከል ከፍርድ ቤት ቀጠሮ በፊት አዲስ ዋስትና የማያሰጥ የፀረ-ሙስና ህግ ማፅደቃቸው የሚታወስ ነው፡፡ ከዚህ በፊት ህውሃት በአመለካከትም ይሁን በግል ጥላቻ የራሱን ሰወች ሲበላ ከቻለ አንዱን በአንዱ ላይ አስነስቶ በማጫረስ አልያም በአደባባይ በደላቸውን እንዲናዘዙ በማስገደድ ከተጠያቂነት እራሱን ሲከላከል መቆየቱ አንድም እራሱን ላለማጋለጥ አልያም በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚፈፅማቸው በደሌች ሰርዞም ደልዞም ህግዊ ለመምሰል የጥር ነበር፡፡

ከምርጫ 1997ዓ.ም በሗላ ያለው በፊት ከነበረው ጋር ማነፃፀር ይከብዳል እጅግ ብዙ እርቀት ወደ ሗላ የመመለስ ያህል ነው ምክንያቱም በዛን ወቅት በተፈጠረው በጣም ጠባብ አጋጣሚ ህዝቡ ለስርዓቱ ይለውን ጥላቻና ለውጥ ፈላጊነቱን እንዲሁም እነሱ በተግባር የማያውቁትን ዴሞክራሲ ህዝቡ ሲዘምርላቸው፣ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከነሱ እንደሚሻል ሲያሳያቸው፣ ይበጁኛል የሃገሬንና የእኔን ህልውና ይጠብቁልኛል፣ ብሩህ የነፃነት ጊዜ ያመጡልኛል ይሆኑኛል ብሎ የሚላቸውን እንደራሴዎቹን ሲመርጥ ለአፍታ ይስተዋልባቸው የነበረው ሰዋዊ ባህሪየቸው ጠፍቶ ጫካ ተወልዶ ጫካ ያደገው አውሬነታቸው ሲመለስ የሚችሉትን ገለው ገሚሱን ወደ ማጎሪያቸው አግዘው ጭልጭል ትል የነበረች ተስፋችንን አደበዘዟት፡፡

ከዚህ በሗላ ያለችው ኢትዮጲያ የግል የህትመት ውጤቶች ሙሉ በሙሉ በማፈን በሃገራችው በሞያቸው ይህ ነው የሚባል ለውጥ ማምጣት የሚችሉ ጋዜጠኞችን በማሰርና በማሳደድ፣ ለሃገራችን ክብርና ለህዝቧ ነፃነት የሚሟገቱ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት ወይም በሃገራቸው በነፃነት የመኖር መብት አጥተው የሚሰደዱባት አልያም የነሱ የሆነው በሌሎች ተቀምተው የመከራ ቀንበር ከብዶ በግዞት የሚኖርባት ስትሆን ለኢምንት ባለ ጊዜዎች ግን የምድር ገነት ሆና ያሻቸውን የሚሆኑባት የግል እርስት አድርገዋታል፡፡

ይህ ከላይ ያነሳሁትና ተነግሮ የማያልቀው በህዝብ በሃገር ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍ በወያኔ ጥንካሬ ብቻ ሳይሆን የኛም ግፍና በደልን የመሸከም አቅም ወይም እንደ ሰው መብታችንን የማስጠበቅ፣ ህልውናችንን ያለማስደፈር ወይም በውርደት መኖር በቃኝ ብለን ሃላፊነታችንን ሳንወጣ እንዲሁ ከድርጅት ድርጅት ስንላተም፣ ከፓርቲ ፓርቲ ስንከለስ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሳሪያ ሆነን በህዝባችንና በሃገራችን ላይ የሚደርሰውን በደልና እንግልት ዘመን እናሻግራለን፡፡

ለዚህ ሁሉ በሃገርና በህዝብ ላይ ለሚደርሰው እንግልትና መዋከብ ምንም እንኳን የመንግስትን እርካብ የተቆናጠጡት ገዢዎቻችን ከተፈጥሮ ባህሪያቸው አንፃር የፈለጉትን ያሻቸውን ቢያደርጉም በየግዜው በህዝብ ላይ የሚያደረሱትን ሰቆቃ የየሰሞኑ መነጋገሪያ ከማደረግ በዘለለ ህዝብ እንደ ህዝብ በደል በቃኝ፣ ግፍ በቃኝ፣ መሰደድ በቃኝ፣ መታሰርና መገረፍ በቃኝ፣ ከሃብትና ከቀዬ መፈናቀል በቃኝ ብሎ ለለውጥ እንዲነሳ በህብረት ከመስራት ይልቅ የነሱን መበታተንና መሰነጣጠቅ አውርተን በድክመታቸው ሳንጠቀም መልሰው ተደራጅተው መብትና ክብራችንን ሲገፉንና ሲፃረሩን እናያለን፡፡ ሃገርና ህዝብን ከዚህ እኩይ ስርዓት መታደግን ለተወሰኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ብቻ ትተን በሰሞነኛ የወያኔ የጭካኔ ገድል ላይ ቡና እየጠጣን ስናነሳና ስንጥል ከወሬ የዘለለ ተግባራዊ የትግል እንቅስቃሴ ውስጥ ሳንገባና የታደሉት ለሃገራቸውና ለህዝባቸው የሚከፍሉትን መስዋህትነት የሚሰሩትን ታላቅ ስራ ስናፈርስና ስንክብ የዜግነት ግዴታችንን በአግባቡ ሳንወጣ ለገዢዎቻችን መሳሪያ ሆነን በዛ ደሃ ህዝብና ሃገራችን ላይ ቁማር እንጫወታለን፡፡

ነፃነት በወሬና በዲስኩር አይመጣም የመስዋህቱ አይነት የለያይ እንጂ አነሰም በዛም የነፃነት ትግል ወይ ሃብትን ወይም የህይወት መስዋህትነት ይፈልጋል፡፡ ዶክተር መርቲን ሉተር ኪንግ ጁንየር እንዳለው “ለውጥ በመንኮራኩር ተጭኖ የሚቀርብ ነገር አይደለም ሊገኝ አይችልም፣ በማያቋርጥ ትግል እንጂ ወገባችንን ጠበቅ አድርገን ለነፃነታችን መጣር አለብን ወገብህ ለመጥ ካላለ ጠላትህ ሊጋልብህ አይችልም. . . . . ከልምድ እንዳየነው ጨቋኝ ገዢ ነፃነትን በፈቃደኝነት አይሰጥም በተጨቋኞች መገደድ እንጂ” ይህ ነው እውነቱ ይህንን ሁሉ በህዝብና በሃገር ላይ የሚደርሰውን ለከት ያጣ ጭቆና የምናይና የምንሰማ በተለይ በሰለጠነው አለም የምንኖር ወገኖች እኛ በሰው ሃገር የምናገኘውን ነፃነት ወገናችን በገዛ ሃገሩ ሲያጣ፣ ይህ ነው የማይባል ችግር ሲወርድበት ከወሬ ያለፈ በተግባር የተፈተን ስራ መስራት ስለምን ተሳነን፣ ስለምን የህይወት መሰዋትነት ለሚከፈልበት የነፃነት ትግል በገንዘብ ለማገዝ ሰነፍን፣ስለምን ከወያኔ ለምናገኝው ቁራሽ መሬት ብለን የወገኖቻችንን የመከራ ጊዜ እናራዝማለን፣ ቁጥር ስፍር የሌለው ህዝብ በውጪው አለም እየኖረ ስለምን የህዝባችን የመረጃ ምንጭ የሆነው ኢሳት መስራት ያለበትን ያህል እንዲሰራና ህዝባችን እየተራበ መጥገቡን፣ እየከሰረ ማትረፉን፣ እየተቸገረ መበልፀጉን ከሚነግረው የወያኔ ዲስኩር አውጥተን አማራጭና እውነተኛ መረጃ የሚያገኝበትን፣ ወያኔ የስልጣን ዘመኑን ለማራዘም በከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲው እያደረገ ያለውን ዘርን ከዘር ሃይማኖት ከሃይማኖት የማጋጨትና የመሳሰሉትን የወያኔን ሴራ ህዝቡ እንዲያቅና በአንድነት ለመብቱና ለነፃነቱ እንዲነሳ ኢሳትን በመረዳት የዜግነት ግዴታችንን አንወጣም?

በነፃነት በመኖር የምንቀድማቸው ሃገራት ሰልጥነው በዴሞክራሲያዊ ስርዓትና መልካም አሰተዳደር የህዝቦቻቸውን ሰብዓዊ መብት ለማስጠበቅ ደፋ ቀና በሚሉበት በዚህ ዘመን የሗሊት የሚጓዘው ከዘመኑ ጋር መዘመን ያቃተው ህውሃት ከብዙ ዘመናት በፊት በነበረው አስተሳሰብና የሃይል አገዛዝ ተሸብቦ ያልደረሰበት ጫፍ፣ ያላስነባው ህዝብ፣ ያልጣሰው ህግና ስርዓት፣ ያላፈረሰው አንድነት፣ያላዋረደው የህዝብ ስብእና፣ ያልገባበት የእምነት ተቋም፣ ያልበተነው የሞያ ማህበራት ከከተማ ነዋሪ እስከ ገበሬው አልፎም እስከ አርብቶ አደሩ ያልገደለው፣ ያላሰረውና ያላስለቀሰው የህብረተሰብ ክፍል የለም፡፡

በአሁኑ ወቅት አዛዥና ታዛዥ የሌለበት የወያኔ ስርዓት ዘመኑ እያከተመ መሆኑን ከሚሰራቸው ስራዎች መገንዘብ አይከብድም ህግ ማሰከበር ያለበት መንግስት ላወጣው ህግ መገዛት የማይችልበት ደረጃ ከደረሰ ህልውናው አደጋ ውስጥ ለመሆኑ ማሳያ ነው ለዚህም መብቱን በወያኔ የተነጠቀው ህዝብ የህገ-መንግስቱን አንቀፅ እያሳየ የህግ ያለህ ሲል መደመጡ፡ በግምት የሚመራን ስርዓት የመጨረሻው ጠርዝ ላይ መቆሙን አመላካች ነው፡፡

ስለሆነም ኢትዮጲያንና ህዝቧን ለመታደግ በየትኛውም የትግል መስክ ተሳትፎ በማረግ ለነፃነት በሚደረገው ትግል ውስጥ የየራሳችንን አሻራ ለማሳረፍ ከወሬ በዘለለ ለተግባራዊ ትግል እንትጋ፡፡
ድል ለኢትዮጲያ ሕዝብ!!!

ሞት ለወያኔ!!!
ለአስተያየቶ-ftih_lewegen.yahoo.com

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 25, 2013

Monday, February 25th, 2013
News, Sports, African Topics and Health

የኢጣልያ ምርጫ

Monday, February 25th, 2013
የሮም ኤጣልያው ዘጋቢያችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ለኢጣልያ 630 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችና ለ 315 የህግ መወሰኛ ምክር ቤት መቀመጫዎች የተካሄደው ምርጫ ውጤት ይህ ሊሆን ይችላል ብሎ ከወዲሁ ለመገመት አስቸጋሪ ነው ይላል

የዴሞክራቲክ ኮንጎ ሬፓብሊክ የሰላም ውል

Monday, February 25th, 2013
የኮንጎ ጎረቤቶች በጋራ በኮንጎ ጉዳይ ጣልቃ ላለመግባት ፣ ለታጣቂ አማፅያንም ድጋፍ ላለመስጠት ቃል ገብተዋል ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በበኩሉ ኮንጎ የሚገኘውን የድርጅቱን ሠላም አስከባሪ ኃይል ይዞታ ገምግሞ ሃገሪቱን በተሻለ ሁኔታ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን መግለጫ

Monday, February 25th, 2013
አወዛጋቢው የኢትዮጵያዊ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን 6 ተኛ ፓትሪያርክ ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ መሠረት እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አስታወቀ ።

የሶሪያ ጦርነትና የተሻረው የድርድር ቃል

Monday, February 25th, 2013
በብሪታንያዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር መልዕክት የልብ ልብ የተሰማቸዉ አንካራ፥ ዶሐ፥ ካይሮና ቤይሩት የከተሙት የአማፂ ሐይላት መሪዎች ከሰወስት ሳምንት በፊት የገቡትን የድርድር ቃል ባለፈዉ ቅዳሜ ሻሩት።

የሣምንቱ ስፖርት

Monday, February 25th, 2013
ያለፈው ሰንበት የኢትዮጵያ አትሌቶች በተለያዩ ዓለምአቀፍ የማራቶን ሩጫ ውድድሮች ግሩም ውጤት ያስመዘገቡበት ነበር። በቶኮዮ ማራቶን ምንም እንኳ በወንዶች ድሉ የኬንያ ቢሆንም በሴቶች የኢትዮጵያ አትሌቶች የማይበገሩ ሆነው ታይተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት 2ኛ ጉባኤ አሜሪካን ውስጥ ተካሄደ (ጀርመን ራዲዮ)

Monday, February 25th, 2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክር ቤት 2ኛ ጉባኤ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ቨርጂኒያ አሜሪካን ውስጥ ተካሄደ። ጉባኤው የምክር ቤቱን የእስካሁኑ እንቅስቃሴ መገምገሙንና የወደፊት አቅጣጫውንም ማስተዋወቁን የዋሽንግተን ዲሲው ወኪላችን ዘግቧል ። በሌላ በኩል በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ በሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን ሙስሊሞች አስተባባሪነት ባለፈው ቅዳሜ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት ሠላማዊ ሰልፍ ተካሄዷል። ስለ ቨርጂኒያው ጉባኤ ና ስለ ዋሽንግተን ዲሲው ሠላማዊ ሠልፍ አበበ ፈለቀ ዝርዝር ዘገባ አለው።

UTC 16:00 የዓለም ዜና 25.02.2013

Monday, February 25th, 2013
ዜና

ሽማግሌዎች ብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን አነጋገሩ፤ አስመራጩ መግለጫ ሰጠ

Monday, February 25th, 2013

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 18/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 25/2013/ PDF)፦ ቅዳሜ የካቲት 16/2005 ዓ.ም ቀርበው በአብዛኛው የቅ/ሲኖዶስ አባላት ይሁንታ አግኝተዋል የተባሉት አስምት ሊቃነ ጳጳሳት በመጪው ሐሙስ ለሚካሄደው የፓትርያርክ ምርጫ ያለፉ መሆናቸውን አስመራጭ ኮሚቴው ዛሬ በጋዜጣዊ መግለጫው ገልጿል።


ከፍተኛ ታቃውሞና የከረረ ተግሳጽ የደረሰባቸውን አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌምን ጨምሮ ሌሎቹ አራት አባቶች የተካተቱበት የአስመራጭ ኮሚቴው ጥቆማ ለቅ/ሲኖዶስ ቢቀርብም ተጨማሪም ተቀናሽም ሳይደረግበት መጽደቁ ዛሬ ይፋ ሆኗል። በዚህም መሠረት ሐሙስ በሚደረገው ምርጫ ከፍተኛ ቁጥር የሚያገኘው ተወዳዳሪ ስድስተኛ ፓትርያርክ ተብሎ ይሾማል ማለት ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ስድስተኛውን ፓትርያርክ ምርጫ ተከትሎ ሰሞኑን የተፈጠረውን  አለመግባባት ለመፍታት የአስመራጭ  ኮሚቴው  ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከሌሎች ብፁዐን ሊቃነ  ጳጳሳት ጋር በመሆን  የምርጫውን  ሒደት የታቃወሙትን ብጹዕ አቡነ ሳሙኤልን ማነጋገሩን ውስጥ አዋቂ ምንጮች ለደጀ ሰላም ገልጸዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ አብርሃምን ለማነጋገር ያደረጉት ሙከራም በብፁዕነታቸው በአካባቢው አለመኖር ምክንያት ሳይሳካ መቅረቱን እነዚሁ ውስጥ አዋቂዎች አስረድተዋል።

በምርጫው ላይ ያነሱትን የዘገየ ነው የተባለ ተቃውሞ እንዲያቀዘቅዙ ለማግባባትና ምርጫው በተጀመረው መሠረት እንዲጠናቀቅ ለማሸማገል የተላኩት አባቶች የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ሐሳብ ለማስቀየር የቻሉ አይመስልም። ብጹዕነታቸው በተቃውሟቸው በመግፋት በቅዳሜ የቅ/ሲኖዶስ ጉባኤ ላይ ያንጸባረቁትን ሐሳብ ደግመውላቸዋል ተብሏል። እንዲያውም አስመራጩ ኮሚቴ መግለጫውን ካወጣ እነርሱም (አቡነ ሳሙኤልና አቡነ አብርሃም?) በበኩላቸው ተቃውሟቸውን በመግለጫ ይፋ እንደሚያደርጉ ለሽማግሌዎቹ አስረድተዋቸዋል ሲሉ ምንጮቻችን ያብራራሉ። ይሁን እንጂ አስመራጭ ኮሚቴው በያዘው ሐሳብ በመግፋት በቅዳሜው ስብሰባ ያስጸደቃቸውን አመስት አባቶች እና አጠቃለይ የጥቆማውን ሒደት በመግለጽ ዋነኛውን ክፍል የምርጫ ጉዞ አጠናቋል።

ይኸው ጋዜጣዊ መግለጫ በተሰጠበት በዛሬው ዕለት እንደተገለጸው በነዚህ ሦስት ቀናት ብፁዓን አባቶችን ጨምሮ ምእመኑ በሙሉ ጉዳዩን በጾም በጸሎት እንዲያስብና የእግዚአብሔርን ፈቃድ እንዲጠይቅ አስመራጭ ኮሚቴው አሳስቧል። ምርጫው ካርድ በመጣል እንጂ እንደ አበው ሥርዓት ዕጣ በማውጣት እንዳልሆነ፣ ይህ ሐሳብ በምርጫ ደንብ ማጽደቁ ወቅት ውድቅ እንደተደረገ፣ ይህንን ሐሳብ ያቀረቡ አባቶች ተሰሚነት እንዳላገኙ ይልቁንም “ምርጫው ልክ በመንግሥት እንደሚደረገው በካርድ ይሁን” የሚል ሐሳብ እንደተንጸባረቀ መዘገቡ ይታወሳል። በርግጥ በዕጣ ቢሆንና ፈቃደ እግዚአብሔርን ጠይቁ ቢባል እንዴት ባማረ፣ እንዴትስ ሃይማኖታዊ በመሰለ ነበር። የመንግሥት እጅ ለሚዋኝበት፣ ፈቃደ ቤተ መንግሥት ፈጻሚ ሞገስ ለሚያገኝበት፣ ሁሉም ወገን “አባቴ ነው፣ ይደልዎ፣ መመረጥ ይገባዋል” ለማይልበት ምርጫ በጾምና በጸሎት አስቡን ማለት ሰውን ለመፈታተን እና ሃይማኖታዊ መስሎ ለመታት ካልሆነ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ነው።

ከዚህ አስቀድመን በተደጋጋሚ እንደገለጽነው ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ዘኢየሩሳሌም ፓትርያርክ እንዲሆኑ የመንግሥት ዓላማ መሆኑን ምንጮችን ጠቅሰን ዘግበን ነበር። በወቅቱ በግልም በሚዲያ ደረጃም ይህ የደጀ ሰላም ዘገባ የተሳሳተ መሆኑን ለመጠቆም ብዙ መልእክቶች ደርሰውን ነበር። ጊዜው ሲደርስ እየሆነ ያለው ይኸው ይመስላል።

ደጀ ሰላም ብፁዕ አቡነ ማቲያስ ላይ ተቃውሞ የላትም። ለሃይማኖታቸው ተቆርቋሪ፣ በብዙ ሰዎችም ዘንድ የመሰገኑ ንፁህ መነኩሴ መሆናቸውን የሚሰጠውን ምስክርነት ደጀ ሰላምም ታውቃለች። የምርጫው ሒደት ትክክል አይደለም ማለት አቡነ ማቲያስ መጥፎ ናቸው እንደማለት መቆጠር የለበትም። ሌለቾዩን ብፁዓን አባቶች አሠራራቸውን በየጊዜው እያየን ሊመሰገኑ ሲገባቸው የምናመሰግናቸው፣ ትክክል አይደሉም ብለን በምናስብበት ወቅት የምንቃወማቸው በዚያ ወቅት ባራመዱት ዓላማ ምክንያት ብቻ ነው።

ከዚህ በፊት አቡነ ሳሙኤልንና አቡነ አብርሃምን ታደንቁ ነበር አሁን ለምን የያዙትን አቋም አልተቀበላችሁም ለሚሉን የምንሰጠው መልስ ይኼው ነው። አቡነ ሳሙኤል በተለይ የቀድሞው ፓትርያርክ ያራምዱት በነበረው አውዳሚ እንቅስቃሴ ላይ በነበራቸው ተቃውሞ፣ ሙስናን ለማጥፋት ባደረጉት ትግል እኛም ደግፈናቸዋል። አሁንም ለዚያ እንቅስቃሴያቸው ያለን አክብሮት ትልቅ ነው። አቡነ አብርሃምም አሜሪካ በነበሩበት ወቅት ለሠጡት ትልቅ አገልግሎት ስናመሰግናቸው ቆይተናል፣ አሁንም እናመሰግናቸዋለን። ሁለቱም አባቶች ዕርቀ ሰላሙን በተመለከተ ባራዱት አቋም ደግሞ እንኮንናቸዋለን። ተሳስተዋል እንላለን።

ከዚህ ባሻገር ምርጫውን በተመለከተ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንዳለበት መግለጻቸው ትክክል ነው። ስንቃወመው የነበረው፣ አሁንም የምንቃወመው ተግባር ነው። በዕጣ መሆኑን ስንመኝበት ከነበረው ምክንያት አንዱ ለእግዚአብሔር ፈቃድ የተመቸ ሥራ መሥራት እንዲቻል ነበር። አልሆነም። በካርድ የሚመረጠው አባት ማንም ይሁን ማን “የመንግሥት ወገን” ተደርጎ መቆጠሩ አይቀርለትም። ያሳዝናል።
ቸር ወሬ ያሰማን አሜን

የቡዳዎቹ ሠፈር የትኛው ነው? ወልደማርም ዘገዬ

Monday, February 25th, 2013

የቀድሞው ኢትዮጵያዊ የአሁኑ ኤርትራዊ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን መድኃኔ “ኤርትራ እንደ እናት አገር፤ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም” በሚል ርዕስ በአውሮጳውያኑ የዘመን አቆጣጠር ጥር ወር 2013 የጻፉትን ጥናታዊ ዘገባ በፍላሼ አሰንብቼ ዛሬ ጧት ቁርሴን አወራረድኩበት፡፡ ኤርትራ ለእርሳቸው የምታስጨንቀውን ያህል ኢትዮጵያም – ባለቤት ያጣችዋ ከርታታዋ ኢትዮጵያም ለእኔ እንደእናት ሀገር ታስጨንቀኛለችና የተሰማኝን ልናገር ብዕሬን አነሳሁ፡፡

ግን በዚህች የተረገመች ሀገር – በዚህ የዜጎች መብት ክፉኛ በሚረገጥባት ሀገር የመብራት መጥፋት በየደቂቃው ስለሚከሰት በምፈልገው ፍጥነት መጨረሴን እጠራጠራለሁ፡፡ አንዳንዴ በቀን ለቁጥር ለሚያታክት ጊዜ ያህል መብራት ይቆራረጣል፤ አሁን ድርግም ይልና ከደቂቃዎች በኋላ ሊመጣ ይችላል፤ የምትሠራውን ቅጥ ያሳጣብሃል – በልጆቼ አነጋገር ‹ሙድህን ይሠርቅብህ›ና ልትሳነፍ ባስ ሲልም ልትጽፍ ያሰብከውን ከነጭራሹ ልትተወው ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ በኛ መንደር በቀደም ዕለት የጠፋ ከ27 ሰዓታት በኋላ ትናንት ማታ ነው መብራት የመጣልን፡፡ ስልኩም ውኃውም እንደዚሁ ነው፡፡ የቤት ስልክ ከሚሠራበት ጊዜ የማይሠራበት ይበልጣል፡፡ የአንዱን ሊጠግኑ ሲመጡ የሌላውን አበላሽተው ሊሄዱ ይችላሉ – ጠርተሃቸው በመቁሽሽ እንድታሠራቸው፡፡ ውኃ ወር እስከወርም ላታገኝ የምትችልባቸው አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ማንን ትጠይቃለህ? በየቢሮው አናት ‹የዚህና የዚህ የሥራ ሂደት ባለቤት› የሚል ጽሑፍ ተለጥፎ ብታይም ማንም ጉዳይህን ከቁብ የሚጥፍልህና የሚያነጋግርህ ሰው የለም፡፡ ስቃይ ነው ልጄ፡፡ የዴሞክራሲው ነገር እዬዬም ሲዳላ ነውና አታስበውም፡፡ አሁን በአንጻራዊነት ከሚታዩ መልካም ነገሮች ውስጥ ዋናው የመንገዶች መስፋፋት ነው፡፡ ይህም ቢሆን በየቀኑ በመቶዎችና በሺዎች ከሚጨምረው የተሸከርካሪዎችና የእግረኞች ብዛት ጋር በጭራሽ ሊጣጣም ባለመቻሉ ችግሮች ሲወሳሰቡ እንጂ ሲፈቱ አታይም፤ የሕዝቡን ብዛት በየሥፍራው እንደጉንዳን ሲርመሰመስ ስታይ ሰው ነገር ዓለሙን እርግፍ አድርጎ ትቶ ከመፈላፈል ውጪ ሌላ ሥራ ያለው ላይመስልህ ይችላል፤ የሀገሪቱ ዋና ራስ ምታት የራሴ ነው የምትለው ለሀገርና ለወገን የሚቆረቆር፣ ሁሉንም እኩል በሚያሣትፍ የዕቅድና የበጀት ምደባ ሀገሪቱን በተገቢው የዕድገት ጎዳና የሚያራምድ ተቆርቋሪ መንግሥት ማጣት ብቻ ሳይሆን የሕዝብ ቁጥር በአደገኛ ሁኔታ መጨመርም ነው – እኔ ራሴ ባለቤቴ ዘጠንኛውን ልጃችንን ልትገላገል ጥቂት ሣምንታት ይቀሯታል፤ ይህን የምናደርገው ተስፋ ከመቁረጥና በነሱ ለመጦር ከማቀድ አንጻር ነው – ሌላ መዝናኛም ከማጣት ጭምር(እንዴ! ምን ማለታችሁ ነው – እስከግማሽዋ በአረፋ የተሞላች አንዲት ብርጭቆ ድራፍት እንኳን ባቅሟ በሰባት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከብር 2.20 ሽቅብ ተወንጭፋ አሥር ብር ስትገባ! – ታዲያ መራባት ይነሰን?)፡፡ ሰው ተስፋ ሲቆርጥ ከ‹መብላት› እና ‹መጠጣት› ውጪ ያሉትን አብዛኞቹን የ‹መ›ሕጎች ያከብራል፡- መናደድ፣መበሳጨት፣መሰደድ፣መጠጣት፣መዋለድ፣መእንትን…፤ “ጠጪነትና የሕዝብ ብዛት በአስደንጋጭ ሁኔታ መጨመር የተስፋ መቁረጥ ምልክቶች ናቸው” የሚባለው አዲስ ምሳሌያዊ አባባል ለካንስ እውነት ነው! ምን ልበልህ ወንድሜ! የሀገርህ ነገር እጅግ አሳሳቢ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሁለተኛና ሰባተኛ ዜጋ ሆነህ ከመኖር አውሮፓ ውስጥ ውሻና ድመት ሆነህ ብትፈጠር በእጅጉ ይሻልሃል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የወያኔ ተለማማጭ ሀብታም ከምትሆን የጓንታናሞ የፍርድ እሥረኛ ብትሆን ላንተ ሉተሪ ነው፡፡ ብሬቪክ የሚባለው ሰባ ምናምን ሰው የገደለው ስዊድናዊ ታራሚ ከእሥር ስወጣም ገና ብዙ ሕዝብ እፈጃለሁ እያለ መስፈራርቾውን በቀጠለበት ወቅት ‹ክፍሌ በሰዓቱ አልጸዳልኝም› ወይም ‹ክፍሌ በቂ ብርሃን ስለሌለው በአስቸኳይ ይለወጥልኝ!› በሚል የማያዳግም ቃል (‘ultimatum’) የማረሚያ ቤቱን ባለሥልጣናት እያሽቆጠቆጠ መብቱን በሕግ ማስጠበቁን ስትሰማ ከጫካ የመጣ ወሮበላ እንደፈለገው የሚደፈጥጥብህን የአንተን ኢትዮጵያዊነት ያሻው ቀቅሎ እንዲበላው ከአእምሮህ መንትገህ ለመጣል ልትዳዳ ትችላለህ፡፡ ጊዜው የፈተና ነው ወንድሜ፡፡ እናም ይህችን ጊዜ እንደምንም ታገላትና ሳትበለሻሽ ተወጣት፡፡ ታሪክ እንደሆን ይቅርታ ማድረግን አያውቅም፡፡ ጽጌረዳን በቀላል አናገኝም፤ እሾኋ ውድነቷን ሳይጨምርላት አልቀረም፡፡ ኢትዮጵያዊነት ሲሞቅ በማንኪያ ሲቀዘቅዝ በእጅ አይደለም፡፡ ዛሬ በስሟ የነገዱና ሕዝቧን የዶጋ ዐመድ ያደረጉ ዱርዬ ልጆቿ ሁሉ አይቀጡ ቅጣት ሲያገኙ ዳፋው እንዳይደርስህ ተጠንቀቅ! ለአንድ እንጀራ ብለህ እንደዔሣው ብኩርናህን ለሆድህ አትሽጥ፡፡ የሰው ወርቅ አያደምቅምና የጠፋህ ወገኔ በጊዜ ተመለስ!!

አንተ ዴሞክራሲ ዴሞክራሲ እያልክ በየሰው ሀገር አደባባይ ትጮሃለህ፡፡ እዚህ ሰዎች ከሰውነት ተራ እየወጡ ተንቀሳቃሽ በድን እየሆኑልህ ነው፡፡ ያንተን ጩኸት ራሱ አይሰሙም – ብዙዎቹ የሚሰሙበት ፍላጎትና መንገድም የላቸውም፤ደንበኛ ሰሜን ኮሪያውያን ሆነንልሃል፡፡ ‹ወንድሞቼንና እህቶቼን ነጻ አወጣለሁ› ብለህ ብትመጣ እንኳን፣ ነጻነት የሚገባው(የሚያስፈልገው) መሆኑን የሚረዳ ዜጋ ለማግኘት ይቸግርሃል፤ የሚመጣውን ቁጣና መቅሰፍት ሁሉ በቀላሉ እየተለማመደ ለሁሉም የግፍ አገዛዝ ተንበርካኪ ትውልድ እየተበራከተ ነው፡፡ ግዴለህም አንዳች የተደገመብን ነገር መኖር አለበት፡፡ ፈዘንና ደንግዘን በመተታዊ የአንደርብ ሥራ ወደ ጋንነትና እንሥራነት የተለወጥን ግዑዛን ነገሮች መስለንልሃል ወንድምዬ፡፡

አንድ ለአንድ አካባቢ እንግዳ የነበረ ሰው መንገድ ይጠፋውና አንዱን መንገደኛ ይጠየቀዋል፡፡ “የኔ ወንድም እንደዚህ የሚባል መንደር ልሄድ ፈልጌ ነበር፡፡ እስኪ እንዴት እንደምደርስ ጠቁመኝ ወዳጄ” ያም ሰው “ ይሄን መንገድ ቀጥ ብለህ ትሄድና እመስቀልኛው መንገድ እዚያ ወዲያ ስትደርስ ግራህን ይዘህ ትታጠፋለህ፤ ከዚያም ጥቂት እንደሄድክ ግራና ቀኝ የሚገኙ ሠፈሮችን ታገኛለህ፡፡ አንደኛው ግን የቡዳዎች ሠፈር ስለሆነ ሰው ጠይቅና ተጠንቅቀህ እለፍ፡፡” ይለዋል፡፡ እዚያ ጠንቀኛ መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲደርስ ቀድሞ የተነገረውን ያስብና በቡዳነት ይታማ ከነበረው ሠፈር የመጣ አንድ ሰው እዚያ አካባቢ ስለነበር በየዋህነት “ አንቱ ጋሼ – የቡዳው ሠፈር የትኛው ነው?” ብሎ ይጠይቃል፡፡ ያም ሰው ምንተፍረቱን “እኛም እነሱን እንላለን፤ እነሱም እኛን ይላሉ” ይለውና ወዶ እንዲገባብት ምርጫውን ለጠያቂው ትቶ ንዴቱ እንዳይታወቅበት ለማድረግ በመጣር ይለየዋል፡፡ “እነሱም እኛን ይላሉ፤ እኛም እነሱን እንላለን!”

‹ኤርትራውያን› የኛ የ‹ኢትዮጵያውያን› ችግሮች መባቀያ እንደሆኑ የምናምን ወገኖች ጥቂቶች አይደንለም፡፡ በተገላቢጦሹም እኛ የነሱ ችግሮች ምንጭ እንደሆንን የሚያምኑ ኤርትራውያን አሉ፡፡ የሁለታችንም ችግሮች አንድ መሆናቸውን ግን እያጤንን መጥተናል – ለዐይን ይበጃል ያሉት ኩልም ዐይንን ሊያጠፋ መቃረቡን እየተረዳን ነው – ‹ናጽነት› ወይ ‹ባርነት›፤ ዕድሜ ደጉ የነጻነትንም የባርነትንም አዲስ ፍቺዎች እየተገነዘብን ነው፡፡ በዕንቆቅልሾች ታጥረናል ማለት ይቻላል፡፡ ለቅጣት በተላኩ ሁለት የአክስትና የአጎት ልጆች ጦስ 100 ሚሊዮን የሚጠጋ ሕዝብ እየታመሰና የቁም ስቅሉን እያዬ ነው፡፡ ‹ዘይገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈኔ› ይላሉ ወንድሞቼ የሚደንቅ ነገር ሲገጥማቸው፡፡

ከአንድ ምንጭ የሚቀዳ ውኃ ጣዕሙ አንድ ነው፡፡ መለስና ኢሳይያስ – የአንድ ሣጥናኤል ሁለት ገጽታዎች – ከአንድ የጥፋት ወንዝ የተቀዱ በመሆናቸው በሃሊዮ በገቢር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ የበሰበሰና የገማ የገለማ ዓላማቸው ኢትዮጵያን ማፈራረስ ሕዝብንም ከሕዝብ ማቃቃርና ማፋጀት በውጤቱም የራሳቸውን ሰይጣናዊ ተልእኮ ማሣካት ስለሆነ እነዚህ ሁለት የሥጋ ዝምድናና የዓላማ ቁርኝት ያላቸው ሰዎች በሁሉም ነገር አንድ ናቸው፡፡ የተረገሙና ከእግዚአብሄር መንገድ የወጡ – ለቅጣት የመጡ እንደመሆናቸው መጨረሻቸው ቀርቶ መነሻቸውና መገባደጃቸው ራሱ የሚያምር አልሆነም፡፡ መለስ በ‹ለጋነት› ዕድሜው ሊቀጭ የቻለው በሕዝብ ፍቅር ምክንያት እንዳልሆነ እንኳን ፈጣሪ ሰይጣን ካቦኣቸውም(Foreman) ያውቃል፡፡ በቀላል ትዝብት መለስ ትዳርና ልጅ ሊወጣለት ያልቻለው በሕዝብ እርግማንና በሕዝብ ዕንባ ምክንያት እንጂ የመልካም ሥራ ተፈጥሮ ኖሮት ያንን ደግነቱን ፈጣሪ ዋጋ አሳጥቶበት እንዳልሆነ አሁንም እንኳንስ እግዚአብሔር ዲያብሎስ ራሱም ጠንቅቆ ያውቃል፡፡ ኢሳይያስ አፈወርቂ እንደጎረምሳ ትዳሩን እያመናቀረና ባለቤቱ በሽማግሌዎች ብርታት እየለዘበች እሱ የመጠጥና የቁማር ሱሰኛ ሆኖ የቀረው፣ የረባ ግለሰብኣዊና ማኅበራዊ ሕይወት ሳይመራ ዕድሜውን በከንቱ እየጨረሰ ያለው፣ የበሽታና የጋንጩሮች ዋሻ ሆኖ እንዳበደ ውሻ እየተቅበዘበዘ የሚኖረው በሕዝብ እርግማን እንጂ በጽድቅ ሥራው ምክንያት አይደለም(ልብ አድርጉ! አማሮችን ለተዋጊዎቹ የዒላማ ማለማመጃ እያደረገ የነበረ የሉሲፈር ቀኝ እጅ ነው! To be honest, I was not there in any form of presence, but I can assume as if I were there; my instinct tells me that he and his protégé, His Crookedness Meles Zenawi, have been doing every crime that men can do against the so called Amharas! And it is my sincere conviction that their karmatic uncleanliness will never let them go without punishment, possibly here or probably there, or maybe in both realms until the time they become as immaculate as a newborn sinless babe!)፡፡ የእንጨት ሽበቶቹ ስብሃት ነጋ፣ ሞራ-ራስ የኑስ፤ ሥዩም መስፍን … በልዩ ልዩ ሱሶችና የበሽታ መርዞች ተለክፈው ባብዛኛው እንደነሱው ሰካራምና ሀሺሻም በስተቀር እዚህ ግባ የሚሉት አንድም ቁም ነገረኛ ልጅ ሳይወጣላቸው ዕድሜያቸውን በመንዘላዘል እንዲሁ በከንቱ እየጨረሱ የሚገኙት በእርግማን እንጂ በምርቃት በረከት አይደለም – ጎበዝ በደንብ እንደማመጥ! የእርግማን ጦር ሲወጋ እንጂ ሲወረወር አይታይም የሚባለውን ነባር ሥነ ቃል አንርሣ! ከጥንትም ቢሆን ሕዝብ ያለቀሰበት መቅኖ የለውም – በተለይ በኢትዮጵያ፡፡ ለዚህም ነው አሁን ማንም በማንም ላይ እንትኑን እንትን ይበል በሂደት ግን ‹በሠፈረው ቁና ይሠፈርለታል› በሚለው ነባር መለኮታዊና ተፈጥሯዊ ሕግ መጽናት የሚገባ መሆኑን በጥብቅ የምሰብከው፡፡ የቻለ እንዲያውም በክፉዎች አይቅና – ብድራታቸውን ያገኛሉና፡፡ ክፉዎች ለጊዜው የተሳካላቸው ቢመስልም የማታ ማታ ተጎጂዎች ናቸው፡፡ ሁለት ስህተቶች አንድን የተበላሸ ነገር ሊያስተካክሉ ወይ ሊያቃኑ እንደማይችሉም መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ስህተት ስህተትን ይወልዳል እንጂ የተዛነፈን አያቃናም፡፡ (Two wrongs don’t make a right.) ለዚህም ነው ወያኔን ሳይወለድ እንደጨነገፈ ሽል መቁጠር የሚገባን፡፡ ግርፋቱ ግን ከባድ ነው!

እውነት መስሎ የታየኝን እናገራለሁ፤ እጽፍማለሁ፡፡ በእንትን የተጥለቀለቀ የንግግር ዘይቤያችንን የምጥሰው ሆን ብዬ ነው፡፡ ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን መጥፎ ድርጊት ላለማድረግ እንጂ ቋንቋ በማሳመር እውነትን ለመሸፈን መሆን የለበትም፡፡ ባለፈው ሰሞን የላክሁትን አንድ ጽሑፍ አንብቦ አንድ ወዳጄ በስልክ እንዲህ አለኝ፡፡ “አንተ ወልዴ! ምን ነካህ? አበድክ እንዴ? እንዴት በስሜት ውስጥ ሆነህ ትጽፋለህ? ለምን ቀዝቀዝ ስትል አትጽፍም? ተናደህ ከጻፍክ እኮ ሰው ይቀየምሃል፤ተናደን የምንቀጣው ልጅ ሊጎዳብን እንደሚችል አታውቅምን? የምትለው ነገር እውነትነት ቢኖረው እንኳን በቃላት መረጣ ተጠምዶ አንዱ የሌላኛውን ስሜት ላለማጎፍነን እርስ በርስ ሲሞከሻሽ በኖረ ማኅበረሰብ ውስጥ ይህን ያህል ግልጽነት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ለምሳሌ አንድ ድረ ገጽ ያን ጽሑፍህን ለጥፎት ሲያበቃ ከሁለት ቀናት በኋላ ከውጪ ዐዋቂ ይሁን ከውስጥ ዐዋቂ አስተያየት በመነሳት ገንጥሎ ጣለው፤ አንድ ቦታ ደግሞ ስሜታቸውን እንዴት እንደነካህባቸው ባልገባኝ ሁኔታ መርቅነህ እንደጻፍከው አስተያየት የጻፉብህ አሉ፤ ለምን …” ሲለኝ ብልጭ አለብኝና “ኦ!ኦ! የኔ ወንድም ዝም ብለው ካዳመጡህ ብዙ ትቀባጥራለህ፤ አንተ ራስህም የፈለግኸውን ልትለኝ ትችላለህ፡፡ የፈለጋችሁትን በሉ ሃሳቡ አይበላኝም፡፡ እኔ ካልተናደድኩ አልጽፍም፡፡ ስናደድ የምጽፈው ለእኔ እውነትነት አለው፡፡ ያልተበረዘና ያልተከለሰ – እከሌን ላስቀይም ወይም ላስደስት የማልልበት እንደወረደ ዓይነት ሃሳብ የማገኘው ተናድጄ ስጽፍ ነው፡፡ አንባቢም ያሻውን የማለት መብት አለው፡፡ የሚዲያ መድረኮችም ሲፈልጉ ይለጥፉ ሳይፈልጉ ቀድደው ይጣሉት – በኔ የቁጣ ንግግር ሰማይና ምድር አያልፉም፡፡ ሰለጠነ በሚባለው ዓለም የአሜሪካ ሴኔትና ኮንግረስ፣ የእንግሊዝ ፓርላማ፣ የእስራኤል ክነሴት፣ የራሽያ ዱማ… በስብሰባዎቻቸው ‹f**k off, idiot, son of a bitch, …› እየተባባሉ ተሰዳድበው ሲያበቁ ከስብሰባው ሲወጡ ሁሉንም ረስተው አብረው ይጫወቱ፣ ይበሉና ይጠጡስ የለምን? እኔስ ምን አጠፋሁ? ‹የትግሬ ወያኔ እንትን አለብን፤ እነእንትና ከፈለጉ እንትን ይሁኑ፤ እንትኔ መጥቶብኝ ወደ እንትን ቤት ልሄድ ነው፣እንትንህ ተከፍቷልና እንትንህ ሳይታይብህ እንትንህን ዝጋ…› እያልኩ ሁሉን ነገር በግድ በእንትን ጀምሬ በእንትን መጨረስ አለብኝ? ለምን? ከፈለግህ አንተም እንደነእንትና መሆን ትችላለህ፣ የእንትን አቀንቃኝ ሁላ! ለካንስ አፈሩን ገለባ ያድርግለትና ስብሃት ገ/እግዚአብሔር ‹እንትን›ን እንደጠላና ስም አይጠሬዎችን(taboo words) እነእንትንንና እንትንን በቁልምጫ ሳይቀር እንደጠራ የሞተው ማፈንገጥ አምሮት ሳይሆን እውነትን እንዳለች መግለጽ ፈልጎ ኖሯል?” አልኩና በንዴት ፎግልቼ ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀምሁበት፤ የታባቱንና፡፡ ነገር ግን የራሽያው ዱማ በቦሪስ የልሲን የደረሰበት የመድፍና የታንክ እሩምታ ትዝ አለኝና ከጠቀስኩለት ዝርዝር ውስጥ እንዲያወጣልኝ ሳልነግረው ስልኩን በመዝጋቴ ቆጨኝ፡፡ ራሺያና እኛ ለካንስ በአንዳንድ ነገሮች እንመሳሰላለን፡፡ ፑቲን – መድቬዴቭ፤ መለስ – ደሳለኝ፡፡ አይይይ፣ የኛዎቹ ቲያትር እንኳን የነዚያኞቹን ያህል ወዝ ያለው አይደለም፡፡ በምን ተገናኝቶ ልጄ!

እንትን ስል አንድ እንትን ትዝ አለኝ ይልቁናስ – ፈገግ በሉ እንጂ – ግንባርን አኮሳትሮ እስከመቼ ይዘለቃል፡፡ በአንድ መንደር ውስጥ ኃይለኛ ርሀብ ይገባል አሉ፡፡ ከመንደሩ አባውራዎች አንዱ ውሻውን ይዞ አንዳች የሚታደን ነገር ባገኝ ይልና በቅርብ ወደሚገኝ ጫካ ይሄዳል – ወደ ደደቢት በረሃ፡፡ ጉድጓድ ይቆፍርና ወጥመዱን አዘጋጅቶ ቢጠብቅ ቢጠብቅ ወደ ወጥመዱ ዝር የሚል ሰስና ሚዳቋ ይጠፋል፡፡ ከዚያ እግሩን አፍታትቶ ለመመለስ ከሄደበት ዘወርወር ብሎ ሲመጣ ያጠመደው ጉድጓድ ውስጥ አንድ አውሬ ገብቶ ያገኛል፡፡ ይሄኔ በመደሰትና ዘመኑ የችግር በመሆኑ ግዳዩን ሌላ ሰው እንዳይካፈለው በመሥጋት በኮድ የታሰረ መልእክቱን ለሚስቱ እንዲህ ሲል ጮክ ብሎ ያስተላልፋል፡-

እንትናችን ውስጥ እንትን ገብቶበት፤
እንትን አምጭልኝ እንትን እልበት፤
አንቺም ነይልኝ እንትን ትይልኝ፡፡

ነገሩ ቢላዎ ይዘሽልኝ ነይ ነው፡፡ ሁሉም አልፎ ፣ የቀኒቱ ርሀብም ለጊዜው ጠፍታ ጧት ላይ ቆዳና ጭንቅላት ሲታይ በጨለማ የተበላችው ለካንስ ቡችዬ ናት፡፡ ከዚያን ጊዜ አንስቶ ነው እንግዲህ ‹ውሾን ያነሳ ውሾ ይሁን› የሚል ሥነ ቃላዊ ብሂል በቋንቋችን የተዘነቀውና አሁን ድረስ እየተጠቀምንበት የምንገኘው ይባላል፡፡

ለማንኛውም አካፋን አካፋ ማለት ጥሩ ነው፡፡ በመሠረቱ ኢትዮጵያ ሳይጠጡ የሚሰክሩባት፣ ሳይቅሙ የሚመረቅኑባት፣ ጠብ ከመነሳቱ አቧራ የሚጨስባት፣ በጠብ ያለሽ በዳቦ የስድብ ውርጅብኝና የአግቦ ውሽንፍር አየሩ የሚሞላባት የለየላቸው አማኑኤሎች ሀገር እየሆነች በመምጣቷ ብዙ ነገሮች ሊያስገሩሙን አይገባም፡፡ አምባጓሮ በሽበሽ ነው፡፡ መነቃቀፍ የሠርክ ልማድ ነው፡፡ ሌብነትና ውሸት፣ ሙስናና ንቅዘት አያስነውሩም፡፡ የሚያሾምና የሚያስሞግስ ተግማምቶ መገኘት እንጂ የኅሊናና የሞራል ንጽኅናን መጠበቅ አይደለም – ንጽሕና እንዲያውም ሊያስቀጣና ሊያደኸይ ቤተሙከራ ውስጥ በተፈለሰፈ ወንጀል አስከስሶም በዕድሜ ይፍታህ ዘብጥያ ሊያወርድ ይችላል – ሁሉን ቢያወሩት ሆድ ባዶ መቅረቱ ከፋ እንጂ በዚህ ረገድ ስንትና ስንት የምነግራችሁ ነበረኝ! እናም ወደተነሳሁበት ስመለስ… የወያኔዎች የከረፋ ተፈጥሮና በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጽሙት ሰይጣናዊ ድርጊት እያናደደኝ እውነትን ባለማለሳለስ እንዳለ እጽፋለሁ እንጂ በምንም ዓይነት ሰው ሰራሽም ሆነ የተፈጥሮ ንጥረ ነገር ተመርቼ አልጽፍም፡፡ በሀብት ብዛትና ኅሊናን በሚያዛቡ የአልኮል መጠጦች እየሠከሩ እንደዕንቁላል የገማ አስተሳሰባቸውን በጉልበት በተቆጣጠሩት ሚዲያ አማካኝት ሕዝብ ላይ የሚያስታውኩና የሚቀረሹ ስብሃትን የመሰሉ ዘረኞች ሞልተውናል፡፡ “አሜሪካ ቀርቶ መንግሥተ ሰማይም ብትሆን አታመልጠንም! አምጥተን እናስርሃለን” የሚሉ ልበ ድፍን የወያኔ ሰካራሞችና ቅዠታሞች እያሉ እኔ እውነትን ለመጻፍ ጫትም ሆነ መጠጥ አያስፈልገኝም፡፡ እንደውነቱ ከሆነ ውቅያኖሶች ቀለም፣ ሰማይና ምድር ብራና ሆነው የወያኔን ታሪክ ብንጽፍ አያልቅም፡፡

ከዚህ በላይ እስካሁን ምን እንዳልኩ አላውቅም – የምርቃና ነገር – ቂ…ቂ…ቂ… ሣቅ አምሮኝ ነበር እንደጉድ ተንከተከትኩላችሁ፡፡ ቢሆንም ትርጉም ሰጠም አልሰጠም ነገሬን መቋጨት አለብኝና ወደዚያው ወደሚወስደኝ ጎዳና ላዝግም፡፡ ኤርትራውያን ችግር ላይ እንደሚገኙ ከፕሮፌሰሩ ጽሑፍ በኛና በነሱ የነገሮች ግጥምጥሞሽና ምስስሎሽ እያዘንኩ ተረድቻለሁ፡፡ የኛም የነሱም ችግር አንድ ነው ማለት ነው፡፡ እኛ፣ ኤርትራውያኑ እነበረከትና ስብሃት ገደሉን እንላለን፤ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን ደግሞ ‹ትግራውያኑ› እነስብሃትና በረከት እነሱን ኤርትራውኑን ገደሉን እያሉን ነው፡፡ ማን ማንን መግደሉ ለጊዜው ለውጥ አያመጣም – ትኩረት ሊሰጠውና ሊቆምም የሚገባው ግድያው ነው፡፡ ይህን የተቀናበረ ታሪካዊ የሀገርና የሕዝብ ግድያና ጭፍጨፋ ማን ነው የሚያቆመው? እነዚህ ታሪካዊ የጋራ ጠላቶቻችን ቅጥረኞች(mercenaries) ምን እስኪያደርጉን ነው የምንጠብቀው? በኛ ስም እየማሉና እየተገዘቱ እስከመቼ ነው ግድያቸውን የሚቀጥሉት? ዐይጥ በበላ እስከመቼ ነው ዳዋ እየተጨፈጨፈ የሚዘልቀው? እንደኔ እንደኔ ሥጋዊ ሞት ከመንፈሳዊ ሞት በጣም ተመራጭ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ታላላቅ ሰዎች የሚፈሩት ሞትን ሳይሆን አሟሟትን ነው፡፡ ነገሩ ‹ከሞቴ አሟሟቴ ያስፈራኛል› እንደሚባለው ነው፡፡ የፕሮፌሰሩ አባባል እውነት ከሆነ የሞተችው ኢትዮጵያና ሕዝቧ ብቻ ሳይሆኑ ሳትወድ በግዷ የተለየቻት ልጇ ኤርትራም ናት ማለት ነው፡፡ ያሳዝናል፡፡

በእኔ እምነት እናትና ልጅ እንደተለያዩ አይቀሩም – በግሌ ያን ጊዜ ልደርስበት ወይ ላልደርስበት እችል ይሆናል – ግን ላምና ጥጃ በርግጥ ይገናኛሉ! ይህን ስል – ማለትም ‹እደርስበት ወይ አልደርስበት ይሆናል› ብዬ በኩራት ስናገር የስድስተኛውን ስሜቴን ‹ትንቢት› ለመግለጽ ያህል እንጂ የአንድ ትንኝ ወደ አንድ ታሪካዊ ኹነት(An historic event which really is inevitable!) መድረስ ወይ ያለመድረስ ጉዳይ አሳስቦኝ አይደለም፡፡ ስትፈልጉ ቅዠት ወይም ቅብዥር በሉት ኢትዮጵያና ልጇ ኤርትራ በአዲስ መልክ ይዋሃዳሉ፡፡ የተበለሻሹ ነገሮች ተቃንተው ይስተካከላሉ፡፡ ይህ የሚሆነው ግን ቂም በቀልና ጥላቻ፣ ዘረኝነትና ጎጠኝነት ተወግደው ሰው እንደውሻ ደምና አጥንት እያነፈነፈ ሳይሆን በሰውነቱ ብቻ ሲሳሳብና ሁሉም ዜጎች በአንድ የወል ሀገራዊ ስሜት ሲተሳሰሩ ነው – የመለስ-ኢሳይያስ የትግራይ ትግሪኝ ዘፈን ቅኝት ወረቱን በመጨረስ ከስሞ የኢትዮጵያዊነት ሥልት ሲናኝ፡፡ ይህን የተቀደሰ ትውልዳዊ ኃላፊነት በብቃት የሚወጡ ዜጎች በቅርብ ይሾማሉ፡፡ በቤተ ሙከራ ተሠርተው እንደዕርዳታ ስንዴ ለየጎጡ የተከፋፈሉ ባንዲራዎች ይቃጠላሉ፤ የዚህ መሠሪ ተንኮል ጠንሳሾች፣ አስጠንሳሾችና አራማጆችም በገሃድ መሞት እንደጀመሩ አንድ ባንድ ግን ሁሉም ተራቸውን ጠብቀው ያልቃሉ፤ በሰማይም በምድርም ተረግመዋልና – በደም ባህር የሚዋኙ ናቸውና – በሕዝብ የምሬት ዕንባ ዶፍም በስብሰዋልና ዘር አይወጣላቸውም፤ ለነሱ የተፈቀደችዋ ዘመን ይህቺ የአሁኗ ጊዜ ብቻ ናት – ባለቻቸው ጊዜ ይደሰቱ፤ ይጠጡ፤ አንዳቸው በሌላኛቸው ቤት ይሸራሞጡ፤ አንዳቸው የሌላኛቸውን ልጅ ያሳድጉ – ከእርጉማን የሚጠበቅ የልክስክስነት ባሕርይ ነውና፤ ዳንኪራና ጮቤም ይርገጡ (የዐዋጁን በጆሮ ባትሉኝ እነዚህ የታሪክ ጉዶች እኮ አልጋንም የሚጋሩና ‹የተቀደሰውን ለውሾች አውጥተው የሚጥሉ› ጋጠወጦች ናቸው! አንዳችም ማሠሪያና የሚፈሩት ነገር የሌላቸው ከሃይማኖትም ከባህልም ማዕቀፎች የወጡ ስዶች እኮ ናቸው!)፡፡ ታዲያን እነሱ ሰይጣንን ይዘው ይህን ያህል ተዓምር የሠሩ እኛ እግዚአብሔርን ይዘን ከነሱ የበለጠ ልዩ ተዓምር እንዴት አንሠራ!? “እመን እንጂ አትፍራ!” መባሉም ለዚህ ነው፡፡ አይዞን ምዕመናን!!

ነጻነትን እንደቀድሞው የሙሤ ዘመን በኅብስተ መና መልክ ከሰማይ መጠበቅ ግን የዋህነት መሆኑን እንረዳ፡፡ ፈረንጆች “There is no free lunch!” ይላሉ፡፡ ምን ማድረግ እንደሚገባንና እንደሚቻለንም እናስብ፡፡ ቢያንስ ቢያንስ ግን ከክፋት ሥራ ተጠብቀን ወደፈጣሪ መዞር እንደሚገባን እንወቅ፡፡ ፈጣሪን ግማሽ መንገድ ድረስ ሄድን እንቀበለው፡፡ የሞተን ለመርዳት የሚተጋ ሰማያዊም ሆነ ምድራዊ ኃይል እንደሌለ እንገንዘብ፡፡ እናም ሕይወት እንዳለን፣ እንዳልሞትን፣ ለዲያብሎስ መንጋ እንዳልተንበረከክን የምናሳውቅበት የመነሳሳት ቅጽበት እንዲፈጠር እንትጋ፡፡ ያ ጊዜ ደግሞ አሁንና ዛሬ ነው፡፡ የኛን የቤት ሥራ ከሠራን ቀሪው ቀላል ነው፡፡ ለመሆኑ አሁን ፈጣሪ ምን እየሠራ እንደሆነ እናውቃለን? አዎ፣ ሁሉንም ባናውቅም ይህችን ያህል የምናውቅ ግን አለን፡- ‹ቁናውን እየሰፋ ነው› ወይም ‹ሰፍቶ ጨርሷል›፡፡ መሥፈር ሲጀምርስ? እሱን አያድርስ!ሦርያን ያየ፣ ሊቢያን ያዬ፣ የመንን ያዬ፣ ሩዋንዳን ያዬ፣ማሊን ያዬ፣ቱኒዚያን ያዬ… በእሳት ሊጫወት ማሰብ የለበትም፡፡ ግን ግን ‹የዱባ ጥጋብ ካለስንቅ ያዘምታል› መባሉ ለካንስ እውነት ነው? ውድ ወያኔዎች – መጥፊያችሁ ደርሷል! መጥፋታችሁ እንጂ እንዴት እንደምትጠፉ ግን እኛም እናንተም አናውቅም – ከፈጣሪ በስተቀር፡፡

በመሠረቱ ገዢዎች ይሳሳታሉ፡፡ እንዲያውም የማይሳሳት ገዢ ማግኘት የሚቻል አይመስለኝም፡፡ በዚህች ምድር ፅድቅን ስለማንጠብቅ ለምሳሌ ባገራችን የመንግሥትን ሥልጣን የሚይይዘው ከበደም ይሁን ሐጎስ ወይም ዘበርጋም ይሁን ሂርጳሳ በአንጻራዊነት እገሌ ከእገሌ በዚህ ወይ በዚያ ጉዳይ ይሻላል ማለት እንችል እንደሆን እንጂ በአስተዳደር ረገድ ፍጹም እንከን የለሽ የመንግሥት አካል አናገኝም፡፡ ከዚህ አንጻር የአሁኑን የወያኔ አገዛዝ ካለፉትም ሆነ ወደፊት ይመጣሉ ብለን ከምንጠብቃቸው ጋር ስናወዳድረው በጥፋት ተልዕኮው ወደር የማይገኝለት መሆኑን መገንዘብ አያዳግተንም፡፡ ፕሮፌሰር ተስፋጽዮን – የውጭ ሀገር ሰው በመሆናቸው ፕሮፌሰር መድኃኔ ልበልና ባባታቸው ስም ልጥራቸውና – ፕሮፌሰር መድኃኔ በጥናታቸው እንደጠቆሙት የአንድ ሀገር አመራር ትልቁ የሞራል ዝቅጠት በሚያስተዳድረው ሕዝብ መሀል ግርድና አመሳሶ እያወጣ ራሱንም ወደ አንድ ሸጥና ጎጥ እየወተፈ ሌሎችን በወርቅነትና በኩበትነት እየፈረጀ ሲያንጓልል ነው፡፡ ይህ በታሪካችን ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ መቅሰፍት – በምንም መንገድ ሊሽር የማይችል ጠባሳ መሆኑ ሳይረሳ – ምን ያህል መሪዎቻችንን ከስብዕና በታች እያወረደና በመዘዙም እኛን ከመኖር ወዳለመኖር እየለወጠን እንደሚገኝ ከተረዳን ቆይተናል፡፡ ከሞላ ጎደል ሁሉንም የሀገሪቱን የመንግሥት ሥልጣን በቀጥታና በተዛዋሪ ከያዘ የአንድ ሀገር የፖለቲካ አመራር ቡድን ውስጥ 3.6% ብቻ ኢትዮጵያን እንደእናት ሀገር የሚቀበል ሆኖ ሲገኝ ሌላውና 96.4% የሚሆነው በትግራይ እናት-ሀገርነት ሲጸና ከዚህ በላይ ማፈሪያ የታሪክ አንጓ የለም – በጭራሽ! ትግራይ ውስጥ በናሙናነት ከተወሰደ የሕዝብ ክፍል መሀል 82.1% የሚሆነው ‹ቀንደኛ ጠላትህ ማን ነው?› ተብሎ ሲጠየቅ ‹አማራ ነው› ካለ አስታራቂ የሚያስፈልገው ግን ቀን ሊሰጠው የማይገባ ችግር አለ ማለት ነውና ሀገር ሰላም ብለን መተኛት የለብንም፡፡ እነዚህን ዘግናኝ መረጃዎች በዝርዝር ለማንበብና በሃዘን ለመቆራመድ የፈለገ ሰው የተጠቀሰውን የፕሮፌሰሩን ጽሑፍ ማንበብ ነው፡፡ የአጻጻፍ ሥልታችንና የይዘታችን ድምፀት (style and tone) ይለያይ እንጂ እኔን መሰሎች ዘባራቂ የብዕር ‹ጦረኞች›ም የምንለው ይሄንኑ ነው፡፡ ችግር አለ! (‹ነገ እዚህ አካባቢ ቤት ይቃጠላል!› ነበር ያለችው የደሴዋ ዕብድ ሴት በማግሥቱ ራሷ ልታጋየውና ጉድ ልትሠራቸው?) ችግሩ ታዲያ እንደሌሎች ሀገሮች ችግር ሳይወሳሰብና ጥርስ ወደሌለው የተቃቃሩት መንግሥታት(DN/Disunited Nations) መሮጥ ሳይመጣ ከአሁኑ እንፍታው ነው እያልን ያለነው፡፡ ሦርያ ላይ የሚጮህ ጅራፍ ጊዜውን ጠብቆ ኢትዮጵያ ውስጥ አይጮህም ብሎ ማሰብ የለየለት ድንቁርናና ትዕቢት ነው፡፡ ትብታብም ይፈርሳል፤ ፍርሀትም ይጠፋል እያልን ነው የምንገኝ፡፡ አሁን ዓለምን የገዙ የመሰላቸው የትግሬ ወያኔዎች በሕዝብ ላይ መፈንጠዛቸውንና ጥሬ እንትናቸውን በጭቁኑ ወልደማርያም ላይ መጣላቸውን ትተው ወደኅሊናቸው ይመለሱ ማለት ኃጢኣት አይደለም፤ ትርፍ እንጂ ኪሣራም የለውም፡፡ ችግሩስ ቁስልን እየሸፋፈኑ ይብስ እንዲነፈርቅ ማድረግ ነው፡፡ በጭቁን ዜጎች ላይ ፋንድያን ማለትም እንትንን እዬጣሉ ለስንት ዘመን መኖር እንደሚቻል የጋዳፊንና የኢዳሚንን የሙት መንፈስ በጠንቋዮቻቸው አማካይነት ያስጠይቁና ከጥጋብ መንገድ በአፋጣኝ ይውጡ ነው እያልን ያለነው፡፡ በተረቱ ከተራበ ለጠገበ አዝናለሁ መባሉ የጥጋብን መዘዝ ለማጠየቅ ነው፡፡ ሰከርክም ልባል መረቀንህ – አሁንም እደግመዋለሁ፡- እነዚህ ዋልጌ የዲያብሎስ ውላጆች ባስከተሉት መዘዝ ኢትዮጵያ በ‹ጥቂት› ትግሬዎች እጅ ገብታ በወለድ አገድ እየተመጠመጠች ናትና ይህ ታሪክ ይቅር ሊለው የሚከብደው አሰቃቂ ድርጊት ተጨማሪ ጥፋት ሳያስከትል በአስቸኳይ ይቁም፤ ብሔራዊ ዕርቅ ይፈጠር፤ ፖለቲካችን ሰው ሰው ይሽተት፤ በዘረኝነት ከርፍቷል፤ በጎጠኝነት ገምቷል፤ በሙስና ጠንብቷል – የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ መጥፎ ጠረን የዚህችን ዓለም አድማሳዊ ድንበር አልፎ ጽርሐ አርያምን እያጥነገነገ ነውና በቶሎ መፍትሔ ካልተፈለገለት ጦስ ጥንቡሱ ከኢትዮጵያ ድንበሮችም ይሻገራል እያልን የምንገኝበት ሁኔታ ተፈጥሯል የሚል ግንዛቤ ወስደናል እያልን ነው – በበረከት ስምዖን አማርኛ፡፡ ለዚህ ሁሉ ችግራችን ዋናው መፍትሔ ‹አማራ ገዳይ! ትግሬ ገዳይ!…› የሚለው የጅሎች ፉከራና ሽለላ ሳይሆን መደማመጥና መግባባት ብቻ ነው፡፡ ይሄኛው የሃያና ሠላሳ ዓመት አበቅቴ ለነዚህ ቢሆን ያኛው የሠላሣና ዐርባ ዓመት አበቅቴ ደግሞ ለነዚያኞቹ ይሆናል፤ የዚህች ምድር ነገር የጽዋ ማኅበር ዓይነት ነው – ማንም የማንንም ዝክር ቀፈቱ እስኪያብጥ ሰልቅጦ ሰልቅጦ ሲያበቃ በ‹ጨዋታው ፈረሰ – ዳቦው ተገመሰ› የልጆች ጨዋታ የበላ የጠጣትን ሳይከፍል ከማኅበሩ ልሰናበት ሊል አይችልም – በየትኛው ሒሳብ! ዛሬ ለተቀናጀ መንግሥታዊ የበቀል ጥማት ማርኪያ የሆነ ሕዝብ በቀል አርግዞ በተራው በዳዮቹን ለመቅጣት ምቹ ቀንን የሚጠብቅ እንዳይሆን የክፋት ምንጭን እናድርቅ እያልን ነው – አንዳንድ “የሩቅ ተመልካቾች”፡፡ ማሰብ በተሳናቸው የትግሬ ወያኔዎች፣ ይሉኝታንና ሀፍረትን ሸጠው በበሉ ወንድምና እህቶቻችን እያየነው ያለነው አበሳ የሰቆቃችን የመጨረሻ ምዕራፍ ይሁንና ከዚህ መጥፎ ታሪክ ትምህርት ቀስመን የወደፊቱን ትውልድ ከመርዘኛ ፖለቲካና ፖለቲካው ካበሰበሰው አጠቃላይ ማኅበረሰብኣዊ ቀውስ ነጻ እናውጣው፡፡ በሎሚ ተራ ተራ ዜጎች ለማያባራ ስቃይ መዳረግ የለባቸውም፡፡ መለስ በስብሶ የሞተው፣ ኢሳይያስ ለያዥ ለገራዥ አስቸግሮ ሞትን በሚያስመርጥ የቁም መቅበዝበዝ ላይ የሚገኘው አላንዳች ብልሃት አይደለምና ዜጎች ወደጤናማ ኅሊናቸው ባፋጣኝ ይመለሱ – ቢያንስ ከነዚህ ሁለት የጠፉ ዜጎች እንማር፡፡ በሀገር ዕርቅ ይውረድ፡፡ ቂም በቀል ይወገድ፡፡ የጠገበ ይስከን፤ የተራቡና የተጨቆኑ ወገኖቹንም ያስብ፤ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባም ሆነች አሥመራ(I can imagine,) የሎጥን የሶዶምና ገሞራ የእሳት ዝናብ የሚጠሩ የሲዖል ከተሞች ሆነዋል ብንል አልተሳሳትንም – ብዙኃን በርሀብ አለንጋ እየተገረፉ ጥቂቶች በሚመዘብሩት የሕዝብና የሀገር ሀብት ይሠሩትን አጥተው በነውረኝነት ጎዳና መትመምን መርጠዋል…እኛም እነሱም አናሳዝንም? – በሬ ካራጁ ጋር ይውላል፡፡ ቂም በቀል ቂም በቀልን ይወልዳል፡፡ አመፅ አመፅን ይወልዳል፡፡ ፍቅርና መተሳሰብ ግን የበቀል ቁርሾን አስወግዶ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመሠረት ያደርጋል፡፡ ዛሬ አንድ የሚፏልል ጥጋበኛ የወያኔ ካድሬ በቢሊዮን የሚገመት ሀብትና ንብረት ቢያከማች – እመኑኝ – አይበላውም፤ መቼምና የትምም አይጠቀምበትም፡፡ ‹እባካችን› ልብ እንግዛ፡፡ እርግጥ ነው ሀብታምና ፖለቲከኛ በአብዛኛው ደናቁርት ስለሆኑ ዛሬን እንጂ ነገን ማሰብ አይቻላቸውም – ለማሰብ የሚጠቀሙበት ሆዳቸውን እንጂ ጭንቅላታቸውን አይደለም፡፡ አንጎላቸው የተቃኘው በሶስት ነገሮች ብቻ ነው፤ እነሱም ሥልጣን፣ ገንዘብና ወሲብ ናቸው – አንቀሳቃሽ ሞተሮቻቸው እነዚህ ናቸው፤ የእነዚህን ፍላጎቶቻቸውን ጥሪ ለመመለስ ሲሉ ከሰማይ በታች ከምድር በላይ የማይሠሩት ወንጀልና ኃጢያት የለም፡፡ በእነዚህ ሦስት ፈታኝ ነገሮች ያልታወረ ሰው ግን ብፁዕ ነው – አእምሮውንም በአግባቡ ይጠቀማል፤ ከቅሌትና ውርደትም ይድናል፡፡ አቅሉን ስቶ ለነዚህ ነገሮች የሚንበረከክ ከሰውነት ተራ ይወጣል – በመጨረሻው መጨረሻ ላይ ታዲያ ውድ ዋጋ ይከፍላል፡፡

በተረፈ ትግሬ፣ አማራ ፣ ኦሮሞ የምንለው ነገር የቋንቋ ፈሊጥ እንጂ ተጨባጭ የሆነ አመክንዮኣዊ ልዩነት የላቸውም፡፡ በነዚህ የጎሣና የብሔር ስሞች የሚንቀሳቀሱ ሰዎችን ሌቦች በሏቸው – አጭበርባሪዎች፡፡ ለአብራኩ ክፋይ ለልጁ ግድ የሌለው – ሚስቱን በወጣ በገባ ቁጥር የሚነተርክ – ከጎረቤቱ ጋር ዐይንና ናጫ ሆኖ የሚኖር፣ ለቸገረው ወንድሙ አምስት ሣንቲም የማያቀምስ፣ ለተጨነቀ ጓደኛው አሥር ብር የማያበድር… ስግብግብና ፍቅርን የማያውቅ ዜጋ ለሥልጣን አራራውና ለግል ኢኮኖሚያዊ ጥቅሙ ሲል የዚህን ወይም የዚያኛውን ብሔረሰብ ስም በታፔላነት አንስቶ ቢጮህ እውነት አይምሰላችሁ፡፡ ለማያውቅህ ታጠን በሉት፡፡ በአባቱ ኦሮሞ በእናቱ አማራ የሆነ ለማን ሊታገል ነው የጎሣ ቡድን ውስጥ የሚገባው? ለምሳሌ ስብሃት ነጋ ኤርትራዊነቱንም ኢትዮጵያዊነቱንም ትቶ ለትግራይ የበላይነትና ለወያኔ ንግሥና ቆሜያለሁ የሚል ሰው ነው ይባልለታል፡፡ ይህ ሰው፣ እውን ለትግራይ ይጨነቃል? ለትግራይ ሕዝብስ እንቅልፍ አጥቶ ያድራል? እንዲያ ከሆነ ስንትና ስንት ትግራውያን በርሀብ ሲሰቃዩ እንደማንኛውም ወገናቸው ሲለምኑና ሲቸገሩ በምዝበራና በሕገወጥ የገንዘብ ክምችት ብዙ ቢሊዮን ብር አለው ከሚባልለት ኤፈርት ትንሽ ገንዘብ ቆንጠር አድርገው ለምን አይረዱም? አዎ፣ ብዙ ነገሮች የታይታ ናቸው፤ ብዙ ነገሮች የብልጭልጭ ናቸው፡፡ የእንትና ብሔረሰብ ይልና በቁስልህ ሊገባ ይፈልጋል – ቁስልህን ተገን አድርጎ ወደልብህ ለመግባት ከሞከረ በኋላ ግን የርሱን ቁስል ባንተ ሀብትና ጥሪት ፈውሶና የድህነት ጭቅቅቱን አራግፎ ያንተን ቅስል ይብስ ያነግልብሃል፤ አንተም ከነድህነትህ እህህ እያልክ ትኖራለህ – ለሌላ ዙር እንግልትም ትጋለጥና የራበው አዲስ ተኩላ ከጫካም ይሁን ከከተማ መጥቶ በአዲስ መልክ ይግጥሃል፡፡ ሕይወት እንዲህ ናት፡፡ አንዱ መሰላል ነው – ሌላው በመሰላሉ የሚወጣ ነቀዝና ተምች ነው፡፡ ታችኛው ግን ሞኝና እንደነዱሽ እንደሆነ ይቀራል፡፡ እነገሌ መጡብህ ካሉት እየደነበረ ከየሽርንቁላው ይወጣና አሰለጦች ባዘዙት መሠረት በንጹሓን ላይ ጦሩን ሰብቆ መሰል ወገኖቹ ላይ ይዘምታል፤ ብዙኃኑ ታችኛው የጥቂቶች ላይኞች መጠቀሚያ ጎጋ ነው፡፡ ከስቅሎ ስቅሎ በፊትም ሆነ በኋላ የዓለም ታሪክ እንደዚሁ ነው፤ ጥቂት ብልጦች ብዙኃንን ዕቃ’ቃ እንደተጫወቱባቸው ዓለም ‹ፍጻሜዋ ደረሰ›፡፡ አንዳንዱ እንደተሸወደ የሚገባውና ዐይኑን የሚገልጠው ራሱ ችግር ውስጥ ከገባ በኋላ ነው፡፡ እነመለስ፣ እነኢሳይያስ በዚህ መልክ ሲጫወቱብን ከቆዩ በኋላ ነው እንግዲህ እነሱም በፋንታቸው የማይቀርላቸውን መሪር ጽዋ ሊጎነጩ የመጨረሻው ፊሽካ ብቻ እንደቀረው አምነን ያቺን የፍርድ ቀን በጉጉት እየተጠባበቅን የምንገኘው፡፡ በቃ፡፡

የነስብሃትና መሰሎቹ አገርና ወገን ሆዳቸው ነው፤ ሃይማኖታቸው ከፍ ሲል እንደጠቀስኩት ወሲብና መጠጥ ነው፡፡ የሚሉት ሁሉ ለማደናገሪያነት እንጂ የአንጀታቸውን አይደለም፡፡ ትዳርን የማያከብር ዘልዛላ፣ የክፉ ቀንን የትዳር ጓደኛና የልጆቹን እናት ሲያልፍለት አስወጥቶ የሚጥል ጉደኛ፣ ልጆቹን የማይሰበስብ የሌሊት አውሬ ዳንኪረኛ፣ በሽምግልና ዕድሜው ከልጅ ልጆቹ ጋር የሚማግጥ ሠካራም ነውረኛ… በምን ሒሳብ ለሀገር ጠቃሚና ለወገን ተቆርቋሪ ሊሆን እንደሚችል አስቡት፡፡ ይቅርታ – ባደጉ ሀገሮች ከሕጻንነት ጀምሮ የሚመዘገብ የግል ሕይወት ይዞታ ለሥልጣን ዕጩነት ታላቁ መለኪያ በመሆኑ ይህን ስለባለሥልጣኖቻችን ዋልጌነትና እንስሳነት የምላችሁን ነገር በምን አገባህ አናንቃችሁ አትመልከቱት – በኛ ሀገር ደግሞ በተገላቢጦሹ ባለጌ ባለጌው እየተመረጠ ይመስላል ለሥልጣን የሚበቃው – አልጋውና ወንበሩ የሚወደው ጥፍራሞችንና መደዴዎችን መሆን አለበት፡፡

ሀገር ወዳድነት ላግጣ አይደለም – ሀገርን የመምራት ጠንካራ ጎን ደግሞ ከቤተሰብና ከራስ ጤናማ ኑሮ ይመነጫል፤ በሽተኛ ሰው እንኳንስ ሀገርን ራሱንም መምራት አይችልም፤ ሠካራምና እንደልቡ ተናጋሪ ሰው ደግሞ ከዕብድ ተለይቶ አይታይም፡፡ አሁንም ከዚህ ከምለው ነጥብ አኳያ እነስብሃትን ‹ለማያውቋችሁ ታጠኑ!› በሉልኝ፡፡ መቆሚያቸውን ለማደላደል የትግራይን ሕዝብ ‹ያንተዎቹ ነን፤ ከኛ ወዲያ ላንተ የተሻለ አማራጭ የለም፤ አማሮች ከመጡ ሥጋህን ዘልዝለው ይበሉሃል…› በማለት ሊያስፈራሩበት እንጂ በውነት የትግራይነት ስሜት ኖሯቸው አይደለም፡፡ ቀደም ካለ የትግላቸው ወቅት ጀምሮ እስካሁን ድረስ በትግራይ ሕዝብ ላይ የሠሯቸው ወንጀሎች ይህን የሚሉትን ነገር አያረጋግጡላቸውም፡፡ ብሎም ቢሆን ለትግራይ ምድርና ሕዝብ የሠሩት የልማትና የዕድገት እመርታ የለም ለማለት እንዳልሆነ በትህትና ላስታውስ እወዳለሁ፡፡ ሀገራችን ለሚሉት ብዙ ሠርተዋል – ይሁን፡፡ ጥጃ ጠባ እሆድ ገባ ነው፡፡ ቦዕ ጊዜ ለኩሉ ፤ ሌሎቹም በጊዜያቸው ይለማሉ፡፡

ነገር ቢበዛ በአህያ አይጫንም፡፡ ቀጥሎ በቅንጭብ ያመጣሁትን የፕሮፌሰርን ንግግር አዳምጡ፡-

ኤርትራ ዛሬ በሁሉም መስፈርት አስጠሊና የተገለለች አገር ሆናለች። ሕዝባችን ባሁኗ ወቅት ደቃቃዋ የፖለቲካ መብት እንኳ የሌለው፡ ሰብኣዊ መብቱ ፈጽሞ ያልተጠበቀ፡ እጅግ ከባድ ድህነት ያጐሳቈለው፡ ማህበራዊ ኑሮው ሰብኣዊነት የራቀው፡ የህላዌው ሁኔታ በፍርሃትና ስጋት ተበክሎ የደህንነትና የዋስትና ጭላንጭል እንኳን የሌለው ነው፡፡ የወጣቶቹ ሁኔታ በተለይ እጅግ የሚያሳዝን የከበደ ትራጀዲ ሆኗል፡፡ ወጣቱ ሊደሰትበት በሚገባ አፍላ ዕድሜው በግድ እየታፈሰ ሳዋ ወይም አገልግሎት ለሚባለው ባርነት እየተዳረገ ነው። ወጣቶቹ ከዚያ ገሃነማዊ ሁኔታ ለማማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ፡ ከስደት ወደ ስደት አገር ለመሸጋገር ሲሞክሩ አንዳንዱ ባሕር ውስጥ እየሰጠሙ ለምህረት-የለሽ ዓሳ ሲሳይ እየሆኑ ነው፣ አንዳንዱ ደግሞ በአረሜኔዎች ተጠልፈው እንደ እንስሳ እየታረዱ ኩላሊታቸውና ሌላ ውስጣዊ አካላቸው እየተነጠቀ ሬሳቸው በሳሃራና በሲናይ ምድረ-በዳዎች እየበሰበሰ ነው፡፡ ይህ መከራ በጣም የሚዘገነን፡ ስትሰማውም እጅግ የሚያስደነግጥ ነው።

ለመሆኑ ዜጎች ለዚህ አሰቃቂ መከራ ሲጋለጡ አስመራ ውስጥ ያለው መንግሥት ምን እየሰራ ነው? የሚል የዋህ ጠያቂ አታጣም። አስመራ ውስጥ ያለው አምባገነን ኢሳያስ የሚመራው መንግሥት እውነትም ኤርትራዊ መንግሥት አይደለም፣ በኤርትራውያን ላይ የጥላቻና የቂም በቀል ቁርሾ በያዙ፡ ድብቅ ሴራ ባላቸው አካላት የቆመ ቡድን (ካባል) ነው። እነኚህ ሴረኞች በትውልድ ትግሬዎች ቢሆኑም ኤርትራዊያን ሊሆኑ ይችሉ የነበሩ፡ ሆኖም ግን ምንነቱ ባልተመረመረ ችግር ምክንያት፡ ሕዝባችንን በሚያጠቃ መልኩ የ“ትግራይ-ትግርኚ” ንድፍ አዝማቾች ለመሆን የመረጡ ናቸው።

ከዚህ ጋር በተዛመደ ሊነሳ የሚገባው አሳዛኝ ነገር አለ። ለብዙ ዓመታት ከበረሃ ትግል ጀምሮ እስከ ህግዲፍ መንግሥትነት ድረስ ኢሳያስን ያገለገሉ፡ እንደ እነ ሃይለ ወልደትንሳኤ፡(ድሩእ)፡ማሕሙድ ሸሪፎ፡ እስጢፋኖስ ስዩም፡ ጴጥሮስ ሰለሞን፡ ጀርማኖ ናቲ፡ ኣስቴር ፍስሓጽዮን፡ በራኺ ገብረስላሴ፡ ዑቕበ ኣብርሃ፡ ብርሃነ ገረዝጊሄር የመሳሰሉ፡ በዛ ገሃነማዊ የዒራዒሮ እስር ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው አንዳንዶቹ ሞተው፤አንዳንዶቹ ደግሞ እየተሰቃዩ ሞታቸውን ይጠባበቃሉ። እነኚህ ታጋዮች የፈጸሙት ወንጀል የለም። ኤርትራ ውስጥ ዲሞክራሲ እንዲጀመር ጥገናዊ የሆነ ለውጥ በመጠየቃቸው ብቻ ነው ለዚሁ አበሳ የተዳረጉት። እነዚህንና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞችን የምትመለከት አንዲት አንገብጋቢ ነጥብ አለች፤ እርስዋም እኚህ በኢሳያስ የሚታሰሩና በተለያየ ዘዴ እየተገደሉ ያሉት ዜጎች በሙሉ ንጹሃን “ኤርትራዊያን” መሆናቸው ናት። በተቀረ፡ ብዙ ሰዎች እንደነገሩኝ ከሆነ፡ በትውልዳቸው ትግሬዎች የሆኑ ኤርትራውያን በኢሳያስ መንግስት እንዲገደሉ ወይንም እንዲታሰሩ የተደረጉ የሉም። ይህ አሳሳቢ የሆነ ትዝብት ነው!!

***
በጥያቄው የተሳተፉት የዛሬው የትግራይ ፖለቲከኞች (ወይም የፖለቲካ ተዋንያን – ማለት ኤሊት) እናት አገራችሁ ማነች ለሚለው ጥያቄ የሰጡት መልስ በመንፈስም በአስተሳሰብም ኤርትራውያን ፖለቲከኞቹ ከሰጡት መልስ አሳሳቢ በሆነ መጠን ይለያል። ከተሳተፉት የትግራይ ፖለቲከኞች መሃል እናት አገራችን ኢትዮጵያ ነች ብለው የመለሱ 3.6% ብቻ ናቸው። አብዛኛዎቹ በጥያቄው የተሳተፉ የትግራይ ፖለቲከኞች ግን እናት አገራችን ትግራይ ነች ነበር ያሉት። ኢትዮጵያ አላሉም። አቶ ስብሓት ነጋ ይህንን ጥያቄ ሲመልስ፡ ላንዳፍታ “ዝግ ካለና ካመነታ በኋላ”፡ እናት አገር ሲባል በአእምሮው ውስጥ ድቅን የምትልበት “ትግራይ“ መሆኗን ገልጿል። አንደዚሁም አቶ ጸጋይ በርሄ – እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የትግራይ ክልል ፕረዚደንት የነበረና፡ ዛሬ ግን የሕዝባዊ ወያነ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አባል የሆነው – ይህ ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ ሳያመነታ በቀጥታ “እናት አገሬ ትግራይ ነች“ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ነች አላለም። “ብትግሬነቴ በኩል አድርጌ ነው ኢትዮጵያዊ የምሆነው“ በማለት ግን መልሷን ስስ በሆነች ኢትዮጵያዊነት ሸፋፍኗታል።

ይህ እናት አገራችን ትግራይ እንጂ ኢትዮጵያ አይደለችም የሚል መልስ ከታወቁ የሕዝባዊ ወያኔ አመራር አካሎች ሲደመጥ የሚያሳስብ ክስተት ነው። (ለምሳሌ አንድ በኤርትራዊ የፖለቲካ ድርጅት አመራር ውስጥ ያለ ሰው እናት አገሬ ብሎ ኤርትራን ከመጥቀስ ይልቅ ባርካን ወይም ቢለንን ወይም ኩናማን ቢጠቅስ፡ ወይንም ደግሞ ከደጋማው አውራጃዎቻችን – ማለትም ሓማሴን፡ አከለጉዛይ – ብሎ ቢጠቅስ፡ ለኛ ለኤርትራውያን እጅግ የሚያሳስበን ይመስለኛል!!

በስዊድን ከስደተኞች ጉዳይ አጥኚ ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ

Sunday, February 24th, 2013

አቶ ፋንታሁን አሰፋ Fantahun AssefaEthiopia Zare(እሁድ የካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. February 23, 2013)፦ በስዊድን የሚገኘው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማኅበር የኢትዮጵያን ጉዳይ ከሚከታተሉ የኢሚግሬሽን ተወካዮች ጋር ፌብሪዋሪ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ውይይት አደረገ። ይህንኑም ጉዳይ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እስር ቤት ከርመው የተፈቱት ጋዜጠኞች ማርቲን ሼቢ እና ዮሃን ፐርሾን ለኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እንዳስረዱ አቶ ፋንታሁን ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

በስዊድን የስደተኞች ማኅበር ከስደተኞች ጉዳይ አጥኚ ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ

Sunday, February 24th, 2013

አቶ ፋንታሁን አሰፋ Fantahun AssefaEthiopia Zare(እሁድ የካቲት 17 ቀን 2005 ዓ.ም. February 23, 2013)፦ በስዊድን የሚገኘው የኢትዮጵያ ስደተኞች ማኅበር የኢትዮጵያን ጉዳይ ከሚከታተሉ የኢሚግሬሽን ተወካዮች ጋር ፌብሪዋሪ 6 ቀን 2013 ዓ.ም ውይይት አደረገ። ይህንኑም ጉዳይ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ እስር ቤት ከርመው የተፈቱት ጋዜጠኞች ማርቲን ሼቢ እና ዮሃን ፐርሾን ለኢሚግሬሽን ባለስልጣናት እንዳስረዱ አቶ ፋንታሁን ገልጸዋል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 24, 2013

Sunday, February 24th, 2013
News, Radio Magazine or Mestawot

የኢትዮጵያ መለኮታዊ ዕጣ በንግሥተ አዜብ የፍርድ ሚዛን ላይ

Sunday, February 24th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የደም እንጀራ ከቴድሮስ ሐይሌ

Sunday, February 24th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ያረቢ ኑ ባሲ!!!..ያረቢ ኑ ባሲ… ኢትዮጵያዊያንን ከነ ህይወታቸው እየቀበሩ መቅጣት.. በግሩም ተ/ሀይማኖት

Sunday, February 24th, 2013

አንድ ወዳጄ ከወዳጅም የሞያ ጓደኛዬ የሆነው ጋዜጠኛ ግርማ እንድሪያስ የእህቱ ልጅ በባህር ወደ የመን ሲመጣ መያዙን ነገረኝ፡፡ ትንሽ ቆየ እና እህቱ ማለት የተያዘው ልጅ እናት ደወለች፡፡ እናት ጉዷን አላወቀችም፡፡ የመን መጥታ ችግሩን አላየች በምን ትወቅ? ደግሞስ ችግሩን ለማወቅ የግድ የመን መምጣት አለባት እንዴ? የለባትም፡፡ በየጊዜው ይጻፋል፡፡ ይነበባል፡፡ ግን ማንበብና ማስተዋል አንድ አይደለም፡፡ ልጇ ያን ነው የሆነው፡፡ ልጅ በሚውልበት እናት አትውል፡፡ በዛ ያለ ሰው እየሰማ እያየ ነው መልሶ በባህር የሚመጣው፡፡ ልጇ ደላሎች ጋር እንዳለና ወደ ሳዑዲያ ሊገባ እንደሚፈልግ ደላሎቹ ለማድረስ 3500 የሳዑዲ ሪያል መጠየቃቸውን ነገረችኝ፡፡

ወዲያው የገባኝን ያህል ገባኝ፡፡ የተባለውን ገንዘብ ብትልክላቸው እንደማያደርሱት አውቃለሁ፡፡ በዛ ላይ ልጁ ገንዘብ የሚልክልህ ሰው ስልክ ቁጥር እያሉ ሲያዋክቡት፤ ሲያሰቃዩት እናቱ ጋር አስደወለ፡፡ ስልኩ ስላልተነሳ ግርማ እንድሪያስ ጋር አውሮፓ ደውሏል፡፡ አውሮፓና አሜሪካ ከተደወለ ደግሞ እንዲህ በዋዛ አይፋቱም፡፡ ለግርማም ሆነ ለእህቱ አጓጓዥ ደላሎች ጋር ሳይሆን ያለው አፋኞች መሆናቸውን ብናገር አረ አይደለም ደላሎች ናቸው ተባልኩኝ፡፡ ክርክሩን በዝምታ አልፌ ልጁ እኔ ወደ አለሁበት ሰነዓ እንዲመጣ በተሰጠኝ ስልክ ቁጥር ደወልኩ፡፡

‹‹እህ ማነህ ጃል..ምን ኮነክ ነው? ማንን ፈለክ..›› የሚል ገጠርኛ ቃና ያለው አማርኛ ተናጋሪ አወራኝ፡፡ ልጁን እንዲያቀርብልኝ ስሙን ነገርኩት፡፡ ማውራት ያለብኝን ያህል አወራሁ፡፡ አከል አድርጌ ሳዑዲ ሳይሆን የሚሄደው ወደ ሰነዓ እንዲመጣ ምን ያህል እንደሚጠይቁ ተነጋገርኩ፡፡ ሁኔታዎችን እኔ በማውቀው መንገድ ለማስኬድ ከአፋኞቹ ጋር ተደራደርኩ፡፡ 1500 የሳዑዲ ሪያል እንድልክ ነው የተስማማነው፡፡ የተባለው ገንዘብ ተላከልኝና ላኩኝ፡፡ ልጁን ለመልቀቅ ማንገራገራቸው ለምን እንደሆነ ስለማውቅ ታግሼ እጠብቃለሁ፡፡ ገንዘቡ ከተላከላቸው እንደማይደበድቡት በተደጋጋሚ በሰማሁት መረጃ አውቃለሁ፡፡ ወዲያው ባይሆንም አንገራግረው ከቀናት በኋላ ለቀውታል ይደውልልሀል ተባልኩ፡፡

ሁለት ሶስት ቀን ምንም የለም፡፡ የሚያደርሱት ሀረጥ የተባለው ቦታ ድረስ ነው፡፡ ካለሁበት ሰነዓ 750 ኪሎ ሜትር አካባቢ ስለሚርቅ ይህን ያህል ርቀት ብቻውን ከመጣ ድጋሚ በሌሎች እንዳይያዝ እና ለእነሱ ስለተከፈላቸው ለሌላ እንዳያሳልፉት ተነጋግረን መክፈል ያለብኝን መሰዋእትነት ከፍዬ ለማምጣት ጉዞ ሀረጥ ወደሚባለው ቦታ አደረግሁ፡፡ ይህ ቦታ በግሩፕ የተደረጁ መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች ኢትዮጵያዊያኑን ስደተኞች ባህር ሲሻገሩ አፍነው ብር አስልኩ ብለው የሚያሰቃዩበት ቦታ እንደሆነ በተደጋጋሚ ዘግቤያለሁ፡፡ ወገኖቻችን ወደሚሰቀዩበት ቦታ ሀሙስ እለት(የካቲት 7 ቀን) እንደሚፈልጉኝ እያወኩ ስለሆነ የምሄደው ካልድ ከሚባል ጓደኛዬ ጋር ነው አካሄዴ፡፡ የእናትንም ሆነ የጓደኛዬን ጭንቀት ስላወኩ ስራዬን ትቼ፣ ካለችኝ ሳንቲም ላይ ቀናንሼ፣ ራሴን ለውጬ..ነው ችግር ቢገጥመኝ ብዬ ካልድን አስከትዬ ጉዞዬን የጀመርኩት፡፡ አሳዛኙ ነገር እኔ እናት ተግባብተን አልተግባባንም፡፡ ወይም አልተማመንም መሰለኝ፡፡ ያለምን ጥቅም ይህን ያህል መሰዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቴ፣ ትንስፖር ማውጣቴ፣ ስራዬን ጥዮ መሄዴ..ምን ቢጠቀቀም ነው ያሰኝ ይችላል፡፡ ከዚህ በፊት ብዛ ያለ ሰው ጥቅምህ ምንድን ነው? የሚሉኝ ስላሉ አይገርመኝም፡፡ ግን ከህሊና እርካታን መን አይነት ጥቅም እንለካው ይሆን? የጀመርኩት ጉዞ ትዕዝ የሚባለው የየመን ሶስተኛ ከተማ ላይ ተገደበ፡፡

ትዕዝ ላይ ያገኘኋቸው ሰዎችና የሰጡኝ መረጃ ግን ኢትዮጵያዊያን ምን እየጠበቅን ነው? ከዚህ በላይ ጭካኔስ በአለማችን ላይ ይኖር ይሆን? ያሰኛል፡፡ ትዕዝ የሚባለው ቦታ ተቅብሎ ያስተናገደን ልጅ ጋር የመጣ አንድ እንግዳ..ውይ እንግዳ አልኩ እንዴ? እኛው አስጠርተነው መሆኑን ዘነጋሁ፡፡ ታክሲ ስላለው እና ወደዛ መንገዱን ያውቃል ስለተባለ ያስጠራነው እኛ ነን፡፡ በጫዎታ ጫዎታ ስላየው እና ስለሚደረገው ያወጋን በስንተኛው ዙር ወግ ላይ እንደሆን በማላስታውሰው ጊዜ ‹‹..እነዚህ የሚያግቱት ጋር እኮ ሰው በቁሙ እየቀበሩ ማሰቃየት ጀምረዋል፡፡…›› ሰውነቴን ውርር አደረገኝ፡፡ እስካሁን ያልሰማሁት በመሆኑ ደነገጥኩኝ፡፡ በእርግጥ በአንድ ወቅት ወደ እዛ ስሄድ የሞተ ኢትዮጵያዊ የሚቀብሩበትን ቦታ አይቼዋለሁ፡፡ በጣም በጣም ሰፊ ነው፡፡ ግን እንዲህ በህይወት ያለ ሰው ይቀብራሉ ሲባል አልሰማሁም፡፡

‹‹ቅብር!..ቅብር?…በምን አወክ አንተ አይተሀል?›› ስል ጠየኩት፡፡ አላንገራገረም፡፡ አብሮት የመጣውን ልጅ እሱ ከባህር እንደመጣ ይዘውት ከእነሱ ጋር ለመስራ ሞክሮ ነበር፡፡ አሁንም ሄድ መለስ ይላል፡፡ አለና ልንቁስ ያለ ልጅ አሳየኝ፡፡ ወገኑን ከሚያሰቃዩ ጋር በመስራቱ ከሱ ጋር ማውራት ተጠየፍኩት፡፡ በጠላትኛ አየሁት ግን የሚሰጠኝን መረጃ እፈልገዋልሁ እና ሞባይል ስልኬን የተደወለልኝ አስመስዬ ነካካሁና ሪከርድ የሚለው ላይ አደረኩኝ፡፡ እንዲነግረኝ ጠየኩትም፡፡

‹‹አዎ! ግን ያየሁት ልጁ ራሱን ነው፡፡ የተቀበረውን፡፡››
‹‹ከተቀበረ ከየት አየኸው?››
‹‹እስከ አንገቱ ድረስ ቀብረውት አሰቃይተውት ከዚህ ከወገቡ በታች አልታዝህ ብሎት እየተንፏቀቀ ህክምና እንዲያገኝ ሀረጥ ካምፕ ሲገባ አይቻለሁ፡፡›› አለኝ፡፡ አላናገርከውም? ብዬ ለየጠኩት የሰጠኝ መልስ ግን በጣም ሰቅጣጭ ነበር፡፡ ልጁ በተፈጥው መስማት የተሳነው ስለሆነ እንዴት ላውራው አለኝ፡፡ ከዛ ወዲህ ወይም ከዛ በፊት እንዲህ አይነትነ ነገር አይቶ ሰምቶ እንደሆነ ስጠይቀው ከዛ በኋላማ እዚሁ ትዕዝ ውስጥ ትላንት የገባ ልጅ አለ፡፡ እዚህ ማር መሸጫ መደብሩ ጋር መኪና ከሚያጥቡ ልጆች ጋር አሁን ስመጣ ራሱ አይቼዋለሁ፡፡ ቀብረውት አሰቃይተውት አንድ አይኑን አጥፍተው ለቀቁት፡፡

አስቡት አይኑን አጥፍተውት ሲበል የሚሰማውን ስሜት አስቡት…

ጫዎታውን አቋርጦ መሄዱ ተሰማኝ እንጂ የተባለው ቦታ ሄጄ ልጁን ማናገር ፈለኩ፡፡ ቀልቤ ፈጽሞ ከእነሱ ዘንድ አልነበረምና ካልድን ጠቅሼው መጣን ብለን ወጣን፡፡ ልጁን አፈላልጌ ለማግኘት ቢከብድም ከብዙ ድካም በኋላ አገኘነው፡፡ ሊያወራልን ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ እንዲያወራልን በተደጋጋሚ ያደረኩት ሙከራ ስላልተሳካ ተቃራኒውን አውርቼ ሀቁን እንዲነግረኝ ማድረግ አማራጭ ነውና አደረኩት፡፡ ‹‹እንዴት አይንህን ሊያጠፉህ ቻሉ? ገንዘብ እንድታስልክ ሲሉ በጣም ይንከባከባሉ ሲባል ነው የሰማሁት፡፡

‹ምንድን ነው የምታወራው? የምታወራውን ታውቃለህ? እብድ..እነሱ ናቸው የሚንከባከቡት?..›› ሲል ጀመረ፡፡ እኔም የምፈልገው ይሄን ነውና ስድቤን ጠጥቼ ለመስማት ጆሮዬን በተጠንቀቅ አደረኩ፡፡ ቀጠለ…‹‹..እንኳን ሊንከባከቡህ ገና ጊቢው ውስጥ ስትገባ ነው ዱላው የሚጀምረው፡፡ አስደውሎ የሚያስልክበት ቦታ ያለው አስደወለ፡፡ እኔ ደግሞ ማንም የለኝም፡፡ ቡዙ ተደበደብኩ፡፡ ከየትም አምጥቼ አልሰጠኋቸውም፡፡ እይ!..ይንከባከባሉ ያልካቸው ናቸው ያቃጠሉኝ፡፡
ደረቱ ላይ በሲጋራ ያቃጠሉትን አሳየን፡፡ የበለጠ እንዲጨምርልኝ ፈልጌ ‹‹ለመጀመሪያ ጊዜ ካንተ ሰማሁ፣ አየሁ..›› አልኩት፡፡

‹‹ሂድና ሀረጥ እይ ምን ታደርቀኛለህ? ይሄን ታዲያ ራሴ ነኝ ያጠፋሁት? ምን ማለት ፈልገህ ነው?..›› አለና አይኑን አሳየኝ፡፡ ‹‹እንዴ ይህን እነሱ ናቸው እንዲህ ያደረጉኝ እንዳትል?..›› ሰምቼ ቢሆንም ፍለጋ የጀመርኩት እንዳላወቀ ሆንኩኝ፡፡ ‹‹እየነገርኩህ? ገንዘብ የሚልክ ዘመድ የለኝም፡፡ በሲጋራ አቃጠሉኝ፡፡ መቀመጫዬ ላይ ላይተር ለኩሰው አቃጠሉኝ፡፡ የሌለኝን ዘመድ ከየት ላምጣ ጉድጓድ ቆፍር ብለው አስቆፈሩኝ፡፡ እስከ አንገቴ ድረስ ቀበሩኝ፡፡ እኔስ ተርፌያለሁ ዝም ብለው ሙሉ ለሙሉ የቀበሯቸው አንድ ሴት እና ሶስት ወንዶች ልጆችን አያቻለሁ፡፡

እኔን አንገቴ ድረስ ቀብረውኝ እነሱ ጫታቸውን እየቃሙ በእኔ ስቃይ ይዝናናሉ፡፡ በመጨረሻም ለ22 ቀን አስቃይተውኝ እንደነገ ሊለቁይ እንደዛሬ የሀይላንድ ውሀ ላስቲኩን ክዳኑን ከፈተው እና አፉን አይኔ ላይ አደረገው፡፡ በቀዳዳው እይ አይንህን ግለጽ አለኝ፡፡ ያው ያዘዙህን ማድረግ ግዴታ ነው ገለጥኩ፡፡ በቂጡ በኩል በሀይል ሲመታው ራስን ስቼ ወደኩ፡፡ ምን ያህል ጊዜ እንደቆየሁ እንጃ ፌቴ ሁሉ ደም ለብሷል፡፡ እንዲሁ አሞኝ ዋልኩ፡፡ አይኔ ግን መውጣቱን ያወኩት ስነቃ ነው፡፡ በማግስቱ ሲለቁኝ መሄድ በሙሉ አልችልም ነበር፡፡ የወጣው አይኔ የሀይላንዱ እቃ ውስጥ እንደተቀመጠ ከድኖት ‹‹አላስልክም ባልከው ብር ታከምበት..›› ብሎ ሰጠኝ፡፡

ምን እንደተሰማኝ አላውቅም፡፡ የነበረኝን ስሜት አሁን መናገር አልችልም፡፡ አጥወልውሎኝ የምወድቅ መሰለኝ እና ካልድን ለገሰን ለመያዝ ዞር ስል በሁለት እጁ ራሱን ይዞ ያለቅሳል፡፡ እኔ ግን ማልቀሱም ሆነ ማሰቡ አልሆነልኝም፡፡ እዚህ ጋር በአንድ ወቅት ሶማሊያ እያለሁ የሚሰቃዩትን አይቼ የጻፍኳትን ግጥም ዳግም ብጠቀማት ወደድኩ….

ዋ!! ማንባት ብችልማ
ያሉትን ይበሉ ብልማ
ጥንድ..ጥንዱን አንዠቅዥቄ
ህቅ!!! ባልኩ ተንሰቅስቄ
ሀዘኔ በወጣ በታወቀ ለሰው
አምቄ ከማልመሰምሰው
እርዱኝ…እርዱኝ እባካችሁ
ትርፍ እንባ ያለችሁ
አልቅሱልኝ ለእኔ አሮ ሞተ ብላችሁ….ከማረርም በላይ ሆኖብኛል፡፡

አፌን ሁሉ ደም ደም አለኝ፡፡ ምሳ እንብላ ብለውም እሺ አላለም፡፡ አሁን ምን አሰብክ? ወደ ሰነዓ ከሆነ የምትሄደው አብረን እንሄዳለን አልኩት፡፡ ረድዓ የሚባለው ቦታ ሄዶ ባለ እርሻ ሰዎች ጋር ተቀጥሮ ትንሽ መስራትና ወደ ሳዑዲ አረቢያ መሄድ እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ እንዴት ረድዓን የምትባለውን ቦታ እና እዛ ስራ እንዳለ እንደወቀ ካልድ ጠየቀው፡፡ ከዚህ በፊት እንደመጣና ሳዑዲ አንድ አመት ቆይቶ ተይዞ ድጋሚ እንደተመለሰ ነገረን፡፡ ወዳለው ቦታ ለመሄጃ ከዛሬው ጋር ሁለት ቀን መኪና እንዳጠበ ነግሮን ሳንቲም ከቻልን እንድንሰጠው ጠየቀን፡፡

ይሄ በባህር የሚደረግ ጉዞ ስቃዩን እለት ከእለት እየጨመረ መምጣቱ ብቻ ሳይሆን አፋኞቹን ለማስቆም ምንም አይነት ጥረት አለመደረጉ አሳሳቢ ነው፡፡ እነሱም በማን አለብኝነት ጭካኔያቸውን እየጨመሩ የፈለጋቸውን እያደረጉ ነው፡፡ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ አካባቢ ከየመናዊያን ጋር በጥምረትም ሆነ በተናጠል ሰውን ወደ ሳዑዲያ የሚያጓጉዙትን ኢትዮጵያዊ ደላሎች ለማስያዝ አዲስ እንቅስቃሴ እንደተጀመረ ተሰምቷል፡፡

በ2012 ከ85000 በላይ ኢትዮጵያዊያን በባህር ተሻግረው ወደ የመን እንደገቡ ብሎም ግማሹ ወደ ሳዑዲ አረቢያ እንደተጓዙ አለም አቀፉ የስደተኞች ጽ/ቤት IOM የሚባለው ድርጅት መግለጹ ይታወቃል፡፡ እኔም በተደጋጋሚ ይህንን መግለጫ ጠቅሻለሁ፡፡ አብዛኛውም ከወሎ፣ ከአርሲ፣ ከሀረር እና ባሌ አካባቢ ነው የሚሰደዱት፡፡ ይህን ያህል ኢትዮጵያዊ የሚሰደደው በኑሮ ችግር ምክንያት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ለዚሁም እማኙ በወሎ ቦረና ወረዳ መካነሰላም የሚባል አነስተኛ ከተማ ውስጥ ከዋለልኝ መኮንን ትምህርት ቤት ከ9 እና 10ኛ ክፍል ብቻ በዚህ አመት ከ500 ተማሪዎች በላይ አቋርጠው ስደት ወተዋል፡፡ ካቋረጡት እና ስደት ከወጡት ውስጥ አብዛኛዎቹ ቤተሰቦቻቸው በዝቅተኛ ኑሮ ላይ ያሉ ናቸው፡፡ በኩር የተባለው የአማራ ክልል ጋዜጣ በዚህ ወር እትሙ ያሰፈረውን እንደቀልድ የማይታይ ነው፡፡ የፍልሰታችን አስፈሪ ሂደት ወዴት እየተጓዝን እንደሆነ ያመላክታል፡፡

ሰዒድ ሙሳ አህመድ የተባለ ወዳጄ ከገጠር ትምህርት ቤቶች በየአመቱ ትምህርት የሚያቋርጠው ተማሪ ብዛት አስደንጋጭ መሆኑን ጽፎልኛል፡፡ በጽሁፉ ላይ ሀይ ግሩም በደቡብ ወሎ ምዕራባዊ ዞን በረና ዋለልኝ መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ከ9-10 ካለው ክፍል ብቻ በ2004 ከ500 በላይ ተማሪዎች እንዳቋረጡ ታውቋል፡፡ ይሄው ወዳጄ ከጻፈልኝ በተጨማሪ አያይዞ የላከልኝ በኩር ጋዜጣ ላይ ከወረዳው አስተዳደር በተገኘው መረጃ በ2004 በአጠቃላይ 4000 በላይ እንዳቋረጡ ዘግቧል፡፡ ወሎ አርባ ወረዳዎች ስላሏት ስሌቱን 40X400 ማባዛት ነው፡፡160.000 አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ ጋዜጣው ትምህርት የሚያቋርጡበት ምክንያት መንግስትን የያዘው ብልሹ ፖለቲካ እንደሆነ ላለመጥቀስ ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ አረብ ሀገር ልከው ገንዘብ የማግኘት ፍላጎታቸው ማየል ነው ሲል ዘግቧል፡፡

የዋለልኝ መኮንን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ተስፋው ደመቀ ከአምናው ችግር ዘንድሮም የባሰ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ጋዜጣውን ማየት ይቻላል፡፡

የዕጩዎች ምርጫው እንደፈለጉት ያልሆነላቸው ጳጳሳት ሙግት ገጥመዋል

Saturday, February 23rd, 2013
(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2013/ PDF)የስድስተኛው  ፓትርያርክ  አስመራጭ   ኮሚቴ  በዛሬው   ዕለት  የዕጩዎቹን  ዝርዝር  ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበበት ወቅት ምርጫው በፈቀዱት መልክ አልሔደላቸውም የተባሉ ጳጳሳት ሙግት ገጥመው መዋላቸውን የደጀ ሰላም ምንጮች ገለፁ።

አምስቱ እጩዎች  መሆን ያለባቸው ብፁዕ  አቡነ  ማትያስ፣  ብፁዕ  አቡነ  ማቴዎስ፣ ብፁዕ  አቡነ   ዮሴፍ፣ ብፁዕ  አቡነ  ሕዝቅኤል እና ብፁዕ  አቡነ  ኤልሳዕ  ናቸው የሚለውን ውሳኔ አስመራጭ ኮሚቴው ካሰማ  በኋላ  አስተያየት የሰጡት እጩ ፓትርያርክ ብፁዕ  አቡነ ማቴዎስ  “በቀደመው የአበው  ገዳማዊ  ሥርዓት  መሠረት  በዕጩነት መግባት  አይገባኝም።  አባቶቼ  ስለ እግዚአብሔር  ብላችሁ እኔን ተዉኝ” ሲሉ ተሰምተዋል፡፡ ይህንን የትህትና ንግግር  የተመለከቱ አንዳንድ አባቶች “እንዲህ ያለ ትህትና በዚህ ዘመን ማየታችን የሚደንቅ ነው” በማለት ሲናገሩም ተሰምተዋል፡፡ እጩነቱን በአኮቴት እንዲቀበሉ በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ግፊት የተደረገባቸው ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በመጨረሻ  የአባቶችን ቃል አድምጠው በዝምታ ተቀብለዋል ተብሏል፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌሎቹ እጩ ፓትርያርኮችም ተመሳሳይ ሐሳብ  ለማንሳት ቢሞክሩም  በቅዱስ  ሲኖዶስ  አባላት  ግፊት  ጉዳዩን ለመቀበል ተገደዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአስመራጭ ኮሚቴው አሠራር፣ ጥቆማና ውሳኔ ትክክል አይደለም በሚል ከረር ያለ ሐሳብ ያሰሙት ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና ብፁዕ  አቡነ አብርሃም  በየተራ  ባደረጉት ንግግር በተለይ በብፁዕ  አቡነ  ማትያስ  ለዕጩነት  መቅረብ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንደተናገሩት የብፁዕ  አቡነ ማትያስ ዜግነት ጉዳይ ዕልባት ሳያገኝና ነገሩም በሥርዓቱ ሳይጣራ ከዝርዝሩ ውስጥ መግባታቸውን ኮንነዋል። አጠቃላይ የምርጫው ሒደት ትክክል አለመሆኑንም ለማስረዳት ሞክረዋል ተብሏል።

የሁለቱን አባቶች ተቃውሞ ያልተቀበለው ምልዓተ ጉባዔው ይህን ጥያቄ በዚህ ሰዓት ማንሳታቸው ተገቢ አለመሆኑን፣ “ትናንት ምርጫው እንዲካሔድ ስታቻኩሉ የነበራችሁ እናንተ ናችሁ፡፡ ‘ይዋልና ይደር፣ ጉዳዩን በጥሞና እንመልከተው’ ስንላችሁ አይሆንም ብላችሁ አጣደፋችሁት፡፡ አሁን ስምንት መቶ መራጭ መንገድ ከጀመረ በኋላ፣ የውጭ እንግዶች   እየተጠባበቅን ባለንበት ሁኔታ እንዲህ ያለ ግርግር ማንሳት ቤተ ክርስቲያኒቱን  ማዋረድ ነው” የሚል መልስ እንደተሰጣቸው ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

ተክለ-ስብዕናቸውን በመገንባት፣ የትምህርት ደረጃቸውን ከፍ በማድረግ፣ የመንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎችን በማስተባበር  የምረጡኝ  ቅስቀሳ ላይ  እንደሰነበቱ ሲነገርባቸው የሰነበተው ብፁዕ  አቡነ ሳሙኤል እና እርሳቸውን ለማስሾም ደፋ ቀና እያሉ ነው፣ የአባቶችን እርቅ አኮላሽተዋል የሚል ወቀሳ የሚሰማባቸው ብፁዕ አቡነ አብርሃም ባለቀ ሰዓት የምርጫው ተቃዋሚ ሆነው መቅረባቸው “የሚያስቡት ለቤተ ክርስቲያኒቱ  ሳይሆን  ለራሳቸው ነው” የሚል አስተያየት እንዳሰጠባቸው ደጀ ሰላማውያን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም 6ኛው ፓትርያርክ ሊሆኑ የሚችሉት ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌም ናቸው የሚለውን ቅድመ ትንበያ ምንጮችን ጠቅሳ ዘገበችው ደጀ ሰላም አረጋዊው አባት ለፓትርያርክነት ቢበቁ ከትህምርትም፣ ከመንፈሳዊነትም፣ ከብስለትም፣ ከልምድም አንጻር የሚበዛባቸው እንደማይሆን ትረዳለች። ዛሬ የተነሣባቸው ተቃውሞም “ይህ ይጎድላቸዋል” ከሚል አንጻር ሳይሆን ከዜግነት ጋር በተገናኘ ነው።

 

በአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን የተሐድሶ ቀንደኛ ተከታዮች ከሆኑት ከነ አባ ሰረቀ ጋር ተገናኝቶ የተዘገበባቸውም ሐሰት መሆኑ አረጋዊው አባት የጥቃቱ ሰለባ የሆኑበትን ምክንያት እንድንመረምር ያደርገናል። ደጀ ሰላም ባለፈው ጽሑፏ እንዳለችው ምእመናን ቅዱስ አባታችን ብለው በሙሉ ልብና በፍቅር የሚታዘዙት አባት ይፈልጋሉበርግጥም። ይህንን ለማግኘት ደግሞ በቂም በቀል እና የራስን ደጋፊ በማስሾም ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን የሚበጀውን በመሻት መሆን አለበት። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያየን ያለነው ግርግር ግን ቤተ ክህነቱ እና ጥቅመኛ ቡድኖች እንዴት መስመር የለቀቀ መንገድ እየተከሉ መሆኑን የሚያመለክት ነው።

 

ዞሮ ዞሮ የሚሰየመው አባት የቤተ መንግሥቱ ይሁንታ (ኢንዶርስመንት) ያለው፣ ቀድሞ ያለቀ ነገር፣ የተበላ ዕቁብ መሆኑን መዘንጋታቸው ግን ገርሞናል። አሁን ደርሶ ምርጫው ይሸጋገር ማለት ራሳቸው በጀመሩት ጨዋታ መሐል ላይ ደርሶ “ይቋረጥልን” እንደማለት ይሆናል። የቤተ ክርስቲያኒቱ አንድነት እንዳይመጣ ተግታችሁ ሰርታችኋል። አንድነቱ ሲቀበር የመጨሻውን ምስማር የመታችሁትን አትርሱት። ተሳክቶላችኋል። ያቺ ያለማችኋትን “ወንበር” ግን ተሸውዳችኋል።

 

በዛሬው ጉባዔ ተቃውሞ በብርቱ የቀረበባቸው አረጋዊው ብፁዕ አቡነ ማትያስ ዘኢየሩሳሌም ጉዳዩን በዝምታ ማለፍ መርጠዋል፡፡ ውይይቱ በዚህ መልኩ  ከተከናወነ በኋላ አምስቱ እጩዎች ጉዳይ የተጠናቀቀ ሲሆን ሰኞ በፊርማ ይቋጫል ተብሏል። ቅ/ሲኖዶሱ ካጸደቀው ዘንዳ የሚቀረው የምርጫውን ሒደት ለሕዝብ ይፋ ማድረግ እንደሚሆን ይጠበቃል፡፡ ድራማው ይቀጥላል!!!!!

 

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

“ፓትርያሪክ እንድሆን የመንግስት ባለሥልጣን አላግባባሁም” (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)

Saturday, February 23rd, 2013

  • ‹ካህናትና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብለው ብቻ ማሰብ፣ ይገባቸዋል›› - (ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)

(አዲስአድማስ ጋዜጣ፤ የካቲት 17/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 24/2013/ PDF)የምርጫው ሂደት በይፋ ከተጀመረ አንሥቶና ከዚያም በፊት ቀጣዩ ፓትርያሪክ እንደሚኾኑ ብዙ ከተነገረላቸው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል አንዱ ናቸው፡፡ ብፁዕነታቸው በፓትርያሪክነት ምርጫው ከሚሳተፉ ከ800 በላይ መራጮች የምርጫ ድጋፍ ለማሰባሰብ በሥልጠና ስም በርካታ ገንዘብ ማውጣታቸውን፤ በሕንፃ ኪራይ፣ በሥራ ምደባ፣ በውጭ ተልእኮና በሹመት አሰጣጥ ለብዙዎች ቃል መግባታቸውን፤ ከዚህም አልፎ ቀጣዩ ፓትርያሪክ እርሳቸው እንደሚኾኑ ራሳቸውን ለመንግሥት አካላት ስለ ማስተዋወቀቸው በአንዳንድ ሚዲያዎች ተዘግቧል፡፡


በእኒህ ጉዳዮች ላይ የብፁዕ አቡነ ሳሙኤልን አስተያየት ከራሳቸው አንደበት ለመስማት የአዲስ አድማስ ሪፖርተር ሰላም ገረመው ከብፁዕነታቸው ጋር አጭር አጠር ያለ ቆይታ አድርጋለች፡፡

አዲስ አድማስ፦ በያዝነው ዓመት በኮሚሽኑ ድጋፍ ለአህጉረ ስብከት ሓላፊዎች የተሰጡ ሥልጠናዎች፣ በአዲስ አበባ ከግብጽ ቤተ ክርስቲያን ጋር የተደረጉ የልምድ ልውውጦች ከፓትርያሪክ ምርጫው ጋር በተያያዘ ለብፁዕነትዎ ድጋፍን የመሸመት ዓላማ እንደነበራቸው ይነገራል፡፡ የተሰጠው ሥልጠና ምን ነበር? ዓላማውና የበጀት ምንጩስ?

(ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)፦ ከግብጽ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከመጡ ልኡካን ጋር የተደረገው የልምድ ልውውጥና የተሰጠው ሥልጠና፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ከግብጹ ፖፕ አቡነ ሺኖዳ ጋር ቀድሞ በደረሱበት ስምምነት መሠረት የተፈጸመ፣ ነገር ግን ዘግይቶ የተፈጸመ ስለኾነ እንጂ ከፓትርያሪኩ ኅልፈት በኋላ የታቀደና ለምርጫ ድጋፍ ቅሰቀሳ የታሰበ አይደለም፤ በቀጣይም ከሌሎች አኀት አብያተ ክርስቲያናት ለምሳሌ ከሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር በተመሳሳይ መድረኮች የመገናኘት ዕቅድ አለን፡፡

አዲስ አድማስ፦ ለአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆችና ሌሎች ሓላፊዎች በጥቅምት ወር ከሀገር አቀፉ አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ጋር ተያይዞ የተሰጠው ሥልጠና አምናም በተመሳሳይ ወቅት የነበረ ነው፡፡ በ2004 ዓ.ም ጥቅምት ወር ፓዝፋይንደር ኢትዮጵያ በሰጠው የገንዘብ ድጋፍ በሥነ ተዋልዶና የሴት ልጅ ግርዛት ላይ ያተኮረ ሥልጠና ለቅዱስ ሲኖዶስ አባላትና ለአህጉረ ስብከት ሥራ አስኪያጆች ተሰጥቷል፡፡

በዚህ ዓመት ‹‹ዳቦ ለዓለም›› በተባለ ገባሬ ሠናይ ድርጅት ድጋፍ በአቅምና የሰላም ግንባታ ጭብጥ ዙሪያ በታቀዱ በርካታ ርእሰ ጉዳዮች ላይ በመስኩ ባለሞያዎች ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡ ዋና ዓላማው በቤተ ክርስቲያናችን መልካም አስተዳደር እንዲጠናከር፣ ፍትሕ እንዲሰፍንና የልማት አቅም እንዲፈጠር ነው፡፡ ስለዚህ ምርጫው ስላለ ወይም ከምርጫው ጋር ተያይዞ የታቀደ ነገር አይደለም ማለት ነው፡፡

(ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)፦ ለሥልጠናው ተሳታፊዎች በአበል መልክ እንደተጨማሪ ክፍያ ወጥቷል የተባለው 500,000 ብርና የበጀት ምንጩስ? የዚህ ዓመት ሥልጠና የበጀት ምንጩ እንደተናርኹት እኛው ቀርጸን ለ‹‹ዳቦ ለዓለም›› (Bread For the World) ገባሬ ሠናይ ድርጅት ባቀረብነው ፕሮፖዛል መሠረት የተገኘ ገንዘብ ነው ለሥልጠናው ማስፈጸሚያና ለአበል የተከፈለው፡፡ ይህም በየዓመቱ በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ፕሮፖዛል እየቀረጽን፣ ድጋፍ ሰጪ ድርጅቶችን እየጠየቅን ስንሠራው የቆየና ለወደፊቱም የሚቀጥል ነው፡፡ ለሥልጠናው ወጭ የተደረገው ገንዘብ ለአፋርና ለሶማሌ ክልሎች ለሚሠሩ የልማት ፕሮጀክቶች የተገኘ ገንዘብ ነበር ለተባለው በክልሎቹ ለምንሠራው ሥራ ድጋፍ ያገኘነው ከተመድ የስደተኞች ማእከል (UNCR) ነው፤ ገንዘቡንም የሚቆጣጠረው ራሱ ማእከሉ ነው፡፡ ስለዚህ ከሥልጠናው ወጪ ጋር አይገናኝም፡፡

ከምርጫው ጋር በተያያዘ÷ ሹመት እንደሚሰጣቸው፣ በሥራ እንደሚመደቡ፣ በሕንጻ ኪራይ፣ በውጭ ዕድል ቃል የተገባላቸው መራጮች አሉ ተብሏል…

ለመሾምም፣ ሕንጻ ለማከራየትም፣ በሥራ ለመመደብም፣ ወደ ውጭ ለመላክም ሥርዐት አለው፡፡ ከተጠቀሱት የትኛውም ነገር ከሥርዐት ውጭ እንዳይፈጸም ተከፍቶ የነበረው መንገድ ተዘግቷል፡፡

በሌላ በኩል የፓትርያሪክ ምርጫ መንፈሳዊ ጉዳይ ነው፡፡ በዚህ መንገድ ፕትርክናውን ለማግኘት ማሰብና መሞከር ሕግም አይፈቅድም፡፡ ይህ የሥልጣን ስግብግብነት ነው፡፡ መራጮቹስ እነማን እንደኾኑ በስም ይታወቃሉ ወይ? ይህን አሉባልታ ያመነጩትና የሚያስተጋቡት የምርጫውን ሂደት ለማወናበድ፣ ሕጋዊውን አሠራር ወደ ቤተሰባዊነት፣ ዘረኝነትና አድሏዊነት ለመውሰድ ማመኻኛ የሚሹ ሕገ ወጥ ቡድኖች ናቸው፡፡

ስድስተኛው ፓትርያሪክ ኾነው እንዲመረጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን፣ የቤተ ክህነት አመራሮችንና ታዋቂ ግለሰቦችን አግባብተዋል? ስለጉዳዩ ላይ ሊቃነ ጳጳሳቱ ትችት እንደሰጡ ተዘግቧል።

(ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)፦ ምረጡኝ ብዬ አላልኹም፤ ምረጡኝ ብዬ አላውቅም፡፡ ይህን አድርገኻል የሚሉኝ ወገኖች እውነተኛ ከኾኑ መረጃውን ለምን አያቀርቡም? የቤቱን [የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን] ዕድገት፣ ልማትና መሻሻል ርምጃዎች ሲያኮላሹ የነበሩ ሰዎች ስሜት ነው፡፡

የመንግሥት ባለሥልጣናትን ማግባባትዎና ‹‹መንግሥት ፓትርያሪክ ኾኜ እንድመረጥ ይፈልጋል›› እያሉ ማስወራትዎ. . .
ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮኻል፤ በየትኛውም አቅጣጫ የተለያዩ አካላት ብዙ ሊናገሩ ይችላሉ፤ ይህንንም የሚሉት የቤታችንን የዕድገትና ልማት ርምጃ ሲያኮላሹ የነበሩ ግለሰቦችና አሁን ደግሞ በምርጫው ዙሪያ የተደራጁ ቡድኖች ናቸው፡፡

(ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)፦ ፓትርያርክነት የአባትነት፣ የቡራኬ ሥልጣን ነው፤ ለእኔ አገልጋይነት ይሻለኛል፤ አገልጋይ መኾን ነው እንጂ፤ አገልጋይነት÷ ሃይማኖትን መጠበቅና ማስጠበቅ፣ ሕዝብንና እግዚአብሔርን በማእከል ኾኖ ማገናኘት እንጂ አዛዥ፣ ገዥ፣ አሳሪ፣ አሳሳሪ መኾን አይደለም፡፡

ለመኾኑ እንዴት ነው የፓትርያሪክነት ሥልጣን ይሰጠኝ ብዬ የምጠይቀው? ሹመቱ የመንፈስ ቅዱስ ምርጫ ነው፤ ሥርዐቱ የሚፈጸመው በፍትሕ መንፈሳዊ፣ በሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ በፓትርያርክ ምርጫ ሕገ ደንቡ መሠረት ነው፤ ሕጉን፣ ሥርዐቱን የሚፈጽመውና የሚያስፈጽመው ቅዱስ ሲኖዶሱና ሕዝቡ እንጂ መንግሥት አይደለም፤ በሕገ መንግሥቱ የመንግሥትና ሃይማኖት ግንኙነት ምን መኾን እንደሚገባው በግልጽ ተደንግጓል፡፡ ያግባባኹትም የጠየቅኹትም የመንግሥት አካል ይኹን ባለሥልጣን የለም፡፡

በምርጫው የሚሳተፉ ካህናትና ምእመናን ለሚኖራቸው ድርሻ እርስዎ ምን ይላሉ? በምርጫው ዙሪያ ይካሄዳል ስለሚባለው የቡድኖች እንቅስቃሴስ?

(ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል)፦ በየብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ ቤት፣ በእኔም ቤት ሳይቀር እየዞሩ እገሌን ካልመረጣችኹ፣ ካላስመረጣችኹ የሚሉ አካላት እንዳሉ ግልጽ ነው፡፡ ሥልጣን ባለው አካል መንፈሳዊ ሥልጣንን ለመያዝ የሚደረገው ሽር ጉድ ሁሉ በፍትሕ መንፈሳዊ፣ በቀኖና ቤተ ክርስቲያን የተወገዘ ነው፤ ይህን የሚያደርጉ አካላት በሰውና በእግዚአብሔር ዘንድ ይጠየቃሉ፡፡ እንዲህ ኾኖ የሚሾመው አባትም ቢኾን ሢመቱ ሥጋዊ ሹመት ይኾንና በነፍስም በሥጋም ያጎድለዋል፤ ያለጊዜውም ሊያሥቀስፍ ይችላል፡፡

ስለኾነም በምርጫው የሚሳተፉ ካህናትና ምእመናን ለቤተ ክርስቲያንና ለቤተ ክርስቲያን ብለው ብቻ ማሰብ፣ መወሰንና መቆም ይገባቸዋል፡፡

አስሩ የጽልመት ቀናት በኢትዮጵያ

Saturday, February 23rd, 2013

(ከየካቲት 8/1929 - የካቲት 17/1929 ዓ.ም)

ሰሎሞን ተሰማ ጂ.

በመስከረም 1927 ዓ.ም የወጣው Detroit Times — (Sept. 22, 1935, p. 3) መጽሔት ከአንድ ታላቅ ሳይቲስትና የፈጠራ ባለሙያ ጋር የኢትዮጵያንና የጣሊያንን ወረራ አስመልክቶ ቃለ-ምልልስ አድርጎ ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ወላጆችና መሪዎች

Saturday, February 23rd, 2013

ቸሩ ላቀው
ለዚህ የተቀደሰ ተግባርና ከባድ ኃላፊነትን ለሚጠይቅ ሥልጣን መታጨት ያለባቸው የሀገር መሪዎች ማሟላት ያለባቸው መመዘኛዎች በርካቶች ቢሆኑም በኔ እይታ አንዳንዶቹን ከወላጆች ጋር እያስተያየሁ ለመጠቃቀስ እፈልጋለሁ።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ድንቄም ምርጫ!

Saturday, February 23rd, 2013

ይኸነው አንተሁነኝ
ላንዲት ሀገር መሰረታዊ የእድገት ኃይል ያላት የተፈጥሮ ሃብትና የሕዝቦቿ ሁለንተናዊ ብቃት ናቸው። የሕዝቦቿን ሁለንተናዊ ብቃት ለመገንባት ደግሞ ካሏት የትምህርት ተቋማትና የትምህርቱ ሥርዓት በተጨማሪ በሕዝቦቿ መካከል ያለው የባህል፣ የኃይማኖትና የአኗኗር መስተጋብር የሚያበረክቱት አስተዋጽኦና በዚሁ ሳቢያም የሚገኘው ቀጥተኛ ያልሆነ የእውቀትና የልምድ አቅምና ዝውውሩ የሚናቅ አይሆንም።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የህወሓት ጉዞ የርስ በርስ መበላላት ታሪክ ነው

Saturday, February 23rd, 2013

ትዕዝብት አድማሱ
የትግራይ መሳፍንት እርስ በራሳቸው ሲናቁሩና ሲገዳደሉ ያየች አንዲት የጎጃም አዝማሪ ስታንጎራጉር "ጎጃሜ ቡዳ ነው ስትሉ ስትሉ፣ አላየህም ወይ ትግሬ እርስ በርስ ሲባሉ" በማለት ትልቁ የታሪክ ጠባሳ በአንዲት ዓረፍተ ነገር አጠቃለለች ይባላል። ይህ የትናንት ታሪክ ነው። ዛሬስ ምን እየተደረገ ነው ያለው?

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ህወሓት ሊወድቅ ነው

Saturday, February 23rd, 2013

(ለነፃነታችን እንጨክን - እንቆሽሽ!)

ያሬድ አይቼህ

ገዢው ፓርቲ ለጥገናዊ ለውጥ ምንም አይነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ጉዳይ አስምረውበታል። ከዚህ የተነሳ ከገዢው ፓርቲ ጋር የነበረው የምርጫ ትግል በአጠቃለይ መክኗል። ዛሬ አገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ነፃነት ትግል ምዕራፍ ገብታለች።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

የዳውሮ ሕዝብ ያካሄደው መራር ትግልና ውጤቱ

Saturday, February 23rd, 2013

ዋካ ከስዊድን
በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኘው የዳውሮ ዞን ሕዝብ ለህወሓት መራሹ መንግሥት በተደጋጋሚ ጥያቄ አቅርቦ እንደነበርና ሕዝቡ ላቀረበው ጥያቄ ተመጣጣኝ ምላሽ በመነፈጉ በመንግሥት ላይ በተለያዩ ጊዜያት ማመጹን በተለያዩ የብዙኃን መገናኛዎች ሲዘገብ ሰንብቷል።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 23, 2013

Saturday, February 23rd, 2013
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana

አፍሪቃ እና የፀረ አደንዛዡ ዕፅ ትግል

Saturday, February 23rd, 2013
አፍሪቃ ውስጥ በያመቱ ሠላሣ ሰባት ሺህ ሰዎች የሱስ አስያዥ ዕፅ በሚያስከትሉ በሽታዎች እንደሚሞቱ የተመድ መዘርዝሮች አስታውቀዋል። ሕገ ወጥ የሱስ አስያዥ ዕፅ ንግድ ዝውውርን እና የዚሁ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቃሚዎችን ቁጥር በተመለከተ ከሰሜን አሜሪካ እና ከካናዳ ቀጥላ አፍሪቃ ሦስተኛውን ቦታ ይዛለች።

የቅድመ ምርመራ ቅድመ ምርመራ

Saturday, February 23rd, 2013
ስለ ቅድመ ምርመራ ስናወራ ሃሳቡን በጠንካራ ሁኔታ ተግባራዊ ያደረገው የደርግ መንግስት ሳይጠቀስ አያልፍም፡፡ ከዚያ በፌት በነበረው ጊዜ ‹ንጉሥ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ› የሚለው አስተሳሰብ በስፋት ስለሚታመንበት ንጉሡን ከሚያወድስ እና የንጉሡን ፈቃድ ከሚያሟላ የህትመት እና የብሮድካስት  ስራዎች ውጪ ለመስራት ሃሳብ አልነበረም፡፡ የደርግ መንግስት የንጉሡን ስርዓት ካስወገደ በኋላ ደግሞ የቅድመ ሳንሱር ጉዳይን ጠበቅ ባለ በሕግ ደንግጎ ቀረበ፡፡ ሳንሱር ሳይደረጉ መፅሃፍት አይታተሙም፡፡ ሌሎች የህትመት ውጤቶችም የሚያስተላልፉት መልዕክት ስርዓቱ የሚደግፈውን ርዕዮተ ዓለም ፅንሰ ሃሳብና አስተሳሰብ ብቻ ነበር፡፡ በሃገራችን ባይታተምም ውጭ ሃገር የታተሙ ከስርዓቱ ጋር የሚፃረር ወይም የሚተች መልእክት ያለውን መፅሃፍ/የህትመት ውጤት ለማንበብ እንኳን አይቻልም፤ ወይም እንደ ሰረቀ ሰው ተደብቀው ነበር የሚያነቡት፡፡

ከደርግ ቀጥሎ የመጣው የኢህአዴግ መንግስት ደግሞ የህትመት ነፃነት ያስፈልጋል በሚል ቅድመ ምርመራም ክልክል እንደሆነ አወጀ፡፡

አንቀፅ 29.3 ሀ/ ‹‹የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን››

ይህን ህግ መሰረት በማድረግም በሬድዬና ቴሌቭዥን ደረጃ የታየ ለውጥ ባይኖርም ብዙ የግል ሃሳብ የሚንፀባረቅባቸው ጋዜጦችና መፅሄቶች ተፈለፈሉ፡፡ ለ97 ሃገራዊ ምርጫም እነዚህ የግል የህትመት ውጤቶች ህብረተሰቡን በማንቃት እና የሃራቸው ፖለቲካ ጉዳይ ያገባኛል ብለው እንዲያስቡ በማድረግ ረገድ አሉታዊ ሚና ተጫውተዋል፡፡ ኢህአዴግም በምርጫው ውጤት እና በህዝቡን ስሜት ተደናግጦ ይመስላል ከ97 ምርጫ በኋላ በሰበብ አስባቡ ጋዜጠኖችንና አዘጋጆችን ማሰር እንዲሁም ለራሱ የሚመች ለትርጉም የማይመች እና ከፕሬስ ጋር የተያያዙ ህጎችን ማውጣት እና ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው፡፡


ኢህአዴግ ስለዲሞክራሲያዊ መብቶች ህግ ላይ የማስፈርና የመናገር ችግር የለበትም፡፡ በግልፅ እንደሚታየው በህገመንግስታችን አንቀፅ 29 ላይ ‹የአመለካከት እና ሃሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት› በሚል ርእስ በሰባት ንኡስ አንቀፆች ተከፋፍሎ በቂ የሚባል ሽፋን ተደርጎለታል፡፡ ባለስልጣኖቹም ይቺን አንቀፅ ደጋግመው ያነበንቡልናል፡፡ የታሰሩ ጋዜጠኞችን በተመለከተም የሚመለከታቸው የመንግስት ሰዎች ሲጠየቁ ‹የታሰረ ጋዜጠኛ እና ፖለቲከኛ የለም› ይሉናል፡፡ እውነቱን እና በተግባር የምናውቀው ግን በተቃራኒው ነው፡፡

ህገመንግስቱ የሰጣቸውን መብት ተጠቅመው ሃሳባቸውን በነፃ ለመግለፅ የሞከሩት የተለያየ የወንጀል ስያሜ እየተፈጠረላቸው እስር ቤት እንዲገቡ እየተደረገ ነው ተብሎ መንግስትም በተደጋጋሚ ሲታማ ይሰማል፡፡ ከእስሩ ጋር ተያያዥ የሆኑት እንግልት፣ ድብደባ እና ስቃይን የመሳሰሉ ውንጀላዎችን ሳንዘነጋቸው ማለት ነው፡፡ ከዚህ ውጪ ያሉት ደግሞ ወይም ተሰደዋል ወይም መስራት አቁመዋል፡፡ የተቀሩት ከነገ ዛሬ የጓደኞቻቸው እጣ እንደሚደርሳቸው የስጋት እና የሰቀቀን ኑሮ ውስጥ ሆነው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ ይህ እንግዲ ለሃገራችን ምን ያክል ኪሳራ እንደሚያስከትል ለመገመት ፊደል መቁጠርም አያስፈልግም፡፡

 የቅድሚያ ምርመራ በማኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን የምትገልፀዋ አንቀፅ የምታገለግለው ልክ አይጥ ወጥመድ ላይ እንደሚቀመጥ ምግብ ነው፡፡ አይጧ ምግቡን ብላ ስትመጣ ወጥመዱ እንደሚይዛት ሁሉ በአንቀፅ 29 ላይ የተደነገገውን መብት ተጠቅሞ ሃሳቡን ለመግለፅ የሚሞክርም እንዲሁ በወጥመዱ የመያዝ አደጋ ይገጥመዋል፡፡ ስለዚህ ህጉ ኖረም አልኖረም ልዩነት የለውም ማለት ነው፡፡ እንዲያውም ኪሳራው ይበዛል፡፡ የፍትሕ ጋዜጣን እንደ ምሳሌ መውሰድ እንችላለን፡፡ ህትመት በሚገባበት ወቅት ከመታተሙ በፊት ጋዜጣው ላይ ሊወጣ የነበረ ዜና እንዲያስወጡት ለአዘጋጆቹ ከማተሚያ ቤት ተነገራቸው፡፡ አዘጋጆቹ ደግም ይህ የቅድመ ምርመራ እገዳውን እንደሚፃረር ሲነግሯቸው ጋዜጣውን አተሙትና ከታተመ በኋላ (ከስርጭት በፊት) እንዲታገድ ተደረገ፡፡ እንግዲህ በአታሚውም በአሳታሚውም ወገን የሚያስከትለውን ኪሳራ አስቡት፡፡ ከቅርብ ጊዜ ትዝታችን እንኳን ብንጀምር፤ ባሳለፍነው ሰባት ወር ጌዜ ውስጥ ሦስት ጋዜጦችና አንድ መፅሔት ታግደዋል፡፡ በነዚህ የህትመት ውጤቶች ተቀጥረው ይሰሩ የነበሩት ፀሃፊያንና ጋዜጠኖችም የስራ አጥነት አደጋ ያጋጥማቸዋል፡፡ ይህን የሚያዩ የጋዜጠኝነት እና ስነፅሁፍ ተማሪዎች እንዲሁም የመፃፍ አቅሙና ዝንባሌ ያላቸው ወጣቶችም ተስፋቸው የመነመነ ይሆናል፡፡ ኪሳራው ብዙ ነው፡፡ ተዘርዝሮ የሚያልቅም አይደለም፡፡

በሕገመንግስቱ የተደነገገልንን ‹የአመለካከት እና ሃሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት› እና ‹‹የቅድሚያ ምርመራ በማኛውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን›› መብት ከመንግስት ባልተናነሰ መልኩ የሚጥሱ አካላት መበራከት ደግሞ ሌላው በቅርቡ እየተስተዋለ ያለ ቀላል የማንለው ችግር ነው፡፡ዋናዎቹ ማተሚያ ቤቶች እና የሆቴል ወይም የአዳራሽ ባለቤቶች ሲሆኑ በአሁን ሰዓት እነዚህ አካላት ህትመቶች ወይም ነፃሃ ሳቦች ለህዝብ እንዳይደርሱ በማድረግ ረገድ ከፍተኛውን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ፡፡ ብዙዎቹ ማተሚያ ቤቶች በራሳቸው ስልጣን ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ወይም መንግስትን የሚተቹ  መፅሃፎችን ለማተም ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ የስብሰባ አዳራሽ ያላቸው ሆቴሎች ባለቤቶች እና መሰብሰቢያ አዳራሽ ብቻ ያላቸው ቦታ ባለቤቶች የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ወይም ሌሎች ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ስብሰባዎችን ለማስተናገድ እንዲሁ ፈቃደኛ አይደሉም፡፡ ዋና ዋናዎቹን ጠቀስኩ እንጂ የመንግስት አካል ጋር ሳይደርሱ የሚከሰቱ እገዳዎች ብዙ ናቸው፡፡ ይህን ነው የቅድመ ሳንሱር ቅድመ ሳንሱር የምለው፡፡ እራሳችን በራሳችን ወይም በቅርብ ጓደኞቻችንም ሳንሱር እንደረጋለን፡፡ ከምናወራው ሰው ጋር ሃሳባችንን ሙሉ በሙሉ ለመናገር የማንደፍር ወይም አይምሯችን ውስጥ እየቆረጥን የምናስቀረው ከሆነ እራሳችንን ሳንሱር አደረግን ማለት ነው፡፡ ፅሁፍም ፅፈን ከሆነ በቅርብ የሚያይልን ሰውም ከመንግስት ሊመጣ የሚችለውን ቅጣት ስጋት ‹ይቺን አስወጣት› የሚል ከሆነ እሱም ሳንሱር እያረገን ነው፡፡ በርግጥ የቅድመ ሳንሱር ቅድመ ሳንሱር መበራከት ከመንግስት ጋር ላለመሳፈጥ፤ ከመንግስት አይን ራቅ ብሎ ሰላማዊ ኑሮ ለመምራት የሚደረግ ጥረት እና የመንግስትን ዱላ ከመፍራት የመጣ ነው፡፡ መንግስትም እንዲህ አይነት አካላት መኖራቸውን አጥብቆ ይፈልጋል፡፡ ባለፈው ፓርላማ ላይ ጠ/ሚ ኃይለማርያም ሲናገር እንደሰማነው የማተሚያ ቤትን እና የመሰብሰቢያ አዳራሽን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ ችግሩን የማተሚያ ቤቱ እና የአዳራሽ ባላቤት እንደሆነ እና ጠያቂውም ከነሱ ጋር እንዲጨርስ እንጂ የመንግስት ጥፋት እንዳይደለ ተነግሯል፡፡

አሁን በሃገራችን እንደምናስተውለው ጥቂት ደፋሮች ወይም ፍርሃታቸውን ያሸነፉ ብቻ ናቸው ሲፅፉ ወይም ሲያወሩ የምንሰማው፡፡ የአብዛኛዎቻችን ስራ ደግሞ ስራዎቻቸውን አይተን/አዳምጠን የገቡበት ገብተን ጎበዝ! ጀግና! በርታ! ማለት፤ ሲታሰሩ ካለንበት ፈቅ ሳንል ዘላቂነት የሌለው አይዞህ! አይዟችሁ! እንላለን-ሄድን ልንጠይቃቸው እንኳን አንፈቅድም ወይም ድፍረቱ የለንም፤ ሲሰደዱ ደግሞ እንሳደባለን፡፡ በቃ ይሄ ነው የአብዛኞቻችን የስራ ድርሻ - ተመልካችና ፈራጅ፡፡ መመልከትና መተወን በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው፡፡

ሃሳቤን ለመጠቅለል ያክል ጥቂት ፍርሃታቸውን ያስወገዱትን ብቻ እንዲናገሩ ወይም እንዲፅፉልን ብቻ ከምንጠብቅ እራሳችንም የድርሻችንን በመወጣት፤ እራሳችንን ወይም በቅርብ ያሉትን ጓደኞቻችን ማስፈራራት፣ ተስፋ ማስቆረጥና ሳንሱር ማድረጋችንን ብንተውና ሁላችንም ፍርሃታችንን በተወሰነ መጠን አሰወግደን ሃሳባችንን ያለፍርሃት መግለፅ ብንጀምር እንዲሁም በመጠኑ ህገመንግስቱ ላይ የተፃፈውን መብታችንን እንኳን ለማስከበር ቆርጠን ብንነሳ ለውጥ ማየት የምንችል ይመስለኛል፡፡ 

#Ethiopia, #StopCensorship: ሳንሱር ዋጋ ያስከፍላል

Saturday, February 23rd, 2013

በናትናኤል ፈለቀ

ለምዕራባዊያኑ የመጨረሻ  ወር በሆነው ዲሴምበር ወር መጀመርያ በሀገረ አሜሪካ ኢትዮጵያዊውን ጦማሪ እና እስክንድርነጋን ለማሰብ የተዘጋጀ መድረክ ነበር፡፡በመድረኩ ላይ ስለ እስክንድር ነጋ የተናገሩት ተዋናይ ሊዬቭ ሽሬ የይበር እና ጸሐፊ ካርል በርንስቴይን ነበሩ፡፡ በርንስቴይን  ከ40 ዓመታት በፊት የዋሽንግተን ፖስት ዘጋቢ ሆኖ በሚሠራት ወቅት ከባልደረባው ቦብ ዉድወርድ ጋር በመሆ ን በአሜሪካ መንግስት ታሪክ ትልቅ የተባለውን እና የዋተርገቱ ቅሌት በመባል ሚታወቀውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ያሳተፈ የሙስና ቅሌት አጋልጠዋል፡፡ በነዚህ ሁለት ዘጋቢዎች ታሪካዊ ማጋለጥ ምክንያት በወቅቱ አሜሪካን በፕሬዝዳንትነት ይመሩ የነበሩት ሪቻርድ ኒክሰን ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው እንዲለቁ ሆኗል፡፡

የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምሳሌ ተደርጋ የምተጠቀሰው አሜሪካ በወቅቱ የመንግሥት ባለሥልጣናትን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ አቅም የሚያንሳት ሀገር አልነበረችም፡፡ የፖለቲካ ባህሏም  (በጥቅሉ) ተጠያቂነትን የሚያበረታታ እና ሙስናን የመሰሉ ተግባራትን አፀያፊ አድርጎ የሚቆጥር ነበር/ነው ማለት ይቻላል፡፡ በዚህም ሥርዓት መሐከል ግን እንክርዳድ አይጠፋውም፡፡ እናም መደበኛው የተጠያቂነት ሥርዓት ያልደረሰበትን ማማ አራተኛው የመንግሥት ክንፍ  (fourth organ of government) በመባል የሚታወቀው ሚዲያ አጋለጠው፡፡

ነጻ የሆኑ መገናኛ ብዙኃን መኖር እና ዜጎች ሐሳባቸውን መግለጽ እና መወያየት መቻላቸው የመንግሥትን እና የባለሥልጣናቱን ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም ሕዝብን ከአደጋ ለመጠበቅ ቁልፍ መሣሪያዎች ናቸው፡፡
እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ደሃ ሀገራት እያንዳንዱ የመንግሥት መዋለ ነዋይ ለሚፈለግለት ዓላማ መዋል አጥብቆ የሚፈለግ ነገር ነው፡፡ እውነታው ግን ይሄ አይደለም፡፡ በደሃ ሀገራት ስልጣን የሚይዙት ሰዎች/የፖለቲካ ፓርቲዎች ግን አንድም የራሳቸውን ግለሰባዊ ችግር ከሀገሪቱ ችግር በማስቀደም ወይንም በስግብግብነት አልፎ አልፎም ደግሞ ከብቃት ማነስ ሀገራቸው እጅግ አድርጋ የምትፈልገውን መዋለ ነዋይ ያባክናሉ፡፡ ይባስ ብሎም አብዛኞቹ ደሃ ሀገራት የሚመሩት ሁሉንም ነገር መቆጣጠር በሚፈልጉ እና ለምንም አይነት ነጻነት እና መብት ደንታ በማይሰጣቸው መሪዎች  (totalitarian) ነው፡፡ በዚህም ምክንያት የሀገር ሃብት ሲመዘበር እና አለአግባብ ጥቅም ላይ ሲውል ለምን ብሎ የሚጠይቅ አካል አይኖርም፡፡ ካለምፍዳው እጅግ ብዙ ይሆናል፡፡


የሕዝብ ውክልና የሌላቸው/የሚጎላቸው የድሃ ሀገራት መሪዎች ስልጣን ላይ በሕይወት እስካሉ ድረስ ለመቆየት ሀገራቸው ላለባት ምጣኔ-ሃብታዊ እና ሌሎችም ችግሮች እራሳቸውን ብቸኛ አማራጭ አድርገው ያቀርባሉ፡፡ ይህንን ለማድረግ አብዛኛዎቹ መሪዎች ሕዝብ በከፈለው ግብር የሚተዳደሩ መገናኛ ብዙኃንን የራሳቸውን ተረክ ለመፍጠር ይጠቀሙበታል፡፡ እነሱ ከሌሉ ሀገሪቷ የምትገባበትን ‹ሲኦል›  ይሰብኩበታል፡፡ ይህ ብቻ አይበቃቸውም፡፡ ምንም ዓይነት የተለየ ተረክ ለሕዝብ እንዲደርስ አይፈቅዱም፡፡ የሐሳብ አሀዳዊነትን በሕዝብ ላይ ለመጫን ይመቻቸው ዘንድ የበይነ-መረብ ማጥለል፣ የተለየ ሐሳብ ያላቸውን ጋዜጦች፣  መጽሔቶች ይዘጋሉ፤ ጋዜጠኞችን ያዋክባሉ፣  ያስራሉ፡፡ በዚህም የተነሳ ስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች ሀገርን የሚጠቅም ነው ብለው የሚያወጧቸው ምጣኔ-ሀብታዊ (ሌሎችም) ፖሊሲዎችን የተለየ ምልከታ ሰጥቶ ጥቅሞቹን እና ጉድለቶቹን ተንትኖ እና ከሕዝብ ፍላጎት ጋር ያላቸውን መጣጣም አመዛዝኖ ለሕዝብ የሚያቀርብ አማራጭ እንዳይኖር ያደርጋሉ፡፡ እናም ፖሊሲዎች መታረም ከሚችሉት ህፀፆቻቸው ጋር በሰሠሯቸው ሰዎች ተደጋግመው ከተወደሱ በኋላ ወደሥራ ይገባሉ፡፡

እነዚህ መሪዎች አንድ መሠረታዊ የሆነ የሰው ልጆች ተፈጥሮን ዘንግተዋል፡፡ ማንኛውም ጤነኛ ሰው የሚቀበለውን መረጃ እንደተሰጠው አይውጠውም፡፡ ሁልግዜም ባይሆን ባመዛኙ፣  የሰው ልጆች የሚሰጣቸውን መረጃ ማመዛዘን ይፈልጋሉ -  በተለይም ድጋፍ መስጠት/አቋም ሊይዙበት ለሚፈልጉት ጉዳይ ሲሆን፡፡ አማራጭ ትንተና ያጡ ዜጎ ችአንድ አንዳንዶቹ (ጥቂቶቹ) የራሳቸውን ትንተና በመስጠት አቋም ሲወስዱ አብዛኞቹ ለድጋፍም ሆነ ለተቃውሞ የሚበቃ አቋም ለመውሰድ በቂ ትንተና ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡በመጨረሻም ፖሊሲውን ተፈፃሚ ለማድረግ የሕዝብ ተሳትፎ/ድጋፍ አጥሮናል ብለው የሚያማርሩ የመንግሥት ድምፆችን መስማት እንጀምራለን፡፡

ምጣኔ ሃብት እና ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት

እ.አ.አ 1989 ድሬዝ እና ሴን የተባሉ የምጣኔ ሀብት ተመራማሪዎች ባያደረጉት ጥናት ነጻ መገናኛ ብዙኃን ባለበት ሀገር አንድም ግዜ ረሀብ ተከስቶ እንደማያውቅ ጠቁመዋል፡፡ ይህንንም ሲደግፉ ነጻ የሆነ የመረጃ ፍሰት ባለባቸው ሀገራት መንግሥታትን (ዴሞክራሲያዊ ባይሆኑም እንኳን) ከሕዝብ የሚመጣ ጫና ውስጥ ስለሚከታቸው እና ይህንንም ለማስወገድ ሲሉ ቀድመው የሕዝብን ጥያቄ የሚመልስ እርምጃ ስለሚወስዱ እንደሆነ ይተነትናሉ፡፡ ኢሻም፣ ካፍ ማን እና ፕሪቼት የተባሉ ምሁራን እ.አ.አ  1997 ባደረጉት ጥናት መሠረት ደግሞ ግለሰባዊ ነጻነቶች  (ሐሳብን የመግለፅን ጨምሮ) ማክበር በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚከናወኑ ፕሮጀክቶችን ምጣኔ-ሃብታዊ ውጤት  (Project’s Rate of return) እስከ 20 በመቶ ያክል ድረስ ይጨምረዋል፡፡ እንደነዚሁ አጥኚዎች ትንተና መሠረት ግለሰባዊ መብቶችን  (ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ/የመሰብሰብ ነፃነት፣ ሐሳብን በነፃነት የመያዝ እና የመግለጽ፣ ሕዝባዊ ጉዳዮች ላይ በነፃነት የመሳተፍ እና ነፃ ማኅበር ማቋቋም) አለማክበር በእኩል መጠን ከሚከሰት የዓመታዊ ምርት መቀነስ፣ የበጀት እጥረት ወይንም የወጪ እና ገቢ ንግድ ላይ ከሚያጋጥም ንዝረት ባልተናነሰ ሁኔታ በመንግስት የሚካሄዱ ፕሮጀክቶች ውጤታነት ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል፡፡

እንደ በመንግስት የሚተዳደሩ ፕሮጀክቶች ባይሆንም በግል ባለሀብቶች እና ተቋማት የሚካሄዱ ንግዶች ሐሳብን በነጻነት መግለጽ በሚቻልበት ሀገር ለገበያ የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች እና አገልግሎቶች የኅብረተሰቡን ደኅንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል እንዳይሆኑ ከፍ አድርገው ይጠነቀቃሉ፡፡ በግድየለሽነት ወይንም በአጭር ጊዜ ለመክበር በሚያደርጉት ሙከራ የህብረተሰቡን ደህንነት ወይንም ጥቅም አደጋ ላይ የሚጥል ዕቃ ወይንም አገልግሎት ቢያቀርቡ ነፃ መገናኛ ብዙሃን ሁኔታውን በማጋለጥ ህብረተሰቡን ከጉዳት ይጠብቃሉ፡፡

የሳንሱርዋጋ

የሐሳብ ብዝኃነትን በመቆጣጠር ሕዝብ እነሱ የሚሉትን ብቻ እየሰማ እንዲነዳ የሚፈልጉ መንግሥታት ሐሳብን ለማፈን ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ሐሳብ ለማፈን ከከሚጠቀሙባቸው መንገዶች በይነ መረብን ማጥለል እና ጦማሮች እዳይከፈቱ ማገድ፣ በይነመረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ መሰለል እና በሳተላይት የሚተላለፉ የሬድዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭቶች ሞገዶችን መከልከል ይጠቀሳል፡፡

የአውስትራሊያ መንግስት  በ2009 ዓ.ም ሊተገብረው ያሰበው የበይነ መረብ ማጥለልን በተመለከተ ዴቪድ በርድ የተባለ ጦማሪ እንደጻፈው በበይነ መረብ የሚተላለፉ መረጃዎችን ለማጥለል ጥቅም ላይ የሚውሉት ቴክኖሎጂዎች የበይነ መረብ አገልግሎት ፍጥነትን ከ2 በመቶ እስከ 70 በመቶ ይቀንሳሉ፡፡ የማጥለል ሥራውን  ‹በውጤታማነት የሚያከናውኑት› ቴክኖሎጂዎች ደግሞ ፍጥነቱን በደንብ የሚቀንሱት ናቸው፡፡

ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ደግሞ ኒውዮርክ ታይምስ አንድዜናለኢትዮጵያዊያን ይዞልን ወጥቶ ነበር፡፡ ፊንፊሸር የተባለ በይነ መረብን በመጠቀም ዜጎች ላይ ስለላ ለማድረግ የሚያስችል የረቀቀ ቴክኖሎጂን እንደሚጠቀሙ ከታወቁት  10 ሀገራት አንዷ ሀገራችን መሆኗን፡፡ እንደዘገባው ቴክኖሎጂውን ለመግዛት ከ350ሺህ  በላይ የአሜሪካን ዶላር ወጪ ማድረግ ይጠይቃል፡፡ ቁጥር አንድ ጠላቷ ድህነት ለሆነ ሀገር ሕገ-መንግሥቱን ጥሶ ዜጎች ላይ ለመሰለል ይህን ያህል ወጪ ማውጣት እውነትም አሀዳዊ ተረክ ለመፍጠር ምን ያህል ርቀት እንደሚኬድ ማሳያ ነው፡፡

በሳተላይት የሚተላለፉትን ሬዲዮ እና የቴልቪዥን ስርጭትን ለመደገፍ ምን ያህል የተወሳሰበ ቴክኖሎጂ እንደሚያስፈልግ እና እሱም ምን ያህል ወጪ እንደሚያስወጣ መገመትም ቀላል ነው፡፡

ምንም እንኳን አከራካሪ ቢሆንም ዜጎች በነጻነት ሲያስቡ እና ሐሳባቸውን በነጻነት መግለጽ ሲችሉ አዳዲስ እና ውጤታማ የንግድ ሐሳቦች ማፍለቅ ቀላል ይሆንላቸዋል፡፡ ይህም ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት መንፈግ ከሚያስከፍሉት ቀጥተኛ ያልሆኑት ዋጋዎች ውስጥ ሊካተት ይችላል፡፡

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 22, 2013

Friday, February 22nd, 2013
News, Community Heroes or Call-in, Crossfire and African Topics

ሙስሊም እስረኞች ጠበቃቸው

Friday, February 22nd, 2013
አቶ ተማም እስር ቤት ያሉ ደንበኞቻቸው ጅሓዳዊ ሐረካት የተባለው ዘጋቢ ፊልም በቴሌቪዥን መተላለፍ ደንበኞቻቸውን እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል።

የጅቡቲ ምክር ቤታዊ ምርጫ

Friday, February 22nd, 2013
አሊ ባራካት እንዳሉት በዚህ ምክር ቤታዊ ምርጫ ተቃዋሚዎች የሚያሸንፉ ቢመስልም በዚህ ምርጫ የሚሳተፉ ፓርቲዎች በብዙ መልኩ ልዩነት እንደሚታይባቸው ይነገራል። መሪዎቻቸውም ቢሆኑ በእድሜ የገፉ ናቸው።

የማኅበራዊ አውታሮች አጠቃቀም ስነምግባር

Friday, February 22nd, 2013
እንደ ፌስቡክ ባሉ የማኅበራዊ መገናኛ ዘርፎች አንዳንዶች የቤተሰባቸውን ሀዘን ጭምር ድንገት የሚረዱበት ደረጃ ላይ ተደርሷል። ከስነምግባር ውጪ የሆኑ አፀያፊ ምስሎችና ፅሁፎችም እንዳሻቸው ይወጣሉ፣ ሌላም ሌላም። የኢንተርኔት አጠቃቀም ስነምግባር እስከምን ድረስ መሆን አለበት?

ሳንሱር እና ሕግ፡ ከትናንት እስከዛሬ

Friday, February 22nd, 2013


የሰው ልጅ ሐሳቡን ለሌላው መግለጽ መጀመሩ ሰዎች የጋራ ባሕርያትን ይዘው ወደ አዲስ ስልጣኔ፤ ወደ አዲስ ሕይወት እንዲወጣ አድርጎታል፡፡ ነገር ግን የዚህ ትስስር ድንበር የለሽ መሆን ጉዳት አለው በማለት፤ በተለያዩ ወቅቶች በተለያዩ ምክንያቶች መረጃን የመለዋወጡ ሂደት ገደብ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ገደብ እንዲደረግ የሚያስገድዱት ዋነኛ ምክንያቶች ሦስቱን ዋነኛ ተቋማት መጠበቅ በሚል ሐሳብ ስር ይጠቃለል፡፡

እነዚህም ተቋማት ቤተሰብ፣ ቤተ እምነት እና ቤተ መንግሥት ናቸው፡፡ ቤተሰብን መጠበቅ ስንል ቤተሰብ የኅብረተሰብ መሠረት በመሆኑ ቤተሰብን እና ስርዓቱን የሚጎዱ ነገሮች (Obscene) በአደባባይ እንዳይኖሩ ማድረግ ማለታችን ነው፡፡ ቤተ እምነትን የሚያጎድፉ ነገሮችም (Blasphemous) እንዲሁ:: እንዲሁም በሦስተኝነት በሕግ የተዘረጋውን ስርዓት ለመጠበቅ ሲባል ሲሆን  ይሄም የግደባ ሂደት ሳንሱር (Censorship) ይባላል፡፡

የሕግ ማዕቀፉ እና ልምዱ ምን ይላል?
 
ከላይ የጠቀስናቸውን ሦስት ተቋማት ከመጠበቅ አንፃር የተለያዩ ሀገሮች የተለያየ የህግ ማዕቀፍ ዘርግተው ጥበቃ ያደርጋሉ፡፡ ከጥንታዊቷ ሮም እስከ የዘመናችን ነጻ እና ለዘብተኛ (Liberal) ሀገሮች ድረስ በተለያዩ ምክንያቶች በመነሳት የሐሳብ ዝውውርን በሕግ ሲገድቡ ነበር፤ አሁንም ይገድባሉ፡፡ ነገር ግን የሕግ ገደቡ ያለ አግባብ ተለጥጦ የግለሰቦችን መብት መግፈፍ ሲጀምር ያኔ የገደቡ ስህተት ይጀምራል፡፡ ለምሳሌ የሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ከመካከለኛው ዘመን መጀመሪያ ጀምሮ ለተከታዮቹ 500 ዓመታት፤ አብዛኛውን የሳይንስት አስተምህሮቶች (የጋሊሊዮን መሬት በፀሐይ ዙሪያ ትሽከረከራለችን የሚል እሳቤን ጨምሮ) እንደ የኑፋቄ ትምህርት (Heresy) በመቁጠር፤ በኅብረተሰቡ ውስጥ ምንም ዓይነት ስርጭት እንዳይደረግ በማለት በሕግ ገድባ ቆይታለች፤ ሕጉንም የተላለፉትን ከእስራት እስከሞት ትቀጣ ነበር፡፡ ይሄም የተደረገው የሕግ ገደብ የሳይንሱን ዕድገት አቀጭጮት ነበር፡፡ በጥቅሉ አሁን ባለው አለም አቀፍ እሳቤ ሕሳብን ማሰራጨት ሙሉ ለሙሉ የተፈቀደ መብት (Absolute Right) እንዳልሆነ ጥቅል ስምምነት ቢኖርም፤ ገደቡ ከየት ይጀምር የሚለው ግን አከራካሪ ነው፡፡

ምኑ ይገደብ?

ከላይ ለመጥቀስ እንደተሞከረው ሊገደብ የሚገባው መብት የትኛው መሆን አለበት የሚለው ሐሳብ ስምምነት  ላይ ያልተደረሰበት ጉዳይ ነው፡፡ ነገር ግን እንደ ኀልዮት ሊቃውንት የተለያየ ሐሳብ ይሰነዝራሉ፡፡ መንግሥት ራሱን እንደ ጠባቂ እና ሁሉን አድራጊ (state as Big Brother) በማድረግ ይህ የተፈቀደ ነው፤ ይህ ደግሞ የተከለከለ ነው የሚል ከሆነ የዜጎችን መብት ሊያቀጭጭ ይችላል የሚለው እሳቤ አንዱ ነው፡፡ ይህም - ይሄን ብትናገር፣ ብትጽፍ፣ ብታሰራጭ ዋ! - ማለት ሳንሱር በማስፈራራት (Censorship through intimidation) የሚለው ሐሳብ ነው፡፡ ሊቃውንቱም ይህ መሆን የሌለበት ነገር ነው ይላሉ፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት እንደ የኅብረተሰቡ ተወካይነቱ (As agent of the Society) ኅብረተሰቡ የማይቀበላቸውን ነገሮች በሕግ መገደቡ ተገቢ ነው የሚለውን ሐሳብ እናገኛለን፡፡ ይህም ማለት መንግሥት እና ኅብረተሰቡ በሚገደበው ነገር ላይ ስምምነት አላቸው እንደማለት ነው - Censorship through consensus፡፡ ይሄም የኅብረተሰቡን የሞራል እሴቶች የሚፃረሩ ጉዳዮች ላይ ገደብ መጣሉ ተገቢ ነው ወደሚለው ሐሳብ ያደርሰናል፡፡

ስንጠቀልለውም በቀዳሚነት (As a Rule) ሐሳብን የመግለጽ ገደብ አይኑር፤ ነገር ግን ኅብረተሰቡ ላይ ጉዳት ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮች ላይ ገደብ ማድረግ ይገባል ወደሚለው ድምዳሜ እንደርሳለን፡፡

ገደብ በኢትዮጵያ (Censorship In Ethiopia)

የተጻፈ ሕግ በሀገራችን መተግበር ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በጣሊያን ወረራ ጭምር በፖለቲካ ቢሮ አማካኝነት ቁጥጥር የነበረ ቢሆንም  ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ላይ ገደብ በማድረግ ቀዳሚነቱን የያዘው፤ የ1935ት ዓመተ ምህረቱ “የቴአትርና የሲኒማ አደራረግን ስለመመርመር” የወጣው አዋጅ ቁጥር 37/1935 ነው፡፡

በርግጥ ነገር ግን ለሳንሱር መሠረት የሆነው የሕግ ማዕቀፍ የተዘረጋው ከወረራው መቀልበስ በኋላ በወጣው አዋጅ ነው፡፡ በዚህ ‹ልዩ ልዩ ጨዋታዎችን ለመመርመር በወጣ አዋጅ› አንቀጽ 4 መሰረት፡ ‹‹ማንኛውንም ፊልም፣ ቲያትር እና ሪቪው ይህንም የመሰለ የልዩ ልዩ ጨዋታ ሁሉ የጨዋታ መርማሪ ሳይመረምራቸው ለሕዝብ እንዲታዩ ማቅረብ አይቻልም›› በማለት ይደነግግ ነበር፡፡ አስከትሎም አንቀጽ 7 ላይ ‹‹የጨዋታ መርማሪው ‹‹ማንኛውንም ፊልም፣ ቲያትር እና ሪቪው ይህንም የመሰለ የልዩ ልዩ ጨዋታ ሕዝብ ይየው ወይም አይየው ብሎ የሚወስን የሕዝብን ፀጥታና ንፅህና (ብልግና የሌለበት መሆኑን) አይቶ ነው፡፡›› በማለት የገደቡ ምክንያት ደህንነት እና ንፅህናን መጠበቅ እንደሆነ ቢነግረንም፤ ስርዓቱን የሚያስኮርፉ ማናቸውም ድምፆችን ለመገደብ እንደ መሳሪያ ተደርጎ ይሠራበት ነበር፡፡ ይህ ሕግ  ንጉሡ ከሥልጣን እስከ ወረዱበት ዘመን ድረስ ዘልቆ ከስርዓቱ ጋር አብሮ ከሰመ፡፡

ደርግ ወደስልጣን በመጣበት የመጀመሪያ የሽኩቻ ዓመታት ገደቦቹ ላልተው ነበሩ ቢሆንም፤ ስልጣኑን አጥብቆ ሲይዝ ግን የበለጠ አክርሮ የተለያዩ አዋጆችን እና ደንቦችን እያከታተለ ያወጣ ጀመር፡፡ ኅብረተሰባዊነትን ይቃወማሉ ያላቸውን ሐሳቦችም በኅብረተሰባዊነት ስም እየማለ ሲያሻው በሕግ አሊያም በጉልበት ‹ሐሳብ የሚታሰብ እንጅ የሚነገር አይደለም› (You can thought anything but, you can’t express it) በሚል ብሂል ሳንሱርን አክርሮ ይሰራበት ነበር፡፡

በንጉሡ እና በወታደራዊው መንግሥት ስርዓቶች ወቅት የነበረውን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ከሎሬት ፀጋዬ ገብረመድኅን ግፍ የበለጠ የሚነግረን የለም፡፡ ሎሬት ፀጋየ እንዲህ ይላሉ፡-

“ከፃፍኳቸው 41 ቴአትሮች ውስጥ (ከተረጐምኳቸውና በእንግሊዝኛም ከፃፍኳቸው ጭምር)፣ ዐሥራ ሁለቱን ሳንሱር ሙሉ በሙሉ አግዶብኛል፡፡ ሃያ አንዱን ቆራርጦብኛል፡፡ ሦስቱን ግማሽ ለግማሽ ጐራርዶብኛል፡፡ አራቱ ግን ገና ለመድረክ [አልቀረቡም] ከሦስቱ የሥነ ግጥም መጻሕፍቶቼ ውስጥ (ሁለቱ ገና አልታተሙም)፣ በሠላሳ ሰባት ነጠላ ዝርዝር ግጥሞቼ ምክንያት፣ የሳንሱር ቢሮ፣ የፀጥታው ክፍል ቢሮና የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቴ ቢሮ ከፍተኛ ሹማምንት ገስፀውኛል፡፡ ቀጥተውኛል፡፡ ዝተውብኛል፡፡ በአንዲት “ጆሮ ገድፍ” በምትባል ትንሽ ቴአትር ምክንያት የጃንሆይ መንግሥት ፀጥታ ቢሮ፣ ለሃያ አራት ሰዓት በቁጥጥር ስር አውሎኛል”

‹ሳንሱር ደህና ሰንብች›

የደርግ ስርዓት መገርሰስ ካመጣቸው መሠረታዊ ለውጦች አንዱ ሐሳብን በነጻነት የመግለጻ መብት መከበሩ ነው፡፡ የሳንሱር ቢሮም መዘጋቱ፡፡ ለዚህም መብት የመጀመሪያ ከለላ የሆነው የ1983 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሽግግር ወቅት ቻርተር ነው፡፡ ቻርተሩ በአንቀጽ አንድ ዓለም አቀፉ የሰብኣዊ መብት ደንጋጌ (Universal Declaration of Human Right) ያለምንም ገደብ ለኢትዮጵያዊያን ተግባራዊ የሚደረግ ሰነድ መሆኑን ከደነገገ በኋላ በተለይም እያንዳንዱ ግለሰብ የእምነት፣ ሐሳብን መግለጽ፣ የመደራጀት መብት አለው›› በማለት ይደነግጋል፡፡ ይሄንም ተከትሎ 1985ቱ የፕሬስ ሕግ መውጣት ሀገሪቱ ሐሳብን የመግለጽ መብትን ያለገደብ ለማክበር ቆርጣ መነሳቷን አመላካች ሆነ፡፡

ለዚህ ነጻነት ሕገ መንግሥታዊ ድጋፍ ለመስጠት በማሰብም በ1987 ዓ.ም በወጣው የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊት ሕገ መንግሥት አንቀጽ 29 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ፡ ‹‹ማንኛውምሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት የመሰለውን አመለካከት ለመያዝ ይችላል፡፡›› በማለት በአመለካከት ደረጃ ምንም ዓይነት ገደብ እንደሌለ አስረግጦ ሲያበቃ፤ በተመሳሳይ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ደግሞ ‹‹ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን የካትታል፡፡›› ብሎ መብቱን ያሰፋዋል፡፡ እንዲሁም በዚሁ አንቀፅ ንዑስ ቁጥር 3 ላይ ‹‹የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውም መልኩ የተከለከለ ነው፡፡›› በማለት ነፃነትን በሰፊው ያውጃል፡፡ ነገር ግን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት በሕግ ገደብ ሊደረግበት እንደሚችል አንቀፁ ያትታል፡፡

‹ሳንሱር እንደገና›!?

እነዚህ ሁሉ መብቶች በሰፊው በሕግ ከለላ ማግኝታቸው ኢሕአዴግ ሥልጣን በያዘበት የመጀመሪያው ዐሥር ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደ ትልቅ እምርታ የሚታይ ሲሆን ይሄንም ተከትሎ በሀገሪቱ ውስጥ የፕሬስ መስፋፋት እንዲሁም ሐሳብ መግለጫ ሜዳው መስፋት አሳይቷል፡፡ የተለያዩ መጽሔቶች ጋዜጦች እና የስነጽሑፍ ሥራዎች (መጽሐፍትን ጨምሮ) ስርጭትም በሚታይ ሁኔታ መስፋፋት ጀመረ፡፡ ይህ ሁኔታ ያልሰከነ በመሆኑ የሚታማውን የቅድመ 97 የፕሬስ ዘመን የሚጨምር ሲሆን ለዓመታት በቋሚነት የቆዩትን እንደነ ጦቢያና ጦማር የመሳሰሉትን የሕትመት ውጤቶችን ይዞ ዘልቋል፡፡  የምርጫ 97 ውጤት ደም አፋሳሽ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መንግሥት በጉዳዩ ላይ የፕሬስ ተቋማት ሰራተኞችን እና ጋዜጠኞችን ማሰሩን አስከትሎ ጠበቅ ያለ አቋም መያዝ ጀመረ፡፡

አዋጆቹ

ከምርጫ 97 በሁዋላ ምንም እንኳን የወንጀል ሕጉ ሐሳብን ከመግለጽ ጋር ተያይዞ ሊከሰቱ የሚችሉ ወንጀሎች እንደሚያስቀጡ ቢደነግግም ከዚህ በተጨማሪ ጋዜጠኞችን የሚጫኑ ቅጣቶችን በማከል ከብዙ አተካራ በኋላ የመገናኛ
ብዙኃን እና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ሕግን አፀደቀ፡፡ ከብዙ አካላትም በዋነኛነት ከጋዜጠኖች ሕጉ አፋኝ  እና ሕገ መንግሥቱንም የሚፃረር መሆኑን በመግለጽ ተቃውሞ መሰማት ጀመረ፡፡

በማስከተልም አወዛጋቢው የፀረ-ሽብር ሕግ ለፓርላማ ቀርቦ ፀደቀ፡፡ መገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነጻነት አዋጅ እንዲሁም የፀረ-ሽብር ሕጉ ሐሳብን ከመገደብ (Censorship) ጋር ያላቸው ተዛምዶ በዋነኛነት ተዘዋዋሪ ነው፡፡ ይሄም ማለት መገናኛ ብዙኃን እና የመረጃ ነጻነት አዋጅ ያስቀመጠው እስከ አንድ መቶ ሽሕ ብር የሚደርስ ቅጣት አቅመ ደካማውን ፕሬስ በአንዴ ከገበያ ውጭ ሊያደርገው ስለሚችል ጋዜጠኞች ራሳቸውን እንዲገድቡ (Self Censorship) የሚያስችል መሆኑ፤ እንዲሁም የፀረ-ሽብር ሕጉ ግልጽ ያልሆኑ እንቅስቃሴዎችን ጭምር በሽብር ተግባርነት የሚፈርጅ መሆኑ ዜጎች ራሳቸውን እንዲገድቡ እና ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን አሳልፈው እንዲሰጡ ማድረጉ ነው፡፡ ይሄም በሕግ ቋንቋ ‹Chilling Effect› ወይም ‹ስጋት ለበስ ቅልበሳ› የሚባለው ነው፡፡ ይህም ማለት ዜጎች ቅጣትን በመፍራት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን ከመጠቀም ወደኋላ ማድረግ (discouragement of the legitimate exercise of a constitutional right) ነው፡፡

እነዚህ ቀጥተኛ ያልሁኑ የራስን ግደባ ሁኔታዎች እንዳሉ ሆነው፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ መንግሥታዊ ተቋማት ‹የሥራ ውል› በሚል መጠሪያ፤ ለሕትመት የሚበቁ ጽሑፎችን በመርማሪ አስመርምረን ነው የምናትመው ማለታቸው፤ ጉዳዩን ከማባስም አልፎ በሕገ መንግሥት በግልጽ የተከለከለውን ሳንሱር በእጅ አዙር እየመጣ ነው እንዴ? ብለን እንድንጠይቅ ያስገድደናል፡፡

ከነዚህ ሕጎች እና ደንቦች በተጨማሪ እያደገ የመጣውን የድረ-ገጽ ተጠቃሚ ቁጥር መሠረት በሚያደርግ መልኩ ከምርጫ 97 ወዲህ ትክክለኛ ቁጥራቸውን ማወቅ የማንችላቸው ድረገጾች በኢትዮጵያ ብቸኛ የቴሌኮምኒኬሽን አገልግሎት አቅራቢ በሆነው በኢትዮቴሌኮም ሰርቨር እንዳይታዩ የሆኑ ሲሆን፤ ይሄም እገዳ (Censorship) ከአረቡ ዓለም መነቃቃት በኋላ እጅግ ተባብሶ በመቀጠል እንደ አልጀዚራ ያሉትን ዓለማቀፍ የዜና አውታሮችን ከማገድ ጀምሮ፤ የግለሰቦችን የማኅበራዊ ድረ-ገጽ አድራሻ እስከማፈን ቀጥሏል፡፡ (ከዚህ ጋርተያይዞ የዞን 9ኝን የጦማሮች ምን ጻፉ ጽሁፍ እዚህ ይመልከቱ) መንግሥት ለዚህ እና ከእገዳ ጋር ለተያያዙ ጥያቄዎች የሚሰጠው ምላሽ፤ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮን መንግሥታቸው ሀገሪቱን ከማረጋጋት አኳያ ማፈኑን እና የአፈና አቅማችን እያጠናከርን ነው ከማለታቸው በስተቀር፤ በደፈናው ‹እኔ  አላገድኩም› የሚል  ነው ፡፡(በተለይ የተለያዩ የፊስቡክ ገጾች እና ጦማሮችን የመዝጋት ልምድ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ መጥቶ የአቤ ቶክቻው የግል ፊስቡክ ገጽ፣ የዞን ዘጠኝ የፌስ ቡክ ገጽ እና ጦማር፣ ድምጻችን ይሰማ እንዲሁም በቀዳሚነት የተዘጋው የቀድሞው አዲስ ነገር ጋዜጣ የፌስ ቡክ ገጽ ይታወሳሉ፡፡)

ስናጠቃልልም የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት በግልጽ እገዳን እና አፈናን (Censorship) ከመከልከሉም በተጨማሪ፤ ኢትዮጵያዊያን መረጃ የማግኝት መብታቸው በሰፊው የተከበረላቸው መሆኑን ያትታል፤ ነገር ግን በተለይም ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ መንግሥት በሚያወጣቸው ሕጎች እንዲሁም ከሕግ ውጭ በሆኑ አካሄዶች እነዚህን መብቶች እያጠበባቸው እና እየገፋቸው እንደሆነ እውነታዎች ያሳያሉ፡፡ ይሄም በሀገሪቱ አንድ ዓይነት አስተሳሰብ (Singular Discourse) እንዲኖር መፈለጉም የዜጎችን በሕገ መንግሥት የተሰጠ መብት፤ በአዋጅ መንጠቅና ግፋም ሲል በጉልበት ወደመቀማት እየመራው ነው የሚለውን እሳቤ አጉልቶታል፡፡ ነገር ግን የ
Ben Shahn ፖስተር “You have not converted a man because you have silenced him." ይለናል፡፡

የዶክተር ዮናስ አድማሱ ትውስታ

Thursday, February 21st, 2013

Audio clip: Adobe Flash Player (version 9 or above) is required to play this audio clip. Download the latest version here. You also need to have JavaScript enabled in your browser.

የዛሬው የባህል ዝግጅታችን ትኩረት በስነ ፁሁፍና እና ቋንቋ መምህርትነት በሚታወቁት ዶክተር ዮናስ አድማሱ ስራዎች ላይ ይሆናል። ዶክተር ዮናስ ከሁለት ሳምንት በፊት በ69 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

በአዲስ አበባ ዮኒቨርሲቲ በቋንቋ እና ስነ ፁሁፍ አስተማሪነት የሚታወቁት ዶክተር ዮናስ ዜና ዕረፍት ሲሰማ፣ በተለይ በቅርብ የሚያውቋቸው በሀዘን ተውጠዋል። ዶክተር ዮናስ ምን አይነት ሰው ነበሩ? የስራ ባልደረባቸው ፣ የቀድሞ መምህራቸው እና አብሮ የመስራት ዕድል የገጠማቸው ሶስት የፕሮግራማችን ተሳታፊዎች ስለ ዶክተር ዮናስ ማንነት እና ስራ በባህል ፕሮግራም አጫውተውናል።

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ስነ-ፁሁፍ ሲነሳ አብሮ ስማቸው ከሚነሱት ሰዎች መካከል ዶክተር ዮናስ እና ታላቅ ወንድማቸው ዶክተር ዮሀንስ አዱማሱ ይገኙባቸዋል። ወንድማቸው ዮሀንስ አድማሱ ስለ ባለቅኔው ዮፍታሄ ንጉሴ የፃፉት መፅሀፍ ለዕትም ሳይደርስ ነበር ሞት የቀደማቸው። ዶክተር ዮናስም ይህንን መፅሀፍ ሲያዘጋጁ ረጅም አመታት እንደፈጀባቸው ዶክተር ሄራን ይናገራሉ። በመጨረሻም መፅሀፉ አልቆ ግን ለምርቃት ጥቂት ቀናት ሲቀረው ዶክተር ዮናስ አረፉ። መፅሀፉ ትናንት በብሄራዊ ትያትር ቤት ለምርቃት በቅቷል። ይህን መፅሀፍ ለዕትም ማብቃት ምናልባትም የዶክተር ዮናስ የመጨረሻ ምኞት ነበር።

ዶክተር ዮናስን እንዴት ልናስታውሳቸው እንችላለች? በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ስነ ፁሁፍ ዘርፍስ ምን አይነት ሚና ተጫውተዋል?የዶክተር ዮናስ አድማሱን ማንነት እና ስራ የቃኘንበትን ዝግጅት ያድምጡ።

[podcast]http://radio-download.dw.de/Events/dwelle/dira/mp3/amh/6DA05C01_2_dwdownload.mp3[/podcast]

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 21, 2013

Thursday, February 21st, 2013
News, Cultural Mosaic, Kebele Lives and Environment or Tech

#Ethiopia, #StopCensorship: ሐሳብን በነጻ መግለጽ በኢትዮጵያ – ሕገ መንግሥት ላይ እና በተግባር

Thursday, February 21st, 2013


በበፍቃዱ ኃይሉ

ሰሞኑ ‹‹የሕገ-መንግሥቱ›› ይከበር የበይነመረብ ዘመቻ 2ኛ ዙር በአንቀጽ 29 (ሐሳብንና አመለካከትን የመያዝና የመግለጽ መብት) ይከበር ዙሪያ በዞን ዘጠኝ አስተባባሪነት እየተካሄደ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ለዘመቻው ግብአት እንዲሆኑ አንዳንድ እውነታዎችን ስለሕገመንግሥቱ እና ስለቀደሙት፣ ስለአተገባበሩም ጭምር እነሆ፡-

ሐምሌ 30/1966 በንጉሡ ነገሥት መንግሥት ረቂቅ ሕገ-መንግሥት፡-

አንቀጽ 25/1

ማንኛውም ኢትዮጵያዊ የሐሳብ ነፃነት አለው፡፡ ማናቸውንም ሐሳብ በንግግር፣ በጽሑፍ ወይም በሌላ ዘዴ የመግለጽና የማሰራጨት እንዲሁም ሌሎች የገለጹትን የማወቅ መብት አለው፡፡

አንቀጽ 25/2

ማንኛውም ሰው በቴሌፎን፣ በቴሌግራፍ፣ በፖስታ ወይም በማናቸውም ሌላ የመገናኛ ዘዴ ሚስጢሩ እንደተጠበቀ የመነጋገርና የመላላክ መብት አለው፡፡

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መስከረም 1/1980 ያወጣው ሕገ-መንግሥት፡-

አንቀጽ 47/1

የኢትዮጵያውያን የንግግር፣ የጽሑፍ፣ የመሰብሰብ፣ ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ የማድረግና በማኅበር የመደራጀት ነጻነት የተረጋገጠ ነው፡፡

አንቀጽ 47/2

መንግሥት ለነዚህ ነጻነቶች ተግባራዊ መሆን አስፈላጊውን ቁሳዊና ሞራላዊ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

ኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት (ሕዳር 29/1987)፡-

አንቀጽ 29

የአመለካከት እናሐሳብን በነጻ የመያዝናየመግለጽ መብት

1.       ማንኛውምሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነትየመሰለውን አመለካከት ለመያዝይችላል፡፡

2.      ማንኛውምሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነትሐሳቡን የመግለጽ ነጻነትአለው፡፡ ይህ ነጻነትበሀገር ውስጥም ሆነከሀገር ውጭ ወሰንሳይደረግበት በቃልም ሆነበጽሑፍ ወይም በሕትመት፣በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃናሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨትነጻነቶችን የካትታል፡፡

3.      የኘሬስናየሌሎች መገናኛ ብዙኃን፣እንዲሁም የሥነ ጥበብፈጠራ ነጻነት ተረጋግጧል፡፡ የኘሬስነጻነት በተለይ የሚከተሉትንመብቶች ያጠኝልላል፣

/ የቅድሚያ ምርመራ በማንኛውምመልኩ የተከለከለ መሆኑን፣

/ የሕዝብን ጥቅም የሚመለከትመረጃ የማግኘት ዕድልን፡፡

በተራ ቁጥር 1 እና 2 ላይ እንደተመለከተው ንጉሡም ሆኑ ደርግ ሙሉ ሐሳብን የመግለጽ መብት መውጫቸው/መውደቂያቸው ሰዓት ላይ ለመስጠት ሞክረዋል/ሰጥተዋል፡፡ የኢሕአዴግ መንግሥት የሽግግር መንግሥቱ ሕገ-መንግሥት ላይ የብሔሮች መብት እስከመገንጠልን ያሰፈረ ቢሆንም ስለሐሳብ ነጻነት የሚናገረው የለም፡፡ በ1987ቱ ሕገ-መንግሥት ግን የተሻለ የሚባል የሐሳብ ነጻነትን ፈቅዷል፡፡ ከሌሎቹ መንግሥታቶች እርምጃም የሚለየው የፕሬስ ሕጉ ወጥቶ በተግባር ላይ የሚውልበት መንገድ መመቻቸቱ ነው፡፡ ሆኖም ሁሉም ነገሮች ባሉበት አልቀጠለም፡፡ የተሻሻለው የፕሬስ አዋጅ፣ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅና ሌሎችም መልሰው የመብቱን ወሰን አጥብበውታል፡፡ ነገር ግን አሁን ሐሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ገደብ የሚከናወነው በአስተዳደራዊ አፈና ነው፡፡

ከ1983 ወዲህ ያሉ እውነታዎች፡-

1.   የመጀመሪያው ነጻ ጋዜጣ ‹‹ዕይታ›› ይባላል፤ የፕሬስ አዋጁ ከመውጣቱ በታኅሳስ ወር 1984 መታተም ጀምሯል፡፡ የቅጁ ብዛት ከ50,000 እስከ 70,000 ይደርስ ነበር፡፡ በወቅቱ በርካታ ‹‹የስም ማጥፋት›› ክሶችን በመንግሥት አስተናግዷል፡፡ በመጨረሻም የቅጂ ብዛቱ ወደ 5,000 ደርሶ በጥቅምት ወር 1986 ሕትመቱ ተቋርጧል፡፡ (ቅድመ ምርጫ 97 አካባቢ ይታተሙ የነበሩ ጋዜጦች እትም እስከ 1050,000 ድረስ ከፍ ብሎ የነበረ ቢሆንም ከዚያ በኋላ እያሽቆለቆለ መጥቶ በ2004 መጨረሻ ላይ ሕትመቱ የተቋረጠው እና የወቅቱን እጅግ ከፍተኛ ቅጂ ያሳትም የነበረው ነጻ ጋዜጣ ፍትሕ ነበር፡፡ ፍትሕ የታገደበትን የመጨረሻ እትሙን በ30,000 ቅጂ ነበር ለብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ያዘዘው፡፡ በጥር ወር ስርጭት ላይ ከዋሉ ጋዜጦችን ያስመዘገበው የሪፖርተር እሁድ እትም ሲሆን እሱም 11,000 ነው /የብሮድካስት መረጃ/)

2.   እስከ ሐምሌ 1989 ብቻ 265 ጋዜጦች እና 120 መጽሔቶች ሕጋዊ ፈቃድ ወስደዋል፡፡ …… (በጥር ወር ለስርጭት የበቁት 12 የፖለቲካ ጋዜጦች፣ 6 የስፖርት እና 1 የጤናና ስነልቦና ጋዜጦች እና 21 መጽሔቶች ናቸው፡፡)

3.   በሕግ ባይከለከልም በኢትዮጵያ ለአንድም የግል ተቋም የቴሌቪዥን አገልግሎት አልተፈቀደም፡፡ ብቸኛው የግል አገር አቀፍ ሬዲዮ ስርጭት የፋና ሬዲዮ ሲሆን ሬዲዮ ፋና ንብረትነቱ የሕወሓት/ኢሕአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ነው፡፡ ሬዲዮ ፋና በተለያዩ ከተሞች ኤፍ ኤም ስርጭቶችን በማሰራጨት፣ የራሱን ሕንፃ በማስገንባት ወደኮርፖሬትነት ለማደግ የቻለ የመጀመሪያው እና ብቸኛው ሬዲዮ ጣቢያ ነው፡፡ ሸገር እና ዛሚ ኤፍ ኤሞች ሌሎች ‹‹በገለልተኛ›› የተያዙ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ሲሆኑ፤ የሸገር ትኩረት ማኅበራዊ ጉዳዮች ሲሆኑ፣ የዛሚ ትኩረት ደግሞ የመንግሥትን ፖሊሲ ማበረታታት እና ማሞካሸት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በኢትዮጵያ መቀመጫውን ያደረገ (.et ኤክስቴንሽን ያለው/ዋና ቢሮው እዚህ የሆነ) በድረገጽ ላይ የሚሠራ አንድም የዜና አውታር የለም፡፡

የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረቶች ግንኙነት

Thursday, February 21st, 2013
ውይታቸው ይበልጥ ያተኮረውም የአፍሪቃና የአውሮፓ ህብረቶችን ግንኙነትና በተለይም በአፍሪቃ ሠላምና ደህንነት ሊረጋገጥ በሚቻላቸው የአሠራር የትብብር መርሃ ግብሮች ላይ ያተኮረ ዶክተር ዙማ አዲሷ የአፍሪቃ ህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ወደ ብራሰልስ መጥተው ከህብረቱ ባለሥልጣናት ጋር ሲወያዩ ይህ የመጀመሪያቸው ነው ።

የአፍሪቃ ና የደቡብ አሜሪካ መሪዎች ጉባኤ

Thursday, February 21st, 2013
የደቡብ ደቡብ ሃገሮች ህብረት ባለፉት 4 አመታት ይህን ነው የሚባል ተጨባጭ ውጤት ባለማሳየት ይተቻል ። በሌላ በኩል 2 ተኛውን ጉባኤ ያደመቁት ፣ 3 ቱ መሪዎች በአሁኑ ጉባኤ ላይ አለመገኘታቸው የነውን ጉባኤ ያቀዘቅዛል የሚል ፍራቻ አሳድሯል ።

የአዲስ ሆስፒታል ፕሮጀክት በአዲስ አበባ

Thursday, February 21st, 2013
ሆስፒታሉን የሚገነባው የኢትዮ አሜሪካውያን ሐኪሞች ቡድን 3 አባላት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለለግንባታው የሚያስፈልጋቸውን ቦታ መረከባቸውንና ግንባታውም ከ 6 ወር በኋላ እንደሚጀመር አስታውቀዋል ።

21 02 13 ዜና 16:00 UTC

Thursday, February 21st, 2013

አባት ሀገር (የመጨረሻ ክፍል)

Thursday, February 21st, 2013


የሚወዱትን ሰው አጥቶ በብቸኝነት መኖር ከተስፋ ይልቅ በትዝታ ውስጥ እንድንኖር የሚያደርግ ነው፡፡ በማኅበረሰባችን ባህል የቤት ውስጥ ሥራዎች የሚባሉትን በአብዛኛው የሚሸፍኑት ሴቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች የተማሩም ቢሆኑ ወይም ያልተማሩ፣ ሠራተኞችም ቢሆኑ ወይም የቤት እመቤቶች የቤት ሥራ ይቀርላቸው ይሆናል እንጂ የቤት አስተዳደር አይቀርላቸውም፡፡ እነዚህ ሴቶች ሊቃውንትም ቢሆኑ ወይም ሳይንቲስቶች፣ የሀገር መሪዎችም ቢሆኑ ወይም የታወቁ ሃሳብ አመንጭዎች የቤት ውስጥ ጭቅጭቅ ግን አይቀርላቸውም፡፡ ጓዳ የራሱ ሳይንስ አለው፡፡ የጓዳ ሳይንስ እስከዛሬ በየትኛውም ትምህርት ቤት አይሰጥም፡፡ የጓዳ አስተዳደር በየትኛውም የአስተዳደር ትምህርቶች ውስጥ አልተካተተም፡፡
ይህ ነው እንግዲህ ለአባቴ የመጀመርያው ፈተና፡፡ ጓዳውን ማስተዳደር፡፡ በቤታችን ውስጥ እናታችን ካረፈች በኋላ ሦስት ዓይነት የቤት ሠራተኞችን አይተናል፡፡ የመጀመርያዎቹ ቤቱን ‹‹የወንድ ቤት ነው›› ብለው የሚያስቡና መደፋፋት፣ ማባከንና ማዝረክረክ ይቻላል ብለው የሚገምቱ ናቸው፡፡ ወንድ ጓዳ ድረስ አይዘልቅም፤ የተጠየቀውን ይሰጣል፣ ግዛ የተባለውን ይገዛል፤ ለምን አለቀ፣ መቼ አለቀ፣ እንዴት አለቀ አይልም ብለው የሚያስቡ ዓይነት ናቸው፡፡
 መጀመርያ አካባቢ አባቴም እንደሚሉት ነበር፡፡ እየቆየ ግን ወገቡን መያዝ ጀመረ፡፡ ቀድሞ የእናቴ ደመወዝና ትከሻ ይሸፍኗቸው የነበሩ ቀዳዳዎች ሁሉ መታየት ጀመሩ፡፡ እርሱም ራሱ በነገሩ ውስጥ ሲገባበት ግራ ይገባው ጀመር፡፡ ለሁለት ሕጻናትና ለአንድ አባወራ እንዴት አንድ ሊትር ዘይት በሦስት ቀን ብቻ እንደሚያልቅ ሊገባው አልቻለም፡፡ ‹‹ወጡ በዘይት ብቻ ቢሠራ እንኳን ይህንን ያህል ሊፈጅ አይችልም›› ማለት ጀመረ፡፡ ነገር ግን ሠራተኛ አሰናብቶ ሠራተኛ ማግኘት፣ እስኪገኝም የኛ መንገላታት እያሳሰበው ሁሉንም ይሸከመው ነበር፡፡ አንዳንዴ ሲመርረው ‹‹ወይ እናት ስንቱን ተሸክመሽው ኖረሻል›› ይልና ዕንባው ዱብ ዱብ ይላል፡፡
ሁለተኛዎቹ ሠራተኞቻችን ደግሞ ጥሩዎች ናቸው፡፡ ለእኛ ያዝኑልናል፡፡ እንደ እናት ለመሆን ይሞክራሉ፡፡ የአባታችን ሁኔታ ያሳዝናቸዋል፡፡ ችግሩ ኀዘናቸው ከልክ ያልፍና ‹አምጵ› እያሉ ከንፈራቸውን ሲመጡለት ይናደዳል፡፡ እርሱ የሚረዳውና የሚረዳው እንጂ የሚያዝንለት አይፈልግም፡፡ ችግሩ ደግ ሠራተኞቻችን አይበረክቱም፡፡
እንዳይበረክቱ የሚያደርጓቸው ዕድርተኞቻችን ናቸው፡፡ በሠፈራችን የወንድና የሴት ዕድር አለ፡፡ የወንድ ዕድር ገንዘብ ከመክፈል፣ ድንኳን ከመጣልና ማታ ማታ ካርታ እየተጫወቱ ከማምሸት በቀር ሌላ ጣጣ የለበትም፡፡ የሴት ዕድር ግን እንጀራ መጋገር፣ ወጥ መሥራት፣ ማስተናገድ፣ ንፍሮ መቀቀል፣ ፍራሽ ዘርግቶ ድንኳን ውስጥ መቀመጥ፣ ቡና ማፍላት አለበት፡፡ በዚህ ሁሉ መካከል ደግሞ ሐሜቱ አለ፣ ጠቡ አለ፣ መተቻቸቱ አለ፤ መነቋቆሩ አለ፡፡ አሁን እናቴ ካረፈች በኋላ የሴት ዕድሩ ጉዳይ የአባቴ ጣጣ ሆነ፡፡ የግድ ዕድሩን ለመሳተፍ በእናቴ ምትክ የቤት ሠራተኞቻችን እየሄዱ ሽንኩርት እንዲከትፉ፣ ሥጋ እንዲዘለዝሉ፣ ወጥ እንዲሠሩ፣ አንዳንዴም እንዲያስተናግዱ ይደረጋል፡፡ አንዳንዶቹ ሠራተኞቻችን እንደ መዝናኛ ስላዩት አያማርሩም፡፡ ደጋጎቹ ግን አይፈልጉትም፡፡ ሁለት ልቅሶ ከሠሩ በኋላ ይሄዳሉ፡፡
ሦስተኛዎቹ ሠራተኞቻችን ለፈተና የሚመጡ ናቸው፡፡ እንዲያውም አንድ ቀን የቤት ሠራተኛ የሚያመጡልን የሠፈራችን ሴትዮ እኛ ቤት ውስጥ መሆናችንን ሳያውቁ ‹‹እንግዲህ ዕወቂበት፤ ካወቅሽበት የቤት እመቤት ትሆኛለሽ፤ ካላወቅሽበት ደግሞ አንቺም እንደሌሎቹ ትወጫለሽ›› ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፡፡ መመርያው አልገባኝም ነበር፡፡ በኋላ ነው የተረዳሁት፡፡ ማታ ማታ ቤቱን የፋሽን ትርዒት ማሳያ ታደርገዋለች፡፡ ሽቱ ተቀብታ፣ ገላዋን ታጥባ፣ ስስ ልብስ ትለብስና ሳሎን ትቀመጣለች፡፡ ነገር ዓለሟ ሁሉ አልገባኝም፡፡
አባቴ ደግሞ እኛን የቤት ሥራ ማሠራት፣ ራት አብልቶ ማስተኛት ስላለበት ከሥራው ሮጦ ቤት ነው የሚመጣው፡፡ ቤት ሲገባ ሽቱዋ ያውደዋል፡፡ አባቴ ወንድ ነው፡፡ ይህንን አትርሱ፡፡ ያውም ገና በወጣትነቱ የሚወዳትን ሚስቱን ያጣ ወንድ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኔን ይዞኝ ወጥቶ በረንዳ ላይ እናመሻለን፡፡ ከራሱ ጋር እየታገለ መሆኑን ዐውቃለሁ፡፡ አባቴ ሌሊት ሌሊት ውኃ የመጠጣት ልማድ አለው፡፡ ማታ ከመተኛቱ በፊት በራስጌው ውኃ ይደረግለታል፡፡ ይህችኛይቱ ልጅ ግን ሆን ብላ ሲተኛ ጠብቃ መኝታ ቤቱ ትሄድና ውኃውን ታስቀምጣለች፡፡ ሁለት ጊዜ ከተኛ በኋላ በር እንዳትከፍት ሲነግራት ሰምቻለሁ፡፡ ነገር ግን አላቆመችም፡፡
አንድ ቀን እኔ ከትምህርት ቤት ግማሽ ቀን ተምሬ ተመለስኩ፡፡ እኒያ ሠራተኛ የሚያመጡልን ሴትዮና ሠራተኛችን በረንዳ ላይ ቡና ይጠጣሉ፡፤ መኛታ ቤቴ ገብቼ ዘጋሁት፡፡ ሲያወሩ ግን በመስኮት ይሰማኛል፡፡ ሴትዮዋ ሠራተኛችንን ይመክሯታል፡፡ የቤት ሠራተኛ ሆነው ገብተው በዚያው ሚስት ስለሆኑ ሴቶች ታሪክ ያጫውቷታል፡፡ ዓላማዋ ገባኝ፡፡ አባቴ ሲመጣ ነገርኩት፡፡ እንደ ልጅ ሳይሆን እንደ እኩያ እኅቱ ነበርና የሚያወራኝ እርሱም እንደገባው ነገረኝ፡፡ ከሁለት ቀን በኋላ እንድትሄድ ተደረገ፡፡
እኒያ የሠፈራችን ሴትዮ ተናደዱ ‹‹አያያዙን አልቻልክበትም፤ በየሳምንቱ እያስወጣችሁ እኔ ከየት አመጣለሁ፡፡ አያያዝ ማወቅ ያስፈልጋል፤ ሲቀጥሩ እንደ ሠራተኛ ሲያኖሩ እንደሚስት ሲሉ አልሰማህም›› አሉና ተቆጡ፡፡
አባቴን የቤት ሠራተኞቹ ብቻ አልነበሩም የተፈታተኑት፡፡ የገዛ ጓደኞቹም ደጋግመው ፈትነውታል፡፡ እርሱ የእኛ ነገር ነው የሚያሳስበው፡፡ በእናታችን አለመኖር በጣም እንደተጎዳን አድርጎ ያስባል፡፡ ጭንቀቱ ጉዳታችን እንዳይሰማን ለማድረግ ነው፡፡ ቤት በጊዜ ከገባ ታናሽ ወንድሜን ሽኮኮ አድርጎ እኔን ያዝልና ያጫውተናል፡፡ የቤት ሥራዬን አብሬው እሠራለሁ፡፡ ቅዳሜና እሑድ አውጥቶ ያዝናናናል፡፡ ልብሳችንን በማሽን ራሱ ያጥባል፤ ይተኩሳል፡፡ በቦርሳዬ የያዝኩትን ምግብ ራሱ ይከታተላል፡፡ ገላችንን የሚያጥበን እርሱ ነው፡፡ አልጋችንን የሚያነጥፈው እርሱ ነው፡፡ ተነጥፎ ካገኘው እንኳን እንደገና ገልጦ ያየዋል፡፡ ሰውነታችን የተኮሰ ወይም የከሳ ከመሰለው ሮጦ ወደ ሐኪም ቤት ነው፡፡ እንዲያውም ጭንቀቱን ያየው የሕጻናት ሐኪሙ ‹‹መጀመርያ ይደውሉልኝና ተነጋግረን ይመጣሉ›› ባይለው ኖሮ በየሦስት ቀኑ እዚያው ይገኝ ነበር፡፡
ይህንን ቤት ቤት የሚል ጠባዩን ግን ጓደኞቹ አልወደዱለትም፡፡ ‹‹ሴቶቹ ወንድ በሆኑበት ዘመን እንዴት ወንዱ ተመልሰህ ሴት ትሆናለህ›› ብለውታል፡፡
ከእነርሱ ጋር ወጥቶ ማምሸት እንዳለበት ደጋግመው መክረውታል፡፡ ሆን ብለው በመሥሪያ ቤቱ መስክ እንዲወጣ አድርገውታል፡፡ እንዳይቀየሙት ብሎ እንድ ቀን አብሯቸው ቢያመሽ በሚጠጣው ቢራ ውስጥ አንዳች ነገር አድርገው ዕንቅልፍ ዕንቅልፍ ሲለው አልጋ ይዞ እንዲያድር አድርገውታል፡፡ የሚስቱ ሐሳብ ይለቀው መስሏቸውም በዚያ ቀን አንዲት ሴት አብራው እንድታድር አድርገዋል፡፡ አባቴ ግን የሚቀየር ሰው አልሆነም፡፡ አዘውትሮ ሐዲስ ዓለማየሁን ይጠቅሳቸዋል፡፡ ደራሲ ሐዲስ ሚስታቸው ካረፈች በኋላ ለምን ሌላ እንዳላገቡ ሲጠየቁ ‹‹እርሷ ቀለበቴን እንዳደረገችው ወደ መቃብር ሄዳለች፤ እኔም ቀለበቷን እንዳደረግኩት እሄዳለሁ›› ብለው ነበር፡፡ ይህ ለአባቴ ትልቅ መመርያው ሆኗል፡፡ ‹‹እኔኮ ባለትዳር ነኝ፤ ከሚስቴ ጋር በተለያየ ቦታ እንኖራለን እንጂ አልተፋታንም፡፡ ባል አሜሪካ ሚስት ኢትዮጵያ ይኖሩ የለም እንዴ! እርሷ በሰማይ እኔ በምድር እየኖርን ነው፡፤ እንድ ቀን እንገናኛለን፡፡ ስንገናኝ ምን እንድላት ነው የምትፈልጉት?›› ይላቸዋል፡፡
ታናሽ ወንድሜንኮ እያዘለ ነበር የሚያስተኛው፡፡ ያውም በልጅ አንደበቱ ‹‹እማዬስ›› እያለ እያስጨነቀው፡፡ የሚመልሰው መልስ እያጣ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ‹‹እማዬ ካላበላችኝ አልበላም›› ይለዋል፡፡ ፊቱን በዕንባ እየታጠበ መልሱ ይጨንቀዋል፡፡ በተለይማ ትምህርት ቤት መሄድ ሲጀምር ‹‹እንደ ልጆቹ የእኔ እናት ለምን አታደርሰኝም›› ይለዋል፡፡ አንድ ፈጣን የሆነ የሠፈራችን ልጅ አለ፡፡ ከወንድሜ ጋር አብረው ነው የሚማሩት፡፡ እንድ ቀን ‹‹እናትህኮ ሞታለች›› አለው፡፡ ‹‹ውሸትክን ነው፤ ለሥራ ውጭ ሀገር ሄዳ ነው፤ ትምጣለች›› ሲል ወንድሜ መለሰለት፡፡ ‹‹ኧ-ራ፣ እናቴ ነግራኛለች ሞታለች፤ የተቀበረችው ደግሞ ገብርኤል ነው›› አለው፡፡ ወንድሜ እየተንቀጠቀጠ ነበር ከትምህርት ቤት የተመለሰው፡፡ እንደመጣ የመኝታ ክፍላችንን ገብቶ ዘጋው፡፡ እኔና ሠራተኛችን ብናንኳኳ ሊከፍት አልቻለም፡፡
ሲጨንቀን አባታችንን ጠራነው፡፤ እርሱ ደግሞ ሲደነግጥ ጊዜ ጓደኛውን ለምኖ በመኪናው ይዞት መጣ፡፡ ቢያንኳኳ ሊከፍትለት አልቻለም፡፡ በመጨረሻ በሩን ሰብሮት ገባ፡፡ አንድ ጥግ ላይ ተቀምጦ ያለቅሳል፡፡ አባቴ እንኳን ይህንን አግኝቶ እንዲያውም ዕንባው ቅርብ ነው፡፡ አብሮት አለቀሰ፡፡ እንኳንም ከጓደኛ ጋር መጣ እንጂ የትኛውን እናባብል ነበር፡፡ ጓደኛው እንደምንም ብሎ አረጋጋው፡፡ ‹‹እናቴ ሞታለች አይደል?›› ሲል አባቴ የሚፈራውን ጥያቄ ጠየቀው፡፡ አባቴ መልሱን አጥቶት ዝም አለ፡፡ ‹‹ንገረኝ›› አለው፡፡ ‹‹ለምን ጠየቅከኝ›› አለው አባቴ፡፡ ‹‹ኤርምያስ እናትህ ሞታለች አለኝ›› አለና አለቀሰ፡፡
አባቴ የሚያደርገው ጨነቀው፡፡ ምን ይበለው፡፤ አሁን ከእውነት ጋር ተፋጠጠ፡፡ ጓደኛው እውነቱን እንዲነግረው አበረታታው፡፡ አባቴ ተረጋጋና እውነቱን መናገር ጀመረ፡፡ እናታችን ምን ዓይነት እናት እንደነበረች፣ እንዴት ልትሞት እንደቻለች፣ አሁን በገነት እንዳለች፣ ወደፊት እንደሚገናኙ ለመናገር ሞከረ፡፡ ወንድሜ በትንሽ ልቡ ያዳምጠው ነበር፡፡ ከዚያም ይዞን በጓደኛው መኪና ወጣ፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ ለወንድሜ በጣም ይሳሳለት ነበር፡፡ ከሠፈር ልጆች ጋር እንዳይገኛኝ ብሎ ሌላ ትምህርት ቤት አስገባው፡፡
እንዲያውም እኛ ራሳችን ለአባታችን ፈተና ነበርን፡፡ ይህን ለምን በላህ፣ ይህን ለምን ጠጣህ፣ ይህን ለምን ለበስክ፡፡ ትታመማለህ፣ ትሞትብናለህ፣ እንዲህ ትሆናለህ ፣ እንዲያ ትሆናለህ እያልን ነጻነቱን የሚገፍ ቁጥጥር እናበዛበት ነበር፡፡ እርሱም እኛን ለማስደሰት ነጻነቱን ሳይቀር ይሠዋልን ነበር፡፡ አሁን ሳስበው ይቆጨኛል፡፡ 
እኔን ሴት አድርጎ ያሳደገኝ አባቴ ነው፡፡ ስለ ሴትነት፣ ስለ ወጣትነት፣ ስለ ፍቅረኛ፣ ስለ የወር አበባ፣ ስለ ሞዴስና ስለ ሌላውም ቁጭ አድርጎ ያስተማረኝ አባቴ ነው፡፡ አባቴ ለእኔ አባቴም፣ እናቴም፣ ጓደኛዬም፣ መምህሬም ነው፡፡ እጅግ ሩኅሩኅ፣ ለልጆቹ የሚያስብ፣ ለልጆቹ ራሱን የሠዋ፣ መልካሙን የወጣትነት እድሜውን ለእኛ ለልጆቹ ሲል እንደ ሽማግሌ ያሳለፈ፤ ሰፍሳፋና ጭንቀታም ነው አባቴ፡፡ እኔ ውስጥ እርሱ አለ፡፡ በራሴ እንድተማመን፣ የማስበውን እንድሆን፣ በትክክለኛውም መንገድ እንድጓዝ፣ ዛሬም በፊታችሁ እንድቆም ያደረገኝ ነው አባቴ፡፡ ልጅ ለማሳደግ ሲል ልጅ ሆኗል፡፡ ሴት ልጅን ለመቅረጽ ሲል ሴት ሆኗል፡፡ ቤቱን ለማስተዳደር ሲል እማወራ ሆኗል፡፡ ለኛ ሲል ጨዋታውን፣ ዕድገቱን፣ ጓደኞቹን፣ የውጭ ዕድሎቹን፣ የትምህርት ዕድሎቹን፣ የዝውውር ዕድሎቹን ሁሉ አምክኗል፡፡
ለዚህ ነው፡፡ ይህች ሀገር ‹‹እናት ሀገር›› እንደምትባለው ሁሉ ‹‹አባት ሀገር››ም መባል አለባት ብዬ የምከራከረው፡፡ በአዳራሹ የነበረው ሰው ሁሉ ማራቶናዊ በሆነ ጭብጨባ አጀባት፡፡

© ይህ ጽሑፍ በአዲስ ጉዳይ መጽሔት የወጣ ነው፤ በተመሳሳይ ሚዲያ መጠቀም አይፈቀድም

ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ለአቶ በረከት ስምኦን

Thursday, February 21st, 2013

ለተከበሩ አቶ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፤ የኮሙኒኬሽን እና ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር፣
ለተከበሩ አቶ በረከት ስምኦን፤ በሚኒስትር ማዕረግ፣ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ፣

ከ20 ዓመታት በፊት ፓርቲዎቻችሁ - ሕወሓትም ሆነ ብአዴን - ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች ሕይወታቸውን የገበሩለትን ጦርነት ያካሔዱት፥ ኢትዮጵያውያን ‹‹ጀርባቸውን ሳይመለከቱ›› በነጻነት አመለካከታቸውን እና ሐሳባቸውን እንዲያንፀባርቁ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ብዙዎች ደማቸውን ያፈሰሱለት፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ የተሰየመለት (አንቀጽ 29) ‹‹የአመለካከት እና ሐሳብን በነጻ የመያዝና የመግለጽ መብት›› ከኢትዮጵያውያን እጅ ቀስ በቀስ አፈትልኮ እየወጣ መሆኑ ቢያሳስበኝ ይህንን ግልጽ ደብዳቤ ለመጻፍ ተገደድኩ፡፡

ደብዳቤዬን መስመር ለማስያዝ እንዲመቸኝ ከኔ የተሻለ የምትረዱትን ነገር በማስታወስ ልጀምር፡፡ ኢትዮጵያ ከ80 ሚሊዮን የሚልቁ ሕዝቦች፣ ከ80 የሚልቁ ብሔሮች እና ብሔረሰቦች፣ በርካታ ሃይማኖቶች፣ እምነቶች እና ባሕሎች ያሏት አገር ናት፡፡ ሁሉም የየራሱ የሆነ ነገሮችን የሚረዳበት መንገድ ያለው ይህ ብዝኃ-ሕዝብ በፓርላማ ውስጥ ባለ አንድ ፓርቲ ሙሉ ድምፅ እና አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ አባል አማራጭ ሐሳብ ብቻ ሊወከል ፈፅሞ አይችልም፤ ስለዚህ ሕዝቦች ሐሳባቸውን በነጻ የሚገልፁበት ሌሎች አማራጮች ያስፈልጓቸዋል፡፡ እነዚህ አማራጮች ጋዜጣና መጽሔቶችን፣ ሬዲዮና ቴሌቪዥኖችን እንዲሁም አዲሱ ብዙኃን መገናኛ (new media) በመባል የሚታወቀውን በበይነመረብ ላይ ባሉ ድረአምባዎች፣ ጦማሮች እና ማኅበራዊ አውታሮች ላይ ዜጎች የሚያሰፍሯቸውን አስተያየቶች እና ሐሳቦች ያካትታል፡፡

በአሁኑ ወቅት በርካታ በማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የሚያወሩ መጽሔቶች እና ጥቂት የማይባሉ የስፖርት ጋዜጦች ለሕዝብ የሚደርሱ ቢሆንም፣ ማዕከላዊ ትኩረታቸውን ፖለቲካ አድርገው የሚጽፉ ሳምንታዊ ጋዜጦች ቁጥር ግን እየተመናመነ መጥቶ ከ10 በታች ሆኗል፤ ከነርሱም ውስጥ ገሚሱ ከተመሰረቱ 5 ዓመት የማይሞላቸው ሲሆን እንደሌሎቹ ከዚህ በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ከስመው እንደቀሩት እልፍ ጋዜጦች መጥፋታቸው አይቀርም የሚል ስጋት አለኝ፡፡ ይህ እንግዲህ የፕሬስ ነጻነት በአገራችን ከተጀመረበት ጊዜ አንጻር ሲታይ በየቀኑ ሁለት፣ ሦስት ጋዜጦች ከሚወጡበት እና የተለያዩ ሐሳቦች ከሚንሸራሸሩበት፣ በቀን ምንም ነጻ ጋዜጣ ላይወጣ ወደሚችልበት (ሰኞ እና ኀሙስን መጥቀስ ይቻላል) ጊዜ ዝቅ ብለናል ማለት ነው፡፡

ሁለት የግል ኤፍ ኤም ሬዲዮ ጣቢያዎች ያሉ ሲሆን አንዱ ትኩረቱን ከማኅበራዊ ጉዳዮች ሳያርቅ፣ ብዙዎች እንደሚሉት ‹‹ከመንግሥት ጋር ሳይጋጭ›› ለመዝለቅ እየሞከረ ሲሆን ሌላኛው ሙሉ ለሙሉ የሚያንፀባርቀው የገዢውን ፓርቲ ሐሳብ እና ርዕዮተ ዓለም ብቻ በመሆኑ አማራጭ ድምፅ ብሎ ለመጥራት ከባድ ነው፡፡ በተጨማሪም፤ አንድም የግል ቴሌቪዥን እስካሁን አልተፈቀደም፡፡

ሕገ-መንግሥቱ በአንቀጽ 29 (5) ላይ ‹‹በመንግሥት ገንዘብ የሚካሄድ ወይም በመንግሥት ቁጥጥር ሥር ያለ መገናኛ ብዙኃን የተለያዩ አስተያየቶችን ለማስተናገድ በሚያስችለው ሁኔታ እንዲመራ ይደረጋል፡፡›› ብሎ ቢደነግግም በተግባር የሚታየው እውነታ ግን ተቃራኒው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሚያሰራጫቸው አራት ቴሌቪዥኖች፣ የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ኤፍ ኤም 97.1 እንዲሁም የኢትዮጵያ ፕሬስ ኤጀንሲ የሚያሳትማቸው ጋዜጦች በሙሉ ለገዢው ፓርቲ የሚወግኑ፣ ተቃራኒ ሐሳብ የሚያመነጩ ወገኖችን የሚያፍኑ እና ፍርደገምድል የፕሮፓጋንዳ መሳሪያ መሆናቸውን ማንም ከሕዝብ የወጣ መንገደኛ አስቁመው ቢጠይቁት ይመሰክራል፡፡

አዲሱ ብዙኃን መገናኛን በመጠቀም የሚቀርቡ ዜናዎች እና መረጃዎች ቀልጣፋ እና በቀላሉ የመሰራጨት አቅም ያላቸው ቢሆኑም፤ መንግሥት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ለዘርፉ ትኩረት ባለመስጠቱ በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚጽፉ፣ ራሳቸውን የድረገጽ ዜና እና መረጃ አገልግሎት ለመስጠት በሕጋዊ መንገድ ያስመዘገቡ ያገር ውስጥ የሚዲያ ተቋማት የሉም፡፡ ይሁን እንጂ በውጭ አገር የሚኖሩ ዜጎቻችን የመሠረቷቸው በርካታ ድረገጾች እና አገር ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵያውያንም በትርፍ ሰዓት ሊጽፉባቸው የመሠረቷቸው በርካታ ጦማሮች አሉ፡፡ እነዚህ የሕዝብ አስተያየቶች፣ እና አማራጭ ምክረሐሳቦች የሚንጸባረቁባቸው ጦማሮች እንኳንስ መንግሥትጋ ደርሰው ለስህተቶቹ የእርምት እርምጃ እና ለብሶቶቹም ምላሽ ሊሰ’ጥባቸው ቀርቶ ከጸሐፊው በቀር ኢትዮጵያ ውስጥ ላለ አንድም ዜጋ ሳይደርሱ እንዲቀር ድረገጾቹ ከስር፣ ከስር እየታገዱ ይገኛሉ፡፡

ክቡራን ሚኒስትሮች፣

ኢትዮ-ቴሌኮም ‹‹ኢትዮጵያን ከመጪው ዘመን ጋር የማገናኘት›› ሕልሙን የሚፈፅመው በተቀላጠፈ እና ነጻ የመረጃና ተግባቦት አገልግሎት እንጂ በከፊል በተገደበ ተግባር ሊሆን አይችልም፡፡ የብሮድካስት አገልግሎት የገዢው ፓርቲን አቋም ብቻ ለይቶ እያሰራጨ ሕዝቡን በአንድ አስተሳሰብ ብቻ ለመቅረፅ የሚያደርገው ሙከራ ከስነምግባርም ሆነ ስለወደፊቷ ኢትዮጵያ ከሚያስብ ሕሊና አንጻር ተገቢ አይደለም፡፡

መንግሥት የፕሬስ ነጻነቱን የሚያፍንባቸው በርካታ መንገዶች ናቸው፡፡ በብሮድካስት ባለሥልጣን መሥሪያ ቤት የሕትመት ፈቃድ ለማውጣት የሚሄዱ የድርጅት ወኪሎች በፖለቲካዊ አመለካከታቸው ምክንያት ይከለከላሉ ወይም ተሰላችተው እንዲቀሩ ተከታታይ እና የተራዘሙ ቀጠሮዎች የሚሰጥበት አስተዳደራዊ በደል ይደርስባቸዋል፤ (የቀድሞው ‹አውራምባ ታይምስ› ጋዜጠኞች ተሰብስበው የመሠረቱት አሳታሚ በዚህ መንገድ አዲስ ጋዜጣ ማሳተም ሳይችል ቀርቷል)፡፡ ማተሚያ ቤቶችም ቢሆኑ ፈቃድ የተሰጣቸውን ጋዜጦች ‹‹በበላይ አካላት ትዕዛዝ›› እንዳይታተሙ ያግዳሉ፤ (የፍትሕ ጋዜጣን እግድ መጥቀስ ይቻላል)፡፡ አዲስታይምስ መጽሔትም በብሮድካስቱ ባለሥልጣን ፈቃዱ እንዳይታደስ ተከልክሏል፡፡ በመንግሥት በጀት የሚተዳደረው ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሳንሱር የሚከለክለውን የሕገ-መንግሥት አንቀጽ (29/3/ሀ) የሚጋፋ የሥራ ውል ያስፈርማል፤ ሌላኛው የመንግሥት ይዞታ ቦሌ ማተሚያ ቤትም በተመሳሳይ መንገድ አንድ ማኅበራዊ ጉዳይ ላይ እና ሌሎች የስፖርት ጋዜጦችን ብቻ ይዞ የፖለቲካ ጋዜጦችን ‹‹ሥራ ይበዛብኛል›› በሚል ሰበብ እንዳይታተም ያደርጋል፡፡

ጥቂት የማይባሉ የግል ማተሚያ ቤቶች ያሉ ቢሆንም፣ ሁሉም ሊባል በሚቻል መልኩ አንድን ጋዜጣ ለአንዴ ብቻ ካተሙ በኋላ ደግመው አያስተናግዱም፡፡ ይህም የሚሆነው ‹‹በመንግሥት ወይም ባለሥልጣናት ጫና›› እንደሆነ አሳታሚዎቹ በተደጋጋሚ የገለጹት ጉዳይ ነው፡፡ ከዚህም በላይ፣ ጋዜጠኞች እየታሰሩ ነው፤ ሌሎችም በመንግሥት አካላት ጫና አገራቸውን እየለቀቁ ለመሰደድ ተገደዋል፡፡  ይሄ ደግሞ በቀሪዎቹ ጋዜጠኞች ላይ ራሳቸውን እና ሐሳባቸውን ሳንሱር እንዲያደርጉ፣ ዜጎች በየተገናኙበት ብሶታቸውን ‹ሌላ ሰው ሰማኝ አልሰማኝ› በሚል ድምፃቸውን ዝቅ አድርገው በሹክሹክታ እንዲያወሩ የሚያደርግ ፍርሐት ውስጥ ከትቷቸዋል፡፡

ብዙ ጋዜጦች በታገዱበት እና ቀሪዎቹም ‹‹መንግሥትን የማያስከፉ›› ይዘቶች ላይ በሚያተኩሩበት በዚህ ጊዜ ዜጎች ብሶታቸውን የሚተነፍሱበት እና መረጃዎችን የሚያገኙባቸውን ሌሎች አማራጮች መፈለጋቸው የማይቀር ነው፡፡ ለዚህም ነው በተለያዩ የድረአምባ ጦማሮች እና የማኅበራዊ አውታሮች ላይ የውይይት መድረኮችን የሚከፍቱት፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ማኅበራዊ አውታሮችም በኢትዮጵያ እንዳይነበቡ እየታገዱ ነው፡፡ ለእገዳው የተለያዩ ኃላፊነቱን ሊወስዱ የሚችሉ ቢሮዎች ቢኖሩም፣ ዋናው ግን የተሌኮም አገልግሎቱን በብቸኝነት የሚመራው ኢትዮ-ቴሌኮም ነው፡፡

የኢትዮ-ቴሌኮም የመረጃ ማጥለል ሥራ፣ በግል ባደረግነው የማጣራት ሙከራ ብቻ ከ200 በላይ ድረአምባዎችን እና ጦማሮችን በኢትዮጵያ እንዳይነበቡ አግዷል፡፡ ይህ እገዳ ሲደረግ ምንም የተሰጠ መግለጫ ባይኖርም መንግሥትን ‹‹የሚያስቀይሙ›› ሥራዎች ላይ መሆኑ በግልጽ ያስታውቃል፡፡ ሌላው ቀርቶ፣ ዓለም አቀፎቹ የሲኤንኤን፣ ቪኦኤ እና አልጄዚራ ድረአምባዎች በተለያዩ ጊዜ ባቀረቡት መረጃ ምክንያት የመዘጋት እና እንደገና የመከፈት ዕጣ ቀምሰዋል፡፡ ይህንን የተመለከተ ዜጋ ምናልባት የሚታገዱት የመረጃ ምንጮች ለሕዝብ ደኅንነት የሚያሰጉ መረጃዎችን የያዙ ይሆናል ብሎ ሊያስብ ይችላል፤ ነገር ግን የሚታገዱትን ገጾች መረጃ ላነበበ እውነታው አያሻማም፤ ገጾቹ የሚያቀርቡት መረጃ እና ዕውቀት ቢሆንም መንግሥት ላይ ያላቸውን ተቃውሞ/ትችት ግን የማይሸሽጉ ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ በኢትዮጵያ ለማኅበረሰብ ደህንነት የማይበጁ፣ ከሕዝቡ ባሕልና ወግ ጋር የማይሄዱ የሚባሉትን የልቅ ወሲብ ቪዲዮ እና ምስል የሚያቀርቡ ድረገጾች - አንዳቸውም አለመታገዳቸው ሌሎቹ ድረአምባዎች የሚታገዱት ለማኅበረሰቡ ታስቦ እንዳልሆነ መልዕክት ይሰጣል፡፡

ስለዚህ ክቡራን ሚኒስትሮች፣

መንግሥት የዜጎችን ሐሳቦች፣ ጋዜጦች እና ጦማሮች በተደራጀ መልኩ እያሰሰ እና እያነበበ የሕዝቦችን ብሶት እና ችግር ተረድቶ ለመፍትሔው መረባረብ ሲኖርበት፣ ዜጎች መረጃዎቹን እንዳያወጡ እንቅፋት መሆንን ከመረጠ በየት በኩል ኃላፊነት የሚሰማው ማኅበረሰብ መፍጠር ይቻለዋል? መንግሥት በምሳሌነት የማያሳየውን ሥርዓት ከሕዝቡ እንዴት መጠበቅ ይቻለዋል?

እንግዲህ እነዚህን ጥያቄዎቼን በቅን ልቦና ተረድታችሁ ለጥያቄዎቼ ሁሉ መልስ እንደምትሰጡኝ በማመን የሕገ-መንግሥቱን አንቀጽ 29 (2) በመጥቀስ ደብዳቤዬን እቋጫለሁ፡-
‹‹ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው፡፡ ይህ ነጻነት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በጽሑፍ ወይም በሕትመት፣ በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠው በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ፣ ማንኛውንም ዓይነት መረጃና ሐሳብ የመሰብሰብ፣ የመቀበልና የማሰራጨት ነጻነቶችን ያካትታል፡፡››

ሕገ-መንግሥቱ ይከበር፤ የአመለካከትና ሐሳብን በነጻነት የመያዝና የመግለጽ መብት ይከበር!


ሐሳባቸውን የመግለጽ ነጻነታቸውን ከተነፈጉት ዜጎች አንዱ፣

በፍቃዱ ኃይሉ

ህወሃት ሊወድቅ ነው በያሬድ አይቼህ

Wednesday, February 20th, 2013

(ለነጻነታችን እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!)

ገዢው ፓርቲ ለጥገናዊ ለውጥ ምንም አይነት ቦታ የማይሰጥ መሆኑን በተደጋጋሚ ግልጽ አድርጓል። አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትርም ይህንኑ ጉዳይ አስምረውበታል። ከዚህ የተነሳ ከገዢው ፓርቲ ጋር የነበረው የምርጫ ትግል በአጠቃለይ መክኗል። ዛሬ አገራችን ሙሉ በሙሉ ወደ ነጻነት ትግል ምዕራፍ ገብታለች።

ፓለቲካ አይነት ፡ አይነት አለው። የምርጫ ፓለቲካ እና የነጻነት ፓለቲካ አንድ አይደሉም። የምርጫ ፓለቲካ ንጹህ ነው ፡ ጭምት ነው። የነጻነት ፓለቲካ ግን ይጨክናል ፡ ይቆሽሻል።

የአገራችን ዘመናዊ የፓለቲካ ታሪክ ሲቃኝ በተደጋጋሚ የሚታየው ፡ ባለፉት 40 ዓመታት አብይ ለውጥ አራማጆች ከየዋህነታቸው እና ከንጹህ የፓለቲካ ስልታቸው የተነሳ ለአገራቸው የነበራቸው ራዕይ ተጨናግፏል ፡ መክኗል ፤ ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ብዙ ታላላቅ ሊሂቃኖቻችንም በከንቱ ጠፍተዋል።

ካለፉት ያልተሳኩ የነጻነት ሙከራዎች ተምረን ፡ አሁን ያለውን ትልቅ የነጻነት ዕድል በተሳካ መልኩ ለመጠቀም ከፈለግን ፡ ለነጻነታችን መጨከን እና መቆሸሽ አማራጭ የሌለው መንገድ ሆኗል።

ሙከራ 1፦ መንግስቱ እና ገርማሜ ነዋይ

አፄ ኃይለስላሴ ላይ ተደርጎ የነበረው የ1953 ዓ.ም የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አራማጆች ፡ ወንድማማቾቹ መንግስቱ ነዋይ እና ገርማሜ ነዋይ ፡ ውጥናቸው ለምን እንደ መከነ ሲመረመር ዋናው ምክንያቱ ንጹህና ጭምት የፓለቲካ ስልት ነው።
የንጉሳዊው ስርዓት በኢትዮጵያ ጭሰኛ ላይ ያደርግ የነበረውን ጭቆና ችላ ማለት ያልቻሉት ወንድማማቾች ፡ ንጉሱን ከስልጣን አስወግደው ፍትሃዊ የመንግስት እና የምጣኔ ሃብት ስርዓት ለመቅረጽ መመኘታቸው ድንቅ ነበር።

ሆኖም ግን እቅዳቸው ያልበሰለ ፡ ያልጨከነና ለመቆሸሽ ያልደፈረ ነበር። ከዚያም የተነሳ መፈንቅለ መንግስቱ ከሸፈ። መግደል የነበረባቸውን በጊዜው አለመግደላቸው ፡ ማሳተፍ የነበረባቸውን ባለማሳተፋቸው ፡ መቅደም የነበረባቸውን ባለመቅደማቸው የተነሳ የነበራቸው ራዕይ ተኮላሽቷል። የመፈንቅለ መንግስቱ ጠንሳሾች የዋህነታቸውና ፡ ንጹህነታቸው አስበልቷቸዋል።

ሙከራ 2፦ ጄኔራል መርድ ፡ ጄኔራል አምሃ እና ጄኔራል ፋንታ

በ1980 ዓ.ም የደርግን ስርዓት የተቃወሙ ጄኔራሎች ኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማሪያምን ከስልጣን አንስተው ፡ በጊዜው ከነበሩ አማጽያን ጋር ተወያይተው አገራዊ ሰላም እና ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመፍጠር መፈንቅለ መንግስት ሞክረው ነበር። ሙከራው አልተሳካም ነበር። ያልተሳካበትም ምክንያት ያው ንጹህና ጭምት ስልት ነበር።

የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራ የተከሰተው ኮ/ል መንግስቱ ወደ ምስራቅ ጀርመን ለጉብኝት ሲሄዱ ነበር። በዚህ ወቅት የጠንሳሾቹ ትልቁ ስህተት ተፈጸመ። ስህተቱም “ኮ/ሉ ይበሩበት የነበረውን አውሮፕላን አየር ላይ እንዳለ ይመታ” የሚለውን ሃሳብ አለመቀበላቸው ነው።

“አውሮፕላኑ የህዝብ ንብረት ነው” ፡ “በአውሮፕላኑ ውስጥ ፡ ከኮ/ል መንግስቱ ሌላ ፡ የሌሎችን ሰዎች ህይወት ማጥፋት የለብንም” ከሚሉ ንጹህና ጭምት የፓለቲካ ስልቶች የተነሳ ኮ/ሉ ምስራቅ ጀርመን በሰላም ደረሱ። መፈንቅለ መንግስቱም መከነ።

የግንቦት 1980ው ሙከራ ከየዋህነት እና ከገርነት የተነሳ ከሸፈ። ያኔ ጄነራሎቹ ጨክነው እና ቆሽሸው ቢሆን ኖሮ ፡ አሁን አገራችን የትግራይ ጠባብ ብሄርተኞች ግዛት ከመሆን ይልቅ ፡ የህዝባዊና ዴሞክራሲያዊ መንግስት የመመስረት አጋጣሚያችን ሰፊ ይሆን ነበር።

ሙከራ 3፦ አዲስ አጋጣሚ

አገራችን ላለፉት 21 ዓመታት ስታምጥ ኖራ አሁን ከምጧ የምትገላገልበት ወቅት ላይ ደርሳለች። ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ሊወጣበት የማይችለው አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ህወሃት እንደ ቀድሞው ተመልሶ ሊያንሰራራ አይችልም።

ሆኖም ግን ካለፉት ሁለት የነጻነት ሙከራዎች ተምረን አሁን ያገኘነውን አጋጣሚ በመጠቀም የስልጣንን ልጓም ለህዝብ ካላስጨበጥን ፡ ከጭምት እና ከንጹህ የፓለቲካ ስልት የተነሳ ፡ አዱሱ አጋጣሚ ሊያመልጠን ይችላል።

ስለሆነም ፓለቲካችን የምርጫ ፓለቲካ ሳይሆን የነጻነት ፓለቲካ ስልትን መጠቀሙ ቁልጭ ያለ ጉዳይ ነው። ሳንጨክንና ሳንቆሽሽ ነጻነት አይኖርም። በፍጹም አይኖርም። በጭራሽ አይኖርም። ልብ በሉ! ካለፈው ተምረን የተለየ ስልት ካልተጠቀምን ወደ ባርነት እና ወደ ጭቆና ተመልሰን እንዳረጋለን።

ምን እናድርግ? እንጨክን ፡ እንቆሽሽ!

ግልጽና ቁልጭ ያለ የነጻነት ትግል አማራጭ የሌለው ስልት ነው። በዚህ ወቅት “የትግራይ ህዝብ ወያኔ ነው ወይስ አይደለም?” የሚለውን የሞኝ ዘፈን ትተን ነገሩን ቀለል ማድረግ ነው። የትኛው ትግሬ ‘ነቅዟል’ ፡ የትኛው ትግሬ ‘አልነቀዘም’ የሚለው የሚታወቀው ከነጻነት በኋላ ብቻ ነው።

በነጻነት ትግል ወቅት ንጹሃን ሰዎች ሰለባ መሆናቸው የማይቀር ነው። ለዚያ ህሊናችንን እናስፋ። ህወሃት በስብሶ እንደ ተነቃነቀ ጥርስ ሆኗል ፡ የሚመነግለውና የሚነቅለው የህዝብ መስዋዕትነት ብቻ ነው።

በዚህ ወቅት ፡ ጽዋው እስኪሞላ እና የሃይል ሚዛኑ እስኪያዘነብል ድረስ ፡ ቢያንስ እንደ ግብጽ አብዮት 1 ሺ ሰማዕታት ፡ ቢበዛ ደግሞ እነደ ሶርያ የነጻነት ትግል ከ30 እስከ 60 ሺ ሰዎች ሊሰዉ እንደሚችል በመገንዘብ ህሊናችንን እናዘጋጅ። የሚሰዉ ይሰዋሉ።

ጥቂቶች ተሰውተው 80 ሚሊዮኖች ነጻ ይሆናሉ።

አዎ! የሚሰዉ ይሰዋሉ። “ለምን የድሃ ልጅ ይሙት?” “ለምን ዲያስፓራ አይዋጋም?” ለሚሉት የሰነፎችና የቱልቱላዎች ንትርክ አሁን ቦታና ጊዜው አይደለም። ህወሃት የትግራይን ህዝብ በዘፈን እና በከንቱ ሽንገላ አታሎ የእሳት ራት አድርጐ ስልጣን ላይ ተንፈራጥጧል። ዛሬ ለአገራችን ነጻነት የሚሰዉ ወገኖቻችን ይሰዋሉ።

ደም ሳይፈስ ነጻነት አይኖርም! ይህንን መራራ እውነታ እንቀበል። እንቆሽሽ። ከነጻነት በኋላ እንጸዳለን ፡ እንቀደሳለን።

ሌላው ጉዳይ ፡ የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ላይ ፡ በተለይም በትግራያን ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጥቃት መገንዘብ ነው። በህብረተሰባችን ውስጥ ትግራያን አበይት የስርዓቱ ተጠቃሚና ‘ባለጊዜ’ ናቸው ፡ የሚለው እምነት በሰፊው ስላለ በልዩ ልዩ ክልሎች የሚኖሩ ትግራያን ላይ ጥቃት ሊደርስ ይችላል። ያ አይነቱ ክስተት ሊያስደነግጠንም ፡ ከነጻነት ትግላችን ሊያደናቅፈንም አይገባም።

የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች እና ‘ባለጊዜዎች’ ቢኮረኮሙ ፡ ኩርኩሙን ታሪክ ሚመዘግበው ለነጻነት ትግል ከሚከፈለው ዋጋ ጋር ደምሮ ነው። እግረ መንገዳችንን እነርሱንም ነጻ እናወጣቸዋለን።

ያም ሆነ ይህ፦ “ጅብ ከሚበላህ ፡ ጅብ በልተህ ተቀደስ።” 

በአዲስ አበባ የፍተሻና የዝርፊያ አቤቱታ

Wednesday, February 20th, 2013

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ልዩ አካባቢዎች “በሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ያነጣጠረ የቤት ለቤት ፍተሻና ዘረፋ እየተካሄደ ነው” የሚል ጥቆማ በደረሰን መሠረት ሁኔታውን ለማጣራት ሞክረናል። በጥቆማው መሠረት በሌሊት ፍተሻ የተሠማሩት ሰዎች ማንነታቸውን እንደሚደብቁና የጥቃቱ ሰለባዎች ደግሞ፥ በየካና ቦሌ ክፍለ ከተሞች፥ በኮልፌ ቀራንዮ፥ ቤቴልና አካባቢው ሠፈሮች የሚኖሩ ሙስሊሞች ናቸው።

ሙስሊሞቹ ይህ በዘመቻ መልክ እየተፈፀመብን ነው ያሉት የቤት ፍተሻና ዝርፊያ በእርግጥ እየተካሄደ ነወይ? ከሆነስ ለምንና ባሁኑ ወቅት ይካሄዳል?
እነዚህንና ሌሎች ጥያቄዎች ይዘን ማምሻውን የጥቃቱ ሰለባ ሆነናል ወደሚሉ ሰዎችና ፖሊስ ደውለን ነበር።

ሰሎሞን ክፍሌ ነው ዘገባውን ያጠናቀረው፤ ያዳምጡት

አዲስ አበባ – የፍተሻና የዝርፊያ አቤቱታ

Wednesday, February 20th, 2013
ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ልዩ አካባቢዎች “በሙስሊሙ ማኅበረሰብ አባላት ላይ ያነጣጠረ የቤት ለቤት ፍተሻና ዘረፋ እየተካሄደ ነው” የሚል ጥቆማ በደረሰን መሠረት ሁኔታውን ለማጣራት ሞክረናል።

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 20, 2013

Wednesday, February 20th, 2013
News, Ethiopians in America, Americana, Democracy and Women and Family

ምድራችንና የስባሪ ከዋክብት አደገኝነት

Wednesday, February 20th, 2013
ባለፈው ሳምንት ዓርብ፤ ከኅዋ በኩል ሁለት አስገራሚም፣ አስደንጋጭም ዜና ለፕላኔታችን ደርሷት ነበር። አንድ የኳስ ሜዳ የሚያክል ፣ 65 ሜትር ርዝማኔ ያለውና 400,000 ቶን ያህል የሚመዝን ስባሪ ኮከብ ከጨረቃ ምኅዋር 15 እጥፍ ለመሬት ቀረብ በማለት፣

የግራዚያኒ መታሰቢያና ተቃዉሞዉ

Wednesday, February 20th, 2013
በሃያ-አምስት ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ተቃዉሟቸዉን በያሉበት አሰምተዋል።በየከተሞቹ የተሰበሰቡት ወይም አደባባይ የወጡት ኢትዮጵዉያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የኢጣሊያ መንግሥትና የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ-ክርስቲያን ለፋሽስቱ የጦር መሪ መታሰቢያ መቆሙን እንዲቃወሙ አቤት ብለዋልም።

የካናዳ ኩባንያና የኦብነግ ማስጠንቀቂያ

Wednesday, February 20th, 2013
የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር፣ ኦብነግ፣ አንድ የካናዳ የነዳጅ ዘይት አውጪ ኩባንያ በኦጋዴን እንዳይሰማራ አስጠነቀቀ። ኦብነግ ባለፈው ሰኞ ባስተላለፈው መግለጫው ኩባንያው በስፍራው ሰላም እስኪሰፍን ድረስ ሥራውን መጀመር የለበትም ብሏል።

የማኅበራዊ ፍትኅ መታሰቢያ ዕለት፤

Wednesday, February 20th, 2013
ዓለም አቀፉ የማኅበራዊ ፍትኅ ቀን በዛሬው ዕለት ታስቦ ውሏል። ይህን ዕለት መንስዔ በማድረግ ጀርመናዊው የማኅበራዊ ኑሮ ባለሙያ ዳንኤል ሽራድ-ቲሽለር ፤ በኢንዱስትሪ የበለጸጉት አገሮች፤ አዳጊ አገሮችን በማቆርቆዝ ፣ የራሳቸውን ኑሮ የተደላደለ ሊያደርጉ

ቡድን-ሃያና የፊናንሱ ችግር

Wednesday, February 20th, 2013
ሞስኮ ላይ በአጠቃላይ ከባንኮች ቁጥጥር እሰከ ግብር፤ ከግብር እስከ ምንዛሪ ይዞታ ብዙ ነገር ተነስቷል። የኮሎኝ ዓለምአቀፍ የምጣኔ-ሃብት ምርምር ኢንስቲቲዩት ባልደረባ ዩርገን ማተስ እንደሚሉት።

20 02 2013 ዜና 16:00 UTC

Wednesday, February 20th, 2013
የዓለም ዜና

የህወኃት ጉዞ የርስ በርስ የመበላላት ታሪክ ነው – ከትእዝብት አድማሱ

Wednesday, February 20th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የህወኃት ጉዞ የርስ በርስ የመበላላት ታሪክ ነው ከትእዝብት አድማሱ

Wednesday, February 20th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የኦርቶዶክስ ቤት ክርስቲያንን አንድ ሊያደርግ የሚችል የመፍትሄ ሃሳብ ! ግርማ ካሳ

Wednesday, February 20th, 2013

«በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ! »

የአቡነ ጳዉሎስን ሕልፈት ተከትሎ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዉስጥ የተፈጠረዉን መከፋፈል ለማስቀረት፣ በመንፈሳዊ አባቶች መካከል፣ የሰላምና የእርቅ ዉይይቶች ተደርገዋል። ለሃያ አመታት የዘለቀዉ፣ ይህ በቤተ ክርስቲያን ላይ የወረደው የመከፋፈል እርግማን ተወግዶ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷ አንድ ሆና፣ «ሂዱና አሕዛብን እያስተማራችሁ፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅድስ ስም እያጠመቃችሁ፣ ደቀ መዛሙርት አድርጓቸዉ» የሚለዉና በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተሰጠዉ፣ ታላቅ ተልእኮን መፈጸም ትችል ዘንድ፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ በየአብያተ ከርስቲያናቱ፣ በየጸሎት ቤቱ ፣ በየገዳማቱ ሲጾምና ሲጸል ነበር።

ነገር ግን ከተጠበቀዉና ከተገመተዉ ዉጭ አስደንጋጭና አሳዛኝ መግለጫዎችን አነበብን። የክርስቶስ መድሃኔአለም ስም ተሰደበ። የዲያብሎስ ስም ገነነ። የትህትሃ የፍቅር እራስን የማዋረድ ክርስቲያናዊ መንፈስ ጠፋ። የእልህ የስደብ የመወጋገዛና የትእቢት መንፈስ ሰፈነ።
በአገር ደረጃ ካያን ፣ የከተማ፣ የክልል ፣ የፌደራል መንግስት ሕጎች ይኖራሉ። ነገር ግን ከህጎች ሁሉ በላይ የሆነ ሕገ-መንግስት የሚባል ሕግ አለ። ፈረንጆች “The Supreme Law of the Land” ይሉታል።

ቤተ ክርስቲያንም የምትተዳደርበት ሕገ ደንብ ወይንም ቀኖና አላት። ካህናት ፣ ገዳማት፣ የሰንበት አስተማሪዎች ወዘተረፈ የሚታዳደሩበት ስርዓት/ሕግ/ቀኖና አለ። እነዚህ የቤተ ክርስቲያን ሕጎችና ቀኖናዎች የቤተ ክርስቲያኒቱ ዋና መመሪያ የሆነዉን፣ የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል የሚያግዙ እንጂ፣ የሚተኩ አይደለም። ወንጌል ከሁሉም በላይ ነዉ። ለዚህም ነዉ በቅዳሴ ወቅት ወንጌልን ቄሱ በሚያነቡበት ወቅት፣ ምእመኑ በአክብሮትና በፍርሃት ቆሞ የሚያዳምጠው።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶችን እያጨቃጨቀ ያለ አንድ ጉዳይ ቢኖር፣ በቤተ ክርስቲያኒቷ የቀኖና መጽሃፍ የተጠቀሱ፣ ፓትሪያርክ እንዴት እንደሚሾምና እንደሚተካካ የሚገልጹ አንዳንድ አንቀጾች ናቸዉ። በዶክትሪን ወይንም በሃይማኖት ጉዳዮች አልተለያዩም። በአስተምህሮ አልተለያዩም። ልዩነታቸው፣ ቅንነትና ትህትና የተሞላ ልብ ካለ፣ በቀላሉ ሊፈታ የሚችል፣ የአሰራርና ማን መሪ መሆን አለበት የሚለዉ ላይ ነዉ።

አራተኛዉ የቤተ ክርስቲያኒቷ ፓትሪያርክ በሕይወት እያሉ አምስተኛ ፓትሪያርክ ይሾማሉ። «አምስተኛዉ ፓትሪያርክ የተሾሙት አራተኛዉ ፓትሪያርክ በፍቃዳቸው ሃላፊነታቸዉን ስለለቀቁ ነዉ» ያላሉ አንዳንዶች። ሌሎች ደግሞ «አይደለም ፤ በአቶ ታምራት ላይኔ ተገደው ነዉ» ሲሉ በፓትሪያርኩ ላይ ተደረገ የሚሉትን ግፍ በምሬት ይገልጻሉ። ይሄ እንግዲህ ከሃያ አመት በፊት የሆነ ነገር ነዉ። ጠባሳዉ ግን ለሃያ አመታት ይኸዉ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ጉዳት አደረሰ። ቤተ ክርስቲያኒቷ ተከፈለች። ለሃያ አመታት ጠብ ነገሰ። ተፋቅረን ተያይዘን በአንድ ላይ ወንጌልን ማስፋፋት የሚገባን ክርስቲያኖችን፣ ከፋፍሎና አጣልቶ ሆድና ጀርባ አደረገን።

እንግዲህ አስቡት፣ የመጽሃፍት ሁሉ የበላይ፣ የሕጎች ሁሉ የበላይ የሆነዉ ፣ ወንጌልን ያካተተዉ መጽሃፍ ቅዱስ ነዉ። መጽሃፍ ቅዱስ የሚያዘው ፍቅርን፣ ይቅር መባባልን፣ አንድነትን፣ ትህትና የመሳሰሉትን ነዉ። የቀኖናዎች ሁሉ የበላይ ከሆነዉ፣ ከማያልፈዉና ከማያረጀዉ ሕያዉ የእግዚአብሄር ቃል ዉስጥ ፣ «እርስ በርሳችሁ ብትዋደዱ የኔ ደቀ መዛሙርት መሆናችሁን ሌሎች ያዉቃሉ»፣ « እራስህን ከሌላ የተሻለ አድርገህ አትቁጠር» ፣ «አንተ የሌላዉን ጉዳፍ ለማወጣት የምትቸኩል በአይን ያለዉ ያለዉን ትልቅ ምሰሶ መጀመሪያ ተመልከት» ፣ ‹‹በመጀመሪያ መባህን በመሰዊያው ላይ ትተህ አስቀድመህ ከወንድምህ ጋር ታረቅ››፣ «ማንም ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ፣ ወፍጮ ባንገቱ ታስሮ ባህር ዉስጥ ቢወረወር ይቀለዋል»፣ «ሌላዉን የሚያሰናክል ከሆነ ስጋ ባልበላ ለዘላለም ልቀር»፣ «እኔ መምህር ና ጌታ ሆኜ ይሄን ካደረኩ ( የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ) እናንተም እንዲሁ አደርጉ» የመሳሰሉትን ትእዛዛት እናነባለን።
የቤተ ክርስቲያን አባቶች በአንድ በኩል ለክርስቲያናዊ ሕግና ቀኖ ቆመናል እያልን፣ በሌላ በኩል ከቤተ ከርስቲያን ሕግና ቀኖና በላይ የሆነዉን የጌታ ክርስቶስን ትእዛዝ ወደ ጎን እያደረገን፣ ያለ ይመስለኛል። ቀኖና፣ ወንጌልንም መደገፍ እንጂ ከወንጌል በተቃራኒ መቆም እንደሌለበት የዘነጋን ይመስለኛል። ዋናዉን ረስተን ትንሹ ነገር ላይ ስናከር ነው የሚታየዉ።

እንግዲህ «ንስሐ እንግባ ። ክርስትናችንን ፣ የክርስቶስ ተከታይና አገልጋይነታችንን፣ በምንለብሰው ካባ ሳይሆን በስራችን አናሳይ» እላለሁኝ። ከወንድሞቻችን ጋር መስማማት አቅቶን፣ ይቅር መባባል ከብዶን፣ «እኔ ነኝ ፓትሪያርክ መሆን ያለብኝ …እርሱ ነዉ መሆን ያለበት ..» እየታባባልን፣ በእልህ መንፈስ ተሞልተን፣ በአኮቴተ ቁርባን ወቅት ስጋ ወደሙን በእጃቸችን ለመያዝ መቆማችን መቅሰፍት ነዉ» እላለሁ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ናት። እንደ እዉነቱ ከሆነ ፣ ከኛ በኋላ ክርስትናን በተቀበሉ አገሮች የሚኖሩ ዜጎች፣ እምነት የሌላቸውን ክርስቲያን እያደረጉ ባለበት ወቅት፣ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን፣ በምስራቅ አፍሪካ ወንጌልን ለማሰራጨት የበለጠ መነሳት አይገባትም ነበርን ? በሚሊዮን የሚቆጠሩ እራሳቸውን ኦርቶዶክ ክርስቲያን ነን የሚሉ፣ ነገር ግን የስላሴንና የስጋዌን ሚስጥራትን እንኳን በደንብ የማያዉቁ አሉ። ብዙ የኦርቶዶስክ ልጆች በሃሺሽ፣ በጫት፣ በተለያዩ ከምእራባዉያን አገራት በመጡ ጸረ-እምነት ተግባራት የተጠመዱ ፣ በስም እንጂ ከክርስትና ጋር በተግባር የማይተዋወቁ ናቸው። አብያተ ከርስቲያናትን ከሚያዘወትሩት ይልቅ፣ የዳንኪራ፣ የጫትና የካቲካላ ቤቶችን የሚያዘወትሩ በጣም ይበዛሉ።
ታዲያ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን፣ በሯን ለመንፈስ ቅዱስ ከፍታ፣ እራሷን ከመንፈሳዊ ባርነት አውጥታ፣ የማያምኑ አሕዛብን እንዲያምኑ ማድረጉን ለጊዜው እንተወዉና፣ ኦርቶዶክስ ነን የሚሉትን እንኳ በቃለ እግዚአብሄርና በእምነት ማጠንከርና ማሳደግ አልነበረባትምን ? የኦርቶዶክስ አማኞች ፣ ወንጌልን አልፎ አልፎ ቅዳሴ ሲመጡ በሚሰሙት ብቻ ሳይወሰኑ፣ ሌት ተቀን የሚያነቡትና የሕይወታቸው መመሪያ የሚያደርጉት፣ ሳይፈሩም በአደባባይ የሚያወጁት መሆንስ አይገባምን ?
ነገር ግን መንፈሳዊ አባቶች፣ እረኝነታችንን ረስተን፣ መንጋዉን ለተኩላ ለመስጠት እየተዘጋጀን ያለ ይመስለኛል። ጥል ባለበት እግዚአብሄር የለም። «የትእቢተኞችን ቀስት ይሰብራል፣ ለትሁታን ግን ጸጋን ይሰጣል» እንዳለችዉ እናታችን ቅድስት ማርያም፣ እግዚአብሄር ትእቢትን ይጸየፋል። ትእቢት ባለበት ቦታ እግዚአብሄር የለም። በመሆኑም የኦርቶዶስክ አባቶች እርቅ መመስረት ካልቻልን፣ ከእግዚአብሄር ክብር ይልቅ የኛን ክብር ካስቀደምን፣ በግልጽ በስራችን የምንናገረዉ፣ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር እንደሌለ ነዉ። እግዚአብሄር የሌለበት ቦታ ደግሞ እንዲሁ መቆዘም እንጂ በረከት የለም።

እስቲ ትንሽ ጠለቅ ልበልና፤ ሁለቱ የኦርቶዶክስ ሲኖዶሶች፣ ሊስማሙበት ካልቻሉበት ነጥቦች መካከል በዋናነት የሚጠቀሰውን ለማየት እንሞክር።
ዉጭ አገር የሚገኘዉ ሲኖዶስ አራተኛው ፓትሪያርክ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰው፣ የፓትሪያክነት ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ይፈልጋል። አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ ደግሞ «ለሃያ አመት የተሰራዉን ሥራ መቀልበስ ነዉ። አምስት ተብሎ ወደ አራት መሄድ አይቻልም» በሚል አራተኛዉ ፓትሪያርክ ተመልሰው አራተኛ ወይንም ስድስተኛ ሆኖ መቀጠላቸዉን ሊደግፉ አልቻሉም። ‹‹አራተኛው ፓትርያርክ ወደ አገራቸው ተመልሰው ደረጃቸውና ክብራቸው ተጠብቆ፣ የሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተሟልቶላቸው በመረጡት ቦታ በፀሎት ተወስነው እንዲኖሩ፣ ነገሮቹም ሆነ በእሳቸው አንብሮተ ዕድ የተሾሙ ቀኖናውን በቀኖና አሻሽሎ ሐዋርያዊ ሥልጣናቸውን ሰጥቶ፣ ስማቸውን መልሶ በሀገረ ስብከት መድቦ ለማሠራት፣ ፈቃደኛ ነዉ» ሲል በአዲስ አበባ ያለዉ ቅዱስ ሲኖዶስ የመጨረሻ አቋሙን ያሳዉቃል። አሜሪካ ያለዉ ሲኖዶስ መልስ በመስጠት «አቡነ መርቆሪዮስ ፓትሪያርክነታቸውን መቀጠል አለባቸው። የቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖና መጠበቅ አለበት» በሚል አቋሙን በድጋሚ የሚያጸና መግለጫ ያወጣል።

ከሁለቱም ወገኖች ላሉ አባቶች እንግዲህ የምለው ይሄን ነዉ። እግዚአብሄርን እንጂ ሰዉን አንፍራ። አላስፈላጊ መግለጫዎችን ከመስጠት እንቆጠብ። አለመስማማት፣ ለጊዜዉ መጋጨት ያለ ነዉ። ሐዋርያዉ ጳዉሎስና በርናባስም አንድ ወቅት ተጋጭተዉ ነበር። እግዚአብሄር ለቁጣ የዘገየ በምህረቱ ግን ባለጠጋ የሆነ አምላክ ነዉ። «የልጁ የየሱስ ክርስቶስ ደም ከሐጢያት ሁሉ ያነጻል« ተብሎ እንደተጻፈ፣ ለሰራናቸው ሐጢያቶች እና ስህተቶች እግዚአብሄር ይቅር ይለናል። የትላንትናዉን ትተን፣ ዛሬ መልካምን ነገር ለማድረግ እንዘጋጅ። ዛሬ እራሳችንን ለፍቃዱ እናስገዛ። ጆሮዎቻችን የጥላቻን እና የእልህ ወሬዎችን ከመስማት የተደፈኑ ይሁኑ። ሁላችንንም ሊያስማማ የሚችል መፍትሄ ማግኘት ይቻል ዘንድ እንመካከር፣ በጋራም አብረን እንጸልይ።
አዲስ አበባ ያለው ሲኖዶስ፣ ፓትሪያርክ የሚሆኑ እጩዎችን ተቀበሎ ስድስተኛዉን ፓትሪያርክ ለማስመረጥ ስራዎችን እየሰራ እንዳለ እያነበብን ነዉ። በቅርቡም አዲሱ ፓትሪያርክ ማን እንደሚሆኑ እንሰማለን። ይሄ ደግሞ ለሃያ አመታት የነበረዉ የቤተ ክርስቲያን መከፋፋልና እርግማን እንዲቀጥል ሊያደርገው አይገባም። የእርቁን ሂደት ይረዳ ዘንድ፣ የኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያንን አንድ የሚያደርግ፣ አንዳንድ ሃሳቦችን በትህትና ለማቅረብ እሞክራለሁ። እነዚህን ሃሳቦች ሳቀርብ ፣ አገር ቤት ያሉም ሆነ በአሜሪካ የሚገኙ አባቶች፣ ትንሽ ሊቆረቁራቸው ቢችልም ትኩረት ሰጠዉ ሃሳቤን ያስተናግዱታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

1.አዲስ አበባ ያሉም ሆነ በዉጭ የሚገኙ አባቶች፣ መግለጫዎችን ከማዉጣት መቆጠብ ይኖርባቸዋል። መግለጫ ማዉጣት ማንነትን አይሳይም። መግለጫ ማዉጣት ክርስትናን አያሳይም። «በፍሪያችሁ ያውቋቹሃል» ተብሎ እንደተጻፈ ክርስትናችንን፣ የክርስቶስ አገልጋይነታችንን፣ የቤተ ክርስቲያን መሪነታችንን በስራችን ነዉ ማሳየት የሚኖርብን። በስራችን ክርስትና ማለት ምን ማለት እንደሆነ፣ አርዓያ በመሆን፣ ለምንመራው ምእመን ማስተማር አለብን።

2.በአዲስ አበባ የሚገኘው ሲኖድስ፣ ስድስተኛዉን ፓትሪያርክ በቅርቡ ያሳዉቀናል። አዲሱ ፓትሪያርክ በዉጭ አገር ካለዉ ሲኖድ ጋር በመነጋገር፣ አንድነት የሚፈጠርበትን፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የወረደው እርግምን የሚገፈፍበትን ሁኔታ በቀዳሚነት ማመቻቻት ቀዳሚ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል። «ከሁሉም በላይ መሆን የሚፈልግ የሁሉም አገልጋይ ይሁን» እንዳለ ጌታችን ኢየሱስ ፣ ፓትሪያክነታቸዉ የከፍታ ቦታን ለማግኘት ሳይሆን፣ ለማገልገል፣ የተበተኑትን ለማሰባሰብ፣ የተሰበረዉን ለመጠገን መሆን አለበት።

3.አቡነ መርቆርዮስ በእድሜ ባለጠጋ የሆኑ አባት ናቸዉ። በርሳቸው ምክንያት ክፍፍሉ መቀጠል የለበትም። ለሰላም ሲሉ ፣ ለቤተ ክርስቲያኒቷ አንድነት ሲሉ፣ ለእግዚአብሄር ክብር ሲሉ፣ እግር ማጠብ ይኖርባቸዋል። እርግጥ ነዉ በቆኖናዉ መሰረት ፓትሪያርክ ሳይሞት ፓትሪያርክ አይሾምም። ከዚህ በፊት ስህተቶች ተሰርተዉ ሊሆን ይችላል። ከዚህ በፊት በደል ተፈጽሞባቸዉ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን አሁን ከዚያ አልፈዉ መሄድ ያለባቸው ይመስለኛል። ይቅር ማለት መቻል ያለባቸው ይመስለኛል። ከሃላፊነታቸው በፍቃዳቸው ቢለቁና አዲስ ለተመረጡ ፓትሪያርክ እዉቅና ቢሰጡ፣ የዲያቢሎስን ሥራ ነበር የሚያፈርሱት። በመሸነፍም ያሸንፉ ነበር።

እዚህ ላይ በቅርቡ የካቶሊኩ ፖፕ ያደረጉትን መመልከት ሊጠቅም ይችላል። «ቤተ ክርስቲያኔን ለመምራት የአካል ጥንካሬ የለኝም። የኔ ፖፕ ሆኖ መቀጠል ጥሩ አይደለም። በኔ ምትክ ሌላ ሊሰራ የሚችል ፖፕ መመረጥ አለበት» ብለው፣ ለቤተ ክርስቲያን ጥቅም ሲሉ፣ ፖፕ ቤኔዲክት ከሃላፊነታቸው ሊነሱ ነዉ። አቡነ መርቆሪዮስም እንደ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያንን ጥቅም አስቀድመዉ፣ ቤተ ክርስቲያኒቷን አንድ ለማድረግ፣ የቤተ ክርስቲያኒቷን ቀኖና በጠበቀ መልኩ፣ ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

እንግዲህ እንደ ክርስቲያኖች ትልቅ መንፈሳዊ ዉጊያ ከፊታችን ይጠብቀናል። ጸረ-ወንጌል የሆነው ዲያብሎስ፣ በታሪክ ትልቅ ስራን የሰራች ቤተ ክርስቲያንን ለማዳከም እየጣረ ነዉ። በመሆኑም ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ ከመቼውም በበለጠ አጥብቆ መጸለይና መጾም ይኖርበታል። በወጡት፣ ጠቃሚ ያልሆኑ መግለጫዎች ተስፋ መቁረጥ የለብን። ክርስቲያን ተስፋ አይቆርጠም። ከንግስት አስቴር መማር አለብን። አማሌቃዊዉ ሃማ እሥራዔላዉያንን ለመጨረስ አዋጅ አሳወጀ። እነ አስቴር ጾም ጸሎት አወጁ። በእግዚአብሄር ፊት አነቡ። አዋጅን የሚሽር ሌላ አዋጅ ታወጀ። ሃማ መርዶኪዮስን ለመስቀል ባዘጋጀው እንጨት ላይ ተሰቀለ። ሃሌሉያ።

እንደዚሁም እኛ በእምነት፣ በጾምና በጸሎት እግዚአብሄር ፊት ከቀረብን፣ ተአምራት ማየት እንችላለን። ቤተ ከርስቲያንን ከመፈራረስ ልናድናት እንችላለን። አንድነቷን ማስጠበቅ እንችላለን። ከርግማን ወጥታ ፈረንጆች ከሚያደርጉት በላይ ለወንጌል መስፋፋት የተሰለፈች ልናደርጋት እንችላለን።

እዚህ ላይ አንድ ትልቅ ቁም ነገር አንርሳ። በቤተ ክርስቲያኒቷ ያሉትን ችግሮች በማባባስ፣ የፖለቲክ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩ፣ ዲያብሎስ እራሱ እየተጠቀመባቸው ያሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ይኖራሉ። በፖለቲካ እንቅስቃሴ ዉስጥ ገብቶ መሳተፍ የራሱ ቦታና ጥቅም ቢኖረዉም፣ በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ግን፣ የእግዚአብሄር ሥራ የሚሰራው በፖለቲካ መድረክ አይደለም። የእግዚአብሄር ሥራ የሚሰራዉ እንደ ወገዛ፣ ስድብ፣ መግለጫ ማዉጣት በመሳሰሉ የፖለቲካ መሳሪያዎችን በመጠቀም አይደለም። የእግዚአብሄር ሥራ የሚሰራዉ በመንፈሱ ነዉ። በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ችግር የሚፈጥሩ ካህንም ሆነ ጳጳስ ካሉ፣ የሚበቀላቸው እራሱ እግዚአብሄር ነዉ። «ፍርድ የኔ ነዉ!» ይላልና የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር።
በመሆኑም የምናቀራርብ፣ የምናስታርቅ፣ ልዩነቶችን የምናጠብ፣ መግባባት ንግግርና መቀባበል እንዲኖር የምናበረታታ ፣ የተሳሳተን በጨዋነት የምንገስጽ፣ የወደቀን የምናነሳ፣ የሚያጠፋን ከጥፋታቸውዉ የምንመልስ እንሁን እንጂ፣ በእሳት ላይ ነዳጅ አናርከፍከፍ።
እግዚአብሄር ልቦናችንን ለፍቅሩ አይምሯችንን ለጥበቡ ይክፈትልን !

ሎውሮ ባግቦ በዓ/አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍ/ቤት

Wednesday, February 20th, 2013
የቀድሞው የኮት ዲቫር ፕሬዚዳንት የሎሮ ባግቦ ክስ ከነገ ጀምሮ እስከ የካቲት ሀያ ስምንት ድረስ ዴን ሀግ በሚገኘው አለም አቀፉ የጦር ወንጀል ተመልካች ፍርድ ቤት መደመጥ ይጀምራል። ባግቦ እኢአ ከ 2000-2010 ዓ ም የቀድሞው የኮት ዲቫር መሪ በነበሩበት ወቅት

አስታራቂ ጉባኤው መግለጫ አወጣ

Tuesday, February 19th, 2013
(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 13/2005 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 20/2013/ PDF)፦ በአባቶች መካከል የተፈጠረውን መለያየት ላማራቅና ዕርቅ ለማውረድ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ የቆየው የሰላምና አንድነት ጉባኤ ጉዳዩን አስመልክቶ መግለጫ አወጣ። የመግለጫው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገር ቤትና በውጭው ዓለም የሚገኙ አባቶችን በማስማማት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ያደረገውን ከፍተኛ ጥረት በዝርዝር ለመግለጽና የዕርቁ ሒደት ምን ይመስል እንደነበር በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ለሚኖሩ መላው ኦርቶዶክሳውያን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምርን እንዲያውቁት ለመግለጽ ነው” ያለው መግለጫ ዝርዝር ሐሳቦችን አካቷል። ሙሉ ቃሉን ከዚህ በታች ተመልከቱ።


በወቅታዊው የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የተሰጠ መግለጫ።
የካቲት12/2005ዓ.ም
Feb 19/2013

የመግለጫው ምክንያት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ላለፉት ሦስት ዓመታት በአገር ቤትና በውጭው ዓለም የሚገኙ አባቶችን በማስማማት ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ ያደረገውን ከፍተኛ ጥረት በዝርዝር ለመግለጽና የዕርቁ ሒደት ምን ይመስል እንደነበር በኢትዮጵያም ሆነ በመላው ዓለም ለሚኖሩ መላው ኦርቶዶክሳውያን ካህናት፣ ምእመናንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምርን እንዲያውቁት ለመግለጽ ነው።

እንደሚታወቀው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የማስታረቅ ሥራውን የጀመረው በኢትዮጵያ በኩል በብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ፤ በውጭም በኩል በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ መልካም ፈቃድ በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ፊርማ በተጻፈ ደብዳቤ ነው። የሰላምና አንድነት ጉባኤው በርካታ ምእመናንና አብያተ ክርስቲያናት የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉለት ሦስት ጉባኤያትን በማዘጋጀት አባቶች ችግሮቻቸውን በጋራ ተነጋግረው በውይይት እንዲፈቱ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። በእያንዳንዱ ጉባኤ ላይም አለመግባባት በተፈጠረባቸው ሐሳቦች ላይ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ለዕርቀ ሰላሙ ሥምረት ይበጃል ያለውን የመፍትሔ ሐሳብ እያቀረበ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት አቅም የፈቀደውን ያህል የበኩሉን አስተዋጽዖ አድርጓል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ እስካሁን ያካሔዳቸውን ሦስቱን የዕርቀ ሰላም ውይይቶች አጠቃላይ ገጽታና ሒደት ከዚህ እንደሚከተለው በዝርዝር እናቀርባለን።

የመጀመሪያውጉባኤ
ይህ የመጀመሪያ ጉባኤ የተካሔደው ከሐምሌ 26-28, 2002 .ም በሰሜን አሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ማክሊን ሆቴል ሲሆን ከኢትዮጵያና ከውጭው ዓለም የተወከሉ አባቶች እንዲገናኙ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ ይታወሳል። ይሁን እንጂ ለዚህ ጉባኤ አለመሰካት ትልቁ ምክንያት ከኢትዮጵያ በኩል ልዑካን ከመሰየማቸው አስቀድሞ በውጭ ካሉት አባቶች ለሰላምና አንድነት ጉባኤው የቀረበ ጥያቄ ነበር። ይኸውም በኢትዮጵያ በኩል በልዑክነት ከተመደቡት ከአንዱ ጋር ከባድ ቅሬታ ስላለን አብረን ቤተ ክርስቲያንን አንድ ለማድረግ የሚያስችል ልባዊ ንግግር ለማድረግ ስለምንቸገር በሌላ ሰው እንዲለወጡ ይደረግልን የሚል ነበር። ይሁን እንጂ ጉባኤው ወደ አዲስ አበባ ደውሎ ለመጠየቅ ከልዑካኑ መሪ ጋር በተነጋገረበት ጊዜ «እኛ የምንመጣው ትልቁን ችግር ልንፈታ ስለሆነ ችግር የለም፤ ስንመጣ እዚያው እንፈታዋለን» የሚል ምላሽ ተሰጠን። ከኢትዮጵያም ሆነ ከውጪው ዓለም የተወከሉት አባቶች ስብሰባው ቦታ እንደተገኙ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ከስብሰባ በፊት ልዑኩን በውጪ ካሉት አባቶች ጋር ያለባቸውን ችግር በመፍታት ወደ ዋናው ድርድር ለመግባት ጥረት ሲያደርግ ከአዲስ አበባ የመጡት ልዑካን ጸሐፊ «ከመመሪያ ውጭ ያደርገናል፤ አይሆንም አሉ።» በወቅቱ ለሰጡት መልስ ያቀረቡት ምክንያት “በጋራ እንድንነጋገር እንጂ በግል ይቅርታ ልንጠያየቅ አልመጣንም” የሚል ነበር። የሰላምና አንድነት ጉባኤው ቀደም ሲል በውጭ ያሉት አባቶች ባቀረቡለት ጥያቄና ጉባኤውም በገባው ቃል መሠረት ልዑኩ ይቅርታ እንዲጠይቁ ያደረገው ጥረት ባለመሳካቱ ምክንያት ጉባኤው ሁለቱንም ወገኖች በእንባ ጭምር ቢለምንም የሚሰማ ባለመገኘቱ የመጨረሻ እንደ መፍትሔ አድርጎ ያቀረበው ከኢትዮጵያም ከውጭውም ዓለም የመጡት አባቶች ሊቃውንቱ ቀርተው የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሆኑት በሊቃነ ጳጳሳት ደረጃ ብቻ ተነጋገሩ የሚል ሲሆን ይህም ተቀባይነት አላገኘም። ይሁን እንጂ ልዑካኑ ፊት ለፊት ተገናኝተው ባይነጋገሩም ሁለቱም አባቶች በሰላምና አንድነት ጉባኤው አማካኝነት በተዘወዋሪ መልኩ እንዲደራደሩ ተደርጓል። በዚህም ለወደፊቱ ግንኙነት እንቅፋት የሚሆኑ ቅድመ ሁኔታዎች ተስተካክለው የሰላሙ ጉባኤ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ተስማምተው ነበር።

ሁለተኛውጉባኤ
ሁለተኛው ጉባኤ ከየካቲት 2-11 ቀን 2004 .ም በአሜሪካ ፊኒክስ፤ አሪዞና ከተማ የተካሔደ ሲሆን ከ20 የልዩነት ዓመታት በኋላ አባቶች ለመጀመሪያ ጊዜ ፊት ለፊት ተገናኝተው ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ተነጋግረው በአንድነት የጋራ መግለጫ ማውጣታቸው ይታወሳል። በዚህ ጉባኤ ላይ በዋነኛነት ቀርበው የነበሩት የመነጋገሪያ አጀንዳዎች፦

1ኛ/ ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በሚመለከት፤
2ኛ/ አራተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን በተመለከተ ነበር።

በውይይቱ ወቅት በሰሜን አሜሪካ ያሉት አባቶች ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው የወረዱት ተገድደው ነው፤ አቡነ ጳውሎስም አራተኛው ፓትርያሪክ በሕይወት እያሉ በመሾማቸው ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ፈርሷል። ስለዚህ የፈረሰውን ቀኖና ለማረምና ለማደስ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው የሚል ነበር። ከኢትዮጵያ የመጡት ልዑካን ደግሞ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ሥልጣናቸውን ራሳቸው ለቅዱስ ሲኖዶስ አልችልም፥ አሞኛል” ብለው ስላስረከቡ ጉዳዩ በምልዓተ ጉባኤ ተወስኖ እርሳቸው ከሥልጣናቸው ከወረዱ በኋላ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በሚፈቅደው መሠረት አምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ የተሾሙ ስለሆነ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን አልፈረሰም። ይልቁንም በቤተ ክርስቲያን ታሪክ የሌለ ስደተኛ ሲኖዶስ አቋቋምን በማለት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ያፈረሳችሁ እናንተ ናችሁ ብለዋል። አያይዘውም “አራተኛው ፓትርያርክ ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ ቀደም በወሰነው መሠረት ቅዱስነታቸው በፈቀዱት ቦታ የሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተሟልቶላቸው ይኑሩ፤ ለሾሟቸው ጳጳሳትም ሀገረ ስብከት ይሰጣቸዋል” ብለዋል።

የሰላምና አንድነት ጉባኤው የሁለቱንም አካላት ሐሳብ በሚገባ ካዳመጠ በኋላ አባቶች ይበልጥ በሚያቀራርባቸውና ወደ አንድነት በሚያመጣቸው ሐሳብ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ብርቱ ጥረት አድርጓል። በዚህ መሠረት ለሃያ ዓመታት የቆየውን ችግር በቀላሉ መፍታት ባይቻልም ውይይቱ በመደማመጥና በመከባበር ሊቀጥል ችሏል። ስለሆነም የአሪዞናው ዕርቀ ሰላም ጉባኤ ጽኑ የሰላም መሠረት የተጣለበት ጉባኤ ነውብለው የጋራ መግለጫ ያወጡበትና ቀጣይ ስብሰባ እንዲዘጋጅ ተስማምተው የወሰኑበት ጉባኤ ሆኖ ተጠናቅቋል። የሰላምና አንድነት ጉባኤውም ከውይይቱ ያጠናቸውን ነገሮች መነሻ በማድረግ ባለ ሰባት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳብ ለሁለቱም ወገን በጹሑፍ አቀርቧል። ለዚህም ልዑካን ሰይሞም ወደ ሁለቱም ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በመላክ ጉዳዩን በጥንቃቄ እንዲያስረዱ አድርጓል። በአሪዞናው ጉባኤ ላይ በተደረሰው የጋራ ስምምነት መሠረት መሠረት ሦስተኛው የዕርቀ ሰላም ድርድር ጉባኤ ዝግጅት ቀጠለ። ይህ በዚህ እንዳለ ግን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ድንገተኛ ዕረፍት መሰማቱ አሳዛኝና አስደንጋጭ ነበር። ስለሆነም የሰላምና አንድነት ጉባኤው በወቅቱ ልዑካንን ልኮ በቅዱስነታቸው ሥርዓተ ቀብር ተገኝተው የጉባኤውን የኃዘን መግለጫ መልእክት እንዲያሰሙ አድርጓል። በዚህም የዕርቀ ሰላሙ ጥረት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥልና በአፋጣኝ ለፍጻሜ እንዲበቃም ለቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄውን አቅርቧል።

ሦስተኛው ጉባኤ
በመሠረቱ የሰላምና አንድነት ጉባኤው አንዱን ችግር አሳለፍኩ አሁንስ ሰላም ይገኛል ብሎ ተስፋ ሲያደርግ ሌላ ያልታሰበ ችግር ከፊቱ ይደቀንበታል። ይሁን እንጂ በየጊዜው የሚከሰተውን ችግር ፈትቶ ሂደቱን መልክ ለማስያዝ የሚጠይቀው ጊዜና ድካም ቀላል አልነበረም። በዚህም ሁኔታ ሦስተኛውን ዙር ጉባኤ ከኅዳር 26-30 ቀን 2005 .(Dec. 5-9, 2012) በዳላስ፤ ቴክሳስ ለማካሔድ ተቻለ። ይህ ጉባኤ ከዚህ ቀደም ካሳለፍናቸው ሁለት ጉባኤያት እጅግ በተለየ መልኩ የመቀራረብና የመከባበር መንፈስ የታየበት ልዑካኑ ገና እንደተገናኙ የፍቅር ሰላምታ የተለዋወጡበት ነበር። በጉባኤው ዋዜማ በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል ደማቅ አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ በአንድ ቤተ መቅደስ ውስጥ ተገኝተው ጸሎተ ኪዳን በጋራ አድርሰዋል። ከሕዝቡ የተደረገላቸውን የአቀባበል ሥነ ሥርዓት በእጅጉ አድንቀውና አመስግነው በደስታ ተቀብለውታል። ጉባኤው ሲጀመርም የጉባኤውን መክፈቻ ጸሎት እርስዎ ይጀምሩ” “የለም እርስዎ ይጀምሩ” እየተባባሉ በፍቅር በመገባበዝ ጀምረውታል።

በውይይቱም ወቅት ሁለቱም ወገኖች ከላካቸው አካል ይዘውት የመጡትን መሠረተ ሐሳብ በሰፊው ተነጋግረውበታል። ይኸውም የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ አገራቸው መመለስ ለዕርቀ ሰላሙ ስኬታማነት ዋነኛ መሠረት መሆኑን በጋራ የተስማሙበት ቢሆንም በሁለቱም ወገን ቅዱስነታቸው እንዴትና በምን ሁኔታ ይመለሱ በሚለው ዐቢይ ጉዳይ ላይ የአቋም ልዩነት ታይቷል። ስለሆነም በኢትዮጵያ ልዑካን በኩል የቀረበው ዋና ሐሳብ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ ቅድስት አገራቸው ገብተው፣ ክብራቸው ተጠብቆና የሚያስፈልጋቸው ሁሉ ተሟልቶላቸው እርሳቸው በፈለጉት ቦታ ይኑሩየሚል ነው። አያይዘውም ምክያቱን ሲገልጹ “ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ወደ መንበራቸው ቢመለሱ ታሪክ ይፋለስብናል” የሚል ነበር። በአንጻሩ ደግሞ በውጭ አገር ያሉት ልዑካን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ሲባል ቅዱስነታቸው ከነሙሉ ሥልጣናቸው ወደ መንበራቸው መመለስ አለባቸው፤ ፓትርያርክ እያለ ሌላ ፓትርያርክ መሾም ሥርዓት አልበኝነትን ያስከትላልብለዋል። ምክንያቱም «ቅዱስነታቸውን ወደ መንበራቸው እንዳይመለሱ የሚያደርጋቸው ቀኖናዊ በደል ስለሌለባቸውና በአሁኑ ጊዜም መንበሩ ክፍት ስለሆነ ሊመለሱ ይገባል» ብለዋል።

ስለዚህ ልዑካኑ ልዩነት በታየባቸው መሠረታዊ ሐሳቦች ላይ አሁን በራሳችን ለመወሰን ከአቅማችን በላይ በመሆኑ ሰይሞ ወደላከን አካል ተመልሰን ጉዳዩን በስፋት አስረድተን እንደገና የምንገናኝበትና የዕርቀ ሰላሙን ውይይት የመጨረሻ ምዕራፍ የምናደርስበት ቀጣይ አራተኛ ጉባኤ በቅርቡ ያስፈልገናልሲሉ ለሰላምና አንድነት ጉባኤው ሐሳባቸውን አቅርበዋል። ጉባኤው ከልዑካኑ በቀረበለት ጥያቄ መሠረት አራተኛው ጉባኤ ከጥር 16-18 ቀን 2005 .(Jan. 24-26/2013) በሎስ አንጀለስ፤ ካሊፎርኒያ እንዲካሔድ ሐሳብ አቅርቧል። የሰላምና አንድነት ጉባኤው ያቀረበውን ሐሳብ የሁለቱም ወገን ልዑካን በአንድ ድምፅ ተቀብለው ተስማምተውበታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የግራ ቀኙን ፍሬ ሐሳብ በጥሞና አዳምጦና በጉዳዩ ላይም በስፋት ተወያይቶ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ሥምረት ይበጃል ብሎ ያመነበትን ባለ አራት ነጥብ የመፍትሔ ሐሳብ ለልዑካኑ በጽሑፍ አቅርቦ በንባብ አሰምቷል። ለልዑካኑ ያቀረበውን የመፍትሔ ሐሳብም በልዑካኑ ስምምነት መሠረት ለሁለቱም ሲኖዶሶች ምልዓተ ጉባኤ በደብዳቤ ከዚህ እንደሚከተለው አቅርቦ ነበር።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ያቀረበው የመፍትሔ ሐሳብ።
1. ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን አስመልክቶ ከምንም በላይ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ሲባል ቅዱስነታቸው ወደ መንበራቸው ተመልሰው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠንቶ በሚጸድቀው የጋራ መመሪያ መሠረት የቤተ ክርስቲያኒቱን መንፈሳዊ ተግባራት ብቻ እንዲያከናውኑ ቢደረግ፤

2. የቤተ ክርስቲያኒቱን የአስተዳደር ዘርፍ በተመለከተ ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ተጠንቶ በሚወጣው መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ከሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ አባላት መካከል በሚመረጥ እንደራሴ ወይም በጋራ ስምምነት በሚሰየም የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እንዲመራ ቢደረግ፤

3. ከላይ የተገለጸውን የመፍትሔ ሐሳብ ከጠቅላላው የቤተ ክርስቲያናችን ታሪክ አንጻር ለማገናዘብ እንዲቻል የዐራተኛውና የአምስተኛው ዘመነ ፕትርክና እንደ ተጠበቀ ሆኖ በየጊዜው የተከናወኑትን ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ የሆኑ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ተግባራትንም ሙሉ በሙሉ አክብሮ በመቀበል በዕርቀ ሰላሙ አማካይነት የቤተ ክርስቲያናችንን የታሪክ ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚቻል በመሆኑ፤

4. ከዚህም ጋር ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ በኋላ በጋራ የሚሾመውን ቀጣይ ፓትርያርክ ስድስተኛ ፓትርያርክ አድርጎ በመሰየም የታሪክ ሒደቱ እንደተጠበቀ ሆኖ እንዲቀጥል ቢደረግ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ሊሰጥ ይችላል ብሎ ጉባኤው ያምናል።

5. በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን በከባድ ችግር ውስጥ መሆኗንና ዕርቀ ሰላሙ የቅዱስ ሲኖዶስ ተቀዳሚ አጀንዳ መሆን እንደሚገባው ይታመናል። ስለሆነም ለሦስት ዓመታት ሲካሔድ የቆየው የዕርቀ ሰላም ንግግር ለሠመረ ውጤት እንዲበቃና ሃያ አንድ ዓመታትን ያስቆጠረው አሳዛኝ የልዩነት ታሪክ በአንድነት እንዲተካ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዩን በጥልቀት ተመልክቶ ለዕርቀ ሰላሙ የመጨረሻ እልባት መስጠት ወቅቱ የሚጠይቀው ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ኃላፊነት መሆኑን የሰላምና አንድነት ጉባኤው በእጅጉ ያምናል።

በእንጥጥል ላይ እንዳለ ሳይቋጭ የቀረው የአራተኛው ዙር ጉባኤ እንቅፋቶችና የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ዕርቀ ሰላም ሒደት እንዳይሳካ ያደረጉት ዋና ዋና ምክንያቶች፤
1. በኢትዮጵያ ያሉ አንዳንድ አባቶች ከቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት ይልቅ ለሢመተ ፓትርያርክ ቅድሚያ በመስጠታቸውና የላኳቸውን ልዑካን ሪፓርት ሳይሰሙ አስመራጭ ኮሚቴ መሰየማቸው፤

2. የኢ////ክ የሰላምና አንድነት ጉባኤ አባላት በልዑካኑ የስምምነት ውሳኔ መሠረት ወደ አዲስ አበባ ቅዱስ ሲኖዶስ ተሰይመው ከሔዱ በኋላ የተላኩበትን ዐቢይ የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለቅዱስ ሲኖዶስ እንዳያቀርቡ እስካሁን ድረስ እንኳን ማንነታቸው ባልታወቀና ባልተረጋገጠ ግለሰቦች ተላለፈ በተባለ ሕገ ወጥ ትእዛዝ ወደ መንበረ ፓትርያርኩ ቅጽረ ግቢ እንዳይገቡ በጥበቃ ሠራተኞች መከልከላቸው፤

3. ከዚህም በላይ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ አንደኛውን ልዑክ ካለአንዳች ምክንያት በግዳጅ ከሀገር እንዲወጡ መደረጉ፤ ሁለተኛውንም ልዑክ በማጉላላትና ወደ ቤተ ክህነት ግቢ እንዳይገቡ በማገድ፤ በቀጠሮ እንኳን ለሚጠብቃቸው የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ከላይ የዘረዘርናቸውን የመፍትሔ ሐሳቦች የያዘውን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ደብዳቤ አቅርበው እንዳያስረዱና ቅዱስ ሲኖዶስ በጉዳዩ እንዳይመክርበት መደረጉ፤

4. ገና ከጅምሩ ጀምሮ ዕርቀ ሰላሙን የማይፈልጉና በግልጽ ይቃወሙ የነበሩ አንዳንድ አባቶች ፈጽሞ የተዛባና ከእውነት የራቀ መሠረተ ቢስ መረጃ ለመንግሥት ባለሥልጣናትም ሆነ ለኅብረተሰቡ መስጠታቸው፤

5. በሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ፍጹም ሰላምና አንድነት እንዲሰፍን ለማድረግ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሲካሔድ የቆየው የዕርቀ ሰላም ጥረት ከዳር እንዲደርስ በማይፈልጉ ጥቂት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት አማካይነት ቅዱስ ሲኖዶስ እንደ አንድ ልብ መካሪ፣ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆኖ የተጀመረው የዕርቀ ሰላም ውይይት ለውጤት እንዲበቃ ባለማድረጉ ምክንያት መንግሥት በቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ሥልጣን ላይ ግልጽ ተጽእኖና ጫና በማድረጉ፤

6. በመጨረሻም ጥር 8 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ስድስተኛ ፓትርያርክ ለመሾም በችኮላ መወሰኑ የሰላሙን በር ከመዝጋቱም በላይ የዕርቀ ሰላሙን ውጤት በጸሎትና በታላቅ ተስፋ ሲጠባበቅ ለቆየው መላው ሕዝበ ክርስቲያን ታላቅ መርዶ ሆኗል።

በዚህ አጋጣሚ በብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ አባታዊ ቡራኬና በቅዱስነታቸው በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መልካም ፈቃድ እንዲሁም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አባታዊ ቡራኬና በቅዱስነታቸው በሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መልካም ፈቃድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ የዕርቀ ሰላሙን ጥረት እንዲያካሒድ በመደረጉ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ከዚህም ጋር ጉባኤው በጠየቀው መሠረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ መመሪያ ሰጪነት ቅዱስ ሲኖዶስ ለሁለት ጊዜያት የልዑካኑን የአየር ቲኬት በመሸፈን ስላደረገልን ከፍተኛ ትብብር ጉባኤው ከልብ ያመሰግናል። በአጠቃላይ የሰላምና አንድነት ጉባኤው ባለፉት ሦስት ዓመታት ባደረገው የዕርቀ ሰላም ጥረት በጸሎታችሁ፣ በሐሳባችሁ፣ በምክራችሁ፣ በገንዘባችሁና በጉልበታችሁ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ላደረጋችሁልን አብያተ ክርስቲያናት፣ ምእመናን፣ ማኅበራትና ደርጅቶች ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አምላክ ዋጋችሁን አብዝቶ ይክፈላችሁ እንላለን። አሁንም ስለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት የተለመደውን ትብራራችሁንና ድጋፋችሁን እንዳታቋርጡ በአክብሮት እናሳስባለን።

ይልቁንም ከኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ልዑካን ሆነው የመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በልዑካኑ ጸሐፊ አማካኝነት የሚደርስባቸውን ከፍተኛ ጫና ተቋቁመው ለዕርቀ ሰላሙ አጠቃላይ ሒደት ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረት እንዲሁም በውጭ ሀገር ያሉት አባቶች ለዕርቀ ሰላሙ ሒደት ስላደረጉት ቀና ትብብር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ልባዊ ምስጋናውን ያቀርባል። ምንም እንኳን በጥቂት አባቶች አቀነባባሪነት የሰላምና አንድነቱ በር ለጊዜው የተዘጋ ቢመስልም የቤተ ክርስቲያን አምላክ እግዚአብሔር በጥበቡ ከፍቶ የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት እንደሚያሳየን ተስፋ እናደርጋለን። እነሆ በእግዚአብሔርም ሆነ በሰዎች ዘንድ በግልጽ እንደሚታወቀው ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሰላምና አንድነት ስንል እስካሁን ድረስ አቅማችን በፈቀደው ሁሉ የሚቻለንን ያህል ጥረናል። ይሁን እንጂ “ፈደዩኒ እኪተ ህየንተ ሠናይት” እንደተባለው የሰላምና አንድነት ጉባኤው አባላት ፍጹም ሰላማውያን መሆናቸው እየታወቀ ለቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት አብዝቶ መድከም እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ብዙ እንግልት ደርሶባቸዋል።

እንደሚታወቀው የዕርቀ ሰላሙን ሒደት ለማሰናከል የፈለጉ ጥቂት አባቶችና “የቤተ ክርስቲያን” ባለሥልጣናት የሆኑ ግለሰቦች ለመንግሥት አካላት የተዘባ መረጃ በመስጠት የሰላም ልዑካኑ ከሀገር በግዳጅ እንዲወጡና እንዲጉላሉ ተደርጓል። ከዚህም ጋር በሰላም ልዑካኑ ስም ከሰላሙ በቀር አንዳችም አጀንዳ የሌለውን ጉባኤያችንን የማይወክል የሐሰት ወረቀት በመበተን ያለስማቸው ስም ለመስጠት ተሞክሯል። ለዚህ ሁሉ ግን የቤተ ክርስቲያን አምላክ ራሱ በጊዜው እንደሚመልስና እንደሚፈርድ ወደፊትም ታሪክ እንደሚያስታውሰው ስለምናምን ሁሉንም በአኰቴት እንቀበለዋለን። ነገር ግን ትናንትም፣ ዛሬም ነገም እጅግ የሚያሳስበን የቤተ ክርስቲያናችን ጉዳይ ነው። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና መምህራን፣ መዘምራንና ወጣቶች በግልጽ ለማሳወቅና በአጽንዖት ለማሳሰብ የሚፈልገው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሰላምና አንድነት እስኪመጣ ድረስ ከመላው ሕዝበ ክርስቲያን ጋር በመሆን እስከ መጨረሻው ጥረቱን የሚቀጥል መሆኑን በአጽንዖት እንገልጻለን።

እግዚአብሔር አምላክ የቤተ ክርስቲያናችንን የሰላምና አንድነት ዘመን እንዲመልስልን ተግተን እንጸልይ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ።

በሠማእታት ቀን፤ በጣሊያን ለበደለኛው ክብር የቆመው ሃውልት እንዲፈርስ ተጠየቀ

Tuesday, February 19th, 2013
ዛሬ የካቲት 12 2005 ዓም ነው። እለቱ በኢጣሊያ ፋሽስት ወራሪዎች ከ30ሽህ በላይ የአዲስ አበባ ሰላማዊ ነዋሪዎች በግፍ የተፈጁ ሰማእታት የሚታሰቡበት። ይሄንን የጅምላ ጭፍጨፋ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ያዘዘውና የጦር ወንጀለኝነቱ በፍርድ ቤት የተረጋገጠው ሩዶልፎ ግራዚያኒ በጣሊያኗ የአፊና ከተማ የመታሰቢያ ሀውልትና በሥሙ የሚጠራ ቤተ መዘክር መናፈሻ መሠራቱ ያስቆጣቸው ኢትዮጵያዊያን አዲስ አበባን ጨምሮ፤ በዩናይትድ ስቴትስና በአውሮፓ በጣሊያን ኢምባሲዎች ደጃፍና ከሃያ በላይ ሌሎች ኢትዮጵያውያን በሚገኛቸው ከተሞች በተለያዩ መንገዶች ተቃወሟቸውን ለመግለጥ ተሰባስበዋል። ከአዲስ አበባና ከዋሽንግተን ዲሲ የተቀናበሩትን ዝግጅቶች ይከታተሉ።

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 19, 2013

Tuesday, February 19th, 2013
News, Ask the Doctor, Agriculture and Business

የአቶም ሳይንቲስቱ ዶ/ር ጌድዮን ጌታሁን

Tuesday, February 19th, 2013
ዶክተር ጌድዮን የሚሰሩት ጀርመን ቢሆንም ሃገራቸውንና ህዝባቸውን አልረሱም ለረዥም ጊዜ በሊቀመንበርነት በሊቀመንበርነት በመሩት ማህበር አማካይነትና በግላቸው የኢትዮጵያን የሳይንስ ትምሕርትና ተማሪዎች ይረዳሉ ።

አባይ፤ ኢትዮጵያ እና ግብፅ

Tuesday, February 19th, 2013
የአባይ ወንዝ ውሃን በመጠቀሙ ጉዳይ ላይ በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል የነበረው የኃይል ሚዛን ወደ ኢትዮጵያ እያደላ መሆኑ ተነግሯ። ግብጽ ከአባይ ወንዝ የምታገኘውን ጥቅም ማጣት አትፈልግም። የኢትዮጵያና ግብጽ ፍጥጫ ምሥራቅ አፍሪቃን ይበልጡን ያልተረጋጋ አካባቢ እንዳያደርገው ያሰጋል።

ኢትዮጵያውያን በሳውዲ

Tuesday, February 19th, 2013
ኢትዮጵያውያን ለደረሰባቸው ግፍ ካሳ የሚያስጥ በአጠቃላይ መብቶቻቸውን የሚያስከብር የመንግሥት ተወካይ ባለማግኘታቸው ለልዩ ልዩ ችግሮች መጋለጣቸው መቀጠሉን ነብዩ ሲራክ ከጅዳ የላከው ዘገባ ያስረዳል

የአዲሱ የፓሪያርክ ምርጫ በኢትዮጵያ

Tuesday, February 19th, 2013
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ቅዱስ ሲኖዶሱ በወሰነው መሰረት የካቲት 21 የፓትሪያርክ ምርጫ ይካሄዳል። የካቲት 24 ደግሞ በአዕለ ሲመቱ ይከበራል።

ታንዛንያ የወርቅ ማዕድን ሃብት

Tuesday, February 19th, 2013
ታንዛንያ የተፈጥሮ ማዕድን ባለ ሃብት ናት። በምስራቅ አፍሪቃዊትዋ ሀገር ታንዛንያ 36 ሚሊዮን አዉንስ ወርቅ፤ ማለት ወደ አንድ ሚሊዮን ኪሎ ግራም የወርቅ ክምችት እንዳላት ይገመታል። በዚህም በአፍሪቃ አህጉር በወርቅ ሃብት ክምችት ከደቡብ አፍሪቃ እና ጋና ቀጥላ ሶስተኛ ደረጃን እንድትይዝ ያደርጋታል። ህዝቧ ግን የዚህ ሃብት ተጠቃሚ አይደለም።

19 02 2013ዜና 16:00 UTC

Tuesday, February 19th, 2013
የዓለም ዜና

ፍኖተ ነጻነት ቁጥር 65 ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

Tuesday, February 19th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር የረታ ‹‹ይቅርታ!›› ከዕንቁ መጽሔት የተወሰደ – ጸሐፊው በፍቅር ለይኩን፡፡

Tuesday, February 19th, 2013

በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን ከተማ የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ጓደኞቿና የነፃነት ትግሉ አጋሮቿም፡- ‹‹እናዝናለን ኤሚ…ፍቅርሽ፣ ርኅራኄሽ፣ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት መከበር ያለሽ ጽኑ አቋም በልባችን ለዘላለም ይኖራል፡፡ ትግላችን እንዳቺ ያሉ የእውነት፣ የፍትሕ ጠበቃዎችንና ሐቀኞችን በአጥፍ ጨምሮ ይቀጥላል…፡፡ ኤሚ እንወድሻለን፣ ሁሌም እናስታውስሻለን! አንቺ የዘረኞችን የመለያየት ግንብ የናድሽ ጀግናችን ነሽ፣ አንቺ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ሕያው ነሽ…ሞት በአንቺ ላይ ስልጣን የለውም፣ ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ያሸነፈሽ የሕዝባችን ታላቅ ሰማዕት ነሽና …ደህና ሁኚ ኤሚ ደህና ሁኚ፣ ሁሌም እንወድሻለን…!›› በማለት ወደ ትውልድ አገሯ አሜሪካ በእንባና በመሪር ሐዘን ሸኟት፣ ተሰናበቷት፡፡

ውቧ፣ ማራኪዋና ከዓለማችን አስር ምርጥ ከተሞች ተርታ የተመዘገበችው የደቡብ አፍሪካዋ የኬፕታውን ከተማ የደቡብ አፍሪካ የታሪክ፣ የቅርስ፣ የባህልና የፖለቲካ ማዕከል ናት፡፡ የድኅረ ምረቃ ትምህርቴን የተከታተልኩባት ኬፕታውን ለአምስት መቶ ዓመታት ያህል አፍሪካውያን ያለፉበትን ውስብስብ የታሪክ ጉዞ የሚያስቃኙ፣ የጥቁር ሕዝቦችን የአይበገሬነትና የነፃነት ተጋድሎ የሚዘክሩ በርካታ ቅርስና ሕያው አሻራ ያላት ታሪካዊ ከተማ ናት፡፡

ኬፕታውን ታላቁ አፍሪካዊ የነፃነት አርበኛ ኔልሰን ማንዴላና የትግል አጋሮቻቸው ለ27 ዓመታት የተጋዙባትን ቀዝቃዛውን የአትላንቲክ ውቅያኖስንና የከተማይቱን ግርማና ውበት የሆነውን የቴብል ማውንቴንን ተንተርሶ የተገነባው የሮቢን ደሴየት ግዞት ቤት/ወኅኒ ቤት የሚገኝባትም ናት፡፡

ይህን ለዘመናት በርካታ አፍሪካውያንና ጥቁር ሕዝቦች ለሰው ልጆች ነፃነትና ሰብአዊ መብት ሲሉ የተጋዙበትን የሮቢን ደሴየት ግዞት ቤት/ወኅኒ ቤት በየቀኑ በሺህዎች የሚቆጠሩ ጎብኚዎች፣ የታሪክ ተመራማሪዎችና አጥኚዎች፣ ፖለቲከኞች፣ መሪዎች፣ ታላላቅ የሆኑ የዓለማችን የፊልም እንዱስትሪዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም ዝነኞችና ባለ ጠጋዎች ይጎበኙታል፡፡ እናም የደቡብ አፍሪካዋ ‹‹እናት ከተማ›› ኬፕታውን የቱሪስቶችና ውብ የመዝናኛ ከተማም ጭምር ናት፡፡

በዩኒቨርስቲ ቆይታዬ በትምህርት ክፍላችንና የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሙን ነፃ የትምህርት ዕድልና አጠቃላይ ወጪያችንን የሸፈነልን የሮቢን ደሴየት ሙዚየም፣ በኬፕታውን የሚገኙትን ቤተ መዘክሮችን፣ የደቡብ አፍሪካውያንን የነፃነት ተጋድሎ የሚያንጸባርቁ ታሪካዊ ቦታዎችንና ቅርሶችን መጎብኘት እንድንችል ዕድልን አመቻችቶልን ነበር፡፡ በዚህ ዕድልም ከጎበኘኋቸውና በማስታወሻ ደብተሬ ከመዘገብኳቸው አስደናቂ ቦታዎች መካከል አንዱ ለዛሬ ጽሑፌ መነሻ ሆኖኛል፡፡

እኔና የክፍል ጓደኞቼ ጉብኝታችን ፕሮግራሞች ውስጥ ካየናቸው የአፓርታይድ አገዛዝን ጭካኔና ክፋት ከሚዘክሩ ታሪካዊ ቦታዎች በኬፕታውን ከተማ የሚገኘው የጉጉሌቱ ታውን ሺፕ አንዱ ነው፡፡ ይህ ታውን ሺፕ/መንደር በአብዛኛው ጥቁሮች የሚኖሩበት ነው፡፡

እነዚህ በአራቱም የአገሪቱ ክፍል የሚገኙ የጥቁር አፍሪካውያን መንደሮች በደቡብ አፍሪካውያን ሕይወት ዘረኛው የአፓርታይድ ስርዓት የተወው ጠባሳ ገና ፈፅሞ የሻረ እንዳልሆነ ማረጋገጫን የሚሰጡ ናቸው፡፡ እስከ አሁንም ድረስ ጥቁር አፍሪካውያኑ የሚኖሩባቸው እነዚህ መንደሮች ድህነትና ጉስቁልና በእጅጉ የሚንጸባረቅባቸው መሆናቸው የሕዝቦቻቸው ኑሮ ይመሰክራል፡፡

በዚህች በጉጉሌቱ የድኆች መንደር ውስጥ ነዋሪዎቿና ሥራ አጥ ወጣቶቿ ካሉበት አስከፊ ድህነትና ጉስቁልና በመጠኑም ቢሆን ለማውጣትና እገዛ ለማድረግ በአሜሪካውያን ቤተሰቦች የተቋቋመ አንድ ፋውንዴሽን አለ፡፡ በጉብኝታችን ወቅት ስለዚህ ፋውንዴሽን ማብራሪያ የሰጠን አስጎብኚያችን የፋውንዴሽኑን አመሰራረት ታሪክ እንዲህ ሲል አጫወተን፡፡

እኔም በማስታወሻዬ የዘገብኩትንና በዚህች ድህነትና ወንጀል በተንሰራፋበት የጥቁሮች መንደር ‹‹ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ስለረታው›› አስደናቂ የእርቅ/የይቅርታ ድንቅ ታሪክ ከማስታወሻዬ ማኅደር ላስነብባችሁ ወደድኹ፡፡

ደቡብ አፍሪካውያን ጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ትግል በ1970ዎቹ እና በ1980ዎቹ መጨረሻ አካባቢ ላይ እጅጉን የተፋፋመበት ወቅት ነበር፡፡ በተለይም ደግሞ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ያገኙ ደቡብ አፍሪካውያን ጥቁር ተማሪዎች ትግሉን ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ያሻገሩበትን ትልቅ ዕድል ፈጥሮ ነበር፡፡

በዚህ በኬፕታውን ከተማ በዋነኝነት ለክልሶች፣ ለኢንዲያንስ (Colors and Indians) እና ቁጥራቸው አነስተኛ የሆኑ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ተማሪዎች የመማር ዕድል እንዲያገኙ በተቋቋመው የዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ፣ ከአሜሪካን ካሊፎርኒያ ኮሌጅ በFulbright Scholarship ዕድል ያገኘች አንዲት በሃያዎቹ አጋማሽ ላይ የምትገኝ ነጭ አሜሪካዊ ወጣት በዩኒቨርስቲው ያለውን የተማሪዎችን ፀረ አፓርታይድ እንቅስቃሴና ትግል ለማጥናት በዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ ለአስር ወራት ቆይታ ለማድረግ መጥታ ነበር፡፡

ኤሚ የተባለችው ይህች ነጭ አሜሪካዊት ሴት በዩኒቨርስቲ ቆይታዋ ከጥቁር ተማሪዎች ጋር ለመተዋወቅና አጋርነቷን ለመግለፅ ብዙም ጊዜ አልወሰደባትም ነበር፡፡ እናም በአጭር ጊዜ ውስጥ የተማሪዎቹ ጓደኛ ብቻ ሳይሆን ዋና የትግል አጋርም ለመሆን በቃች፡፡ የፀረ አፓርታይድ ትግሉንም በሐሳብና በሞራል መደገፉን ተያያዘችው፡፡ በተጨማሪም ከአፍሪካውያን ተማሪዎች ጋር ስለ አፍሪካውያን የነፃነት ትግል ሂደትን በተመለከተ ሰፊ ውይይትና ጥናት ማድረጓንም ቀጠለች፡፡ ከአፓርታይድ አገዛዝ ወደ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ መንግስት በሽግግር ወቅት ለነበረችው ደቡብ አፍሪካም የምትችለውንና የአቅሟን ሁሉ አደረገች፡፡

ኤሚ ከተማሪዎቹ ጋር ያስተሳሰራት የፀረ አፓርታይዱ ትግል ይበልጥ ወንድማዊና እህታዊ የሆነ ቤተሰባዊ ወዳጅነትን አተረፈላት፡፡ እናም ኤሚ አፍሪካውያን ጥቁር ተማሪዎች በሚኖሩባቸው በተከለሉ የጥቁሮች መንደሮች እየተዘዋወረች የዘረኛውን የአፓርታይድ መንግሥትን አስከፊና ዘግናኝ ጭቆና በዓይኗ ለመታዘብና ምስክር ለመሆን ቻለች፡፡

ጭቆና፣ ድህነት፣ መከራ፣ ጉስቁልና፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የዘረኛው አፓርታይድ መንግሥት ክፉ ተግባርና ግፍ አባሳቸውን በሚያስቆጥራቸው በእነዚህ የድሆች ከተማዎች ውስጥ ያለውን ዘግናኝ ሕይወት ኤሚ በአዕምሮዋና ብዕሯ መከተቡን በሚገባ ተያያዘችው፡፡

የሚሊዮኖች የጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የፍትህ ያለህ ዋይታና እሪታ በሚሰማባቸው የጥቁሮች መንደር ያለውን ዘግናኝ እውነታ የታዘበችው ኤሚ፡- ይህ ግፍ፣ ይህ ኢ-ሰብአዊነትና ጭካኔ ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ፀረ አፓርታይድ ትግልና ታጋዮች ያላትን አጋርነት በይበልጥ እንድታጠናክር አደረጋት፡፡ ኤሚ በሳምንቱ መጨረሻና በበዓል ወቅት ለእረፍት ወደቤተሰቦቻቸው የሚሄዱትን ተማሪዎች ከዩኒቨርስቲ በመኪናዋ በመሸኘት ጭምር ከእነርሱ ጋር ብዙ ጊዜዋን ታጠፋ ነበር፡፡

ታዲያ ከሰብአዊነት ከመነጨ ፍቅርና ርኅራኄ ለጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ተማሪዎች ድጋፏን ስትሰጥ የነበረችው ኢሜ በአንድ ወቅት የትምህርት ቤት ጓደኞቿንና የትግል አጋሮቿን ለመሸኘት ለጥቁሮች ብቻ ወደተከለለ የጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን የድሆች መንደር ወደሆነችው ጉጉሌቱ እንደበፊቱ ሁሉ አገር ሰላም ነው ብላ መኪናዋን በማሽከርከር ትመጣለች፡፡

ጓደኞቿን ከመኪናዋ አውርዳ የምትቸኩልበት ሌላ ጉዳይ የነበራት ኤሚ መኪናዋን አዙራ በፍጥነት ወደ ከተማ ለመመለስ ስትነዳ ሳለች በመንገዷ ላይ ሁከት ከታከለበት ሰልፍ ውስጥ ራስዋን አገኘችው፡፡ ከሰልፉ መካከል የወጡ ሁለት ወጣቶችም መኪናዋን እንድታቆም አጭርና ቀጭን ትዕዛዝን አስተላለፉላት፡፡ ኤሚ በወጣቶቹ ትዕዛዝ በጥቂቱም ቢሆን ግራ ተጋባች፡፡

ይሁን እንጂ ኤሚ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ የመሰላት ጥቁሮች ለነፃነታቸው የሚያደርጉትን ትግል በመደገፍ በመቆሟ አድናቆታቸውንና ምስጋናቸውን ሊገልፁላት መስሎአት የወዳጅነት ፈገግታን በተሞላ መንፈስ ሰላም አለቻቸው፡፡ ያ በኤሚ ፊት የታየው ከፍቅርና ከርኅራኄ የመነጨ ፈገግታዋ ግን በእነዚህ ወጣቶች ዘንድ በምላሹ ጥላቻን ያነገሰ ቅፅበታዊ የሆነ ግብታዊ ስሜትን ፈጠረ፡፡

እናም እነዚህ ጥቁር ደቡብ አፍሪካውያን ወጣቶች በዛ በነጮቹ የአፓርታይድ ዘረኛ ስርዓት አራማጆች ለጥቁሮች ብቻ ተከልሎ በተሰጣቸው ምስኪን መንደራቸው ይህችን ነጭ ወጣት ሴት ማየታቸው በእጅጉን አናደዳቸው፡፡ እናም በውስጣቸው የሚንቀለቀለውን ንዴትና በቀል በኤሚ ላይ ለማዝነብ ፈጣን እርምጃ ወሰዱ፡፡ የኤሚ ተማጽኖና የማንነት ኑዛዜ ሰሚን አላገኘም፡፡

ወጣቶቹ ኤሚን በመኪናዋ ውስጥ እንዳለች በድንጋይ በመውገር ያን የፍቅርና የርኅራኄ ፈገግታዋን በበቀል ደም አጨልመውትና አጠልሽተውት እግሬ አውጪኝ በማለት ከአካባቢው ተሰወሩ፡፡ በደም ተጨማለቀችውን ሴት ፖሊስ ደርሶ ወደ ሐኪም ቤት ይዟት ቢሄድም ሕይወቷን ለማትረፍ አልተቻለም ነበር፡፡ እናም ኤሚ በዚህ ዓይነት ያልተጠበቀ መጥፎ አጋጣሚ ሕይወቷ አለፈ፡፡

ባልታሰበና ባልተጠበቀ አጋጣሚ ኤሚ ለነፃነታቸውና ለሰብአዊ መብታቸው በምትታገልላቸውና አይዞአችሁ በምትላቸው ጥቁሮች ወንድሞቿ እጅ ሕይወቷ አለፈ፡፡ ገዳዮቿም በፖሊስ ተይዘው ወኅኒ እንዲወረወሩ ተደረገ፡፡ ይህን ዘግናኛ አጋጣሚ የሰሙና ያዩ ጓደኞቿ ሀዘናቸው እጅጉን የመረረ ነበር፡፡ የትግል አጋራቸውንና የልብ ጓደኛቸውን ያጡት የዌስተርን ኬፕ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ የትግል አጋሮቿና ጓደኞቿ በዩኒቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐዘናቸውን ለመግለጽ ልዩ የሐዘንና የስንብት ፕሮግራም በማድረግ ኤሚን፡-

‹‹እናዝናለን ኤሚ…ፍቅርሽ፣ ርኅራኄሽ፣ ለሰው ልጆች ነፃነትና መብት መከበር ያለሽ ጽኑ አቋም በልባችን ለዘላለም ይኖራል፡፡ ትግላችን እንዳቺ ያሉ የእውነት፣ የፍትሕ ጠበቃዎችንና ሐቀኞችን በአጥፍ ጨምሮ ይቀጥላል…፡፡ ኤሚ እንወድሻለን፣ ሁሌም እናስታውስሻለን! አንቺ የዘረኞችን የመለያየት ግንብ የናድሽ ጀግናችን ነሽ፣ አንቺ በልባችን ውስጥ ለዘላለም ሕያው ነሽ…ሞት በአንቺ ላይ ስልጣን የለውም፣ ሞትን በሕይወት፣ ጥላቻን በፍቅር ያሸነፈሽ የሕዝባችን ታላቅ ሰማዕት ነሽና …ደህና ሁኚ ኤሚ ደህና ሁኚ፣ ሁሌም እንወድሻለን…!›› በማለት ወደ ትውልድ አገሯ አሜሪካ በእንባና በመሪር ሐዘን ሸኟት፣ ተሰናበቷት፡፡

ከጥቂት ዓመታት በኋላ የእነ ኤሚና የሚሊዮኖች ደቡብ አፍሪካውያንና የሰው ልጆች ነፃነት ተቆርቋሪ የሆኑ ሕዝቦች መራር ትግል በስተመጨረሻ ፍሬ አፍርቶ የአፓርታይድ ስርዓት ከደቡብ አፍሪካ ምድር ተገረሰሰ፡፡ የፀረ አፓርታይድ ትግሉ ዋና መሪ በሆኑት በኔልሰን ማንዴላ ግንባር ቀደምትነትም በአዲሲቷ ደቡብ አፍሪካ ብሔራዊ እርቅና መግባባት እንዲወርድ ታወጀ፡፡

ለዚህም ማንዴላ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ለ27 ዓመታት ግዞት፣ ለሕዝባቸው መከራ፣ እንግልት፣ ስደትና ሞት ምክንያት የሆነውን የአፓርታይዱ ዘረኛ መንግሥት መስራችና ዋና አቀንቃኝ ወደሆኑት ወደ ሟቹ የቀድሞ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ቤት በመሄድ በሕይወት የሚገኙትን ባለቤታቸውን፣ ዘረኛው የአፓርታይድ ስርዓት በርሳቸውና በሕዝባቸው ላይ ላደረሰባቸው የሰው ልጅ ሕሊና ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ለሆነው ግፍና መከራ በፍፁም ልብ ይቅርታ ማድረጋቸውን ለዓለም በይፋ ገለጹ፡፡

ዓለም በአንድ ድምፅ፡- ‹‹ብራቮ ማንዴላ! የሰላም አባት፣ የፍቅር ተምሳሌት፣ የይቅርታ መዝገብ…!›› ሲል አሞካሻቸው፡፡ ይህን የፍቅርና የእርቅ መንገድ ሚሊዮኖች ደቡብ አፍሪካውያን ዘረኛው አፓርታይድ መንግስት ትቶባቸው ካለፈው ህመማቸው፣ ስብራታቸውና ቁስላቸውም ጋር እየታገሉም ቢሆን ‹‹ዳዳ/ማዲባ›› ወይም ‹‹ታላቁ አባታችን›› የሚሏቸውን የማንዴላን ‹‹የሰላምና የእርቅ መንገድ›› ቆርጠው ሊከተሉት ወሰኑ፣ የብዙዎችም ልብ ለፍቅርና ለይቅርታ ጨከነ፡፡

በዚህም ለቂምና ለበቀል፣ ለክፋት፣ ለጥላቻና ለእርስ በርስ እልቂት ከሰገባቸው የተመዘዙ የበቀል ሰይፎች ወደ ሰገባቸው ተመልሰው በአንፃሩ ደግሞ በዚህች የእግዚአብሔር ስጦታ በሆነች ውብና ባለ ጠጋ የአፍሪካ ምድር- በደቡብ አፍሪካ እርቅና ሰላም ይወርድ ዘንድ የሃይማኖት አባቶች፣ ዓለም አቀፍ የሕግ ባለሙያዎች፣ የታሪክ ተመራማሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎችና ተሟጋቾችን፣ ታዋቂ ሰዎችን ጭምር ያቀፈ የእውነት አፈላላጊና የእርቅ ኮሚሽን (Truth and Reconciliation Commission) በይፋ ተቋቋመ፡፡

ይህ የደቡብ አፍሪካ የእውነት አፈላላጊና የእርቅ ኮሚሽንም በአፓርታይድ ዘመን የደረሱትን የመብት ጥሰቶች፣ ጭፍጨፋ፣ እልቂትና ግፍ በመመርመር በበዳይና በተበዳይ መካከል ሰላምና እርቅ እንዲወርድ፣ እንዲሁም የትላንትና ቁስሎች በቂም በቀል ሳይሆን በይቅርታና በካሳ እንዲዘጉ ትልቁን ኃላፊነትና ታሪካዊ የሆነ ድርሻ ወሰደ፡፡

በዚህም የትላንትና የጭቆና፣ የክፋት፣ የጥላቻ፣ የእልቂትና የደም ዘመን ምዕራፍ ተዘግቶ በአገሪቱ አዲስ የሆነ የእርቅና የሰላም ታሪክ እንዲፃፍ አደረገ፡፡ ከዚህም የተነሳ አዲሲቱ ደቡብ አፍሪካ ነጭ፣ ጥቁር፣ ክልስ፣ ህንድ…ወዘተ ሳይባል ሁሉም በሰላምና በአንድነት የሚኖሩባት Rainbow Nation የሚል ቅጽል ስምንና ክብርን አተረፈች፡፡

ወደ ታጋይዋ ኤሚ ታሪክ ፍፃሜ ስንመለስ ደቡብ አፍሪካ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሽግግርን ካደረገች በኋላ በአፓርታይድ ዘመን በደቡብ አፍሪካውያን ሕዝቦች ላይ የደረሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት፣ ግድያ፣ እሥራትና ግፍ ለማጣራት በተቋቋመው የእውነትና የእርቅ አፈላላጊ ኮሚሽን በተደረገላቸው ግብዣ ወደ ደቡብ አፍሪካ የመጡት የኤሚ ወላጆች ሚ/ር ፒተርና ወ/ሮ ሊንዳ በልጃቸው ሞት ምክንያት የተከሰሱ ወጣቶች በተገኙበት በተካሄደው ችሎት ለልጃቸው ገዳዮች ፍፁም የሆነ ከልብ የመነጨ ይቅርታ ማድረጋቸውን በፍቅር ገለፁ፡፡

የኤሚ እናትና አባት በዚህ ብቻ አላበቁም፡፡ ገና አሁንም ከባድ የሆነ ድህነት፣ የሥራ አጥነትና ወንጀል በተንሰራፋባት በምስኪኗ ጉጉሌቱ የፍቅርና የይቅርታ ሀውልትን ለማቆሙ ወደዱ፡፡ የአፓርታይድ ዘረኛ መንግስት ትቶት ያለፈው መጥፎ አሻራው ባልጠፋባት በዚህች መንደር መካከል ወደተቋቋመው ፋውንዴሽን በእጁ እየጠቆመን አስጎብኚያችን አንዳንች ልዩ ስሜት የተጫነው በሚመስል ቃላቶችና የሰውነት እንቅስቃሴ ትረካውን እንዲህ ቀጠለልን፡-

የኤሚ ወላጆች በችሎቱ ፊት ባሰሙት ውሳኔያቸው ለልጃቸው ገዳዮች ፍጹም የሆነ ይቅርታ ማድረጋቸውን በይፋ ገለጹ፡፡ ለሟች ልጃቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድም ልጃቸው በድንጋይ ተወግራ በሞተችበት አካባቢ ለመንደሩ ነዋሪዎችና ሥራ አጥ ወጣቶች እንዲሆን በራሳቸው ገንዘብ በግፍ ለተሠዋችው ለልጃቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የኤሚ ፋውንዴሽንን አቋቋሙ፡፡ የኤሚ ገዳዮችም በዚሁ ፋውንዴሽን ውስጥ ዋና ሠራተኛና ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

ይሄ ፋውንዴሽን ለልጃቸው፣ ለምስኪኗ ሰማዕት ኤሚ የበቀል ደም በፍቅርና በይቅርታ ይደመደም ዘንድ የተቋቋመ መሆኑን አስጎብኚያችን ሲተርክልን ብዙዎቻችን በስሜት ተውጠንና ዓይናችን እንባ አቅርሮ ነበር፡፡ አንድና ብቸኛ ልጃቸውን በሞት የተነጠቁት የኤሚ አባትና እናትም ለልጃቸው ገዳዮች እናትና አባት እንደሚሆኑላቸው ጭምር ነበር ከልብ በሆነ ፍቅር ያበሰሯቸው፡፡ አስጎብኚያችን እጅግ ልብ የሚነካውን ታሪክ መተረኩን ቀጥሏል . . .፡፡

በጉብኝቱ መካከል የነበሩ አብዛኞቹ ሴት ተማሪዎችም እንባቸው መንታ ሆኖ በጉንጫቸው ላይ ሲወርድ በግልፅ ይታይ ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በዚህች በድሆች መንደር ‹‹ለፍቅርና ለእርቅ›› በቆመው ፋውንዴሽን ሕንፃ ላይ ዓይናቸውን ለደቂቃዎች ሰክተው ጥልቅ የሆነ የአሳብ ባሕር ውስጥ የገቡ ይመስሉ ነበር፡፡ አስጎብኚያችን ትረካውን ጨርሶአል፤ ሁኔታው ግን ከእኛው ጋር ቃላት ሊገልፀው በማይችል ጥልቅና በልዩ ስሜት ውስጥ አብሮን የነጎደ ይመስል ነበር፡፡

ይህን አስደናቂ የፍቅር/የእርቅ ገድል ታሪክ ከምመዘግብበት ማስታወሻዬ ላይ እንዳቀረቀርኩ ሕሊናዬ፡- የራሴን፣ የወገኖቼንና አገሬን የእርስ በርስ መበላላት ዘግናኝ ታሪክ፣ የቂም፣ የበቀልና የጦርነት ታሪክ ወደፊትና ወደኋላ እያጠነጠነ ነበር፡፡ ከሰላሙ፣ ከፍቅሩ፣ ከአንድነቱና ከእርቁ ታሪካችን ይልቅ የመበላላት፣ የቂም፣ የበቀልና የመለያየት ዘግናኝ ታሪካችን በዓይነ ሕሊና ገዝፎ ታየኝ፡፡ እናም ካቀርቀርኩበት ቀና ስል ዓይኔ ያረገዘው የእንባ ዘለላ ቁልቁል ወርዶ በማስታወሻ ደብተሬ ላይ ጠብ ሲል ተመለከትኩት፡፡

በማስታወሻ ደብተሬ ላይ ዛሬም ምስክር ሆኖ ያለው የደረቀው እንባ የኤሚንና የወላጆቿን የነፃነት ተጋድሎ፣ የእውነትና የፍትሕ ራባቸውን፣ ድንበርና ዘር ያላገደውን የፍቅራቸውን ታላቅነትና ሕያውነት በአንክሮት ያሳስበኛል፡፡ በእውነትም ይህ በኬፕታውን በጉጉሌቱ የጥቁሮች መንደር በኤሚ ስም የተቋቋመው ፋውንዴሽን በፍቅር ስለፍቅር በተከፈለ መስዋእትነት፣ የይቅርታን ታላቅነት በተግባር ለመተረክ የቆመ ሕያው ምስክር፣ ዘመን አይሽሬ ቅርስ መሆኑን ሁላችንም በጉብኝቱ የነበርን ከተለያዩ ሀገራት የመጣን ተማሪዎች በአንድ መንፈስ በአንድ ቃል ያረጋገጥን በሚመስል መንፈስ ዓይን ለዓይን ተያየን፡፡
ሁላችንም በዛች ቅፅበት በኤሚ የፍትሕ ሰማዕትነት፣ በወላጆቿ የፍቅርና ይቅርታ ቋንቋ ከልብ የተግባባን መሰልን፡፡ ሕሊናችን መልሶ መላልሶ ኤሚን፣ ፒተርን፣ ሊንዳን፣ ፍቅርን፣ ይቅርታን… በዛች ድህነት፣ ጉስቁልና፣ ሥራ አጥነትና ወንጀል በተንሰራፋባት የጥቁሮች መንደር በጉጉሌቱ ለፍቅርና ለእርቅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የቆመውን የኤሚን ፋውንዴሽን ያሰላስል ጀመር፡፡

ልባችንም አንደበታችንም በዚህ ሕያው የፍቅር ገድል የተረታ መሰለ፡፡ እናም ከጉብኝታችን ጉዞ መልስ የኤሚንና የወላጆቿን የፍቅር/የይቅርታ ታላቅ ገድል በመቀባበል እየተረክን ነበር ወደ ዩኒቨርስቲያንችን ቅጥር ግቢ በአድናቆትና በአግራሞት ተሞልተን የተመለስነው፡፡

የካሊፎርኒያዎቹ ሚ/ር ፒተርና ወ/ሮ ሊንዳ የልጃቸው ክቡር ሕይወት በብዙ እልፎች ሕይወት የሚተካውና መንፈሷ ሊያርፍ የሚችለው ገዳዮቿን በመበቀል ሳይሆን በይቅርታ መሆኑን በተግባር ያሳዩበት ይህ የፍቅር ገድል ታሪክ ዛሬም ድረስ በውስጤ ይደውላል፡፡ እነዚህም ቤተሰቦች በደላቸውን በሌላ በደል፣ በቂም በቀል ሳይሆን ከልብ በመነጨ ይቅርታ በበጎ ካሳ በፍቅር ደመደሙት፡፡ በእርግጥም ይቅርታ የተሰበረንና የቆሰለ ልብን ሊጠግን የሚችል፣ መዓዛው የሚያውድ፣ መልካም የፍቅር ዘይትን ማፍሰስ ካልቻለ ሙሉ ይቅርታ ሊሆን አይችልም፡፡

በወቅቱም ይህን የኤሚን ቤተሰቦች ፍቅር፣ ርኅራኄና ይቅርታ የታየበትን ሰላማዊ የሆነ የእርቅ እርምጃ አንድ የደቡብ አፍሪካ ታዋቂ ጋዜጣ እንዲህ በማለት ገልፆት ነበር፡-
Today, rather than having their lives subsumed in bitterness, Amy’s parents are leading important, constructive lives as part of the great South African reconciliation effort. They keep Amy’s spirit alive as a living memory, and they feel hope rather than anger. Strictly from the standpoint of their own self-interest, the Biehls are better off than if they had refused to forgive.

እውቁ የነፃነት ታጋይ፣ የሰላም አርበኛ፣ የአዲሲቱና የዲሞክራሲያዊቱ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያ ጥቁር ፕሬዝዳንት የነበሩት ኔልሰን ማንዴላ በኤሚ ድንገተኛና አሳዛኝ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሐዘን ባደረጉት ንግግራቸው ስሜታቸውን እንዲህ ሲሉ ነበር የገለጹት፡-

“She made our aspirations her own and lost her life in the turmoil of our transition as the new South Africa struggled to be born in the dying moments of apartheid. Through her, our peoples have also shared the pain of confronting a terrible past as we take the path of reconciliation and healing of our nation.”

ፍቅርን ያብዛልን! ሰላም፣ እርቅና አንድነት ለእናት ምድራችን ለእማማ ኢትዮጵያችን ይሁን! አሜን ይሁን!!
ሰላም! ሻሎም!

በሰሜን አሜሪካ የፍኖተ ጋዜጣ ዝግጅትድጋፍ አስተባባሪ ኮሜቴ ጥሪ ለወገኖቻችን

Tuesday, February 19th, 2013

በኢትዮጵያ ሀገራችን ባለፉት ዘመናት ተንሰራፍተው የቆዩትን ጨቋኝ ስርዓቶች ለመጣል ከፍተኛ መስዋዕትነት የተከፈለ ቢሆንም በመስዋዕትነቱ እስካሁን የተገኘው ውጤት የበለጠ መስዋዕትነትን እየጠየቀ የመጣበት ሁኔታ እንጂ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ የሆነበት ስርዓት ለመመስረት አልተቻለም፡፡

በተለይም ባለፉት 21ዓመታት ራሱን በዲሞክራሲያዊ ቀለም በህገመንግስት ጭምር ቀባብቶ ብቅ ያለው አምባገነናዊ የህውሃት ኢህአዴግ መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ የተቀባው ቀለም እየተላጠ ውስጣዊ ማንነቱ ራሱን ሊደብቅ ከማየችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ለተወሰነ ጊዜ በልማታዊ መንግስትነት የምዕራብዓያዊያን ሀገሮችንም ያነሆለለበት የሁለት አሀዝ እድገት በራሱ ቋንቋ እያሻቀለ መሄዱን ለመስማት ተችሏል፡፡

ይህ አዲስ ክስተት አይደለም፡፡ የህብረተሰብ እድገት የአለም የፖለቲካ ሁኔታ መገለጫ ነው፡፡ በምንም ዓይነት ኃይል ማንኛውም አይነት አምባገነናዊ ስርዓት በረሱ ውስጣዊ ቅራኔም ሆነ በህብረተሰቡ የተደራጀና የተቀናጀ ህዝባዊ ትግል ተገርስሶ እንደሚወድቅ ዛሬ የምናያቸው የተሻለ ስርዓት የመሰረቱ አገሮች በተለያየ አካሄድ ያለፉበት ደረጃ ነው፡፡ ለዚህም ነው ወያኔ ኢህአዴግ የፈለገውን ያህል ራሱን ቢቀባባም እንደግለሰብ ህይወት የፖለቲካ ስርዓትም ማለፉ የማይቀር የታሪክ ሂደት ነው የምንለው፡፡

ቁምነገሩ ግን በማለፉ ሂደት ውስጥ በህብረተሰቡ ላይ ጥሎ የሚሄደው ጠባሳና ትውልዱ ከስርዓቱ የሚያገኘው በጎና ቀና ተግባራት በታሪክ ውስጥ የሚኖረው ቦታ ነው፡፡ ለዚህም ነው ዛሬ በተለይም በሀገር ውስጥ ይሄንን ስርዓት በህዝብ ትግል አስገድዶ ባለፉት ትግሎች ያለፍንበትን በሰላማዊ መንገድ ህዝብን የስልጣን ባለቤት የማድረግ ሰላመዊ የፖለቲካ ትግል ላይ እውቀት፡ ጉልበትና ጊዜያቸውን ህይወታቸውን እና ንብረታቸውን ጭምር መስዋዕት በማድረግ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን አይዞአችሁ በርቱ ከጎናችሁ ነን የምንለው፡፡ በመስዋዕትነት ደረጃ ግንባር ቀደሙ ገፈት ቀማሾች በመሆናቸውም ያኮሩናል፡፡

አንዳዶች እንደሚገምቱት ዛሬ ተቀዋሚው ኃይል 4ኪሎ ቤተመንግስት ባለመግባቱ ብቻ የመሪነት ብቃትና መመዘኛ ተደርጎ ሊወሰድ የሚገባም አይመስለንም፡፡ 4ኪሎ በብዙ መንገድ ሊገባ ይችላለል፡፡ በኃይልም፣ በመፈንቅለ ማንግስትም፣ በሸፍጥም፣ በማተራመስም፣ በሽብርም፡፡ ቁምነገሩ መንግስታዊ ስልጣኑ የሚቆምበት ህዝባዊ ኃይል የአገራችንን አንድነትና ሉኣለዊነት የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት ፍትህና እኩልነትን የሚያረጋግጥ ማህበራዊ መሰረት ላይ የቆመ መሆኑን ማረጋገጥ እና መንግስት ወድቆ መንግስት ሲተካ ሌላ 100 እና 200 የሚሆኑ የፖለቲካ ተቃዋሚ ድርጅቶች የማይፈለፈሉበት ሁኔታን ማመቻቸት ሲቻል ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛው መሰረት የህዝቡን ንቃትና አስተሳሰብ መቀየር ወሳኝነት አለው፡፡ በተቀየረ አስተሳሰብ ላይ ተመስርቶ ነባራዊ ሁኔታን የመቀየር ችሎታን ማሳደግ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ሚዲያዎች እና ጋዜጦች ሚና እጅግ የላቀ ነው፡፡ የዛሬ የትኩረት ነጥባችንም የህብረተሰባችንን አስተሳሰብና አመለካከት ንቃት ብሎም ለማደራጀት ስራ ወሳኝነት ያለውን በሀገራችን የነፃ ፕሬስ መዳበር አስፈላጊነት ለመጠቆም እና የዚሁ ነፃ ፕሬስ አካል የሆነችውን ፍኖት ነፃነትን መልሶ ለህትመት ለማብቃትና ህይወት ለመስጠት ጥሪ ለማቅረብ ነው፡

አምባገነኑ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስትን አስከፊ ተግባራትን ከማጋለጥ ባሻገር ምን ዓይነት ስርዓት በአገራችን ሊገናባ እንደሚገባ በመስተማር በነፃ ፕሬስ ውስጥ ቀዳሚነትን በመያዝ ላይ የነበረችው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በትንሹ ተነስታ በስርዓቱ ደባ ህትመቷ ቢቋረጥም በህትመቷ ጊዜ እስከ 30ሺ ኮፒዎች በማሳተምና በማሰራጨት በህዝብ ዘንድ ተነባቢነትን እና ተአማኒነትን ያተረፈች ልሳን ነበረች፡፡ በዚህች ጋዜጣ ላይ ብርቅዬ የሀገሪቱ ወጣት ልጆች እና አዛውንቶች ያቀረቧቸው የነበሩት ፅኁፎች እና መረጃዎች ጋዜጣዋን ከዜና ወይም ከወሬ አቀባይነት አሸጋግሮ ወደ አቅጣጫ አመላካች ቀስቃሽና አስተማሪነት በአጠቃላይም ለትግሉ ከፍተኛ አነቀስቃሽነት መሳሪያነቷን የተረዳው አምባገነኑና አፋኙ የህውሀት ኢህአዴግ መንግስት በልዩ ልዩ ምክንያቶች ለመዝጋት የሞከረ ቢሆንም አዘጋጆቹ በከፈሉተት መስወዕትነት እስካሁን ጊዜ መቆየቱዋ ይታወቃል፡፡ የወያኔ ኢህአዴግ መንግስት በመጨረሻ ላይ ጋዜጣ አታሚዎችን ‹እኛ ማተም እንፈራለን› እሰኪሉ ድረስ አሳታሚዎችን በፍርሀት ሰለባ ተቆጣጥሮ ህትመቷ እንዲቋረጥ መደረጉ ይታወቃል፡፡ ያም ሆኖ ምንም እንኳን በቋሚ መልኩ ባይሆንም በተለያዩ ድህረ ገፆች አማካይነት የህዝብ ልሳን በመሆን አገልግሎቷን ቀጥላለች፡፡

ውድ ኢትዮጵያውያን ፣ ዛሬ በዚህ አምባገነን ስርዓት የነፃ ፐሬሶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ተዳፍነው የሚገኙበትና ወያኔ አፍንጫ ስር ሆነው የዚህን አስከፊ ስርዓት ገበና በማጋለጥም ሆነ እንደ ማደራጃ ኃይልም በማገልገል ላይ የሚገኙ የብርቅዬ የኢትዮጵያ ልጆችና ልሳኖቻቸው በምንም መልኩ እንዲዘጋ መፍቀድ ያለብን አይመስለንም፡፡የነአንዱአለም፣ የነእስክንድር፣ የነተመስገን እንዲሁም በርካታ የተሰደዱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ብዕሮች ይሄንን ስርዓት ምንያህል እደሚያስፈሩት እየወሰዳቸው ያለው አስከፊ እርምጃዎች ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ስርዓቱ አስሮ የማይጨርሳቸው ልጉዋም የሚያቅማቸው በሺህ የሚቆጠሩ ወጣቶች ከቀን ወደቀን እየፈሉ ናቸው፡፡ ከሁሉም በላይ የለውጡ ባህር በሆነው ህዝብ መሃል የሚያሰሙት ድምፅ ከምንም መሳሪያ የበለጠ ህዝባዊ እምቢተኝነት ይፈጥራል፣ያደራጃል፣ ያስታምራል፣ይቀሰቅሳል፣ አቅጣጫ ያለው በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባ ህዝባዊ እምቢተኝነትን ይፈጥራል፡፡ ለዚህ ነው ፍኖተ ጋዜጣ በሳምንታዊ ህትመት እስከ30ሺህ ኮፒ ታትማ ሁለት ሰዓት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ በገበያ ላይ የማትገኘው፡፡ ነፃ ፕሬስ በራሱ ብቻውን ለውጥ ያመጣል ማለት አይደለም፡፡ የለውጥ ኃይልን ያሰባስባል፡፡ ከኢቲቪ፣ ከአዲስ ዘመን ለህብረተሰባችን የሚነሰነሰውን ሳይወድ በግድ እንዲጋት የሚደረገውን ህዝባችንን አማራጭ ሃሳብና እውነታን ያስጨብጣል፡፡

በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የፍኖተ ጋዜጣን ህትመትና ስርጭት ከወያኔ ኢህአዴግ የተለያዩ የመቆጣጠሪያ ዘዴዎች በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ሊያላቅቅ የሚችል የራሱ የህትመት መሳሪያና ዝግጅት ለማደራጀት የሚያስችል ፕሮጀክት ተዘጋጅቷል፡፡ ለዚህ ፕሮጄክት መሳካት የአገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ተፋላሚዎችን ድጋፍና እገዛ ይጠይቃል፡፡ ለዚሁም እንዲረዱ ከ20 እስከ 500 ዶላር(ብር) የሚደርስ ትኬቶች ተዘጋጅተው በቅርቡ ለገበያ እንዲቀርቡ ይደረጋል፡፡ በተለይ በውጪ አገር የሚገኙ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህን ለማሳካት ከፍተኛ ጥሪ ቀርቦልናል፡፡ ጎዳናችን የተለያየ ሊሆን ይችላል፣ የማይለወጥ የጋራ ግባችን ግን በሀገራችን ፍትህ ሰላምና እኩልነት የሰፈነበት፣ ሉአላዊነት የተረጋገጠበት ስርዓት ማየት ነው፡፡ ይህ ደግሞ በምኞት ሳይሆን ሁላችንም ትንሽ ጠጠር ስንወረውር ብቻ ነው የሚሳካው፡፡ የአምባገነኑ ህውሀት ኢህአዴግ መንግስትን በተሻለ አስተሳሰብና ኃይል በልጦ የሚገኝ የፖለቲካ ሀይል ለመፍጠር የነፃ ፕሬሶች በጥራትና በብዛት ለህዝባችን ማዳረስ ምንም አማራጭ የሌለው የዴሞክራሲ ስርዓት ቁልፍ መክፈቻ ነው፡፡ የፖለቲካ ስልጣን በየትኛውም መንገድ ቢመጣ የተገኘውን ስልጣን የራሱ አድርጎ የሚመለከት አስተሳሰብና ህብረተሰብ እስካልተፈጠረ በሚነሱ ህዝባዊ ችግሮች ሁሉ የሚሰጡት ምላሾች ስልጣን የማቆየትና ያለማቆየት ጥያቄ ስለሚሆን በጠማንጃ ታፍኖ ለማይኖር ስርዓት እና ህዝብ በንቃት ላይ ለተመሰረተ ለውጥ የነፃ ፐሬስ ወሳኝነትን እንረዳ፡፡
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!

አይ ጥቅም በበላይነህ አባተ

Tuesday, February 19th, 2013

ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

“ጭንጋፍ (ምቱር) ፓትርያርክ” – በቀሲስ አስተርአየ ጽጌ

Monday, February 18th, 2013

ለማንበብ እዚህን ይጫኑ

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 18, 2013

Monday, February 18th, 2013
News, Sports, African Topics and Health

የሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ቦምብ ሙከራና ዉግዘቱ

Monday, February 18th, 2013
የቀድሞዉ ዩናይትድ ስቴትስ የጠቅላይ ኤታማዦር ሹሞች ጥምረት ሊቀመንበር አድሚራል አርተር ራድፎርድ መስከረም 1956 ለሐገራቸዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ያካፈሉት ዕቅድ ያን በእንጥልጥል የቆመዉን ጦርነት ሐገራቸዉ የኮሪያ ልሳነ-ምድርን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር የምትችልበትን ሥልት ያካተተ ነበር።

አባ ፊልጶስን ፍለጋ(ክፍል አራት)

Monday, February 18th, 2013


ደብረ ታቦር ኢየሱስ ከሩቅ ሲታይ
click here for pdf 
ወጋችንን ደብረ ታቦር ላይ ነበር ያቆምነው፡፡ ሪቻርድ ፓንክረስት እንደሚነግሩን በአካባቢው ትውፊት መሠረት ደብረ ታቦርን መሠረቷት የሚባሉት የኦሮሞው ተወላጅና በትውልድ ሙስሊም ሆነው በኋላ ክርስትናን የተቀበሉት ራስ ጉግሳ መርሳ ናቸው፡፡ ራስ ጉግሳ 1791-1818 ዓም ድረስ አካባቢውን አስተዳድረዋል፡፡ ራስ ጉግሳ ዋና ከተማ አድርገው መጀመርያ የከተሙት ከጎንደር በስተ ደቡብ ምሥራቅ 60 ኪሎ ሜትር ላይ በሊቦ ነበር፡፡ በኋላ ግን ለተፈጥሯዊ ምሽግ ወደምትስማማው ተራራማ ቦታ ሄደው ከተማቸውን በመቆርቆር ቦታውን ‹ደብረ ታቦር› ብለው ጠሩት፡፡
ራስ ጉግሳ አብዛኛውን ዘመናቸውን ያሳለፉት፣ ብዙዎቹን ሥራ የሠሩትና በኋላም ዐርፈው በ1818 ዓም የተቀበሩት እዚሁ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ነው፡፡ የራስ ጉግሣ ልጅ ኢማም ከአባቱ ቀጥሎ የገዛውና በመጨረሻም በ1821 ዐርፎ የተቀበረው እዚሁ ነው፡፡ ከእርሱ በኋላ ራስ ማርዬ፣ ራስ ዶሪ (እስከ 1824 ገዝተው እዚያው ዐርፈው ኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን ተቀብረዋል)፣ ራስ ዓሊ ዐሉላ(ታላቁ ራስ ዓሊ) በደብረ ታቦር መንበራቸውን ዘርግተው ገዝተዋል፡፡

እኤአ በ1843 ደብረ ታቦርን የጎበኛት ፈረንሳዊው ዲ አባዲ በከተማዋ ውስጥ በዚያ ጊዜ ከ1600- 1700 የሚጠጉ ቤቶች እንደነበሩ ጽፏል፡፡ የሕዝቡም ብዛት ወደ 10 ሺ ይጠጋ ነበር፡፡ ለሁለት ዐሥርት ዓመታ ያህል ደብረ ታቦር ላይ የከተሙት ራስ ዓሊ ብዙ አብያተ ክርስቲያናትን በመሥራት ይታወቃሉ፡፡ በደቡብ ምሥራቅ እናቲቱ ማርያም፣ በምሥራቅ ልጅቱ ማርያም፣ በሰሜን ጠጉር ሚካኤል የሚጠቀሱላቸው ናቸው፡፡ በጎንደር ታሪክ ውስጥ በትውልድ ሙስሊም የሆኑት የኦሮሞ ሥርወ መንግሥት ታሪክ የሚጠናቀቀው ደብረ ታቦር ላይ ነው፡፡
ዐፄ ቴዎድሮስ በየካቲት 1848 ዓም መንበረ ሥልጣኑን ሲይዙ ደብረ ታቦር አንዷ የመቀመጫ ከተማቸው ነበረች፡፡ በጥር 1849 ዓም የግብጹን ፓትርያርክ አቡነ ቄርሎስን የተቀበሉት እዚሁ ደብረ ታቦር ነበር፡፡ በ1853 ዓም ከወይዘሮ ጥሩ ወርቅ ጋር የተጋቡትም እዚሁ ደብረ ታቦር ነበር፡፡ ቴዎድሮስ የውጭ ሀገር ባለሞያዎችን በመጠቀም ከደብረ ታቦር እስከ አሞራ ገደል፣ በመጨረሻው ዘመናቸውም ከደብረ ታቦር እስከ መቅደላ መንገድ አሠርተው ነበር፡፡ በከተማዋ የሚገኘውን ደብረ ታቦር መድኀኔዓለምን አሠርተዋል፡፡ ይህ ጊዜ የቴዎድሮስ ጠባይ የተቀየረበት በመሆኑ ምዕራብ ጎጃም አዴት የሚገኘውን መድኃኔዓለምን አቃጥለው ሀብቱንና ቅርሱን ለደብረ ታቦር መድኀኔዓለም በመስጠታቸው
እንግዲህ ለታቦት አልሰጥም ስለት
አዴት መድኃኔዓለም ነዶ አገኘሁት
ብላ አንዲት ሴት ገጥማለች ይባላል፤፤
ዐፄ ቴዎድሮስ ሴፓስቶፖል መድፋቸውንም ያሠሩት በደብረታቦር ከከተማው አጠገብ በሚገኘው ሰላምጌ በተባለው ቦታ ነው፡፡
እጅግ የሚያሳዝነውም ዐፄ ቴዎድሮስ ከተማዋና ለመጨረሻ ጊዜ ለቅቀው ወደ መቅደላ ሲጓዙ ወታደሮቻቸው መስከረም 30 ቀን ከተማዋን አቃጠሏት፡፡

በስማዳ መንገድ የሚገኙ ቋጥኞች
ደብረ ታቦር የዐፄ ዮሐንስ አራተኛም ከተማ ነበረች፡፡ ነገር ግን የቀድሞ ነገሥታት የነበሩበትን አካባቢ ትተው ‹ሠመራ- መረጣት› በተባለው አካባቢ አዲስ ከተማ ቆረቆሩ፡፡
ዐፄ ዮሐንስ ራስ አዳልን ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ብለው በጥር 1873 ዓም በጎጃም ላይ ያነገሡዋቸው ደብረ ታቦር ላይ ነበር፡፡ አቡነ ጴጥሮስ፣ አቡነ ሉቃስና አቡነ ማርቆስ የተባሉት ግብጻውያን አባቶች በደብረ ታቦር ተቀምጠው ነበር፡፡ እንዲያውም አቡነ ማርቆስ ዐርፈው በ1874 ዓም የተቀበሩት እዚያው ነው፡፡ ስለ ከተማዋ አስደናቂ ታሪክ ልቡ ይበልጥ ለማወቅ የፈለገ ቢኖር የሪቻርድ ፓንክረስትን The History of Däbrä Tabor (Ethiopia): Bulletin of the School of Oriental and African Studies, University of London, Vol. 40,No. 2 (1977), pp. 235-266) ቢያነብ ይበጀዋል፡፡
አሁን ከተማዋን እንልቀቅና ወደ ስማዳ እናምራ፡፡ መንገዱ ወደ ስማዳ እስኪገነጠል ድረስ አስፓልት ነው፡፡ ወደ ስማዳ ከተገነጠለ በኋላ ግን ‹ማሩኝ› የሚያሰኝ ኮረኮንጅ ነው፡፡ ደግነቱ በመንገድ ላይ ብዙ የሚታይ ነገር አለው፡፡ የዝማሬ መዋሥዕቱን ማስመስከሪያ ዙር አምባን በሩቁ ትሳለማላችሁ፡፡ ቅዱስ ያሬድ ከዐፄ ገብረ መስቀልና ከአቡነ አረጋዊ ጋር ወደ ቦታው መጣ፡፤ ቦታውን ወደዱት ነገር ግን የመውጫው ነገር ቸገራቸው፡፡ ያን ጊዜ መልአከ እግዚአብሔር ‹አባ ሆይ ዙርና ወደ ተራራ ውጣ› ስላላቸው ቦታው ‹ዙር አባ› መባሉን የአካባቢው ትውፊት ይናገራል፡፡ እልፍ ስትሉ ደግሞ ከሁለት መቶ ዓመታት በላይ እድሜ ያለው የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንደ ዙር አምባው ሁሉ ተራራ ላይ ከነ ሙሉ ግርማ ሞገሡ ይታያችኋል፡፡

የቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን
በመንገድ ላይ ተፈጥሮን እንድታደንቁ የሚያደርጓችሁ የቋጥኝ ተራሮች አትለፉኝ አትለፉኝ ይላሉ፡፡ ስማዳ የጤፍ ሀገር ነው፡፡ ዛሬ በአዲስ አበባና በአካባቢው የተወደደው የአድአ በርጋ ነጭ ማኛ ጤፍ መነሻው ስማዳ ነው፡፡ ዐፄ ምኒሊክ ለቤተ መንግሥታቸው የሚሆን ነጭ ጤፍ ቢያጡ ከስማዳ አስመጥተው በአድአ በርጋ ስለዘሩት ይኼው ጤፉም ለምዶ ቀረ፡፡ የስማዳ ጥንታዊው ታዋቂ ማኛ ጤፍ ‹ስይት› ጤፍ ይባላል፡፡ ችግሩ በአንድ ቦታ የሚበቅለው መጠን አነስተኛ በመሆኑ ለቅንጦት እንጂ ለአዘቦት አይሆንም አሉ፡፡

መሪጌታ ሐረገ ወይን
በመንገዳችን ላይ በላይ ጋይንት ወረዳ ውስጥ የምትገኘውን ወለላ ባሕር ከተማን እናገኛታለን፡፡ እዚያ ደግሞ የታወቁት ሊቅ መሪጌታ ሐረገ ወይን ይገኛሉ፡፡ መሪጌታ ሐረገ ወይን እግዚአብሔር ጸጋ የሰጣቸው የታሪክ ሊቅ ናቸው፡፡ ከመቄት በታች ያለውን ሀገር በተመለከተ የማያውቁት ነገር የለም፡፡ የእያንዳንዱን ጎጥ ታሪክ ያውቁታል፡፡ እጅግ የሚገርመው ደግሞ ታሪኩን እንዳይረሱት በደብተር ላይ ጊዜ ሲያገኙ ይጽፉታል፡፡ 

ዕድሜ ጠገቧ የመሪጌታ ሐረገ ወይን ደብተር
እርሳቸው እንደነገሩን ከሆነ አካባቢውን ከግራኝ ጥፋት በኋላ ያቀኑት በፄ ሠርጸ ድንግል ዘመን ወደ አካባቢው የመጡ አራት ቅዱሳን ናቸው፡፡ ዐፄ ሠርጸ ድንግል ወደ ጎንደር ሲሻገሩ አራት ሊቃውንትን አመጡን አአራት ቦታ መደቧቸው፡፡ አባ መሰንቆ ድንግል(ለቤተልሔም)፣ አባ ለባዌ ክርስቶስ(ለዙር አምባ)፣ አባ ብእሴ እግዚአብሔር (ለገርባ ማርያም)ና አባ ተክለ ወልድ(ለደብረ ማርያም)፡፡ በሌላ ታሪክ ላይ እነዚህ አባቶች የመጡት ከጉራጌ ምሁር ኢየሱስ መሆኑን ይገልጣል፡፡ 
መሪጌታ ሐረገ ወይንን ስለ አቡነ ፊልጶስ ስለ ጌርጌስና ደብረ ሐቃሊትም ጠየቅናቸው፡፡ እርሳቸው የማያውቁት ነገር የለምና፡፡ ‹ወገዳን አልፋችሁ ሂዱ ሁሉንም እዚያ ታገኙታላችሁ› አሉን፡፡ እኛም መስቀላቸውን ተሳልመን ጉዟችንን ቀጠልን፡፡ የስማዳ ወረዳ ዋና ከተማ ወገዳ ስንደርስ እኩለ ቀን ነበር፡፡ እኔና ሙሉ ቀን ወደ ወረዳው ቤተ ክህነት አመራን፡፡ የወረዳው ሊቀ ካህናት በደስታ ነው የተቀበሉን፡፡ ደብዳቤያችንን ተመልከተው እርሳቸው የወረዳውን መስተዳድር ለማነጋገር ሄዱ፡፡
ከወረዳው መስተዳድር አብረውን የሚጓዙ ሁለት ፖሊሶችን ማስፈቀዳቸውንና ነገ በጠዋት ብንነሣ የተሻለ መሆኑን አስታወቁን፡፡ እኛም ለረዥም መንገድ ስለተጓዝን ማረፉን ወደድነው፡፡ በከተማው የተሻለ ነው የተባለው ሆቴል ውስጥ ሃያ ብር ከፍለን አደርን፡፡ ከተማዋ በጸጥታ የተሞላች ናት፡፡ ከእኛ ሆቴል ጀርባ ግን አንድ ጅብ የሚያህል ማይክራፎን ተከፍቶ አገሩን ያተራምሰዋል፡፡ ከምሽቱ አራት ሰዓት በሁለት የእንግሊዝ የእግር ኳስ ቡድኖች መካከል የሚካሄደውን እግር ኳስ እያስተዋወቀ ነው፡፡ ቦታ ሳይሞላባችሁ ግቡ ይላል፡፡ ቤቱ የኳስ ማሳያ ቤት መሆኑ ነው፡፡ ወደ አምስት ሰዓት ላይ እርሱም ጸጥ አለ፡፡ እኛም ተኛን፡፡

የሌሊት ጉዞ
ከሌሊቱ ዐሥር ሰዓት ተነሣን፡፡ የወረዳው ሊቀ ካህነት ከአንድ ሌላ አባት ጋር ቀድመው ደርሰዋል፡፡ አንደኛው የፖሊስ አባልም መጥቷል፡፡ አንደኛው ግን አልመጣም፡፡ በሞባይል ስልኩ ሲደወል ዝግ ነው ይላል፡፡ ለሠላሳ ደቂቃ ያህል ጠበቅነው፡፡ ምንም ነገር ስለ እርሱ ማወቅ አልቻልንም፡፡ በመጨረሻ አንደኛውን ፖሊስ ብቻ ይዘን በፒክ አፕ መኪናችን ጉዞ ጀመርን፡፡ የወገዳን ከተማ ለቅቀን አሥር ኪሎ ሜትር ያህል እንደሄድን መኪናዋ ማቃሰት ጀመረች፡፡ 


ፀሐይ በስማዳ ተራሮች ብቅ ስትል
መንገዱ ድንጋዮች ወጣ ወጣ ብለው የተቀመጡበት እንጂ መንገድ ሆኖ የተሠራ አይመስልም፡፡ ከጎማዋ ቁመት የማይተናነስ ድንጋይ መሐል ላይ ቁጭ ብሎ ‹እስኪ የምታደርጉትን አያለሁ› ይላል፡፡ ከዚያ በላይ ደግሞ መንገዱ ተራራማ ነው፡፡ 

ውጭ- አልወጣም
ድንበሩ ሂጅ ይላል መኪናዋ ‹እንዴት አድርጌ› ትላለች፡፡ እኛ እንጨነቃለን፡፡ በዚህ መሐል የቀረው ፖሊስ ደወለ፡፡ ‹በእግሬ እየመጣሁ ነው ጠብቁኝ› አለ፡፡ ‹ባትልስ የት ይደረሳል› እያልን፣ መኪናችንንም እየገፋን ጠበቅነው፡፡ እውነትም ቆፍጣና ፖሊስ ነው ሮጦ ደረሰብን፡፡ እንደደረሰ ‹እንዴት ይቺን መኪና ይዛችሁ ትመጣላችሁ› ብሎ ሊውጠን ደረሰ፡፡ ‹ዕራቁቱን ለተወለደ ልጅ ደበሎ መቼ አነሰው› አለ የሀገሬ ሰው፡፡

ሂጂ- አልሄድም
መኪናዋ ስንገፋት፣ ስትገፋን ጥቂት ከሄደች በኋላ ‹ከዚህ በላይ በምንም ዓይነት አልንቀሳቀስም› አለች፡፡ ብንገፋት፣ ብንጎረጉራት ወይ ፍንክች፡፡ ሁላችንም በየድንጋያችን ተቀመጥን፡፡ ምን እናድርግ? እንሂድ ወይስ እንቅር? ያንን ሁሉ ለፍተን ጫፍ ላይ ስንደርስ ልንሸነፍ ? ምንስ አማራጭ አለን ?
 (ይቀጥላል)

ውሸት! ውሸት! ውሸት! ውሸት! ውሸት!

Monday, February 18th, 2013

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

የዋሾ መንግስት ጩኸት

ሰሞኑን ወያኔ የተለመደ የውሸት ድራማ ሰርቶ፤ ሲሞን በረከት በሚባል፤ የማያምር፤ የማያፍር የኤርትራ ሰው፤ ጭራሹን አማራ ነኝ ብሎ እንዲያታልል ወያኔ የቀጠረው ባእድ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር፤ የሀሰት ፊልም ደራሲና የበላይ አዘጋጅ የሆነ ሰው፤ ሰርቶ ጨርሶ ያሳለፈውን "ጂሀዳዊ ሀረካት" በሚል ርእስ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ከሚያደርገው ነገር የተለየ ባይሆንም፤ ቀጣይ የማናደድ ስራቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አቅርበው ነበር።

ሙሉውን አስነብበኝ ...

ውሸት!ውሸት!ውሸት!ውሸት!ውሸት!

Monday, February 18th, 2013

ሉሉ ከበደ (ጋዜጠኛና ደራሲ)

የዋሾ መንግስት ጩኸት                           

ሰሞኑን ወያኔ የተለመደ የውሸት ድራማ ሰርቶ፤ ሲሞን በረከት በሚባል፤ የማያምር፤ የማያፍር የኤርትራ ሰው፤ ጭራሹን አማራ ነኝ ብሎ እንዲያታልል ወያኔ የቀጠረው ባእድ የፕሮፓጋንዳ ሚኒስቴር፤ የሀሰት ፊልም ደራሲና የበላይ አዘጋጅ የሆነ ሰው፤ ሰርቶ ጨርሶ ያሳለፈውን “ጂሀዳዊ ሀረካት” በሚል ርእስ ባለፉት ሀያ ሁለት አመታት ከሚያደርገው ነገር የተለየ ባይሆንም፤ ቀጣይ የማናደድ ስራቸውን ለኢትዮጵያ ህዝብ አቅርበው ነበር። እንደድሮው አረፍተነገርና የስእል እንቅስቃሴ እየበጣጠሱ፤ ቆርጠው እየቀጣጠሉ፡ እየገጣጠሙ፤ ውሸት እየደራረቱ፤ ለራሳቸው ያሳምናል ብለው እንደመሰላቸው ለኢትዮጵያ ህዝብም ይመስለዋል ብለው በታመመ አእምሮ ስለሚኢያስቡ ለቀውታል።

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 17, 2013

Sunday, February 17th, 2013
News, Radio Magazine or Mestawot

Amharic News 1800 UTC – ፌብሩወሪ 16, 2013

Saturday, February 16th, 2013
News, Call-in show or special interviews and Ye Musica Qana

ክርስቲያኑ ኢትዮጵያዊ መብቱን ለማስከበር ያልቻለባቸውና የማይችልባቸው ምክንያቶች

Friday, February 15th, 2013

  • ይህ ጽሑፍ የአቅማቸውን ጥቂት ነገር ለማድረግ የሚተጉትን ላይመለከት ይችላል።
(ደጀ ሰላም የካቲት 8/2005፤ ፌብሩዋሪ 15/2012/ PDF)፦ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአገራችን በኢትዮጵያ እየተስፋፋ በመጣው እምነትን በነጻ የማራመድ መብት ገፈፋ ዋነኛ ተጠቂ ከሆኑት ኢትዮጵያውያን መካከል ኦርቶዶክሱ ክፍል ዋነኛ ተጠቃሽ ነው። በወታደራዊው የደርግ ዘመን የነበረውን ግፍና መከራ እንኳን ለጊዜው ብናቆየው “የሕዝብ ብሶት ወለደኝ” ያለው የኢሕአዴግ መንግሥት ከተመሠረተ ወዲህ ቤተ ክርስቲያናችን በዓይነ ቁራኛ ከመታየት እስከ የ“ነፍጠኛ ጎሬ” እስከመባል ድረስ ብዙ ዘለፋ አስተናግዳለች። ከዚያም ገፋ ሲል በአንዳንድ አክራሪዎች ምእመናኗ ታርደዋል፣ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ ከየአካባቢው እንዲፈናቀሉ ተደርገዋል። ለዚህም በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲ የሚያራምደው ፖሊሲ ሁነኛ ምክንያት ነው።


ከዚህ በፊት የተቻኮለ የፓትርያርክ ምርጫ፣የገበያ ግርግር …’ ይሆናል በሚል ርዕስ ነሐሴ 11/2004 ዓ.ም፤ ኦገስት 17/ 2012/ባቀረብነው ጽሑፍ ላይ እንዳተትነው ኢሕአዴግ ገና በትግል ላይ ከነበረበት ዘመን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያናችንን በተመለከተ የያዘው አቋም “ቤተ ክርስቲያኒቱ የጠላት ወገን” እንደሆነች ያስቀመጠ፣ ሌሎች እምነቶችን በተለይም እስልምናን “በተጨቋኝነት” የፈረጀ ስለዚህም ይህንን የተጨቆነ እምነት “በማነቃቃትና ኃይል በመስጠት” ከኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ጋር እንዲገዳደር ያለመ፣ በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያኒቱን ቀስ በቀስ በማዳከም የእርሱ አሽከር እንድትሆን በማድረግ ላይ ያተኮረ ነበር። ይህንን ዓላማውን ለማስፈጸምም ከዋናው የቤተ ክህነቱ አስተዳደር የተለየና የፓርቲውን ዓላማ የሚያራምድ ቤተ ክህነት ለመመስረት በመወሰን የረዥም ጊዜ ዓላማና ግብ ይዞ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። (አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ በፊት በትግራይ ፓርቲውን በፓርቲው የሚመራ ሁለተኛ ቤተ ክህነት አቋቁሞ እንደነበር ይታወሳል)።፡የራሱን አባላትም ወደ ታላላቅ ገዳማት በማስገባት በመነኮሳት ስም ዓላማውን እንዲያስፋፉ ሲያደርግ እንደቆየ የፓርቲው መሥራች ዶ/ር አረጋዊ በርሄ በመጽሐፋቸው አስፋፍተው ገልጸዋል።

ይህ መጽሐፍ ያተታቸው ብዙ ሐሳቦች አሁን በተግባር ላይ መዋላቸው በተግባር እየታየ ያለ እውነታ እንጂ መላምታዊ ሐቲት ወይም በአንድ ወቅት ብቅ ብሎ የጠፋ የፓርቲው ሐሳብ እንዳልሆነ ግልጽ ነው። በመነኮሳት ስም ያደራጃቸው አባላቱም በቤተ ክህነቱ የተለያዩ እርከኖች ላይ በመቀመጥ ቤተ ክርስቲያናችን የክርስቶስ ሳይሆን የአንድ የፖለቲካ ፓርቲ ዓላማ ማስፈጸሚያ እንድትሆን አስገድደዋታል። ወታደራዊው መንግሥት እንኳን ያላደረገውን የቤተ ክህነቱን መዋቅር ከዋናው እስከ አጥቢያው ካባ በለበሱ ካድሬዎች በማደራጀት ቤተ ክርስቲያኒቱ የክርስቶስ መንግሥት ሳይሆን የኢሕአዴግ መንግሥት አገልጋይ እንድትሆን አድርገዋታል።

ይህም ሳያንስ በልማትና በዕድገት ስም የቤተ ክርስቲያኒቱ ይዞታ ከመደፈሩም ባሻገር የገዳማት ርዕስ የሆነውን የዋልድባን ድንበር በመጋፋት እና የቅድስና ኑሮውን በመግሰስ አበው ገዳማውያን የመከራ ኑሮ እንዲኖሩ በማስገደድ ላይ ይገኛል። ታዲያ እዚህ ላይ ተያይዞ አብሮ የሚነሣው ነገር “ሃይማኖቱን የሚወደው፣ ለእምነቱና ለማተቡ ሟች የሆነው ክርስቲያን ሕዝብ እንዴት ዝም አለ? መንግሥትስ እንዴት የሕዝቡን ስሜት ከቁብ ሳይቆጥረው ቀረ? ሕዝቡንስ እንዴት እንዲህ ሊንቀው ቻለ? ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ‘ድምጻችን ይሰማ’ ሲሉ የክርስቲያኑ ዝምታ ከምን የመነጨ ነው?” ወዘተ የሚለው ጥያቄ ነው።

እንደ እኛ እምነት ከዚህ የበለጠ መከራና ችግር በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ቢወርድም አብዛኛው ክርስቲያኑ ሕዝብ፣ ካህናቱ እና ሲኖዶሱ ምንም ዓይነት የተቃውሞ ድምጽ ሊያሰሙ አይችሉም። የሚቃወሙ ጥቂት ድምጾች ከተገኙም በርግጠኝነት በውጪ አገር ካለው ክርስቲያን፣ ካህን ወይም ጳጳስ ብቻ ሊሆን ይችላል። እነርሱም ምንም ችግር እንደማይገጥማቸው እርግጠኛ ከሆኑ ብቻ ነው። የሩቁን ጊዜ ብንተወውና አሁን በመደረግ ላይ ያሉትን ሁለት የመብት ጥሰቶች ማለትም የዋልድባን ገዳም ማረስ እና ከሕዝቡ ይሁንታ ውጪ 6ኛ ፓትርያርክ ለመሾም (ለማስቀመጥ) የሚደረገውን ሩጫ እንኳን ለመቃወም ክርስቲያኑ ለምን እንዳልቻለ መጠየቅ እንችላለን። (የተቃወሙና የሚቃወሙ ጥቂት ድምጾች ቢኖሩም እነርሱም ከውጪ አገር የሚሰሙ ብቻ መሆናቸውን ሳንዘነጋ ነው ታዲያ)። ስለዚህም የዚህ ዝምታ ምንጩ የተለያየ ቢሆንም ለመወያያ እንዲሆኑ የሚከተሉትን ሐሳቦች እናቀርባለን።


  1. መብት የሚለውን ቁምነገር በትክክል አለመረዳት፤

ክርስቲያኑ ክፍል እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሁሉ “መብት” የሚለውን ቁምነገር በቅጡ ገና አልተረዳም። መብት ጠመንጃ በያዙ ሰዎች ችሮታ የሚታደለው እንደሆነ እንጂ ከእግዚአብሔር ያገኘው ነጻ ሥጦታ መሆኑን አይገነዘብም። ፊደል ያልቆጠረው ማይም ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ኮሌጅ የበጠሰው ምሩቅም ቢሆን ተመሳሳይ ሐሳብ የሚያራምድ ሕዝብ ነው። ስለዚህም መንግሥት የሚያደርስበትን የመብት ገፈፋ ሲችል በመለመን፣ ሳይችል ደግሞ ጀርባውን አጉብጦ በመታገስ ወደመቃብር ይወርዳል እንጂ “መብቴ” ብሎ አይጠይቅም።

አንድነት የለውም፤
ከሌላ እምነት ተከታይ ኢትዮጵያውያን በተለየ ክርስቲያኑ ክፍል የተጎዳው አንድነት በማጣቱ ነው። ከሊቃነ ጳጳሳት ጀምሮ እስከ ጥቃቅን ማኅበራት ድረስ አንድነት የሚባል ነገር የለም። ጳጳሳቱ ተከፋፍለው ሁለት ሲኖዶስ አቋቁመናል ብለው ከሚነታረኩ ባሻገር ከእነርሱ በታች ያለውም እዚህ ግባ በማይባል በተለያየ ምክንያት የተከፋፈለ ነው። ይህንን ክፍፍል አንድ ሊያደርግ የሚችል ተአምር ካልተፈጠረ በስተቀር ሊያሰጋው የሚችል ተቃውሞ ሊመጣ እንደማይችል ኢሕአዴግም ጠንቅቆ ያውቃል። ስለዚህ ሕዝቡ ብዙ ቢሆንም፣ ምእመኑን ለእምነቱ ሟች ቢሆንም አንድነት እስከሌለው ድረስ ኃይሉ ከንቱ ይሆናል። ሆኗልም። ሙስሊሙ ሕብረተሰብ ከዚህ የተሻለ አንድነት አለው፤ ይህንንም አንድነቱን በዚህ አንድ ዓመት ባሳየው እልህ አስቆጨራሽ የመብት ትግል በገሃድ አሳይቷል። ፕሮቴስታንቱ ክፍል ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ የመንግሥት ቀኝ እጅ በመሆን በማገልገል ላይ በመገኘቱ የሥርዓቱ ዋነኛ ተጠቃሚና የሥርዓቱ ዋነኛ ደጋፊ ሆኗል።

ትክክለኛ መረጃ የለውም፣
ክርስቲያኑ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ኢትዮጵያዊው ትልቅ የመረጃ እጥረት አለበት። መንግሥት የመገናኛ ብዙኃንን በሙሉ በግል አፍኖ በመያዙ ሕዝቡ የሚያየውም የሚሰማው ነገር የለም። ጋዜጦችና መጽሔቶች አሉ ከሚባሉ ጠፍተዋል የሚለው ይገልጻቸዋል። ያሉትም ቢሆን ውኃ ውኃ የማይል ጽሑፍ ከማንሸራሸር ውጪ መረጃ በመፈንጠቅ ሕዝቡን ከጨለማ ወደ ብርሃን ሊያመጡ የሚችሉ አይደሉም። አገልግሎት እንዲሰጡ የተፈቀደላቸው ሬዲዮኖች “ስፖርት፣ ሙዚቃ፣ ቫለንታይንስ ዴይ አደጋገስ” ወዘተ ካልሆነ ጠለቅ ያለ ሐሳብ ማቅረብ አይችሉም። አይፈረድባቸውም። የተለየ መረጃ ሊገኝበት የሚችለው ነጻ መስኮት (ኢንተርኔቱ) ደግሞ ተቆልፏል። ስለዚህ ይህ መረጃ በማጣት የታወረ ኅብረተሰብ ምኑን ከምኑ ሊያደርገው ይችላል?

“እግዚአብሔር ያውቃል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ” በሚሉ ርዕሶች ዙሪያ ያለው የተሳሳተ የጽድቅ እና የኃጢአት ትምህርት፣
አብዛኛው ክርስቲያን  እምነቱን አፍቃሪና አክባሪ ነው። መምህራኑን ይሰማል፣ ቃላቸውንም ይፈጽማል። ነገር ግን ከሚሰጡት ትምህርቶች አብዛኛዎቹ ሆን ተብሎም ይሁን በሌላ ምክንያት ሕዝቡን የሚያደነዝዙ፣ የጥንት ኦርቶዶክስ አባቶቹ እንዳደረጉት ለአገሩ፣ ለእምነቱና ለቤተሰቡ ከመሞት ይልቅ በቅኝ ግዛት እንደተያዙት ሌሎች አፍሪካውያን መጽሐፍ ቅዱሱን ገልጦ ሰማይ ሰማይ ብቻ የሚያይ ደካማ አድርገውታል። አባቶቹ አድዋ ላይ ታቦቱን ይዘው እንዳልውጡ፣ ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ሰዉንም ምድሪቱንም ለፋሺስቶች እንዳይገዙ ገዝተው እንዳልተሰዉ፣ ብዙዎቹ አበው ለአገራቸውና ለእምነታቸው ደማቸውን እንዳላፈሰሱ አይነገረውም። ስለዚህም በስመ ኦርቶዶክስ የሚመራው ክርስትና ከጥንቱ “አትንኩኝ ባይ” ኦርቶዶክስ ጋር ምንም ግንኙነት ያለው አይደለም።

የተሳሳተ ትርጉም እየተሰጣቸው ሕዝቡ እንዲደነዝዝባቸው ከሚያደርጉት ትምህርቶች መካከል “ሁሉንም ለእግዚአብሔር እንስጠው፣ “እግዚአብሔር ያውቃል፣ እኛ የእርሱን ጊዜ እንጠብቅ” የምትል የራስን ኃላፊነት ሳይወጡ በስንፍና የመቀመጥ አደንዛዥ ትምህርት አንዷ ናት። እግዚአብሔርማ ሁሉን ያውቃል። ምን ጥርጥር አለው። ነገር ግን አዋቂነቱ በዓለም ላይ የሚፈጸመውን ግፍና መከራ ሁሉ እንዲከወን እንደፈቀደ መቁጠር ኑፋቄ ነው።

በዓለም ላይ በየሰከንዱ ብዙ ወንጀሎች ይፈጸማሉ። ያ ሁሉ ወንጀልና ሰቆቃ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውን? በርግጠኝነት አይደለም!!! እግዚአብሔር ያውቀዋል ግን? እንዴታ!! እግዚአብሔር የማያውቀው ምን ነገር አለ? የሰው ልጅ ግን በነጻ ፈቃዱ የሚፈጽመው ወንጀል ነው። ለዚህ ጥፋቱ ደግሞ በእግዚአብሔር ፊት ሲቆም ቅጣቱን ያገኝበታል።

ከዚሁ አያይዘን ስንመለከተው በቤተ ክርስቲያናችን እና በአገራችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እግዚአብሔር ያውቀዋል። ታዲያ ለምን ዝም አለ ለሚል ግብዝ መልሱ ሰዎች በነጻ ፈቃዳቸው ተጠቅመው ያደረጉት ነገር ነው የሚል ነው። ክፉዎቹ በክፋታቸው ተገፋፍተው ይህንን ሲያደርጉ እኛስ በመልካምነታችን ተጠቅመን የአቅማችንን ለማድረግ ያልቻልነው ለምንድር ነው?

ከመጽሐፍ አንድ ምሳሌ እናንሣ። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልአዛርን ከሞት ሊያሥነሣው በሄደ ጊዜ የተፈጸመውን ማወቃችን ከላይ ለመግለጽ የፈለግነውን ሐሳብ ግልጽ ያደርገዋል። ታሪኩ በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 11 ላይ ይገኛል። አልአዛር ታመመ፣ ሞተ፣ ተቀበረ። ከተቀበረ ከአራት ቀን በኋላ ጌታ ወደዚያ ሥፍራ ሄደ። ከዚያም ከመቃብሩ ላይ ድንጋዩን አንሱ ብሎ ቤተሰቦቹን አዘዘ። ከዚያም አልአዛርን ከመቃብር አልጋ ከሞት ሸለብታ ቀስቅሶ ሕያው አደረገው። ከሞት ማሥነሣቱ ካልቀረ ድንጋዩን እንዲያነሱ ለምን አዘዛቸው? ለምን ሁሉንም ነገር ራሱ አልፈጸመውም? በዚህ የአልአዛር ድኅነት ውስጥ የሰው ድርሻ በቤተሰቦቹ ተሰርቷል፣ የእግዚአብሔር ድርሻ ደግሞ በራሱ በባለቤቱ ተሠርቷል። የሰው ድርሻ መቃብሩን መክፈት፣ የእግዚአብሐር ድርሻ ሙቱን ሕያው ማድረግ ነው። በዘመናችን ግን እያልን ያለነው “ሁሉንም ነገር አንተ ሥራው!!!” ነው። መቃብሩን አንተው ቆፍር፣ ሙቱንም አንተው አስነሳው፤ እኛ ዝም ብለን እንመለከትሃለን።  

ሥር የሰደደ አድርባይነት መሰልጠኑ፤
ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ዘመን ከቤተ መንግሥቱ ጋር ተቀራርባ የኖረች እንደመሆኗ ሥልጣን ላላቸው ሰዎች ማጎብደድ፣ አድርባይነት እና እታይ-እታይ ባይነት ከጥንቱም ሰልጥኖብናል። በዘመናችን ደግሞ ገዝፎና ተስፋፍቶ ቀጥሏል። የጥንቶቹ መሪዎች ፓርቲ ስላልነበራቸው አባላትም አልነበሯቸውም። የአሁኖቹ መሪዎች ባለ ፓርቲ ስለሆኑ አድርባዮቹ የፓርቲዎቻቸው አባላት በመሆን መስቀልና ሽጉጥ ታጣቂ ካህናት አፍርተናል። በደርጉ ዘመን የኢሰፓ፣ በአሁኑ ደግሞ የኢሕአዴግ አባል ደባትር፣ ካህናትና መነኮሳት አያሌ ናቸው። ይህ አባልነትና አድርባይነት ከተራ ካህናት፣ ደባትርና መነኮሳት አልፎ (በዘመነ ኢሕአዴግ) ከጳጳሳቱ ደርሷል። አባል ያልሆኑትም ቢሆኑ ከዝምታ ውጪ ምንም ምርጫ የላቸውም። ስለዚህ አድርባይነቱ በቅርብ መፍትሔ ስለማያገኝ መከራችንም በቅርብ መፍትሔ ይገኝለታል ብሎ ለማሰብ ይከብዳል።

መንግሥታት በፈቃደ እግዚአብሔር ሥልጣን ይይዛል የሚለው ትምህርት፣
ከፍ ብለን ከጠቀስነው ጋር አብሮ የሚሄደው ጉዳይ መንግሥት የሆነ ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ነው ሥልጣኑን ያዘው የሚል ሐሳብና ትምህርት ነው። ቤተ ክርስቲያንን የሚሰቅላትን “እግዚአብሔር ወዶ ፈቅዶ አስቀመጠው” ማለት ድንቁርና ካልሆነ ምን ይሆናል?

ኃላፊነትን ለመቀበል መፍራት፣ ኃላፊነትን አለማወቅ፣ ኃላፊነትን ሁሉንም ለእግዚአብሔር መስጠት፣
እንደተጠቀሰው ከርስቲያኑ ራሱን አቅም እያለው አቅም እንደሌለው፣ ዕውቀት እያለው እንደሌለው ስለቆጠረ ያለበትን ኃላፊነት ለእግዚአብሔር ሰጥቶ “እርሱ ያውቃል” እያለ ተቀምጧል። ኃላፊነቱን አለመወጣቱ ስሕተት መሆኑን የሚገነዘበው ራሱ በጣም ጥቂቱ ነው። ዋልድባ ሲፈርስ፣ አበው አልታረቅ ሲሉ፣ በቆረጣ አዲስ 6ኛ ፓትርያርክ ለማስቀመጥ ሲሯሯጡ “እኔ ምን አቅም አለኝ” ብቻ ነው መልሱ። ይህም ኃላፊነትን ካለማወቅና ኃላፊነትን ለመረከብ ከመስጋት የሚመነጭ ክፉ ደዌ ነው።

ማጠቃለያ፦

በአጠቃላይ ስንመለከተው ክርስቲያኑ ክፍል አሁን ያለበት ይህ እና ሌሎች ምክንያቶችም ተጨማምረውበት ለመብቱ ለመቆም፣ ቤተ ክርስቲያኑን ለመታደግና እምነቱን ለማስከበር የሚችልበት ሁኔታ ላይ እንዳልሆነ እንገነዘባለን። በቅርብ ዓመታትም ይሻሻላል ብሎ መጠበቁ ከባድ ነው። በተአምር ካልሆነ በስተቀር አሁን ባለው የክርስቲያኑ አያያዝ ዋልድባንም ያርሱታል፣ አበውንም እንደጀመሩት በማሰር በማንገላታትና በማሰደድ ይገፉበታል፣ የራሳቸው መጠቀሚያ የሆነ 6ኛ ፓትርያርክ በመሾም ሌላ የመከራ ዘመን ያጸናሉ።

መፍትሔውስ?
መፍትሔው አጭር ነው። ከአሁኑ መሰባሰብ፣ መደራጀት፣ የችግሮቹን ትክክለኛ ምንጭ መረዳት፤ ለማያውቁት ማሳወቅ፣ ለአጭር ጊዜ ሳይሆን ለረዥም ጊዜ መፍትሔ መሥራት። ‘እዛው ሞላ እዛው ፈላ’ እንደሚባለው ተረት ቶሎ መፍትሔ በመፈለግና ለአጭር ጊዜ ሆይ ሆይ በማለት ችግሩ አይፈታም። የቤተ ክርስቲያን የሆኑትን ከአድርባዮቹ፣ ከአስመሳዮቹና ከጥቅመኞቹ ለይቶ በመረዳት የራስን ኃላፊነት መወጣት። የቀደሙት አበው ከመቃብር ተነሥተው ቢመለከቱን እንዳያፍሩብን እኛም በትውልዳችን የራሳችንን ኃላፊነት መወጣት።

ይቀጥላል!!!!

ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።