by Obamajr. » 23 Apr 2012, 08:09
ዘረኛው የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በፈጠረው ኢኮኖሚያዊ ችግር ክፉኛ በተመታው አድስ አበባ ከተማ ውስጥ
“ተነሱ የሚል ጥሪ ወረቀት” በስፋት እየተበተነ መሆኑ ተገለጸ
April 19, 2012 አማርኛ ዜናና መግለጫ
የኢትዮጵያ ወጣቶች ተስፋ ድርጅት በሚል ስያሜ የሚንቀሳቀስ አንድ ቡድን በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች ተነሱ የሚሉ የጥሪ ወረቀቶችን መበተኑን የግንቦት 7 ዘጋቢ ከአዲስ አበባ በላከው ሪፖርት ገለጸ።
እንደዘጋቢያችን ሪፖርት በተለያዩ የአዲስ አበባ ከተሞች ውስጥ በተበተኑ ወረቀቶች ላይ የሰፈረው መል ዕክት ” የትግላችን አላማ ሀገራችንንና ራሳችንን ነጻነት ለማቀዳጀት ነው!!።” የሚል እና “ትግላችን በገዛ ሀገሩ ህይወት እየጨለመበትና ተስፋ እየቆረጠ ሀገሩን ጥሎ ሲሰደድ በረሀና ባህር እየበላው ወላጅ እናቱ የት እንደወደቀ ሳታውቅ በገፍ መርገፍ የጀመረውን ወጣት ሰቆቃ ለማስቆም የሚደረግ ትግል ነው!!።” ፤”ወያኔ በቃ!!፣ መለስ በቃ!! ፣ በወያኔ ስርአት በባርነት ከማለቅ የተለየ ነገር የለምና ለነጻነት ታገል!! የሚሉ ናቸው።
አፋኙ የመለስ ዜናዊ አገዛዝ በሺዎች የሚቆጠሩ የጸጥታ ሰራተኞችን፤ ፖሊሶችንና ሰቪል ለባሽ ወታደሮችን በየመንገዱና ጉራንጉሩ እያንቀሳቀሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት እንዲህ አይነት “የተነሱ” ጥሪ ወረቀት መበተን መቻል የሚያመለክተው አገዛዙ በቤተመንግሥት ዙሪያ ካሉት ምርጥ ታማኞቹ በቀር በሌሎች ብዙሃን እየተተፋ መሆኑን አመልካች ነው ተብሎአል።
ከምርጫ 97 ወዲህ በወያኔ አገዛዝ ላይ ተቃውሞአቸውን ለመሳማት እና ለለውጥ ለመታገል የሚፈልጉ ወጣቶች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱ ይነገራል።
"ምርጥ ታማኞቹ "- ፈሶ አንዱ ምርጥ ታማኝ ወያኔ ኣሽከር ነህ:: አስር ምርጥ የወያኔ አሽከሮች በኢር ውስጥ አሉ [I am not going to call your name.All members knows you for sure.]
የወያኔ ምርጥ አሽከሮች አፈር ብሉ