Ethiopian News and Opinion Forum


ፍትህ ጋዜጣን የሚያትም ማተሚያ ቤት መጥፋቱን ምንጮቼ ነገሩኝ

Postby Aragaw » 27 Jul 2012, 16:13




አቤ ቶኪቻው

ይህ ወሬ “ዜና ብጤ” ተብሎ የቀረበው ድሮም የሚጠበቅ በመሆኑ የተነሳ ነው!

ፍትህ ጋዜጣ በትላንትናው እለት ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፤ “ፍትህ ሚኒስቴር እንዳታትም ብሎኛል” በሚል ክልከላ እንዳደረገባት አውርተን ነበር። የጋዜጣው አዘጋጅ ተመስገን ደሳለኝ ከባልደረቦቹ ጋር በመሆን ወደ ፍትህ ሚኒስቴር ቢያመሩም ፍትህ ሚኒስቴር ደግሞ “እኔ አልከለከልኩም ማሳተም ትችላላችሁ!” ብሏቸው ነበር። ነገር ግን ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሲሄድ ከስራ በመወጣታቸው የተነሳ ትላንት ሳትታተም ቀርታለች።

በዛሬው እለት ሌላ ሙከራ ያደረጉት የፍትህ ጋዜጣ ባልደረቦች ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በአቋሙ ቢፀናባቸው በድጋሚ ፍትህ ሚኒስቴር ሄደው አቤት ቢሉም “ማተሚያ ቤቱ ራሱን የቻለ ተቋም ነው እንጂ በኛ የሚታዘዝ አይደለም” በሚል አሰናብተዋቸዋል። አሁንም ፍትሆች በታጋሽነት ወደ ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ሄደው ደጅ ቢጠኑም የማተሚያ ቤቱ ሃላፊዎች “ቢላ በአንገቴ” ብለዋቸዋል። (ቢላ በዚህ ጊዜ ከየት ይመጣል…!?)

የጋዜጣው ባልደረቦች አሁንም ተስፋ አልቆረጡም ወደ ቦሌ ማተሚያ ቤት ሄደው “እስቲ እናንተ አትሙልን!?” ብለው ጠየቁ። ነገር ግን ቦሌዎች “የደንበኞቻችንን ብቻ ነው የምናትመው” ብለው እምቢኝ አሉ። ፍትሆችም በሆዳቸው “እኛስ ደበኛችሁ ነን እንዴ?” ብለው በአንደበታቸው ግን፤ “አረ እባካችሁ ወደፊት ደንበኛ እንሆናለን!?” ብለው ቢያግባቡም እሺ ብሎ የሚያትምላቸው አላገኙም።

በነገራችን ላይ ፍትህ የሚያሳትመውን ከሰላሳ ሺህ በላይ ኮፒ ጋዜጣ ማተም ብቃት ያለው ሌላ ማተሚያ ቤት በኢትዮጵያ የለም።

ስለዚህ አሁንም ፍትህ በኢትዮጵያ ምድር የለችም! የሰዎቻችን ፀብ ከስሟ ከሆነ ምናልባት ስሟን ቀይሮ መሞከር ይሻል ይሆን!? እንጃ….!

Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], CYP450, Degnet, Edenabera, elias, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Gurezza, Halafi Mengedi, MSNbot Media, psbot [Picsearch], Somali_Pirate, Zack