ዶ/ር ብርሃኑ ነጋን ጨምሮ አምስት ሰዎች በሞት እንዲቀጡ ተወሰነ
በታምሩ ጽጌ | The Reporter
ሕገ መንግሥቱንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓቱን በሃይልና በትጥቅ አመጽ ለመጣል ሲንቀሳቀሱ ተደርሶባቸዋል በሚል የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ አምስት ክሶችን መስርቶባቸው በሁሉም ጥፋተኛ ከተባሉ 40 ተከሳሾች መካከል መላኩ ተፈራ ጥላሁን (ከማረሚያ ቤት)፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ (በሌሉበት)፣ አንዳርጋቸው ጽጌ (በሌሉበት)፣ ሙሉነህ ኢዩኤል ፋጌ (በሌሉበት) እና መስፍን አማን (በሌሉበት) በሞት እንዲቀጡ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት በዛሬው ዕለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡
ፍርድ ቤቱ ብ/ጄ ተፈራ ማሞ እና አሳምነው ጽጌን ጨምሮ 33 ተከሳሾች በእድሜ ልክ እስራት፣ 11ኛ ተከሳሽ ሻለቃ አዱኛ አለማየሁ ገ/ማርያም እና ሻለቃ አደፍርስ አሳምነው ክብረት (17ኛ ተከሳሽ) እያንዳንዳቸው በአስር ዓመት እስራት እንዲቀጡ ወስኗል፡፡
ዐቃቤ ሕግ ንብረታቸው እንዲወረስ ጥያቄ ካቀረበባቸው ውስጥ የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ፣ አንዳርጋቸው ጽጌ፣ ጌቱ ወርቁ፣ ኮሎኔል አለሁበል አማረ እና አቶ ያረጋል ይማም ንብረት እንዲወረስ ሲወስን፣ የብ/ጄ/ ተፈራ ማሞ፣ አሳምነው ጽጌና አቶ ጽጌ ሃ/ማርያም ላይ የቀረበውን የውርስ ጥያቄ እንዳልተቀበለው ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አሳውቋል፡፡
|
|
Write a Comment
Related posts: