Ethiopian News and Opinion Forum

ምኒሊክና ኣድዋ

Postby Beles » 01 Mar 2012, 13:26

menelik_awaj.jpg
ምኒሊክ ከኣድዋ በፊት
menelik_awaj.jpg (106.73 KiB) Viewed 868 times

Re: ምኒሊክና ከኣድዋ በኋላ

Postby Beles » 01 Mar 2012, 13:29

menelik post adwa letter.jpg
ምኒሊክ ካድዋ በኋላ
menelik post adwa letter.jpg (31.13 KiB) Viewed 867 times

Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby Shalom » 01 Mar 2012, 15:12

Beles wrote:
menelik_awaj.jpg

There is no question that Minilik had admirable understanding about what country and people mean compare to the contemporary Ethiopian leaders.

Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby revelations » 02 Mar 2012, 12:03

GIGI's Adwa song!

Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby revelations » 02 Mar 2012, 16:45

ዋ ! … .ያቺ ዓድዋ

ዋ !....
ዓድዋ ሩቅዋ
የዓለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ……
ባንች ብቻ ሕልውና
በትዝታሽ ብፀዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዜና
አበው ታደሙ እንደገና…
ዋ !
ዓድዋ የዘር ዐፅመ ርስትዋ
የደም ትቢያ መቀነትዋ
በሞት ከባርነት ሥርየት
አበው የተሰውብሽ ለት፤
ዓድዋ
የኩሩ ትውልድ ቅርስዋ
የኢትዮጵያዊነት ምስክርዋ
ዓድዋ
የኩሩ ደም ባንች ጽዋ
ታድማ በመዘንበልዋ
ዐፅምሽ በትንሳኤ ነፋስ
ደምሽ በነፃነት ሕዋስ
ሲቀሰቀስ ትንሣኤዋ
ተግ ሲል ሲንር ትቢያዋ
ብር ትር ሲል ጥሪዋ
ድው -እልም ሲል ጋሻዋ
ሲያስተጋባ ከበሮዋ
ሲያስገመግም ዳኘው መድፍዋ
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ መቻል ያባ ዳኘው
ያባ ነፍሶ ያባ ቃኘው
ያባ በለው በለው ሲለው
በለው -በለው -በለው -በለው !
ዋ !....ዓድዋ……
ያንቺን ጽዋ ያንቺን አይጣል
ማስቻል ያለው አባ መቻል
በዳኘው ልብ በአባ መላው
በገበየሁ በአባ ጐራው
በአባ ነፍሶ በአባ ቃኘው
በለው ብሎ፤በለው -በለው !
ዋ !...ዓድዋ… .
ዓድዋ የትላንትናዋ
ይኸው ባንቺ ሕልውና
በትዝታሽ ብፀዕና
በመስዋዕት ክንድሽ ዝና
በነፃነት ቅርስሽ ዜና
አበው ተነሱ እንደገና።
……ዋ !...ያቺ ዓድዋ
ዓድዋ ሩቅዋ
የአለት ምሰሶ አድማስ ጥግዋ
ሰማይ ጠቀስ ጭጋግ ዳስዋ
ዓድዋ…… .

የካቲት -1964 ዓም -ዓድዋ (ፀጋዮ ገብረ መድኅን )

Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby revelations » 02 Mar 2012, 19:00

Image
Date: 1896

ጣሊያንና ከኤርትራ ያመጡዋቸው አስካሪዎች ራያ አፋፍ ላይ ሲጸልዩና ሲቀብሩ

Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby Beles » 03 Mar 2012, 03:33

ዮሃ
ምኒሊክ ለኤርትራ ለምን አልተዋጋም የሚል ስሞታ አቅርበህ የሚመስለኝን ለማለት ስሞክር ተሰርዞ ደረስኩበት:: ለማንኛውም ሰሞኑን በዚህ ጉዳይ እያሰብኩ ነበርና ከሞራል ግዴታና ወቅታዊ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር (practical) ብለን ብንከፋፍላቸው ምናልባት የተሻለ መልስ እናገኝ ይሆናል:: ኢትዮጵያ በኤርtra ላይ የይገባኛል ጥያቄ ካላት ያ መብት ከግዴታ ጋርም የተያያዘ መሆን ይገባዋል:: ከግዴታው አንዱ ከባዕድ አገዛዝ መከላከል ነው:: ይህ አስተሳሰብ በተለይ በዛሬ ጊዜ ላይ ሆነን ስንመለከተው የበለጠ ትክክል ነው የሚል ግምት አለኝ:: ይህ እንግዲህ በኢኮኖሚም ሆነ ቤእውቀት በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ አስተሳሰብና አመለካከትን ይጠይቃል:: ኢኮኖሚ ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽዖ አለው:: በቀላሉ በግለሰብ ደረጃ እንኳን ኪስህ ሞላ ሲልና ሲጎል ከአንደበትህ የሚወጣው ድምጽ ይለያያል:: አንደኛው የሚለማመጥ ሲሆን ሌላኛው በራስ መተማመን ያለበት ጎርነን ያለ ነው:: ለአብዛናው ሰው ማለት ነው:: አንዳንድ ግን አሉ በድህነታቸውም ቢሆን ክብራቸውን አቅማቸው እስከቻለ ድረስ ለማስከበር ወደኋላ የማይሉ::
እንግዲህ ከዚ አንጻር ምንም እንኳን ምኒሊክ ጣሊያንን ባህር ውስጥ ገፍቶ በጣላቸው ብለን ብንመኝም አቅሙን ስናገናዝበው ግን የሰራው ስራ ምን ያህል ጀግንነት የተሞላበት እንደሆነ መጋንዘብ እንችላለን:: በየትኛውም መለኪያ ላይ የወቅቱን ጣሊያንና ኢትዮጵያን ብንመዝን ምኒሊክ ተሸንፎ እንደ ቴዎድሮስ ራሱን መግደል ነበረበት:: ምርኮኛ እንደማይሆን ጥርጥር የለውም:: ለዚህም ተዘጋጅቶ እንደሄደ ከአዋጁ ማንበብ ይቻላል:: የተገኘው ድል በሚኒሊክና በጦሩ የሂሊና ጥንካሬ የተገኘ (እምነት ካለህ እግዚአብሄር ታክሎበት) እንጂ ሰው በሚመካበት በገንዘብ, በዕውቀት, በጉልበት የተገኘ አይደለም:: ለዚህ ነው ይህ ድልና ለዚህ ድል ያበቁት ጀግኖች በታሪክ ወደር የማይገኝላቸው ድንቅ መባል የሚገባቸው::
አንድ ደጋግመው ኤርትራዊያን (ከየት እንዳመጡት አላውቅም) ኢትዮጵያውያን የኤርትራን መሬት እንጂ ህዝቡን አይፈልጉትም የሚባለው ነገር ነው:: ምንም እንኳን የኤርትራ መሬት በጣሊያን እጅ ቢወድቅም ኤርትራዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ ያላቸውን ክብርና መብት ተነፍገው እንደማያውቁ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ውስጥ የነበራቸውን ድርሻ በማየት መረዳት ይቻላል:: እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እንዲያውም በኢትዮጵያ ላይ ከሌላው ኢትዮጵያዊ የበለጠ ሃብት, ስልጣንና ከዚያም ጋር ተያይዞ የሚመጣው መብት እንደነበራቸው ምስክር ሆነን ያየነው ነገር ነው:: በጣም የሚገርመው ኤርትራዊያን ይህንን መብት የተነጠቁት በነጻ አውጪዎቻቸው መሆኑ ነው::

Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby yoha » 03 Mar 2012, 05:04

Beles wrote:ዮሃ

Beles !

ልጽፍ ጀምሬ የነበርው በኔ አመለካከት ሚኒሊክን እንደ ጀግና ሳይሆን እንደ አንድ ተራ መሃይም መሪ ነው የማያቸው ምክንያቱም ምንም ዛሬ ኤርትራና ትግራይ ህዝብ መቃቃር ቢኖርም የሁለት ህዝብ የዘር ግንድ አንድ ከመሆን አልፎም አንድ አገርም የነበረ ሲሆን በሚኒሊክ አማካኝንት ከጣሊያን ጋ ሶስት ግዜ መዋዋል ኢትዮጵያ ኤርትራን አጥታለች በሌላ መልኩ የአድዋ ድል ለየኢትዮጵያ ህዝብ እንደአኩሪነት የጠቀሳል በሌላው መልኩ ደግሞ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ነበረች ካልንና የኤርትራ ህዝብ ለ70አመታት በጣሊያን ሲበደል እንደቆየ የሚገልጽ አንድም መጽሃፍ በኢትዮጵያ ታሪክ መጻህፍት ውስጥ የለም ታዲያ እንዴት አድርጎ ነው የህ ሁለት ተጻራሪ ጉዳይ አብሮ የሚሄደው ወይ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ነበረች ያ ሃቅ ካልሆነ ደግሞ ኤርትራ ለ70 አመታት በቅኝ ስለዋለች የኢትዮጵያ አካል ላትሆን ነው ማለት ነው :: አይ አይሆንም ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል ነው ብለን የምንካራከር ከሆነ እንግዲያውስ ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ውስጥ ቅይታለች ሊባል ያስችላል መቼም ይህ አባባል ብዙ ጉረኛ ኢትዮጵያውያንን ሊያስቆጣ ይችላል ይሁን እንጂ ሃቅ ከሚያንቀኝ እውነትን ማሳወቅና ማወቅ ያለብኝ ስለመሰለኝም ነው :: ይህ አባባል ምንም ጥቅም ላይኖረው ይችላል ምክንያቱም አሁን ኤርተራም አገር ስለሆነች ማለት ነው ቢሆንም ስህተት ከመሪዎች እንጂ ከህዝብ አይመጣም ከሚኒሊክ እስከ መለስ ኢትዮጵያ ምንም አኩሪ የመሪ ታሪክ የላትም የአድዋ ድልም የኢትዮጵያ ህዝብና አርበኞች ድል እንጂ የነሚኒሊክ ድል አይደለም በኔ አመለካከት ሚኒሊክ አሳፋሪ መሪ ነበሩም ባይ ነኝ በርግጥ ባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ አስተዋይና ብልህ እንደነበሩ ታሪክ ሁሌም ያወሳቸዋል :: በመጨረሻም ዛሬ የደረስንበት በኢትዮጵያ ህዝብና በኤርትራ ና በትግራይ ህዝብ ተለያይቶ መኖር ዋናው ተዋንያን ሚኒሊክ ለሱም ከጣሊያን ጋር ያደረጉት ውል ምስክር ነው :: እንዳውም ለዚህ ሁለት ወንድማማች ህዝብ ደም መፋሰስና ኢትዮጵያ አሁን ላለችበት ደረጃም በቅታለች::

በለስ ! ሚኒሊክ ለምን አልተዋጋም ለማለት አልነበረም አለመዋጋት በብዙ ጉዳይ ሊገለጽ ይቻላል ግን ህዝብንና አገርን የሚያክል ነገር ለ70አምት ትተህ በቅኝ ግዛት አልዋልኩም ነገር ግን የኤርትራን ህዝብ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ ለጣሊያን ፊርሞ ከመሽጥ ምን ይለየዋል, ለዚህም ነው በኢትዮጵያና ኤርተራ ህዝብ ያን ያህል ልዩነት ብሎም ደም መፋሰስ ያስከተለው መቼም ብዙ ኢትዮጵያዊ ሃቅን ስለማይወድ ሊከፉ ይችላሉ ኢትዮጵያ በጣልያን ተገዝታለች የአድዋ ድል አኩሪ ታሪክም ነው ለህዝቡ እንጂ ለመሪ ሳይሆን::

Next Page

Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Bwendimu, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Gurezza, Rhino, TurnitinBot [Bot]