Ethiopian News and Opinion Forum


Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby revolutions » 03 Jun 2012, 12:56



ገላው
ልጅ ወለደ


ጀግና አምጣ ጀግና ወልዳ አቁማለች፣
እናት ምድር ልጅ ለመውለድ አርጣለች፣
አርባ ዓመታት አልፏት መክና ተክዛለች፣
ብለን አዝነን ቱቢት ለብሰን ባዘንበት፣
ጀግና ወጣ ! ዘራፍ ብሎ ! ከኢሳት ቤት፡፡
የኛ ! ቧዚዝ! የኛ ጀግና ! የቴዎድሮስ ልጅ፣
ጃሎ ! ብሎ በአዳራሹ አዋጅ ቢያውጅ፣
የት ይደበቅ ? የት ይሸገግ የሹምባሽ ልጅ ?
አይኑ ብልጥጥ ! ፊቱ ድንግጥ ፣
እስኪመስል ያችን ድንቢጥ ፣
አሸበረው የገላው ልጅ ያንን አይጥ፡፡


እንግዳ ታደሰ / ኦስሎ ኖርዌይ

Image





Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby revolutions » 04 Jun 2012, 05:35



Thank you ESAT ! You are appreciated !!



Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby revolutions » 04 Jun 2012, 10:06



አበበ ሲያብብ


እንደ አበበ አረጋይ አበባ ቢቂላ

የሚያብብ አበበ የት ተገኘ ሌላ?

አርበኛው አበበ ጣሊያንን የከላ

የቢቂላ አበበ ብዙ ወርቅ የበላ

የገላው አበበ በመለስ ላይ ሰላ

ወያኔ ሰመጠ በሻርክ ተበላ

በስብሰባ መሃለ የአበበ ቃል ጐላ

መንግስታት ሲመክሩ ምን እንደሚበላ

ገዳይ አምባገነን ራሱ ተበላ

ኢትዮጵያ እምትሻው ፍትህ ነው ነጻነት

ወያኔ ገለል በል ስለማታውቅበት

የፍትህ ጠበቆቸ ወርደዋል እስር ቤት

ሰው አስሮ አይወራም ስለ ምግብ እጦት

የጫካው አንደበት በአንድ ቃል ታሠረ

የአምባገነን ዱላ በ’ርሳስ ተሠበረ

ኢትዮጵያ ስታብብ አበበ ያብባል

ትውልድ ተከፍሎ ትውልድ ይከበራል


(ወርቅእሸት ቸርነት)



Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby revolutions » 04 Jun 2012, 10:14



አፍ ዘጊው አፉ ሲዘጋ፣ መተንፈስ ሲያቅተው:-
መለስ ዜናዊ የራሱን መድሃኒት ሲቀምስ

Image



Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby revolutions » 04 Jun 2012, 11:35




ታንክ በጎራዴ!



ጣት ምላስም ሳይቀር አንገት የሚቀጣ
መቸም ለከት የለው የሚለው አያጣ
ኮሮጆ ሊሞላ ሊቀጥፍ ሲቃጣ
ጀግናው ወግድ አለ ሰው ጤፉ ተቀጣ


አገር እንደሸቀጥ እየቸበቸበ
በቁም የገደለን አእላፍ ያስራበ
ለስደት ለውርደት ወገን ያካለበ
ምሁር ጋዜጠኛ በግፍ የሸበበ
በብረት በሰላይ እንደተከበበ
በአለም አደባባይ ራሱን እንደካበ
መለከት ተነፋ መልአኩ ረበበ
ሰላም ለአንት ይሁን አርበኛው አበበ

ከልመና ጉርሻ ከእርጥባን ጎተራ
ነፃነት ይከበር አገርም ትፈራ
የሰው ልጅ ክቡር ነው ሁሉም የአዳም ልጅ
ይወገድ ጥላቻ ሰላም ፍቅር እንጂ
አይበደል ድሃ ፍርድም አይግዋደል
ምሁራን ይፈቱ ፍትኅ ይደላደል


እንዲህ ነው ጀግንነት በስምም በግብር
እንደተናገረ ታላቁ እስክንድር
ልበ ሙሉ ጀግና በጥበብ በዘዴ
ሃይማኖተ አበው ታንክ በጎራዴ


ታንክ በጎራዴ የሚማርከው
ሮምን በባዶ እግሩ የጠቀጠቀው
በነጎድጉዋድ ድምጹ ዲሲን ያራደው
ሹምባሹ ሲደፋ ልቡ ሲከዳው
ሆ! ብሎ ተነሳ ድፍን አርበኛው
ለመለመ ዛፉ አበበ ገላው!!!



ፋኑኤል አበበ
ኒውዮርክ



Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby Shewit » 04 Jun 2012, 12:52


ተልባ ቢንጫጫ
ባንድ ሙቀጫ

ዘራፍ ማለቱ
በያገሩ ማግዋራቱ
ሙጉቱ
መዛቱ
ምንም አልፈየደ ከንቱ

if you are looking for a hero - look at the selfless Qeshi Gebru and Amora. True you cannot be one because you are created to admire!



Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby Aragaw » 04 Jun 2012, 14:13


ተልባ ቢንጫጫ
ባንድ ሙቀጫ


ድሮ ደርግም ወያኔን እንድዚያ ነበር የሚለው። አትርሳ በሰፈሩት ቁና መሰፋር እንደማይቀር።የጊዜ ጉዳይ ነው::

ዘራፍ ማለቱ
በያገሩ ማግዋራቱ
ሙጉቱ
መዛቱ
ምንም አልፈየደ ከንቱ


ምንም አልፈየደ ከንቱ?
ይህው በየሄዳችሁበት ቤተክሪስትያን እንደገባ ውሻ እየተሰደባችሁ ትባረራላችሁ:: አበበ ገላው ያንን ጌታህን እንደቁራሪት የፈጠጡ አይኖቹ በረው ሊሄዱ አስኪደርሱ ድረስ አስደነገጠው:: ሳውዝ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጲያዊያን የውርደት ብልኮ አከናንቦ የመጣበትን ልመና አንኳ ሳይፈፅም በባዶ እጁ እንዲሄድ አደረጉት ከዚያ በላይ ምን ውርደት አለ?
እስኪ በናትህ ጌታህን በደንብ ተመልከተው!

Image



Re: Abebe Gellaw is My Hero! I Love ESAT

Postby Akele-Guzai » 04 Jun 2012, 22:21


Abebe Gelaw became a house house name in Ethiopia and Eritrea!

Previous Page Next Page


Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Degnet, Exabot [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Hawileyto, Majestic-12 [Bot], midwest, Zack