Ethiopian News and Opinion Forum


Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 19 Jul 2012, 08:23


የአቶ መለስ የጤንነት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል

ሐምሌ ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ላለፉት 2 ሳምንታት የኢትዮጵያውያንን ትኩረት ስቦ የቆየው የአቶ መለስ ዜናዊ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ተከትሎ የመከላከያ፣ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ማንኛውንም እንቅስቃሴ በንቃት እንዲከታተሉ ታዘዙ

የኢሳት የአዲስ አበባ ዘጋቢ አንድ የፌደራል ፖሊስ የአመራር አባልን በመጥቀስ እንደዘገበው የፌደራል ፖሊስ እና የደህንነት አባላት የአቶ መለስን የጤና ሁኔታ ተከትሎ በዋና ከተማዋ ወይም በዋና ዋና የክፍለሀገር ከተሞች ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን በፍጥነትና በቅልጥፍና መቆጣጠር የሚያስችል ” የአንድ ለአምስት” የጥቃት አመካከት ስልት ተግባራዊ እንዲሆንና ፖሊሶችም በዚሁ መሰረት ልምምድ እንዲጀምሩ ትእዛዝ ተላልፎአል።

በአሁኑ ጊዜ በአቶ መለስ ዜናዊ የተፈጠረውን የስልጣን ክፍተት ለመሙላት አቶ ስዩም መስፍን በዋና ተዋናይነት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ ምንጮችን ዋቢ በማድረግ ዘጋቢያችን ገልጧል። በህወሀት መንደር ውስጥ ያለው ግራ መጋባት እንደቀጠለ ባለበት በዚህ ወቅት፣ አቶ ስዩም ዋና ዋና የሚባሉ ነባር የህወሀት ካድሬዎችንና የመከላከያ አመራሮችን በማግኘት አገር የማረጋገቱን ስራ እንዲሰሩ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነው ።

ለሳምንታት ዝምታን መርጠው የቆዩት የዲፐሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትም የስልጣን ክፍተት እንዳይፈጠር በሚል ከመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ከአንዳንድ የተቃዋሚ ድርጅት አመራሮች ጋር መነጋገር መጀመራቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የአቶ መለስ ህመም ለህይወት አስጊ መሆኑን አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን መዘገብ የጀመሩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ዛሬ ሊሰጠው አቅዶ የነበረውን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰርዟል። ይሁን እንጅ አቶ በረከት የአቶ መለስን መታመም ለኤኤፍ ፒ አረጋግጠዋል። ኤኤፍ ፒ አንድ ዲፕሎማትን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የአቶ መለስ የጤና ሁኔታ እጅግ አሣሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። አቶ በረከት ግን አቶ መለስ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

አቶ ሽመልስ ከማል ሰሞኑን ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ” እንዲህ አይነቱን ወሬ የሚያስወራው ውሸት መፈብረክ ባህሪው የሆነው ድርጅት ነው” በማለት ኢሳትን መክሰሳቸው ይታወሳል።

መንግስት፤ የአቶ መለስን መታመም ያመነው፤ከሁለት ቀናት በፊት አዲስ አበባ በተካሄደው በ 19 ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ ላይ የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት በምስጢር የተያዘውን የመለስ መታመም ጉዳይ በአደባባይ ይፋ ካደረጉት በሁዋላ ነው።

ሪፖርተር ዛሬ ባወጣው ዘገባ ደግሞ አቶ መለስ የውጪ ህክምናቸውን ጨርሰው በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ፣ ይሁንና ወደ አገራቸው ቢመለሱም በቶሎ ሥራ አንደማይጀምሩ ገልጧል።

አቶ መለስ በከባድ ህመም እየተሰቃዬ እንደሚገኙ በርካታ ሚዲያዎችና ድረ-ገፆች በቤልጅየም ህክምና ከሚከታተሉበት የሴንት ሉክ ሆስፒታል የሚገኙ ምንጮችን እየጠቀሱ በዘገቡበት በአሁኑ ወቅት፤ ዘግይቶ ስለ መለስ ጤንነት ሁኔታ የዘገበው ሪፖርተር ፦”ለ21 ዓመታት ያለዕረፍት ከፍተኛ የአገር ኃላፊነትን ሲወጡ የቆዩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ የሕመማቸውም ምክንያት ካለባቸው የሥራ ጫና ብዛት የመጣ መሆኑ ተጠቁሟል” ብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወሰኑ ጊዜያት ካለባቸው ከባድ ኃላፊነት ርቀው ዕረፍት እንዲያደርጉ በሐኪሞቻቸው መመከራቸውን ምንጮች አክለው እንደገለጹለትም ጋዜጣው ጠቁሟል፡፡

ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት አቶ መለስን በሚታከሙበት ሆስፒታል ሄደው እንደጎበኟቸው የጠቀሱት የጋዜጣው ምንጮች፤ አምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ እስካሁን ድረስ ከጎናቸው ሆነው እያስታመሟቸው እንደሆነ ተናግረዋል።

ጋዜጣው፤በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ግርማ ብሩ፣ በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሥዩም መስፍን፣ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ በረከት ስምኦንና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩን የሚታከሙበት ቦታ ሄደው እንደጎበኛቸው አመልክቷል።

ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉት የግንቦት7 ራዲዮ ዘጋቢዎች ግን አቶ መለስ አሁንም እጅግ አደገኛ በሆነ የጤና ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ፣ ወደ ኢትዮጵያም አለመመለሳቸውን ገልጠዋል።

የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ አቶ መለስ ህክምናቸውን ከሚከታተሉበት ከቤልጅየም ሆስፒታል ወጥተው ከትናንት በስቲያ ምሽት አዲስ አበባ እንደገቡ ገልጦ ነበር።

ኢሳት ዛሬም ሴት ሉክ ሆስፒታል በተደጋጋሚ ቢደውልም፣ የአቶ መለስ ስም በበሽተኞች ስም ዝርዝር ውስጥ የለም የሚል መልስ አግኝቷል። ሁሉም የሆስፒታሉ ሰራተኞች የአቶ መለስን ስም ሲሰሙ ወዲያውኑ “እዚህ የሉም” የሚል መልስ መስጠታቸው፣ የሆስፒታሉ ሰራተኞች በጥየቃ መሰላቸታቸውን ወይም ሆን ብለው መረጃውን እየደበቁ መሆናቸውን ያመለክታል በማለት የኢሳት ዘጋቢ ገልጧል።

ባለፈው እሑድ በአዲስ አበባ በይፋ በተከፈተው 19ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ፣ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢኮኖሚ ልዩ አማካሪ በአቶ ንዋይ ገብረ አብና በአምባሳደር ቆንጂት ሥነ ጊዮርጊስ መወከሏ ይታወቃል።

ይሁንና አቶ መለስ ድነው ተመለሱም አልተመለሱም ከእንግዲህ ባላቸው የስልጣን ሀላፊነት ሊቀጥሉ እንደማይችሉ ሁሉም ወገን ያወቁት እና ያመኑበት ጉዳይ ሆኗል።

ለዚህም ይመስላል ሪፖርተር በዚሁ ዘገባው፤ ስለተተኪ ጠቅላይ ሚኒስትር ጉዳይ ፤የህግ ባለሙያዎችን ማነጋገሩን ገልጿል።

“የሕግ ባለሙያዎች ፣ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ -ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተክቶት ይሠራል፣ ይህ የሚሆነው ግን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አብላጫ ድምፅ ያለው የፖለቲካ ድርጅት በምትኩ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እስከሚመርጥ ድረስ ነው” እንዳሉት ጋዜጣው ጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በ5ኛው የአፍሪካና የቻይና የትብብር ጉባኤ ላይ ለመገኘት አቶ ሀይለማርያም ወደ ቻይና አቅንተዋል። አቶ ሀይለማርያም አቶ መለስን በመተካት ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። አቶ መለስ ካይሮ ውስጥ ተደርጎ በነበረው የ4ኛው የአፍሪካና የቻይና ጉባኤ ላይ ተገኝተው እንደነበር ይታወሳል።



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 19 Jul 2012, 14:30


Newaye Gebreab’s decree, no travelling abroad for TPLF warlords

The Horn Times newsletter July 19, 2012

by Getahune Bekele

Emboldened by the news coming out of Brussels that Zenawi is now blind and wheelchair bound, with no hope of
Newaye Gebreab’s decree, no travelling abroad for TPLF warlords

returning home, acting PM Neway Gebreab is cracking the whip in desperate attempt to keep the sinking TPLF ship afloat, and of course, to consolidate his position to become PM soon.

Known for his demonic temper and insatiable appetite for power, the warlord has already stopped the foul-mouthed Marxist Leninist League Tigraye veteran, Sibehat Nega from leaving the country for medical checkup in South Africa.

Furthermore, fearing mass exodus of criminal warlords and their corrupt spouses, Gebreab (pictured) has reportedly issued a decree that no senior TPLF member would be allowed to board a flight until the end of September.

“At this stage he dreads mass defection. Only diplomats who carry special permit or security clearance from Gebreab’s office will be travelling for state business” revealed the Horn Times reporter from Addis Ababa.

However, the ex Marxist guerrilla, Sibehat Nega did not take the snub kindly. According to our well placed sources inside the TPLF camp, the ageing harridan have vowed to de-throne Gebreab by joining the opposite camp of warlords led by acting PM-2,Tedros Adhanom.

The clash between Neway and Sibehat took place at Zenawi’s residence on Tuesday 17 July 2012, in full view of the stressed out and terror smitten TPLF cc members.

Although Neway, as a veteran himself, tries to confront and even rein in the Zenawi-spoiled hordes of Tigre warlords, reports are he lacks support.

A political analyst told the Horn Times that Neway is isolating himself from the power wielding Tigres by trying to build his support base among the untrustworthy clannish sycophants and the hoi polloi, otherwise known as “the Gujilles.”

“If Zenawi dies and anti TPLF insurrection explodes, Neway Gebreab will be the first to flee. He is one of the top war criminals wanted by the Ethiopians. Nevertheless, there is one man who is watching all this drama from the sidelines. A hardened war criminal. He has nowhere to go. Unless a strong opposition step up to the plate quickly, am afraid we are going to have a brutal military ruler in the form of the feudist Gen Samora Yunise “explains our political analyst who is following events in Addis Ababa.

http://ecadforum.com/blog1/newaye-gebre ... -warlords/



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 20 Jul 2012, 08:39


የጠ/ሚ መለስ ህመም ማነጋገሩን ቀጥሏል። ሪፖርታዥ (ደረጀ ሀብተወልድ፦ኢሳት)

ሪፖርታዥ (ደረጀ ሀብተወልድ፦ኢሳት)

ላለፉት 21 ዓመታት በስልጣን የቆዩት መለስ ዜናዊ፤ የዛሬ ሁለት ወር የቡድን ሀያ አገሮች በዋሽንግተን ዲሲ የሬጋን ህንፃ ውስጥ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ተገኝተው ገለፃ ሲያደርጉ ከጋዜጠኛPM Meles Zenawi አበበ ገላው ተቃውሞ ባጋጠማቸው ማግስት ያደረባቸውን ህመም ተከትሎ፤ ከሥራ ገበታቸው ላይ ከጠፉ በትንሹ ጥቂት የማይባሉ ጊዜያት አልፈዋል።

የአቶ መለስን መታመም ከሁሉ ቀድሞ ከሳምንታት በፊት የዘገበው ኢሳት፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጠና ታመው በቤልጂየም-ብራሰልስ ሴንት ሉክ ሆስፒታል ውስጥ ህክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን ይፋ አደረገ።

በማግስቱ በዋልድባ ስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክትና በአዲሱ ቴሌኮም ህግ ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የኮሙኒኬሽን ም-ሚኒስትሩ አቶ ሽመልስ ከማል፤ ከጋዜጠኞች ፦”መለስ ታመዋል ይባላል” በማለት ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሙሉ ጤንነት እንደወትሮው ሥራቸውን እያከናወኑ እንደሚገኙ በመግለጽ፤ “ታመዋል የሚለው የኢሳት ወሬ ነው” አሉ።

ኢሳትም፦ በአቶ መለስ የተያዙ በርካታ ፕሮግራሞች እየተሰረዙ መሆናቸውን መረጃዎችን በመፈልፈል ይፋ ማድረጉን ቀጠለ።

አቶ ሽመልስን ጨምሮ ሌሎች ባለስልጣኖች ደግሞ ፦”አቶ መለስ አልታመሙም፤ጤነኛ ናቸው” በማለት መከላከላቸውን ቀጠሉ።

በተለይ ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አንድ ዲፕሎማት ለፎርቹን ጋዜጣ፤መለስ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ እና በሚዲያ ከስተው የታዩትም ፤መክሳቱን ፈልገው “ዳይት” ላይ ስለሆኑ ነው” ማለታቸው፤ ብዙዎችን ፈገግ አሰኘ።

እንዲህ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት የአቶ መለስን መታመም በምስጢር በያዙበት ሁኔታ ነው 19ኛ የ አፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ የተጀመረው።

እናም…ስብሰባውን በንግግር ይከፍታሉ ተብለው የተጠበቁት አቶ መለስ የውሀ ሽታ ሆነው በመቅረታቸው፤ በምትካቸው የሴኔጋሉ ፕሬዚዳንት በንግግር ሊከፍቱ ወደ መድረክ ወጡ።
ፕሬዚዳንት ማኪ ሳል ለተናጋሪዎች ወደተዘጋጀው ስፍራ ብቻቸውን ካመሩ በሁዋላ ፦” ይህን ስብሰባ በንግግር መክፈት የነበረባቸው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ነበሩ፡፤ በህመም ምክኒያት ሊገኙ ስላልቻሉ እኔ ለመክፈት ተገድጃለሁ። መለስ በቶሎ ተሽሏቸው ያገግሙ ዘንድ እመኛለሁ” በማለት የጓዳውን በሰገነት አወጁት።

የአቶ መለስ መታመም ምስጢርነት እዚህ ላይ አከተመ።በኢህአዴግ ሳይሆን በሴኔጋል ፕሬዚዳንት ግልጽነት።

ይህ እውነታ አደባባይ በዋለ በማግስቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፦”መለስ፤ማናቸውም ሰው እንደሚታመም ትንሽ አሟቸው እየታከሙ ነው። በቅርቡ ህክምናቸውን ጨርሰው ይመለሳሉ” በማለት ለመጀመሪያ ጊዜ የአቶ መለስን መታመም ለመናገር ተገደዱ።

ከዚያም አንዳንድ የአውሮፓ ብዙሀን መገናኛዎች ምንጮቻቸውን በመጥቀስ የመለስ ጤንነት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሆነ መዘገብ ጀመሩ።

በማስከተልም የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ በረከት ስምዖን ለውጪ ሚዲያዎች ፦”መለስ ሆስፒታል ተኝተው ህክምና እየተከታተሉ እንደሚገኙ፤ሆኖም ህይወታቸው አስጊ ደረጃ ላይ ይገኛል የተባለው ስህተት መሆኑንና በደህና ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ “ገለጹ።

የአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ፦’መለስ ታመዋል የሚባለው እውነት ነወይ?” ብለው ከቀናት በፊት ሲጠይቋቸው፤” ይህ ኢሳት ያናፈሰው የውሸት ወሬ ነው” በማለት ምላሽ የሰጡት የኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት ሚኒስትሮች፤ ለነ ቢቢሲና ለነ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፦”መለስ ታመው ሆስፒታል ናቸው”እያሉ መግለጫ ሰጡ።

የአገር ውስጥ ሚዲያዎችም በራሳቸው ጉዳይ የውጪ ሚዲያዎችን እየጠቀሱ መዘገቡን ቀጠሉ።

የኢህአዴግ ልሳን የሆነውና ከሁለት ወራት በፊት፦”ኢሳያስ አፈወርቄ እጅግ በጠና ታመዋል”( Isayas Afeworki is terminally ill) የሚል ሰበር ዜና ያቀረበው አይጋ ፎረምም፤ዛሬ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ፦”መለስ ሆስፒታል ውስጥ ናቸው፣ መለስ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ” በማለት ዘገበ።

“መለስ አሣሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛሉ” የሚለውን የውጪ ሚዲያዎች ዘገባ ፤ በአገር ውስጥም ሆነ በውጪ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፈጠረው ውጥረት በተጨማሪ፤ በተቃዋሚዎች ዘንድ ከመለስ በሁዋላ ስለምትኖረው ኢትዮጵያ ሀሳቦች መንሸራሸር ቀጠሉ።

ውጥረቱም ሆነ የሀሳብ ፍጭቱ ያየለው፤ ብዙዎች በምንም ምክንያት ይሁን በምን መለስ ከሥልጣን ቦታቸው ከተገለሉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አሰላለፍም ሆነ በሥርዓቱ ላይ የጎላ ለውጥ ይታያል የሚል እምነት ስላላቸው ነው።

ነገሩ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለ ነው የህወሀት መስራች የሆኑትና ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአቶ መለስ መገለል እንደረሰባቸው ሲነገርባቸው የነበሩት አቶ ስብሀት ነጋ ትናንት ምሽት ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ የአማርኛው ክፍል፦”መለስ ታመው ሆስፒታል እየታከሙ እንደሆነና በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራቸው እንደሚመለሱ፤ሆኖም መለስ ኖሩም አልኖሩም፤ሥርዓቱ ያለምንም ለውጥ እንደሚቀጥል የተናገሩት። “መለስ ኖረ አልኖረ፣ በቀለ ኖረ አልኖረ፣ ዘርይሁን ኖረ አልኖረ፣ ፋጢማ ኖረች አልኖረች ለውጥ የለውም። ኢህአዴግ

የገነባው ሥርዓት እያለ ለምን ወደ መለስ እንሄዳለን?” ነው ያሉት አቦይ ስብሀት።

በመለስ መምጣትና መሄድ፤ በድርጅቱ ውስጥ የሚኖር የስልጣን ሽኩቻ እንደማይኖርም አቦይ ስብሀት ተናግረዋል። አቦይ ስብሀት ይህን ይበሉ እንጂ፤ በኢህአዴግ ውስጥ የእርስበርስ የሥልጣን ሽኩቻ የተጀመረው ገና መለስ በታመሙ ማግስት እንደሆነ የውስጥ ምንጮች ይፋ አድርገዋል። ራሳቸው አቶ ስብሀት በዚሁ ቃለምልልሳቸው ስለ አቶ መለስ ጤንነት መሻሻል የገለጹት በቀጥታ የሚያውቁትን ሳይሆን በተዘዋዋሪ ከሌሎች ሰምተው እንደሆነ መናገራቸው፤በህወሀት-ኢህአዴግ መካከል ጫፍ ላይ ለደረሰው መቃቃር- እንደ አንድ ምልክት ነው ሲሉ ፤ቃለ-ምልልሱን ያዳመጡ ወገኖች አስተያት ሰጥተዋል። አይጋ ፎረም በበኩሉ ዛሬ አቦይ ስብሀት ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለ-ምልልስ ከለጠፈበት ራስጌ ፦”ዓለም በመለስ ጤና ዙሪያ የተፈጠረበትን ብዥታ ለማጥራት የመንግስት ቃል አቀባይን መረጃ እየጠበቀ ባለበት ጊዜ፤ልምድ እና ብቃት ያላቸው የህወሀት/ኢህአዴግ መስራቹና መሪው አቦይ ስብሀት በቪኦኤ በመቅረብ፤ ነገሩን ግልጽ አድርገውታል” በማለት እነ በረከትን በመንቀራፈፍ የሚተች እና አቦይ ስብሀትን የሚያሞግስ ፅሁፍ አትሟል። ከዚህ ሁሉ በሁዋላ ፤ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አቶ በረከት ስምዖንና ምክትላቸው አቶ ሽመልስ ከማል፤ በመለስ ጤና ዙሪያ ትናንት ለውጪ ሚዲያዎች የገለፁትን ዛሬ ለአገር ውስጥ ጋዜጠኞች ጭምር ነግረዋቸዋል። መለስ ጥቂት ህመም እንዳጋጠማቸው እና ያም የሆነው በስራ መደራረብና ጫና እንደሆነ ሀኪሞቹ መገንዘባቸውን የጠቀሱት አቶ በረከት፤ ለጥቂት ጊዜ ከሥራቸው ተገልለው ዕረፍት እንዲያደርጉ መመከራቸውን ተናግረዋል። የሐኪም ፈቃዳቸውን ከጨረሱ በሁዋላ በቅርቡ ወደ ሥራቸው እንደሚመለሱም አቶ በረከት አክለዋል። አቶ በረከት ይህን ቢሉም፤በብራሰልስ-ሴንት ሉክ ሆስፒታል የሚገኙ ምንጮች ፤የአቶ መለስ ህመም ከባድ መሆኑን እና የኬሞ ቴራፒ ህክምና ሲከታተሉ መቆየታቸውን ነው ቀደም ሲል ያረጋገጡት። ጉዳዩን በቅርበት እየተታተሉ ያሉ ወገኖች በሰጡት አስተያዬት፤ ከብዙሀን መገናኛዎች፣ከተለያዩ ምንጮችና ከዲፕሎማቶች የተገኙ መረጃዎችም ሆኑ የነ አቦይ ስብሀት መግለጫዎች የሚያመለክቱት ፤ከእንግዲህ መለስ ኖሩም አልኖሩም፤ በቀድሞ ቦታቸውና ጉልበታቸው የሚቀጥሉበት ዕድል ማክተሙን ነው ብለዋል። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የአቶ መለስ ፈላጭ ቆራጭነት ማክተሙ ለተሻለ ለውጥ ዕድል ይፈጥር ይሆን? ወይስ የባሰ ነገር ያመጣል? የሚለው ብዙዎችን ማነጋገሩን እንደቀጠለ ነው።
Attachments
Skype-Ethiopia.jpg
Skype-Ethiopia.jpg (30.89 KiB) Viewed 920 times



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 23 Jul 2012, 11:25


July 22nd, 2012
Poem dedicated to Meles Zenawi “ebakwon ymutu” Henok Yeshitla
Attachments
1338164439535593403962473.gif
1338164439535593403962473.gif (105.26 KiB) Viewed 856 times



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 24 Jul 2012, 09:45


July 24th, 2012
ESAT Ato Yesuf Yasin & Ato Mulugeta Loule July 2012

http://ecadforum.com/ethiopianvideo/201 ... july-2012/



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 25 Jul 2012, 08:52


ESAT Ethiopian News July 24, 2012 [Video]
http://www.ethsat.com/2012/07/24/esat-e ... 012-video/


Zenawi’s silly daughter spotted enjoying the nightlife of Brussels
The Horn Times News Letter – July 23, 2012
by Getahune Bekele
Nick named the Queen of bling by the youth of Addis Ababa, the controversial and scandal-prone Semehal MelesZenawi’s silly daughter spotted enjoying the nightlife of Brussels (pictured) has dominated the blissful nightlife of Addis – wood for the past 10 years. Every Fridays and Saturdays, she has been a common site in bars and restaurants of Addis with her eight bodyguards in the pitch-black Jeep Cherokee.

http://ecadforum.com/2012/07/24/zenawi- ... -brussels/



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 26 Jul 2012, 09:31


ATLANTA: Abebe Gellaw calls on opposition parties to discharge leadership role
Mahdere Andenet | July 26, 2012

What we have is "an Ethiopian Liberation Front" the activist asserted. "The most important change that the day has brought" he said, " is while the incident created fear and horror in the minds of Meles and his clones, it also opened a new opportune time for the rest of us to keep our heads in upright position thereby raising the level of hope to a higher stage.

http://www.ethiomedia.com/2012_report/4095.html



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 27 Jul 2012, 10:32


Let’s Not Fall on the Trap of Meles Zenawi’s Illness

by Samson Gebremariam
These past weeks all our attention was focused on the former “FREEDOM FIGHTER” the current “OPPRESSOR” of all time Dictators’ Mentality, Clouded Mindsin our beloved Ethiopian history. TPLF/EPRDF and its dictator leader Meles Zenawi know how to shift people’s mind from one critical spot to another that seems important; however, has nothing to do with what we all need. I will leave to the readers that how many times we fell into such traps and we forgot our main agenda. Had it not been for the regime and Meles Zenawi’s cruelty all Ethiopians would have been shocked and concerned about his bad health condition. We also would have been in deep prayers for him to recover from his illness soon rather than wished him death. However, the way we heard of his illness through foreign sources and wrong handling of the issue by Ethiopian government left us in limbo. Citizens have been denied their right to know about their leader’s whereabouts and health condition even though his medical expenses are covered with their money collected as tax or donations made in the name of Ethiopian people.
Our constitution has also fuelled the confusion as it does not include the succession process if the prime minister dies, resigns or is removed from office, though the last two options are unlikely to happen in Ethiopia. Was it forgotten? Or Ethiopian leaders were assumed to be immortal? Not at all, TPLF immortality was the basis for the constitution. How? To whatever extent the coalition parties of EPRDF could share power with TPLF; the Prime Minister position is reserved only for someone from TPLF. The President, Deputy Prime Minister and other positions are open to all EPRDF coalition parties. As we all may know, the most common trend in power succession so far is deputies to take over the next higher position in such emergency situations. Had our constitution adopted this healthy trend either we would have seen deputy from TPLF or the party would lose this key (PM) position, the unlikely scenario. If he had died or resigned his position would have been taken over by non-TPLF member, which would cause a major crackdown within the ruling party and the whole country. But the “smart” move was taken by head of the TPLF Meles Zenawi and left it wide open for his party to fight and keep it within themselves. That is what we are witnessing right now. Meles Zenawi has failed to save the lives of millions of Ethiopians from poverty but helped TPLF stuck in power.

Having said that, planned or coincidence I found this situation as a trap too and EPRDF is buying time to sort out its internal problem. Let’s not give them the time they needed rather unsettle them and push them out of office. Let’s unite ourselves and organize the people to peacefully demonstrate and get rid of this tyranny regime. Two decades of oppression creates unbearable pain in the hearts of all Ethiopians. The time has come and it’s NOW! We need to act as a unit and brainstorm to devise the best action plan that will force TPLF/EPRDF share power or leave office. There should not be any violence or bloodshed as we have already scarified many lives in the civil wars we were forced to go through. We need to act cautiously not to trigger their brutality to kill our people. We may also need to use diplomatic pressures as additional force showing we have the will and potential to lead our country in a better way. For all these to happen we have to put aside our differences and build our relationship on our common goal. We all know life is full of compromise and that is exactly political activities should accommodate. So let’s be part of this historic moment and contribute our share as we did in the 2005’s election. We are now given a second chance to free our beloved country from TPLF/EPRDF and get our freedom back. Let’s organize ourselves and move on as a united force before this golden opportunity vanishes. This is a crunching time to worry about our beloved country ETHIOPIA and leave the tyranny to die!!!
UNITY IS STRENGTH!

samsongeb1@gmail.com



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 30 Jul 2012, 08:29


Tukirt- Program On PM Meles and his administration
http://www.youtube.com/watch?feature=pl ... 7FCOTegpE#!
:cry: Tyrant Ashebir is already dead.



Re: OJ is back

Postby Obamajr. » 31 Jul 2012, 08:33


Ethiopia burns as TPLF warlords jostle for positions

The Horn Times NewsLetter-July30, 2012
by Getahune Bekele

More than 20 slaughtered in and around the segregated town of Moyale

When the Horn Times reporter Safia Hajji Liben Hajji Roba arrived in northern Kenyan town of Moyale on July 30, 2012, the stench of death was still hanging in the air.

http://ecadforum.com/blog/ethiopia-burn ... positions/

Previous Page Next Page


Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Halyeyga, Macaanto, Rhino, Somali-Ethio, WediKeren