Ethiopian News and Opinion Forum


የትግራይ መምህራን ወደ አረብ ሀገራት እየተሰደዱ ነው

Postby Aragaw » 16 Aug 2012, 11:57


በትግራይ ክልል መምህራን ስራቸውን
እየለቀቁ ወደ አረብ ሀገራት መሰደድ ላይ
በመሆናቸው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ግራ
እንደተጋባ ለፍኖተ ነፃነት የደረሱ መረጃዎች
አመላከቱ፡፡
መምህራኑ የስራ ገበታቸውን እየለቀቁ
እንዲሰደዱ ያደረጋቸው ዋነኛው ምክንያት
በክረምት ትምህርት መርሃ ግብር የትምህርት
ደረጃቸውን ለማሻሻል እንዳይችሉ አድሎ
መፈፀሙና ደመወዛቸው አሁን ካለው የኑሮ
ውድነት አንፃር ቤተሰባቸውን ለማስተዳደር
በቂ አለመሆኑ እንዲሁም የገዢው ፓርቲ
አባል ባለመሆናቸው ብቻ ከእድገትና ከተለያዩ
ጥቅማ ጥቅሞች ውጪ መደረጋቸው መሆኑን
ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡
ሁኔታው ያስደነገጠው የክልሉ
የትምህርት ቢሮ ባዶ የሆኑትን ትምህርት
ቤቶች በመምሀራን ለማሟላት በአማራና
በአፋር ክልሎች ተቀጥረው የሚሰሩ የክልሉ
ተወላጅ መምህራንን ለመቅጠር ማስታወቂያ
ማውጣቱ ተጠቁሟል፡፡ ማስታወቂያውን
ተከትሎ ከአማራና ከአፋር ክልል ከቀድሞ
ስራቸው እየለቀቁ መምጣታቸው የነበሩባቸው
ክልሎች ላይ ሌላ ክፍተት ሊፈጥር
እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ ስለጉዳዩ
ለማጣራት የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ
የሰው ሀይል አስተዳደር ኃላፊ የሆኑትን
አቶ አብርሃም ተክለሃይማኖትን ለማግኘት
ጥረት ብናደርግም ስልክ ባለማንሳታቸው
አልተሳካም፡፡

http://www.fnotenetsanet.com/wp-content ... -No-55.pdf

Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Alexa [Bot], Bing [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, kokeb, TurnitinBot [Bot]