Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 31157
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሯን መፍታት ለምን አቃታት?

Post by Horus » 08 May 2024, 01:18

ኢትዮጵያዊ የምንባለው ሕዝብ ለምንድን ነው የፖለቲካ ችግራችንን መፍታት ያቃተን?

አንድ ሰው ችግሩን መፍታት የሚያቅተው ምን ሲሆን ነው?

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ቁጥር 1 ችግር ምንድን ነው?

በአንድ ቃል የኢትዮጵያ ጥያቄ በአንድ ቃል ምንድን ነው?

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 1 ችግር የካልቸር፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበረ ሰብነት ችግር አይደለም!

የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 1 ችግር የፖለቲካ ችግር ነው!

ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 1 ችግር የድርጅት ጥያቄ ነው!

የኢትዮጵያ ችግር እንደ ሕዝብ፣ እንደ አገር፣ እንደ ብሄር የፖለቲካ ድርጅት ችግር ነው።

የኢትዮጵያ ችግር የመንግስት ጥያቄ ነው ፤ የመንግስት አደረጃጀት ጥያቄ ነው፤ መንግስት ድርጅት ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ መንግስት የሚደራጁበት ፍልስፍና፣ ንድፈ ሃሳብ፣ ዘዴና ስነ ስርዓት የላቸውም፤ መፍጠርም ያቃታቸው ይህ የመንግስት ማደራጃ ፍልስፍና ፣ ንድፈ ሃሳብ፣ ዘዴና የተግባር ስርዓት ነው ።

ስለሆነም እጅግ ግዙፉና የመጀመሪያ ጥያቄ የሚከተለው ነው ።

WHAT IS THE ORGANIZING PRINCIPLE OF THE ETHIOPIAN NATION? THE ETHIOPIAN STATE? THE ETHIOPIAN GOVERNMENT? THE ETHIOPIAN POLITICAL SYSTEM?

ETHIOPIA DOES NOT HAVE A POLITICAL SYSTEM!

የኢትዮጵያን ፖለቲካ ስርዓት ማደራጃው ብቸኛ መርህ ፣ ብቸኛ መሰረት ምንድን ነው?

ይህን ጥያቄ የማይጠይቅ ፣ ይህ ጥያቄ ምን ማለት እንደ ሆነ ያልገባው ፣ ይህን ጥያቄ ለመመለስ የማይሞክር ሰው፣ ቡድን ሆነ ተቋም ምን እንደ ሚፈልግ የማያውቅ በጭፍን ተጓዥ ነው ።

ለምሳሌ የምክክር ኮሚሽን የተባለውን ግዚያዊ ስብስብ እንውሰድ።

ይህ ኮሚሽን ይህን ጥያቄ ማዕከል ያደረገ ነው ወይ? አይደለም ! የ130 ሚሊዮን ሰው ፍላጎቶች ማዳመጥና መሰብሰብ ከላይ የተጠየቀው ማደራጃ መርህ መፈልግ አይደለም ።

ማደራጃ መርህ ከሰዎች ግላዊና ቡድናዊ ምኞት ሳይሆን የሚመነጨው፣ ማደራጃ መርህ የሚቀዳው ከፍልስፍና፣ ንደፈ ሃሳብ፣ ዘዴዎችና የተግባር ሞዴሎች ነው ።

መንግስት ድርጅት ነው! መንግስት የሚደራጀው በድርጅት ወይም ማደራጃ ፍልስፍና ነው ፤ ማደራጃ ንድፈ ሃሳብ ነው ፤ ማደራጃ ዘዴ ነው ፣ ማደራጃ ፕራክቲስ ተግባር ነው ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆኑ ምሁራን ይህን እስካላደረጉ ድረስ የኢትዮጵያን ጥያቄ ሊመልሱ አይችሉም። በሌላ አባባል በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልሂቃን የሉም! የፖለቲካ ፈላስፎች፣ የፖለቲካ ቲኦሪስቶች፣ የፖለቲካ ጠቢባን እና የፖለቲካ ሙያተኞች የሉም!

ይህ ነው የኢትዮጵያ ችግር ! ለዚህ ነው ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሯን መፍታት በፍጹም ያቃታት !!


viewtopic.php?f=2&t=337752
Last edited by Horus on 08 May 2024, 01:24, edited 1 time in total.

Fiyameta
Senior Member
Posts: 12879
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሯን መፍታት ለምን አቃታት?

Post by Fiyameta » 08 May 2024, 01:23

X = Where you from?
Y = Ethiopia
X = What part?

X = Where you from?
Y = Eritrea
X = Nuff said.

Horus
Senior Member+
Posts: 31157
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግሯን መፍታት ለምን አቃታት?

Post by Horus » 08 May 2024, 01:34

Fiyameta wrote:
08 May 2024, 01:23
X = Where you from?
Y = Ethiopia
X = What part?

X = Where you from?
Y = Eritrea
X = Nuff said.
ፊያሜታ፣
ኤርትራ ለ30 አመት ያለ ፖለቲካ ስርዓት በአንድ ሰው የሚነዳ ነው። በአንድ አለቃ መነዳት አቅቶን አይደለም! ለ3 ሺ ዘመን ባንድ ንጉስ መገዛትን የምናውቅ ሕዝብ ነን! ተው ግዴለም ለኢትዮጵያ ጥያቄ ከመመልስህ በፊት ተመሳሳይ ጥያቄ ለራስህ ለኤርትራ ጠይቅ! የኤርትራ ሕዝብ የፖለቲካ ድርጅት፣ የፖለቲካ ስራዓት የሚባለውን ጽንሰ ሃሳብ ገና አልደረሱበትም ።
አመድ በዱቄት ይስቃል ይባላል! እኛ ቢያንስ ዱቄት ነን! እናንተማ አመድ ናችሁ! ሰላም!

Post Reply