Ethiopian News and Opinion Forum


Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby Beles » 04 Mar 2012, 07:04


[url]
የኤርትራ ህዝብ ችግር እንዳንተ አባባል ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የ70 አመት ቸልተኝነት ነበር[/url]
ከንዲህ ዓይነት የሃላፊነት ሽሽት ጋር, ከንዲህ ዓይነት ጭፍን ክህደት ጋር የሰለጠነ ውይይት ማካሄድ አስቸጋሪ ነው:: ለነገሩ ይህ እንደ መወያያ, ለመማር ወይም ለማስተማር የሚቀርብ ሃሳብ ሳይሆን, ተቀናቃኝን ለማንበርከክ የሚደረግ ስለሆነ መልስ መስጠቱ ብዙም ፋይዳ አይኖረውም:: ችግሩ ከታሪክ አለመማር ላይ ነው:: ይኼ ውሸት ውድቀትን አምጥቶባችኋልና ተውት ነው:: እናንተ ደግሞ አይ ካፈርን አይመልሰን ነውና ቀጠላችሁበት:: ከዚህ እስካልተማራችሁ ድረስ ችግሩም, ሞቱም ይቀጥልኣል:: ዶር በረከት ኃብተስላሴን ስሙ::



Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby revelations » 04 Mar 2012, 12:56


Image
Celebration of the 116th Adwa victory in Ethiopia!



Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby Semira » 04 Mar 2012, 13:05


yoha wrote:እንደማውቀው ግን የሁለተኛው ጣሊያን ወረራ ንጉስ ሃይለስላሴ ለመሸሻቸው በብዛት አርበኛው የሚናገርበት ጉዳይ ሆኖ ሳለ የኢትዮጵያ ታሪክ ግን እንደተዋጉ ነው የሚያሳየው


አይ ወዳጄ: ርእስ እየቀየርክብኝ ተቸገርኩኝ እኮ:: የምናወራው በምኒሊክ ግዜ ስለነበረው ሁኔታ ሆኖ ሳለ አንተ ግን ወደ ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ወሰድከኝ:: አዎ: ሀይለስላሴ በሁለተኛው የጣልያን ወረራ ሽሽተዋል:: ግን እኔ ትክክል አደረጉ እላለሁ:: ምክንያቱም ወቅቱ ተልውጦ ነበር:: እንደድሮው በጦር ሜዳ ከማለቅ በውጭ league of nation ቀርበው የፋሽስትን ወረራ በህጋዊ መንገድ በማቅረባቸው የኢትዮጵያ አርበኞች ለውጊያ የሚያስፋልጋቸውን እርዳታ ከእንግሊዝ በሱዳን በኩል ለማግኘት በቅተዋል:: ሌላው ማሰብ ያለብህ: ኢትዮጵያ ህዝብ በአብዛኛው በመሪ ያመልካል:: መሪው ከተመታ: ከተገደለ ወይንም ከተማረከ: ተስፋ የመቁረጥ እና የመበታተን መጥፎ ባህል አለው:: የአጼ ዮሃንስን ታሪክ ብትመለከት: የሱዳን ደርቡሾች በውግያው ተሸንፈው ሳለ: አጤ ዮሃንስ በጥይት በመቁስላቸው ብቻ የኢትዮጵያ ጦር ለመሽሽ በቅቶ የዮሃንስ ሬሳ ለመያዝ በቅቶኣል:: ሀይለስላሴ በያዝ ወይንም ቢገደል ኖሮ ለፋሽስቶቹ ለጣልያኖችና ለአሽከሮቻቸው አዝካሪ እና ባንዳዎች ትልቅ moral boast ነበር:: እንዲሁም ሃገሩ ሁሉ ተስፋ በመቁረጥ ለወራሪው ይንበረከክ ነበር:: አንዳንዴ ነገሮችን ከሚያመጡት consequence ጋር አጣምሮ መመልከት ተገቢ ይመስለኛል::

ታረክ እንዳልከው ጸሃፊው ተጽእኖ ያሳድርበታል:: ነገር ግን ከአንድ ወገን የወጡትን የኣመራር አካላት ወይንም ህዝብ ጠዋት ማታ መወንጀል (አንተ እንደምታደርገው) ተገቢ አይደለም:: እኔ በ/ሀይለስላሴም በደርግም ግዜ ኖርያለሁ:: ነገር ግን አንድም ቀን የዮሃንስ ክህደትና የአሉላ ኤርትራን ለመሸጥ ያደርጉት የነበሩት ድርድር በ media/book/publications ሲተረት ሰምቼ አላውቅም:: ይህ የሆነው አመራሩ ለሃግር አንድነትና ደህንነት ካላቸው የቀና አመለካከትና አስተሳሰብ የተነሳ ነው:: ነገር ግን በወገኖችህ ዘመን: የአማራ ክልል ያፈራቸው ጀግኖችና አመራሮች ዘወትር ሲተቹ እና ሲሰደቡ ነው የምናየው:: ከሁለት ቀናት በፊት ስለአድዋ ታሪክ በ tv-Tigray የተሰራጨውን documentary (in tigrigna) ስከታተል ነበር:: በዛ ዶክመንታሪ: አንድ ግዜ እንኩዋን የምኒሊክ ስም አልተጠቀሰም:: ይህ የሚያሳየው ወገኖችህ ምን ያህል ለህዝብ እና ለሃገር ጠንቅ እንደሆኑና ቢቻላቸው አኩሪ ታሪክን ለማጥፋት ወይንም ለመሰረዝ ወድሖዋላ እንደማይሉ ነው:: አንተም ከዚያው የበቀልክ ስለሆንክ: በምኒሊክ ላይ የምታወርደው የ ስድብ እና የነቀፋ ጋጋታ አይደንቀንም:: አንተ ባታከብረው: ምኒሊክ በአለም ደረጃ የሚዘከር አኩሪ ታሪክ አስመዝግቦ ያለፈ ስመጥር መሪ ነው::



Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby yoha » 04 Mar 2012, 19:38


Beles wrote:[url]
የኤርትራ ህዝብ ችግር እንዳንተ አባባል ሳይሆን የኢትዮጵያውያን የ70 አመት ቸልተኝነት ነበር[/url]
ከንዲህ ዓይነት የሃላፊነት ሽሽት ጋር, ከንዲህ ዓይነት ጭፍን ክህደት ጋር የሰለጠነ ውይይት ማካሄድ አስቸጋሪ ነው:: ለነገሩ ይህ እንደ መወያያ, ለመማር ወይም ለማስተማር የሚቀርብ ሃሳብ ሳይሆን, ተቀናቃኝን ለማንበርከክ የሚደረግ ስለሆነ መልስ መስጠቱ ብዙም ፋይዳ አይኖረውም:: ችግሩ ከታሪክ አለመማር ላይ ነው:: ይኼ ውሸት ውድቀትን አምጥቶባችኋልና ተውት ነው:: እናንተ ደግሞ አይ ካፈርን አይመልሰን ነውና ቀጠላችሁበት:: ከዚህ እስካልተማራችሁ ድረስ ችግሩም, ሞቱም ይቀጥልኣል:: ዶር በረከት ኃብተስላሴን ስሙ::





በመጀመሪያ እኔ ስለ ኤርትራ የግል ስሜቴን ነገርኩህ እንጂ ከራሴ በቀር ለሌላ ሰው መብትና ፍላጎት መናገርም አልችልም አንድ ግለሰብ ኤርትራዊም ሆነ ኢትዮጵያዊ ኢትዮጵያዊነቱን አልፈልግም ካለ ግድ መሆን አለብህ ብለህ ማስገደድ ተገቢም አይደለም ባንጻሩ የኤርትራን ችግር ቅኝ ገዥዎች ቢያምጡትም ዋናው ተባባሪ የኢትዮጵያን አስተዳዳሪዎች ለመሆናቸው ግልጽ ስለሆነ ብንከራከር ምንም ጥቅም አያመጣም ምክንያቱም አሁን ኤርትራ የእትዮጵያ አካል ስላልሆንች ስለ ዶክተር ሃብተስላሴ ላልከው በመጀመሪያ እሱ ራሱ ማነው? ትላንት ማንስ ነበር ብለህ ብትጠይቅ የተሻል መልስ ልታገኝ ትችላለህ እኔ ግን ትንሽ ልነግርህ ዶ/ር በረከት ሃብተስላሴ ኤርትራ የኢትዮጵያ አካል አይደለችም ብሎ ጫካ ገብቶ ጠመንጃ ይዞ የነበረ ከዛም ትቶ የመንግስቱ {ደርግ} ሰራተኛ ሆኖ ሲሰራ የነበረ ኤርተራ ነጻ ከወጣችም አብሮ ሲሳተፍ የነበረና ትልቅ የስልጣን ጥም ያለበት ሰው በመሆኑ የሱ ኢትዮጵያዊነት መጣም ቀረ ጥቅም የለውም በግምትም አንተ ትግሬ ወይም ኤርትራዊ ልትሆን ትችላለህ ማንነት የግል ነው ስትፈልግ እንደ ልብስ የምትቀይረው አይደለም ለዚህም ነው አስቀድሜ ግድ ኢትዮጵያዊነት የለም ምክንያቱም ማንነት የግል ክብር ስለሆነ ስለኤርትራውያን አትቸገር ባይሆን ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው ብለህ አርቀህ ተመልከት በባዶ ሜዳ ኢትዮጵያ አገሬ ፋይዳ የለውም እድሜ ለወያኔ መሪዎች ዛሬ የኢትዮጵያ ህዝብ ከገባው አዘቅት እንደሚወጣ ጸሎት ማድረግ አለብን የኤርትራን ችግር ለኤርትራውያን እንተወው ካለዚያ ያዛኝ ቅቤ አንጎች ልንሆን ነው::

ሰሚራ ! መሪዎቹ አማራ ይሁኑ አይሁኑ አላውቅም በርግጥ መለስ አማራ ላይሆን ይችላል መንግስቱም አማራና ኦሮሞ ነው እኔ አባቱን አውቃቸዋለህ አባ ሃይለማርያምን ባጠቃላይ ስራቸውን እንጂ ማንነታቸውን አለወቀስኩም ለምሳሌ እኔ አፄ ቴድሮስን በጣም ነው የምወደው ምክንያቱም ዘርና ሃይማኖትን የማይለይ ታሪክ ስለነበርው ለበላይ ዘለቀ ያለኝም ክብር ትልቅ ነው እነዚን ግለሰቦች ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በክፉ ሚያነሳ አለ ብዬ አላምንም ስለዮሃንስና አሉላ አገር ሸጠው ሊሆን ይችላል በዶክመንት ማረጋገጥ ግን አይቻልም ሚኒልክም የኢትዮጵያ ንጉስ የሆነው ከዮሃንስ ሞት በሃላ ስለሆነ የጣሊያን ጦርነትን ያአድዋ ድል ታሪክ ከሚኒሊክ ታሪክ ጋር አብሮ የሚሄድ በመሆኑ የውጫሌውም ሆነ ሌሎች ውሎች ጅቡቲን ለፈረንሳይ መሸጥን ጨምሮ በሚኒሊክ ፊርማ ስለሆነ ይህንን መውቀሴ አማራ ስለሆነ ነው ካላችሆ አምላክ ይቅር ይበላችህ አስኪ እሺ የኤርትራንስ ጉዳይ በምክንያት እንተወው የአቅምም ማጣት እንበለው የጅቡቲንስ ጉዳይ ፈረንሳይ አልወረርን አንስቶ መስጠት ምን ይባላል ሰዎች እኔ አሁን ሚኒሊክንም ሆነ ሌሎች መሪዎችን ከመቃብር አንስቼ ክስ ልመሰርትባቸው አልነበረም እኛ በዛ ስህተት መመጻደቅ የለብንም ታሪክ እራሱን በመድገም ለመለስ ዜናዊ ስለዳረገን ካዛ ስህተት ምንወጣበትን ታሪክ ብናልም መልካም ነው::



Re: ምኒሊክና ኣድዋ

Postby yoha » 04 Mar 2012, 20:58


Semira wrote:
yoha wrote:አሉላማ ሚቻለውን ሞክሮ ነበር ጣላት በዝቶበት ካልሆነ አንዱም ጠላት ሚኒሊክ ነበር ምክንያቱም ሚኒሊክ የዮሃንስ ገባሪ ሆኖ ዮሃንስ ደርቡሽን ሲዋጋ ሚኒሊክ በአፈር መሬት የጦር መሳሪያ ሲያከማች ነበር ይህም ታሪክ ነው ሚኒሊክ ይህንን ሁለት ትግርኛ ተናጋሪ ህዝብ ለመነጣጠል ያላረገው የለም ለዚም ነው ሁለት ትግርኛ ክፍለ ሃገር የነበረው ሃይለስላሴም ኤርትራን በስጦታ ተረክበው ያንኑ መከፋፈል ነበር ስራቸው በዛው መጠንም ያመጣባቸውን ጦስ አይተናል ለኛም ለዛሬው ትውልድ ሞልቶ ተርፎናል::


ወዳጄ: ሳታውቀው ማንነትህን ገልጽህ:: ከወያኔ ድንጋይ ማምረቻ ኮሌጀ(civil service college) እንደተመረቅህ ራስን አጋለጥህ:: ምክንያቱም: ይህ አንተ የምታወራው : ምኒሊክ ሁለቱን ትግርኛ ተናጋሪዎች ለመለየት ያደረገው ነው የምትለው የህጻን ወሬ መለስ ዜናዊና ስብሃት ነጋ የጻፉልህ ነው:: ሃቁ ግን በትግራይና በትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን መሃከል የነበረው ጸብ ምኒሊክ የፈጠረው ሳይሆን ስር ሰዶ የነበረና ልክ እንደአሁኑ ግዜ የትግራይ ገዚዎች ለማስገበር ብዙ ግዜ የዘመቱበትና በኤርትራ የምይወደድ ጉዳይ ነበር:: ለምሳሌ ራስ አሉላ በዮሃንስ ትዛዝ ምድረ ኤርትራን እየወራሩ ሕዝቡን ያሽብሩት እንደነበር ታሪክ ይነግረናል:: እንድያውም: በአድዋ ውጋያ የተማረኩትን ኤርትራውያን አስካሪዎችን ምኒሊክ ምህረት ለማድረግ ባሰቡ ግዜ ከወገኖችህ ከትግራይ ገዚዎች ብዙ ተቃውሞ ደርሶባቸዋል:: እውነት ምኒሊክ እናንተ እንደምትሉት ከፋፋይ ቢሆን: እስካሪዎችን በ40 ግርፋት ብቻ ነጻ ሊያወጣቸው ነበር:: ወገኖችህ ግን እናዚያን ማስኪን ኤርትራውያን ነፍሳቸውን ካላጠፋን ወይ ፍንክች ስለማለታቸው ታሪክ ዘግቦታል:: ነገሩ ይህ ሆኖ ሳለ ያንተው ወገኖች የኤርትራውያን ጠላት ሆነው ሳሉ ምንሊክን የኤርትራውያን ጠላት እድርገህ ማቅረብህ የመለስ ዜናዊ ምሩቅ ካድሬ መሆንህን ይገልጻል::

ሌላው ደግሞ: ምኒሊክን በመተማ ዘመቻ ከዮሃንስ ጋር ባለመዝመቱ ከምትወነጅል: ለቴዎድሮስ ሞት ዋና ምክንያት የሆነውን ዮሃንስን ከመውቀስ ለምን እንደተቆጠብክ ሰው ሊጠይቅህ እንደሚችል ልብ አድርግ:: እነ ራስ አሉላና የትግራይ ራሶች ምኒሊክን ለማቃት ለጣልያን ምድረ ኤርትራን እንደገጸ በረከት ያሰጡበትን የታሪክ ማስረጃ ለጥፌልህ ነበር:: ነገር ግን መልስ ስለሌለህ ዝምብለህ ዘለልከው:: ለኤርትራውያን አዝካሪዋች ከጣልያን : ከቱርክ ከዝያም በፊት ከግብጾች ጋር መተባበር ዋናው ተጠያቂዎች የወገኖችህ የትግራይ ገዢዎች ጭካኔ የተሞላበት የማያቅዋርጥ ወረራ እንጂ አንተ እንደዘባረቅከው ምኒሊክ አይደለም::



መለስ ከኔጋ ምንም ሊያገናኘው ሚችል ጉዳይ የለም ምናልባት የኢትዮጵያን ታሪክ የነገስታት ተረት ስላለ ልንጠላው እንችል ይሆናል ለነገሩ እውነቱን ነው ሚኒሊክ ስንት አሽከር ነበራቸው ሃይለስላሴ ስንት በርዝደይ አከበሩ እየተባለ የተተረከ ታሪክን መለስም ሆነ ማንኛውም ሰው ቢቃወም ተገቢ ነው ለነገሩ አሁንም ቶሎ አትፍረድ እኔ ከወያኔም ሆነ ከማንኛውም ፓሪቲጋ የሚያገናኝ ምንም ጉዳይ የለኝም እኔ መለስን ስለጠላሁት መጥፎ ሲሰራ ኤርትራዊ ደግ ሲሰራ ኢትዮጵያዊ ነው ከሚሉ አይደለሁም የወያኔን የበረሃ ትግል የመብት ትግል ነበረ መጨረሻው አላማረም እንጂ ማለት ከወያኔ ኮሌጅ መመረቅ አይደለም እኔ መለስን ከመጥፎ ኢትዮጵያዊ ለይቼ አላየውም ለኤርትራ ያለውንም አስተያይት በግልጽ አስቀምጦአል "የየአይን ቀለም" ስለ የታሪክ ማስረጃ ላልከው ያው የነገስታት ታሪክ እንዳመቻቸው የለጠፉትን ከሆነ አመሰግናለሁ እሱ ተመርጦ ለናሙና የተቀመጠ ስለሆነ እዛው አንኮበር ይቀመጥ ምናልባት መለስን ልንጠላው እንችላለን በኢትዮጵያ ታሪክ ሲመጣ ግን ሃቁን ነው ያስቀመጠው ይሁን እንጂ ዘንድሮ ማናቸውም መሪዎች የግል ጥቅምን ስለሚያስቀድሙ ለታሪክ ያላቸው እምነትና ፍላጎት እምብዛም ነው መለስም ከዛ ምድብ ውስጥ ነው :: ወያኔ ማለት 7000 ሺ የተበደለ የትግራይ ህዝብን ሚወክል ድርጅት ነበር በወቅቱ አሁን 7 ሰዎች ብቻ ቀሩበት እንጂ ስለዚህ እኔ ማንኛውም ለመብቱ የሚታገለውን ሁሉ እደግፋለሁ ኦነግንም ሆነ ኦብነግ ጨምሮ ማለት ነው ምክንያቱም አሁንም በመሪዎች የተነሳ ታሪክ እራሱን ስለደገመ ::


Previous Page


Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: amantu, Bing [Bot], elias, ER1, ereview, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Halyeyga, Kibret, manny, tarku, YEBANDAMERZE