መንግስትና ዓለም ዓቀፍ ደጋፊዎቹ የሚደርስብንን የመብት ጥሰት አናይም አንሰማም ብለው ይህንን ያህል ጊዜ ተሰቃይተናል። ካሁን ኋላ መብታችን እስኪመለስ ድረስ በድምጻችን ህሊናቸውን እናውካለን። "ድምጻችን ይሰማ"።
የዒድ "ድምጻችን ይሰማ" አዲስ አበባ ስታዲዮም
ቅድመ ዝግጅት
አንድ ጠርሙስ ውሃና ሁለት ነጭ ጨርቆችን ይዘን እንመጣለን። አንድ መሃረብ የሚያክል አንድ ረዘም ያለ።
ከሰላት በፊት
1ኛ. ጧት 1 ሰዓት ላይ እስታዲየም እንገኛለን። አስቀድሞ ሰላት የሚጀመር ከሆነ ሰላቱን ሰግደን ቀሪ ወንድሞችና እህቶች እስኪመጡ እንጠብቃለን፡፡
2ኛ. ህልውናችንን ሲሸጡ የከረሙ የመጅሊስ አመራሮችና የመጅሊስ ዑለማ ም/ቤት አባላት ንግግር ሲያደርጉ መዳፋችንን ጆሮዋችን ላይ በማድረግ ከመድረክ እስኪወርዱ ‹‹አሸዕብ ዩሪድ ኢስቃጠል መጅሊስ›› እንላለን።
3ኛ. ሙስሊሞችን የሚያጣጥልና የሚወርፍን በተክቢራ እናስቆመዋለን፡፡
4ኛ. የመንግስት ባለስልጣን ተጋባዥ ሲናገር ጆሮዎቻችንን በመዳፎቻችን በመያዝ ‹‹ድምፃችን ይሰማ›› መፈክር በማሰማት እናስቆማለን፡፡
ከሰላት ቡኋላ
1ኛ. ሰላት እንደተሰላመተ ባለንቦት ቦታ ቆመን ለ8 ደቂቃ ነጭ ሶፍት/መሃረብ/ወረቀት ማውለብለ።
2ኛ. ተንበርክከን ለ5 ቀቂቃ እጃችንን በካቴና ምልክት።
3ኛ. 5 ደቂቃ እጅለ ለእጅ ተያይዘን ተክቢራ።
4ኛ. 5 ደቂቃ "ጥያቄያችን ይመለስ"።
4ኛ. 5 ደቂቃ ኮሚቴው ይፈታ!!
5ኛ. 5 ደቂቃ የታሰሩት ይፈቱ!!
6ኛ. 5 ደቂቃ ምርጫችን በመስጂዳችን!!
7ኛ. 5 ደቂቃ ድምፃችን ይሰማ!!
8ኛ. 10 ግዜ አቋማችን!! - አቋማችን!! እንላለን፡፡
9ኛ. 10 ግዜ ኮሚቴው ሳይፈታ - ምርጫ አንሳተፍም!! እንላለን፡፡
10ኛ. 10 ግዜ በእምነታችን - ጣልቃ አትግቡ!! እንላለን፡፡
11ኛ. 10 ግዜ ሀስቡን አላህ - ወኒዕመል ወኪል!!
ከዚህ ቡኋላ ወደየመጣንበት እንመለሳለን፡፡
ሊፈጠሩ የሚችሉ ክስተቶች!
1ኛ. መንግስትና መጅሊስ የሚያደራጇቸው ቡድኖች እኛን ወደ ሁከት ለመቀስቀስ ቢጥሩ በምንም መልኩ ምላሽ ባለመስጠት እናከሽፍባቸዋለን፡፡
2ኛ. በማንኛውም ቦታ በሴቱም በወንዱም በኩል ግርግር ቢፈጥሩ አንሮጥም ባለንበት ቦታ ቆመን እጅ ለእጅ ተያይዘን ግርግራቸውን እናከሽፋለን፡፡
3ኛ. መሃላችን ገብተው ህዝቡን ሰልፍ እናድርግ ብለው የሚቀሰቅሱ ካሉ እናጋልጣቸዋለን፡፡
4ኛ. ዝናብ ቢኖር ከዚህ በፊት እንዳሳየነው ሁሉ ፀንተን ድምፃችንን ከማሰማት አይገድብንም፡፡
5ኛ. አስለቃሽ ጭስ ቢተኮስ ውሃ ረጅሙ ጨርቅ ላይ በማድረግ አፍንጫና አፋችን ላይ እናስራለን፣ አይናችንንም እንታጠባለን።



