Ethiopian News and Opinion Forum


የህወሀት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ

Postby DE ESAT » 08 Sep 2012, 22:16


ጳጉሜን ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ሾልከው የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት፤ ጀነራል ሳሞራ ዩኑስ እና በሥራቸው ያሉ የህወሀት ጀነራሎች ለጠቅላይ ሚኒስትርነት ብቁ የሆነ ሰው ከነሱ መካከል ስላለ በመለስ ቦታ ምንም ዓይነት ሹመት እንዳይሰጥ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጀነራሎቹ፦“መለስን መተካት የሚችል ብቁ ሰው አለን። ከኛ ፈቃድና ዕውቅና ውጪ ማንም ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሾም አይችልም!”ነው ያሉት።

የጀነራሎቹ መልዕክትና አቋም መሰማቱን ተከትሎ በኢህአዴግ አመራሮችና አባላት መካከል ጭንቀት መፈጠሩም ታውቋል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለ ኢህአዴግ ሊቀ-መንበሩን እና ምክትል ሊቀመንበሩን እንደፈረንጆቹ አቆጣጠር የፊታችን ሴፕቴምበር 16 እንደሚመርጥ የኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሽመልስ ከማል ለብሉምበርግ ነግረውታል።

የግንባሩ ሊቀመንበር የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሆን እንደሚችል ቃል አቀባዩን አቶ ሽመልስ ከማልን በመጥቀስ ብሉምበርግ ዘግቧል።

የ አቶ መለስ ማረፍ በመንግስት ብዙሀን መገናኛ በተገለጸበት ወቅት ፤ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፦”ተጠባባቂ ጠ/ሚ/ር” እንደሆኑ የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ በረከት ቢያስታውቁም፤ በ አሜሪካ የተመድ አምባሳደር ሱዛን ራይስን ጨምሮ በአቶ መለስ ቀብር ዕለት የተገኙ የውጪ አገር መሪዎች፦አቶ ሀይለማርያምን ፦”ተጠባባቂ ጠ/ሚ/ር እያሉ ቢጠሩም፤ እስካሁን ድረስ ሹመታቸው ሊጸድቅ አልቻለም።

የ አቶ ሀይለማርያም ሹመት የፊታችን መስከረም 16 ይጸድቃል ተብሎ በስፋት እየተጠበቀ ባለበት ጊዜ የህወሀት ጄነራሎቹ ያልተጠበቀ ጥያቄ ማንሳታቸው፤ የመለስን መሞት ተከትሎ በኢህአዴግ ውስጥ እየተባባሰ የተፈጠረውን ሽኩቻ ይበልጥ ያወሳስበዋል ተብሎ ተፈርቶአል።

በ ኢትዮጵያ ከሚገኙ ወደ 60 የሚጠጉ ጀነራሎች 58 ቱ የህወሀት አባላት እንደሆኑ፤ የግንቦት ሰባት ራዲዮ ከነ ስም ዝርዝራቸው እና ከያዙት ሀላፊነት ጋር በዝርዝር ማቅረቡ አይዘነጋም።

ስለ ጉዳዩ አስተያየታቸውን ይሰጡ ዘንድ ኢሳት ያነጋገራቸው አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አገር ቤት ያሉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ፤ ጀነራሎቹ አነሱት የተባለውን ጥያቄ እርሳቸውም እንደሰሙት በመጥቀስ፤ይሁንና ካለውና ከሆነው ተጨባጭ ሁኔታ በመነሳት ኢህአዴግ አቶ ሀይለማርያምን ከመሾም ውጪ ሌላ አማራጭ እንደሌለው አስረድተዋል።

“ከ እንግዲህ ከዚያ ውስጥ ሹመት እንስጥ ቢሉ፤ ከራሳቸው ጋር ብቻ ሳይሆን ከብዙሀኑ ህዝብና ከለጋሽ መንግስታት ጋር ጭምር ነው የሚጣሉት”ብለዋል-የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩ።

የአቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትርነት የማይጸድቅ ከሆነ፤ ኢህአዴግ መራሹ መንግስት ዩናይትድስቴትስን ጨምሮ በለጋ ሽ አገሮች ዘንድ ከፍተኛ አጣብቂኝ እንደሚገባ ሌሎች የፖለቲካ ተንታኞችም ሲናገሩ ይደመጣሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ህወሀት ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ ” ታጋይ መለስ የትግራይን ህዝብ በብቃት በመምራት ከመሰል ጓዶቹ ጋር በመሆን ግንባር ቀደም ሚናውን የተጫወተ የህዝብ ልጅ ነበር ካለ በሁዋላ፣ ህወሐት ከውልደቱ ጀምሮ በድል እሰኪጠናቀቅ ድረስ ያጋጠሙ ውስብስብ ችግሮችን በመተንተንና መሠረታዊ መፍትሄዎቻቸውን በማስቀመጥ የመሪነት ሚና መጫወቱን ገልጧል።



Re: የህወሀት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ

Postby Guest1 » 09 Sep 2012, 06:11


Parties or fronts are organised by ethnicity (except within the opposition). In this kind of arrangement positions are filled by ethnicity or shared by ethnic parties. For example, upto now PM position by TPLF, Speaker of parliament by OPDO, Deputy PM by SNNP etc... All powerful positions are divided by ethnicity. This power sharing arrangement can be fixed. So far we have seen changes in deputy PM position, first was ANDM representing Amhara now SNNP and the speaker of parliament also changed hands. Now some are looking for changes in PM position, may be changes in all high positions.

EPRDF has to choose 1. fixed 2. rotating every election or two. This is something the EPRDF have to discuss in the future.

Therefore there is nothing wrong if TPLF or TPLF generals say it should be TPLF forever, for now till end of term or up to next election or two.



Re: የህወሀት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ

Postby azene-libe » 09 Sep 2012, 12:01


TPLF members are power thirsty vultures .For 21 years they did not share the power and now they say they bring every pretext to grab power by force till they maximize the looting of the country. The so called OPDO and ANDM deserve the humiliation as they are the ones who let the gun to be in the hands of the vultures. What a shame fot the two Robot parties who claim to represent the great majority of the people. you will be humiliated by your bosses tplf agents. cause you pay their spy network agents. shame on OPDO and ANDM!



Re: የህወሀት ጀነራሎች የመለስ ቦታ የሚገባው ለኛ ነው የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ተሰማ

Postby Gera » 09 Sep 2012, 12:15


assasinating the acting PM might be another option for the would be ,, Junta`` in order to widen the vacum. Don´t forget the TPLFs are blind even till not see what happened to Gadafi who depended on his war machine and a clan. :lol: :lol: :lol: :lol:



Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: alex1, Beleche, Bing [Bot], elias, Exabot [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Gurezza, Halafi Mengedi, MatiT, whereisthefrog, yaredgh