Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 31163
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 09 May 2024, 14:47

ከዚህ ቀደም አንድ ሰው ወይም አንድ ሕዝብ ችግር መፍታት የሚያቅተው ለምንድን ነው ብዬ ነበር ። መልሱ ይህ ነው ።

ችግር የምንለው ቃል አንድ የሆነ የአለም ምስል ማለት ነው ። ችግር የምንለው ነገር አንድ አለምን በትክክል የማየትና አንድ ተግባርን በትክክል ለማድረግ አለመቻል ነው ።
ይህ የሚሆነው አለምን (ሪያሊቲን) የሳልንበት ምስል ስሀተት ስለሆነ ነው ። ስለ አለም ያለን ባንጎላችን ውስጥ የሰራነው ፎቶ የተሳሳተ ስለሆነ ነው ። ስለዚህ ትክክልለኛ የሪያሊቲ ሞዴል ባይምሮአቸው ውስጥ የሌላቸው ሰዎች ትክክለኛ ሃሳብ የሌላቸው ናቸው።

ስለዚህ አንድን ችግር መፍታት ያቃተው ሰው ወይም አገር ስለ ችግሩ የተሳሳተ ሃሳብ (ምስል) ያለው ወይም ስለ ችግሩ ምንም ሃሳብ (ምስል) የሌላው ሲሆን ነው ። በሌላ አነጋገር የተሳሳተ አይምሮ ያለው ሰው ማለት ነው። አይምሮ ከምስል የተሰራ ሞዴል ነው ። በአንድ የተሳሳተ ሞዴል አማካይነት አንድን ትክክለኛ ተግባር መስራት አይቻልም።

አንድን ችግር ለመፍታት ትክክለኛ ሞዴልና አይምሮ፣ ትክክለኛ ሃሳብ ምን እንደ ሆነ ማግኘት አለብን ።

የቃላት ስራ ይህን ትክክለኛ ሃሳብ መፍጠር ነው ። ሃሳብ ምስል ነው ። ምስል የሚፈጠረው በቃላት ነው። ስለ አንደ ነገር ትክክለኛ ቃል ካገኘንለት ያ ነገር እንደ ተፈጠረ መቁጠር አለብን ። በመጀመሪያ ቃል ነበረ ። ቃልም አለም ሆነ፣ ቃል ተግባር ሆነ የምንለው ለዚህ ነው ።

ለምሳሌ ጎሳ ፣ ዘር፣ ዘውግ፣ ብሄር ፣ ወገን፣ ብሄረ ሰብ፣ ቡዲን ፣ ፓርቲ የሚባሉት ቃላት አገር መግምቢያ ቃላት አይደሉም! የአገር ሞዴል ፣ የፖለቲካ ስርዓት ሞዴል መስሪያ ቃላት አይደሉም ። አይምሮ የተሰራው በቃላት ነው! በተሳሳተ አይምሮ ችግር አይፈታም ።

በተቃራኔ አገር ማቆሚያ ቃላት ግለሰብ፣ ሕዝብ፣ መንግስት፣ ሕግ፣ ፍትህ፣ መብት፣ ነጻነት፣ ዴሞክራሲ፣ እኩልነት፣ እውነት፣ ትብብር፣ መረዳዳት፣ ሕብረት የመሳሰሉት ናቸው።

የኢትዮጵያ ችግር የሃሳብ ችግር ነው ። የኢትዮጵያ ችግር ያይምሮ ችግር ነው ።

Horus
Senior Member+
Posts: 31163
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 11 May 2024, 15:19

ልሂቅ ታላቅ ማለት ነው። ልሂቃን ታላቆች ማለት ነው ። አንድ ሰው ልሂቅ የሚባለው ሊቅ ሲሆን ነው፤ በአንድ ነገር ሊቅ፣ የላቀ፣ ታላቅ ሲሆን ነው።

ኢትዮጵያዊ የሚባሉ ሕዝቦች ከድህነት እስከ ረሃብ፣ ከድንቁርና እስከ ጥንቆላ፣ ከፍርሃት እስከ ድብርት፣ ከጥላታ እስከ አስከፊ ጦርነት፣ ከልዩነት እስከ ዘር ማጥፋት፣ ከሌብነት እስከ አረመኔ ዝርፊያ፣ ከስንፍና እስከ ልመና፣ በእልፍ አአላፍ ችግሮች፣ መከራና ሰቆቃዎች ተደፍቀው፣ ማያ ዐይን አጥተው፣ ማሰቢያ አንጎል ፣ማስተዋያ አይምሮ ተነፍገው አላንዳች አላማና ብሄራዊ ፣ሕዝባዊ ፋይዳ እንደ ዱር እንሰሳ በሚታመሱባት አሳዛኝዋ ኢትዮጵያ እዚም እዛም ራሳቸውን ልሂቃን የሚሉ ሰዎችን ስንሰማ ማፈር አይደልም መሳቀቅ ይገባናል ።

በእውቀትና ጥበብ ዕጦት ሳቢያ በምንም ነገር ላይ ሊቅ (ኤክስፐርት) ያልሆኑ ፣ ምንም አይነት ችግር የማይፈቱ ፣ የሰርተፊኬት ታፔላ የተለጠፈላቸው ኢምሁራን ፣ ኢልሂቃን እውቀት አልባዎችና ጥበብ የለሾችን ልሂቃን እያልን ስለ ልህቀትና ታላቅነት በመስበክ እራሳችንን ባናታልል ይበልጥ በሌሎች ዘንድ ያስከብረናል ።

በኢትዮጵያ ሊሂቃን የሉም!

የኢትዮጵያ ችግር ደሞ ያ ነው!

Horus
Senior Member+
Posts: 31163
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 16 May 2024, 14:15

ሃተታ ቢበዛ በአህያ አይጫንም ። የጎሳ ትርክትና ተረት እንደ አገር ማደራጃ ሃሳብ ለ30 አመት ተወቅጦ ተወቅጦ ይህው ኢትዮጵያ የአለም መሳቂያ መሳለቂያ አድርጓታል ። የጎሳ ትርክትና ተረት አገር አያደራጅም፣ ኢኮኖሚ አይገነባም ፣ ከተማ አይቀይስም፣ ስልጣኔን አይጸንስም ። የጎሳን ትርክትና ተረት የተጋቱት ጎሳዎች እራሳቸው እየፈረሱ እየታመሱ ነው ።

በጎሳ ተረትና ትርክት ሰላም ለዘላለም አይመጣም ። የጎሳ ፖለቲካ የራሱን ጎሳ ይበላል።

የኢትዮጵያ ጥያቄ መፍትሄ ፍትህ ብቻ ነው ።

የሰላም ምንጭና መፍትሄ ፍትህ ብቻ ነው ።

የፍትህ መነሻና መድረሻ የሰው ልጅ ክቡርነትና የግለ ሰብ ልዕልና ብቻ ነው ።

ይህን እጅግ ቀላል ሃሳብ እስከ ሚገባቸው ድረስ የኢትዮጵያ ምሁር ተብዬ ደንቆሮች የጭለማ መታመሳቸውን ይቀጥላሉ ። አለምም በኢትዮጵያ መሳለቋን መሳቀቋን ትቀጥላልውች ።

Horus
Senior Member+
Posts: 31163
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: THE HORUS MANIFESTO: WHAT IS ETHIOPIA?

Post by Horus » 17 May 2024, 13:53

እንደ ገና፣ ቃላት መፍለጥና ሃረግ መሰንጠቅ እውቀት አይደለም ።

አንድ ግለሰብም ሆነ አንድ ሕዝብ፣ ብሎም አንድ አገር አንድ መንግስት የሚቆመው፣ ካልሆነም የሚወድቀው በ4 ምክንያቶች ነው

(1) እራሱን በትክክል ሲመራና ራሱን በትክክል ሲገዛ ነው ። እራሱን በራሱ የማይመራና የማይገዛ አይደለም የተሳሳተ የሌሎች አሽከርና ተገዥ ነው ።

(2) እራሱን በትክክል የሚከተልና በራሱ ላይ የራሱን ዲሲፕሊን የሚጠብቅ ራስ ታዛዥ ሲሆን ነው ። ዲሲፕሊን አልባ ራሱን በትክክል የማይከተል ደካማ ዉሸታም የሌሎች ደቂቅ ፣ ላቅመ ራስነት ያልደርሰ ሰው አገር ወይም መንግስት ማለት ነው ።

(3) እራሱን በራሱ በትክክል የሚቆጣጠር፣ የሚከታተል ፣ ስርዓታዊ ፣ ስኛታዊ ሲሆንና የሌሎችን ቁጥጥርና አለቃነት የማይፈልግ እራሱን ፖሊስ አድራጊ መሆን ነው ። እራሱን መቆጣጠር የማያውቅና የማይችል ስድና ሴራ አልባ ለስርዓታዊ ሕይወት ያልበቃ ሰው ፣ አገር ወይም መንግስት ነው።

(4) እራሱን በራሱ በትክክል ስህተቱን የሚያርም ከቁጥር 1 እስከ 4 ድረስ በንቃት ራሱን እና ተግባሩን የሚያውቅ ክህሎታዊ ፣ ጥበባዊ (intelligent) ሰው፣ ሕዝብ ፣ አገር ወይም መንግስት ሲሆን ነው ። የራሱን ስህተት የማያውቅ ፣ ስህተቱን የማረም ችሎታና አስተውሎት የሌለው ከንሰሳ የማይልቅ ሰው ወይም መንግስት ነው ።

ዛሬ ላይ በመንግስት ወምበር ላይ ቂጥጥ ብለው 120 ሚሊዮን ሕዝብ በራዕይ፣ ፐርፐዝና መሪነት እጦት እየታመሰ ስለ ልሂቅነትና አስተውሎት፣ ስለክህሎትና ሰው ሰራሽ ኢንተለጀንስ ሲቀባጥሩ ማሳቅ አይደለም ያሰቅቃል ።

ይህን ያስተዋልው ጥቁር አሜሪካዊ ወጣት አምባሳደር ነው 3 ሺ ዘመን የኖርነውን ሕዝብ እንዴት መኖር እንዳለብን ሌክቸር ሊያደርገን የደፈረው! እጅግ እጅግ ያሳስናል የወረድንበት ዝቅጠት ጥልቀት ።

Post Reply