Ethiopian News and Opinion Journal


  • HOME
  • SUBSCRIBE
  • CONTACT
  • FORUM
  • VIDEO
  • DIRECTORY
  • ADVERTISE
  • ALBUM
  • DICTIONARY
  • CLASSIFIEDS
  • EXERCISE
  • Login

የኢትዮጵያ የነዳጅ ዘይት ፍለጋ ስምምነት

August 10th, 2007 |

ኢትዮጵያ ከአንድ ነዳጅ አውጭ ድርጅት ጋር በኦጋዴን አካባቢ የተፈጥሮ ጋዝ ማውጣት የሚያስችል የአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመች ። አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የማዕድንና የኤነርጂ ሚኒስቴር ባለስልጣን ለሮይተርስ ዜና ወኪል እንደተናገሩት ፔትሮናስ በተባለው የማሌዥያ ኩባንያና በኢትዮጵያ መካከል የተፈረመው ስምምነት ኦጋዴን ውስጥ በካሉብና በሂላል የሚገኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ማልማትና ለገበያ ማቅረብን ይመለከታል ። በሮይተርስ ዘገባ እንደተጠቀሰው የኢትዮጵያ የማዕድንና ኤነርጂ ሚኒስትር አቶ አለማየሁ ተገኑ ጨረታውን ካሸነፈው ከፔትሮናስ ኩባንያ ጋር ባለፈው ወር ማሌዥያ ዋና ከተማ ክዋላላምፑር ውስጥ ተፈራርመዋል ። በስምምነቱ መሰረት ፔትሮናስ የተፈጥሮ ጋዙን በአቅራቢያው ወደ ሚገኝ ወደብ ማስተላለፊያ ቧንባ ይዘረጋል ተብሎ ይጠበቃል ። ሮይተርስ የጠቀሳቸው ተንታኞች እንዳሉት በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ወደብ አልባ ስለሆነች የተፈጥሮ ጋዙ ምናልባትም ፑንትላንድ ወደ ሚገኘው የቦሳሶ ወደብ ወይም ደግሞ ወደ ሳማሌላንድዋ በርበራ ወደብ ነው ሊተላለፍ የሚችለው ። በኦጋዴን ክልል የሚንቀሳቀሰው የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር ኦብነግ የውጭ ነዳጅ አውጭ ኩባንያዎች ወደ አካባቢው እንዳይመጡ ከዚህ ቀደም ማስጠንቀቁ ይታወሳል ።

Source: DW

Email This Post | Add a comment FORUM



Related Posts

  1. ፍንዳታ በኦጋዴን
  2. ታላቁ የኢትዮጵያ ሩጫ ላይ ሃይሉ ሻውል ተወገዙ
  3. የኢትዮጵያ ሕዝብ ለሰጠን ኃላፊነት ብቁ ሆነን አልተገኘንም – ዶ/ር ያዕቆብ ኃ/ማርያም
  4. የሱዳን ጦር መንደር አቃጠለ፣ ኢትዮጵያውያን ታሥረው ወደ ሱዳን ተወሰዱ
  5. ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በጦርነት እየታመሰች ነው

Leave a Comment

To write your comment in Amharic click here. አስተያየትዎን በአማርኛ ለመጻፍ እዚህ ይጫኑ:: ጽፈው ከጨረሱ በኋላ የጻፉትን ኮፒ አድርገው ወደዚህ ተመልሰው አስተያየት መስጫ ቦክስ ውስጥ ፔስት ያድርጉ::



Click to cancel reply








Recent Posts
  • Ethiopian Youth Public Meeting in Dallas – Saturday, Feb. 11
  • DC area Ethiopian churches under attack
  • Saudi pressured to release detained Ethiopians
  • International Ethiopian Women Conference March 9-11
  • ALEJE and OLF Public Meeting in Washington DC – Feb. 19
  • Where the truth lies in Ethiopia
  • Transformative Reconciliation for Unity in a Nutshell
  • When we were the peacemakers
  • Cooperative Behavior for Transformatve Reconciliation & Unity
  • A resurgent Ethiopian opposition in a new form
  • African Beggars Union Hall?
  • Kilil system is an instrument of Ethiopian disenfrachisement – Part 4
  • Several Meles Zenawi bodyguards arrested
  • UN experts dismayed by growing repression in Ethiopia
  • Swedish journalists appeal to Ethiopia’s dictator
  • Another sign of worsening repression in Ethiopia – IFEX
  • Using Anti-Terror Laws to Terrorize Dissent
  • We’ve met the enemy and he is us
  • Essentials to Resolve Differences for Reconciliation
  • Ethiopian delegation delivers letter to Saudi Arabia embassy in DC


©2012 Ethiopian Review
Publisher & Editor-in-Chief: Elias Kifle
Powered by WordPress