Ethiopian News and Opinion Forum


Awolia uprise updates: መሪዎቹ በሽብርተኝነት ተከሰሱ; leaders being tortured; savage police beatings

Postby Beles » 20 Jul 2012, 06:54


ባሳለፍነዉ እሁድ ክዋስ ሜዳ በሚገኘዉ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ ታላቁ የዳዕዎ መርከዝ የዳዕዎ ሰዎች መደበኛ የሶስት ወር ሹራ ለማድረግ ከተለያዩ ቦታዎች ተሰብስበዉ የነበረ ሲሆን በስብሰባዉ ለተገኙ ሙስሊሞች የተዘጋጀዉን ምግብ የፌደራል ፖሊስ ለሰደቃ የተዘጋጀ ነዉ በማለት ምግቡን ማስደፉቱ ተገለፀ!!

በዛሬው እለት በታላቁ አንዋር መስጂድ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሕዝበ ሙስሊም እጅግ ሰላማዊ የሆነውን ተቃውሞ በአስጨናቂ ዝምታ ገለፀ መንግስት ኢስላም ላይ የከፈተውን ዘመቻ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አሰምቶአል ከመፈክሮቹ ውስጥ ኮሚቴዎቻችንን መንካት ሕዝበ ሙስሊሙን መንካት ነው !! መብትን መጠየቅ ካሳሰረ ለመብታችን ለመሰዋት ዝግጁ ነን !! በሚዲያ ስም ማጥፋቱ ይቁም !! ሕገ መንግስቱ ይከበር !! መንግስት ከኀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ !! የሚሉና ሌላ ብዙ መፈክሮች ታይተዋል:: በዛሬው የጁመዐ ሠላት ላይ የሕዝቡ ብዛት ከወትሮው የተለየ ነበር ሕዝቡ በሲኒማ ራስ እስከ ተክለ ኀይማኖት በጣና ገበያ እስከ መርካቶ ባስ ስቴሽን በበፒያሳ እስከ ሀብተ ጊዮሪጊስ በአውቶቢስ ተራ ጎጃም በረንዳን አልፎ ነበር:: ኢቲቪና መንግስት እንደሚሉት ይሔ ሁሉ ሕዝብ አሸባሪ ከሆነ ሀገሪቱ ውስጥ መንግስት የለም ማለት ነው::...
Last edited by Beles on 21 Jul 2012, 06:33, edited 4 times in total.



Re: Awolia uprise updates

Postby Beles » 20 Jul 2012, 06:58


አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት ከሼህ ሱልጣን
በስጠቀር ሁሉም የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ
አፈላላጊ ኮሚቴ አባላቶች አለመታሰራቸዉን
ምንጮች ዘግበዎል:: ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ እና
ኡስታዝ ሀሰን አሊም መኖሪያ ቤታቸዉ
ከመፈተሽ ዉጪ አለታሰሩም ተብሏል::



Re: Awolia uprise updates

Postby Beles » 20 Jul 2012, 07:00


የኣንዋር መስጂድ ኡስታዝ ፈድሉ ትናንት ማታ ከምሽቱ 5 ስዓት ላይ ተወስዶ ታስሯል።




Re: Awolia uprise updates

Postby Beles » 20 Jul 2012, 10:05


በዛሬው እለት በታላቁ አንዋር መስጂድ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሕዝበ ሙስሊም እጅግ ሰላማዊ የሆነውን ተቃውሞ በአስጨናቂ ዝምታ ገለፀ መንግስት ኢስላም ላይ የከፈተውን ዘመቻ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አሰምቶአል ከመፈክሮቹ ውስጥ ኮሚቴዎቻችንን መንካት ሕዝበ ሙስሊሙን መንካት ነው !! መብትን መጠየቅ ካሳሰረ ለመብታችን ለመሰዋት ዝግጁ ነን !! በሚዲያ ስም ማጥፋቱ ይቁም !! ሕገ መንግስቱ ይከበር !! መንግስት ከኀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ !! የሚሉና ሌላ ብዙ መፈክሮች ታይተዋል በዛሬው የጁመዐ ሠላት ላይ የሕዝቡ ብዛት ከወትሮው የተለየ ነበር ሕዝቡ በሲኒማ ራስ እስከ ተክለ ኀይማኖት በጣና ገበያ እስከ መርካቶ ባስ ስቴሽን በበፒያሳ እስከ ሀብተ ጊዮሪጊስ በአውቶቢስ ተራ ጎጃም በረንዳን አልፎ ነበር ኢቲቪና መንግስት እንደሚሉት ይሔ ሁሉ ሕዝብ አሸባሪ ከሆነ ሀገሪቱ ውስጥ መንግስት የለም ማለት ነው ምክንያቱም ይሔ ሁሉ አሸባሪ በነፃነት የሚንቀሳቀስ ከሆን መንግስt መኖሩ አጠራጣሪ ነው አሸባሪ ተባልንም ሌላ የመብት ጥያቄያችን ይቀጥላል




Re: Awolia uprise updates

Postby Beles » 20 Jul 2012, 10:14


ሕዝቤ እና ውሎው በአንዋር! ሐምሌ 13/2004

“ድንቅ” የሚለው ቃል ዛሬ ህዝበ መስሊሙ በአንዋር ያሰየውን ይገልጠው ይሆን? በፍፁም!

ኮሚቴዎቻችንን እና ታላላቅ ዳዒያንነንና የተከበሩ ዓለሞችን ሲያዋክቡ እና ሲያስሩ ያደሩ የመንግስት ኃይላት በአንዋር ዛሬ ጁምዓ ላይ የጠበቁት ከዚህ የተለየ እንደነበረ ይታወቃል፡፡
ወኪሎቻቹ በእንግልት እና እገታ ስር ሁኔታው የእግር እሳት ቢሆንበትም መስሊሙ የመረጠው ምላሽ ዝምታ እና ቀጣይነት ያለውን ሰላማዊ የትግል ስልት ብቻና ብቻ ነው፡፡ ምንግዜም ከአላህ ራሕመት ተስፋ አንቆርጥም፡፡አላህ ከእኛ ጋር ነው፡፡ ጥሎ አይጥለንም፡፡
አንዋር መስጂድ ጁምዓ ከተሰደ በኋላ የታየው ትዕይንት ለአገራችን ህዝባዊ የተቃውሞ ታሪክ አዲስ እና እንግዳ ብቻ ሳይሆን አርዓያም ጭምር ነው፡፡ ልክ በላለፈው መልዕክት መሠረት ህዝቤ እጅ ለእጅ ተሳስሮ ፣አንደበቱን ለጉሞ እና ትንፍሽ ሳይል በአንድነት እና ትግል አይሞትም በሚል ስሜት ያቆላለፈውን ክንዶቹን ወደ ላይ በማንሳትና በማርገብገብ ተቃውሞውን ገልጧል፡፡ ይህም እንደባለው ከ15 እስከ 20 ደቂዎች ቆይታ ነበረው፡፡ ኮሚቴዎቻችንን በአካል ተገኝተው ይህን አይተውት ይሆን ስንል ጠይቅን፡፡ ኢንሻ አላህ! ሕዝቤ ተቆጥቷል! ሙስሊሙ ተቆጥቷል! ረብ የሌሽ እና የፖለቲካ ጠገግ ያላቸውን ዘዴዎች በመጠቀም ሙስሊሙን ከአቋሙ እንዲያፈገፍግ የሚደረጉ ሙከራዎች እውነት ለዲናችን ከሆነ እንዲህ የምንሆነው አላህ ያግዘናል፡፡
ልብ በሉ ጥያቄያችን ሐይማኖታዊ እና ሐይማኖታዊ ብቻ ነው፡፡ ነገሩ እጅግ ቀላል እና ቀላል ነው፡፡ ሦስት ጥያቄ ሦስት መልስ ብቻ ነው የሚሻው፡፡ ያኔ የሁሉም ነገር መቋጫ ይቀርባል፡፡
ኮሚቴዎቻችንን መገት፣ማንገላታት እና ለእስር መዳረግ ብሎም በየቦታው ሰዎችን በአንድ ወይም በሌላ መንገድ በመሰብሰብ የሙስሊሙን ህዝባዊ እንቅስቃሴ ስላሸት ለመቀባት ሞከርና ኮሚቴው የጥፋት ሃይል ነው ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ፕሮፓጋንዳ መንዛት ቦታውን ለለይ ይገባል ብቻ ሳይሆን ህዝብ እነኚህን ግለሰቦች ምን ያክል እንደሚያምናቸው፣ እንደሚወዳቸው እና እንደሚያከብራቸው ያለማወቅ ነው፡፡ ይህ አካሄድ ለፖለቲካ ሊበጅ/ሊሰራ/ ይችላል ለሐይማኖት ግን ቢያንስ ያጠራጥራል፡፡ ባይሆን የሚበጀው ለጥቂቶች አሉታዊ እና አፍረሽ አጀንዳ ከመሮጥ ሰፊው ህዝ ሙስሊም ከያዘው ሀቅ ጎን በመወገን ነገሩን ማብረድና መታረቅ ብሎም ፊታቸችንን ወደጀመርነው የልማት መንገድ ማዞር ነው፡፡
አላህ ከኛ ጋር ነው፡፡ ሠላማዊ መብታችንን የማስከበር ሂደት በአላህ እርዳታ እስከ መጨረሻው ቀጥላል፡፡
ህዝቤ ታዛዥነቱ ትላንትም ተመስክሮለታል፣ ዛሬም ተመስክሯል፣ ኢንሻ አላህ ነገም ይመሰከርለታል!




Re: Awolia uprise updates

Postby Beles » 20 Jul 2012, 12:09


mesage from the demonstration
Image



Re: Awolia uprise updates

Postby Beles » 20 Jul 2012, 12:11


message from the demonstrants face book

ወንድሞቼና እህቶቼ፤
በኢትዮጵያ ታሪክ እንዲህ አይነት ሰላማዊና ስልጡን ህዝብ አልተነሳም፡፡ የዚህ ትዉልድ አባል በመሆኔ ወላሂ ኮራሁ!!!!!!!
ዛሬ በአንዋር መስጅድ የታየዉ ክስተት ለሃገር ብቻ ሳይሆን ለአለምም ምሳሌ መሆን የሚችል ነበር፡፡
ይህንን ህዝብ ”በአሸባሪነትም ሆነ በፀረ ሰላምነት” መፈረጅ የታሪክም የትዉልድም ተጠያቂ ያደርጋል፡፡ ይዘገይ እንደሁ እንጂ እዉነት አሸናፊ መሆንዋ የማይቀር ነዉ፡፡
አላሁ አክበር !!!!!!!!!!!!

Next Page


Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, royal, Shewit, Somali-Ethio, Zack