Ethiopian News and Opinion Forum


ከ ወያኔ ፖሊስ ጽህፈት ቤት የጦር መሳሪያ ተዘረፈ

Postby Aragaw » 16 Aug 2012, 11:51


:lol: በደቡብ ክልል በሚገኘው ደራሼ ወረዳ ፖሊስ
ጽ/ቤት መጋዘን የጦር መሳሪያ መዘረፉ ተገለፀ፡፡
የጦር መሳሪያው በጊዜያዊነት በመጋዘን ተሰብስቦ
የነበረው በአሁን ወቅት አሌ ወረዳ የሚገኘው
ህዝብ በደራሼ ልዩ ወረዳ ስር በነበረበት ጊዜ
በ1997 ዓ.ም የወረዳ አስተዳደርነት ጥያቄያ
ተግባራዊ እንደሚደረግ ቃል ቢገባለትም በወቅቱ
በአካባቢው የቀድሞ ቅንጅትን ማሸነፍ ተከትሎ
እውን ባለመሆኑ ቅሬታ በመፍጠሩ እነደነበር
ይነገራል፡፡
በዚህም ምክንያት በ2002 ዓ.ም መሳሪያ
ያላቸው የአካባቢው ማኅበረሰብም ከፖሊስ እና
አጋአዚ ጦር ጋር ውጊያ ገጥመው ከፍተኛ
የሰው ህይወት እና ንብረት ጠፍቶ እንደነበር
የተጠቆመ ሲሆን በመጨረሻም በአካባቢው
ሽማግሌዎች ግጭቱ መብረዱን ምንጮቻችን
ጠቁመዋል፡፡
ከግጭቱ መርገብ በኋላም በልዩ ፖሊስ
ኃይል ከማኀበረሰቡ የወረሳቸውን መሳሪያዎች
በወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ጊዜያዊ መጋዘን
የተቀመጠ ሲሆን ነገር ግን ሐምሌ 27 ቀን
2004 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ማንነታቸው
ባልታወቁ ሰዎች መጋዘን ተሰብሮ የተቀመጡት
ክላሽንኮቭን ጨምሮ ሌሎች የጦር መሳሪያዎች
መዘረፋቸው እንደተረጋገጠ ከሥፍራው የፖሊስ
ምንጮቻችን አስታውቀዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በወረዳው ፖሊስ ጽ/
ቤት ለረጅም አመታት ህዝቡን ሲያገለግሉ
የነበሩ ወንጀል መርማሪዎችና የጥበቃ አባላት
የኢህአዴግ አባል ካልሆናችሁ በሚል በወረዳው
መስተዳድር አመራሮች ከፍተኛ የስራ ምደባና
የስነ ልቦና በደል እየተፈፀመባቸው እንደሆነም
ተጠቁሟል፡፡
በተለይ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉት
የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ወንጀል ምርመራ
ክፍል ባልደረባ እንዳሉት ከሆነ በተጠቀሰው ቀን
የጦር መሣሪያ ዝርፊያ መፈፀሙን አምነው
ዝርዝር ጉዳዩን ግን ከመግለጽ ተቆጥበዋል፡
፡ በመሳሪያ ዝርፊያ ዙሪያና ውጤቱ ያለበትን
ሂደት ለማረጋገጥ የወረዳው ምክትል አስተዳደር
አቶ ግንኙነት ኪንተቦን ብንጠይቃቸውም
“የተባለው ነገር ሐሰት ነው” በማለት መልስ
ከሰጡ በኋላ የዝግጅት ክፍሉ ዘገባውን
እንዳይሰራ ለማስፈራራት ሞክረዋል፡፡
አንዳንድ የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አባላት
በበኩላቸው በ2002 ዓ.ም ግጭት ወቅት
ከማኅበረሰቡ የተሰበሰቡ የጦር መሳሪያዎች
ዝርዝርን ማወቅ ለሚገባው የመንግስት
አካል ሪፖርት መደረጉን እንደሚጠራጠሩና
የተዘረፉትም መሳሪያዎች ወደ ህገወጦች እጅ
ገብቶ የአካባቢውን ፀጥታ ሊያናጋ ስለሚችል
የሚመለከተው የበላይ የመንግስት አካል
ጉዳዩን አጣርቶ እርምጃ ሊወስድ እንደሚገባ
ጠቁመዋል፡፡ ባለፈው ሳምንት በዚሁ ወረዳ
ዝርፊያ የፈፀሙ ሁለት ፖሊሶች በወረዳው
አስተዳደር በነፃ እንዲለቀቁ መደረጋቸውን
መዘገባችን ይታወሳል፡፡

http://www.fnotenetsanet.com/wp-content ... -No-55.pdf

Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Abdelaziz, Asab, Bing [Bot], DAnnni, elias, ethiopianunity, Facts, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Halafi Mengedi, Shewit, YEBANDAMERZE