Comments on: The Guns of Anarchy in Somalia

By: Moresh
ኢትዮጵያ፤ አሜሪካና ሶማሊያ፡ ወደር የለሽ እንክፍነት

ወደር የለሽ እንከፎች  የዳርዊን ሽልማት እንደሚሰጣቸው ሁሉ  የአገር መሪዎችም የዚህ ተመሳሳይ ሽልማት ለራሳቸው ማዘጋጀት ቢችሉ መልካም ነው። ልዩ የዳርዊን ሽልማት የሚዘጋጀው  ተወዳዳሪ ላልተገኘላቸው ደደቦች ሲሆን ዓላማውም ለሰው ልጆች የወደፊት ህይዎት ቀጣይነት በአጋጣሚ ራሳቸውን ከመኖር ምዕራፍ በመፋቅና ራሳቸውን ባለመተካት ለሚያበረክቱት ጠቃሚ ክንውን ለማስታዎሻነት ታስቦ ነው። የዚህ ዓለማቀፋዊ ሽልማት ተመሳሳይ የድክቼኒ-መለስ ሽልማት ተብሎ ሊሰዬም ይገባዋል።

ይሀን ለማለት ያስደፈረኝ ዋና ምክንያተ አለ። በአሁኑ ወቅት በአሜሪካው ም/ፕሬዚደንትና መለስ ዜናዊ የታየው አንጸባራቂ ደደብነት  የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሁለት ዓመት ወረራ በኋላ ሶማሊያን ሊያጠፏቸው ለነበረው የሶማሊያ ሽምቅ ተዋጊዎች አገሪቱን አስረክበው ለመውጣት ዝግጅት እያደረጉ ባሉበት ወቅት የሁለቱ ሰዎች የአመራር ንዝህላልነት በግልጽ ሰሞኑን ለዕይታ በመቅረቡ ነው። ብልሹ ተምሳሌቶች ያስፈልጉን ይሆናል፤ ሆኖም ግን ከነዚህ ሁለት ጥንዶች የተሻለ የሚጠይቅ ያለ አይመስለኝም።

ኢትዮጵያ ሶማሊያን እንድትወር ሃሳቡ የፈለቀው ከድክቼኒ ለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ ይሳነኛል። ሆኖም ግን ወረራው ያልተጤነ፤ ግንፍልተኛና በስህተት ጤነኛውን ጥርስ የነቀለ ስልት በመሆኑ ዕቅዱ ድክቼኒ ድክቼኒ ይሸታል።

መለስ ዜናዊን በተመለከተ ዘመናችን ካፈራቻቸው  ቀንደኛ ደደቦች አንዱ መሆኑን በአፍሪካ ታሪክ  አቻ የማይገኝለት የድንበር ጦርነት በማካሄድ ማንነቱን አስመስክሯል። ከመነሻው ግን ስህተቱ የሱ አይመስልም ነበር፤. ኢትዮጵያ ባልታሰበ ሁኔታ በዕብደቱና በጠብ አጫሪነቱ ዝናን ባተረፈው የኤርትራ መንግስት ተወራለች ይሁንና የኢትዮጵያ ወታደሮች ወራሪዎቹን ወደመጡበት መልሰዋቸዋል። የተኩስ አቁም ስምምነቱ አንደተፈረመ በ 2000 ዓም አጋማሽ ላይ ኢትዮጵያ በጦርነቱ አጥታ የነበረውን የመሬት ይዞታ ሙሉ በሙሉ አስመልሳለች።

በሁለቱም አገሮች ስምምነት የተሰየመው ዓለማቀፉ የድንበር ኮሚሽን ኤርትራን ወረራውን በመፈጸሟ ጥፋተኛ አድርጓታል። ሌላው አወዛጋቢ የነበረውን የድንበር ወሰን በመከለል ኢትዮጵያ ይገባኛል ስትል የጠየቀችውን አብዛኛውን ቦታ እንድታገኝ ተደርጓል። ሁለቱ  ተፋላሚዎች ለኮሚሽኑ ውሳኔ ተገዥነታቸውን ካረጋገጡ በኋላ መለስ ዜናዊ ከስምምነቱ አፈነገጠ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከኤርትራ ጋር ሌላ የድንበር ግጭትና ጦርነት ለማስነሳት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከኤርትራ ጋር እንደገና ጦርነት መጀመር የተባበሩት መንግስታትን ስምምነት መጣስ ይሆናል። ስለሆነም መለስ ከተባበሩት መንግስታት ነቀፌታ ሊታደገው የሚችል አንድ ሃያል መንግስት እርዳታ እንደሚያስፈልገው ጠንቅቆ ያውቃል። ለዚህ ተግባር ደግሞ በቡሽ አስተዳደር የተባበሩት መንግስታትን ሚና ያንኳሰሰ ከአሜሪካ የተሻለ አገር የት ሊገኝ ይችላል? ከዚህ ቀጥሎ የሚነሳው ጥያቄ ደግሞ መለስ ለቡሽ አጸፋውን እንዴት ሊመልስ ይችላል? የሚለው ነው።

አዎ፣ መለስ ሶማሊያን ሊወር ይችላል። የዋሽንግተን አስተዳደር የአሜሪካን ወታደሮች ሁለተኛ ሶማሊያ ውስጥ ማስገባት አያስበውም። ምክንያቱም በ 1993ቱ ጦርነት የደረሰበትን ሽንፈት ያስታውሰዋል፤ ይሁን እንጅ በደቡባዊ ሶማሊያ እያየለና ሰላም እያስከበረ የመጣውን ህዝባዊ መንግስት አጥፍቶ የአሜሪካ ቡራኬ የተሰጠውን ነፍጠኛ አስተዳደር በምትኩ ስልጣን ኮርቻ ላይ ለማፈናጠጥ ተፈለገ። ይህን ደግሞ የኢትዮጵያ ወታደሮች በአግባቡ ሊፈጽሙት ይችላሉ።

ድክቼኒ ይህን ስምምነት እንደፈጸመ የተሰማውን ልባዊ ደስታ በፊቱ ላይ ሲነበብ አይቸዋለሁ። ይህ በጣም እየረቀቀ ለመጣው የጅኦፖሊቲካዊ ክስተት ተጨማሪ ድል ነው። መለስ ይህን በተመለከተ የተሰማውን ከፊቱ ማንበብ ይቸግረኛል ምናልባት እሱም በስክምምነቱ ስኬት ፈገግ ያለ ይመስለኛል።

ከፊት ለፊት የተደቀነው ስራ በሶማሊያ ህይዎትን አስቸጋሪ ያደረገውን ዘረፋና አፈና ለማስወገድ በሞቃድሾ ንግድ ህብረተሰብ በመታገዝ የተቋቋመውን የዩኒየን ኦፍ እስላሚክ ኮርትን ህዝባዊ መንግስት ማፍረስ ነው።   የዩኒየን ኦፍ ስላሚክ ኮርትስ የመላውን የሶማሊያ ዜጎች ፍላጎት በማስከበር አገሪቱን ለ15 ዓመታት ሲንጣት የነበረውን ብጥብጥ አስዎግደው በአብዛኛው ደቡባዊ ሶማሊያ ሰላም እንድሰፍን አድርገዋል።

የሚያሳዝነው ኮርቶች “እስላማዊ” ስለሆኑ የሸሪያን ህግ በተግባር ማዋል ፈለጉ፤ ይህም በዋሽንግተን መዝገብ አሸባሪ ተብለው እንድፈረጁ አድርጓቸዋል። በርግጥ እንደ አል-ሻባብ ያሉ የተወሰኑ አክራሪ ድርጅቶች በኮርቶች ውስጥ ተካተዋል። ሆኖም ግን ለሞቃድሾ ኗሪዎች የመጀመሪያውን እውነተኛ ሰላምና ፍትህ የተስፋ ጮራ ፈንጥቀዋል። ስለሆነም እንድጠፉ መሞከር አልነበረበትም።

የኢትዮጵያ ጦር በታህሳስ 2006 ዓም ሶማሊያን ወረረ፤ የኢስላሚክ ኮርቶችንም በአጭር ጊዜ ጠራርጎ ከሞቃድሾ አባረረ። በምትካቸውም አብዱላሂ ዩሱፍን የሽግግሩ መንግስት ጊዚያዊ ፕሬዚደንት አድርጎ ሾመ። በርግጥ አብዱላሂ ስልጣን ያዘ ማለት አያስደፍርም ምክንያቱም የሞቃድሾ ኗሪዎችና ሚሊሻዎች ወዲያውኑ መጥሌዎቹን የኢትዮጵያ ወታደሮች ማጥቃት በመጀመራቸው መቆጣጠር የቻሉት በጠመንጃቸው አፈሙዝ ርቀት ላይ ብቻ ያሉ ቦታዎችን ነበር። አብዱላሂ ዩሱፍን በተመለከተ  የተቆጣጠረው ነገር ቢኖር የተወሰኑ የመኖሪያ ክፍሎችና ከነዚህም ጋር የተገጠሙትን የስልክ አገልግሎቶች ብቻ ነው።

አብዱላሂ ዩሱፍ የሽግግሩ መንግስት ፕሬዚደንት ሆኖ የተመረጠው የሶማሊያ ነፍጠኞች ፓርላሜንት የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው በኬንያ አገር በተካሄደው የ2004 ዓም ስብሰባ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስን ሙሉ ድጋፍ አግኝቷል። በኢትዮጵያ ወታደሮች ባይታገዝና የዩናይትድ ስቴትስን ድጋፍ ባያገኝ ኖሮ እግሩ ሞቃድሾን ለመርገጥ ዕድል አያገኝም ነበር። ኣብዱላሂ ይህንን ዕርዳታ በመቀበሉ በሶማሊዎች ዓይን በከፍተኛ ጥርጣሬ እንድታይ አድርጎታል።

በአለፉት ሁለት ዓመታት የሶማሊያ አርበኞች የኢትዮጵያን ጦር ከአብዛኛው የደቡብ ሶማሊያ ጠራርጎ አስወጥቷል፤ ሰሞኑን ደግሞ ጠቅሎ ወደአገሩ ሊመለስ ነው። አብዱላሂም ቢሆን መልቀቅ ሊኖርበት ነው ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ወታደሮችና ከአሜሪካ በስተቀር ሌላ ድጋፍ የለውም። ይህ ክስተት በሚገርም ሁኔታ ሞቃድሾን ለመቆጣጠር ያስቻለው የኢስላሚክ ኮርቶችን ሳይሆን በትግሉ ወቅት ያገለሏቸውን አክራሪ ሚሊሻዎችን ነው።

መለስ በሶማሊያ ጦርነት የተዘፈቀበት ሁኔታ የቡሽ አስተዳደር የኢራንን ሁለት ታላልቅ ጠላቶች ማለትም ሳዳም ሁሴንና ታሊባኖችን  ለማጥፋት ከወሰደው ርምጃ ጋር በቅርብ ይመሳሰላል። ኢትዮጵያና አሜሪካ አላስፈላጊ ባልነበረ የሶማሊያ ጦርነት መዘፈቃቸው ብቻ አይደለም፤ እጂግ ጋጠወጥና አደገኛ ለሆኑ አክራሪዎች በሶማሊያ የስልጣን መወጣጫ መንገዱን መጥረጋቸው ነው፡፡

ተወዳዳሪ ለማይገኝለት እንከፍ የፖለቲካ ስልት ማስታዎሻ ይሆን ዘንድ ዓለም የቼኒ-ዜናዊ ሽልማት ማዘጋጀት ይኖርባታል። በርግጠኝነት ለዚህ የክብር ሽልማት የመጀመሪያው ዕጩ ማን እንደሚሆን ጠንቅቄ አውቃለሁ።

Translated by Moresh

ምንጭ፡

Posted By Gwynne Dyer

http://www.woodstocksentinelreview.com/ArticleDisplay.aspx?e=1354333

ታህሳስ 20 ቀን 2008