Ethiopian News and Opinion Forum

ወያኔ የዋልድባ መነኮሳትን ማሰር ጀመረ

Postby ደጀ ሰላም » 31 Jul 2012, 18:37

(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 23/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 30/ 2012)፦ ምሽቱን ወደ ገዳሙ በገቡት ዐሥር ያህል የማይ ፀብሪ ፖሊሶችና ታጣቂዎች የተወሰዱት ሁለት መነኰሳት አባ ወልደ ጊዮርጊስ ከዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም፣ አባ ገብረ ማርያም ጎንዴ ከማይ ለበጣ (የማኅበረ መነኰሳቱ ሰፊው የአትክልት ቦታ) ናቸው፡፡ ሁለቱ አበው መነኰሳት በፖሊሶቹ ተይዘው ከመወሰዳቸው አስቀድሞ በኣቶቻቸው በፖሊሶቹ ፍተሻ እንደተካሄደበት ተገልጧል፡፡ ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት መኾኗ የወረዳው አስተዳደር ለገዳሙ ትውፊታዊ ሥርዐትና ክብር መጠበቅ ያለውን የወረደ ግንዛቤ የሚያሳይ ነው፡፡

ትናንት ምሽት በገዳሙ ውስጥ ከተካሄደው ፍተሻ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ዓርብ፣ ሐምሌ 20 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ከጠዋት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በዋልድባ ዶንዶሮቃ ገዳም የሚገኙ ከኀምሳ ያላነሱ መነኰሳትና መነኰሳዪያት ቤት ቁልፎች በኀይል እየተሠበሩ ፍተሻ እንደተካሄደበት ተመልክቷል፡፡

ኻያ ስምንት ያህል የገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት የሁለቱን አባቶች መወሰድ በመቃወም ወደ ማይ ፀብሪ ተጉዘው አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ወረዳ ከተማው ከሚወስደው ፅርጊያ መንገድ ሲደርሱ በፖሊሶቹ የኀይል ርምጃ መገታቱ ተነግሯል፡፡ የጉዟቸው መገታት ብቻ ሳይኾን ‹‹መመለሳቸውም አሳሳቢ ነው ብለዋል›› ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የተናገሩ አንድ የገዳሙ መነኰስ፡፡
ያለፈው ሳምንት መጨረሻ መጠነ ሰፊ ፍተሻ እና እስር ምክንያት በተለይ ከቆላ ወገራ የመጡ ናቸው በተባሉ አርሶ አደሮች ድንገተኛ ርምጃ እንዲሁም በጅብ መንጋና በእባብ በፕሮጀክቱ የጥበቃ ኀይል አባላት እና ሠራተኞች የሕይወት እና አካላዊ ደኅንነት ላይ ደርሷል የተባለው ጉዳት ነው፡፡

አስገራሚው ጉዳይ ግን በሽታቸው ይኹን የወቅቱ መገኛቸው አነጋጋሪ ስለኾነው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጽኑ ሕመም የፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊሶች በመነኰሳቱ ላይ የተናገሩት ቃል ነው - ‹‹እናንተ ምታታሞች [ምትሃተኞች] ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችኹ፡፡››

በተደጋጋሚ በወረዳው ፖሊስ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተጋልጠው ከሚገኙት የዋልድባ አብረንታንት ቤተ ሚናስ መነኰሳት መካከል ‹‹ፕሮጀክቱን እንቃወማለን፤ ለገዳማችን ክብር እና ህልውናም እንሰየፋለን›› በሚል ግልጽ ተቃውሞ ያሳዩ 49 መነኰሳት ስም ዝርዝራቸው ተይዞ በፖሊስ እየተፈለጉ መኾኑን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል፡፡ ፖሊሶቹ በየጊዜው እየመጡ መነኰሳቱን እየለዩ ለሚያደርሱት እንግልትና እስር ከዋልድባ ቤተ ሚናስ መነኰሳት ጋራ የአስተምህሮ ልዩነት ያላቸው የዋልድባ ቤተ ጣዕማ መነኰሳት ‹‹ተባባሪዎች ናቸው›› ተብሏል፡፡ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም ከዋልድባ አብረንታንት ገዳም በማይ ፀብሪ ፖሊስ ተወስደው የታሰሩት መነኮስ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ አሁንም ያልተለቀቁ መኾናቸውን ምንጮቹ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በተለይም ከሰኔ ወር ጀምሮ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትና የዛሬማ ወንዝ ግድብ በዋልድባ ገዳም ላይ ከሚያደርሰው ተጨባጭ አደጋ እና ታሳቢ ስጋቶች ጋራ ተያይዞ በፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊስ በማኅበረ መነኰሳቱ ላይ የሚደርሰው ወከባ፣ እስርና እንግልት ተባብሶ ስለ መቀጠሉ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የማይ ፀብሪ ፖሊሶች እንደተናገሩት ለገዳማቸው ክብርና ህልውና መጠበቅ የቆሙት ጽኑዐኑ የዋልድባ ማኅበረ መነኮሳት ‹ምታታሞች› ባይኾኑም÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ የተያዙበትን ጽኑ ሕመም እንደ እግዚአብሔር ተግሣጽ (እንደ መቅሠፍት) የሚቆጥሩ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጥቂት እንዳልኾኑ በሕመማቸው ዙሪያ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚተላለፉ መልእክቶች ያስረዳሉ - ‹‹ደዌ ዘመቅሠፍት›› እንዲሉ፡፡

በርግጥም ሰው ኾኖ መታመም የሚያነጋግር ባይሆንም የታላቁ ገዳም መነኰሳትና ባሕታውያን አባቶች የዘወትር ሐዘንና ልቅሶ÷ በተለይም በዚህ የሱባኤያቸው ወቅት÷ ግዳጁን አይፈጽምም ለማለት አይቻልም፡፡

Re: ወያኔ የዋልድባ መነኮሳትን ማሰር ጀመረ

Postby revolutions » 31 Jul 2012, 19:18

When Meles Zenawi desecrated holy sites in Ethiopia, he felt God's burning wrath, and it killed him.

Re: ወያኔ የዋልድባ መነኮሳትን ማሰር ጀመረ

Postby Wedi..... » 31 Jul 2012, 22:33

Quite nonsense.
Why didn't u say it is muslims' duaa that made Meles sick?
U guys appear narrow minded.

Re: ወያኔ የዋልድባ መነኮሳትን ማሰር ጀመረ

Postby techie » 31 Jul 2012, 23:59

I feel Meles is feeling burning with fire for what he has done to Waldiba monks. Of all possible things, yeegziabheren bet medifer min ametaw? Sewun hulu defere, ena yekerew Amlak neber, hedena ende Nimrod from Babylon tried to poke a finger ! Egziabher sile andd kidus tselot Melesin atefaw. Everybody take a lesson!

Re: ወያኔ የዋልድባ መነኮሳትን ማሰር ጀመረ

Postby Wondo » 01 Aug 2012, 00:25

This is the beginning of the END of TPLF regime,m they will be crumbling, because they pass their line and Meles is struck and will soon see the result of his transgression

ደጀ ሰላም wrote:(ደጀ ሰላም፤ ሐምሌ 23/2004 ዓ.ም፤ ጁላይ 30/ 2012)፦ ምሽቱን ወደ ገዳሙ በገቡት ዐሥር ያህል የማይ ፀብሪ ፖሊሶችና ታጣቂዎች የተወሰዱት ሁለት መነኰሳት አባ ወልደ ጊዮርጊስ ከዋልድባ አብረንታንት መድኃኔዓለም፣ አባ ገብረ ማርያም ጎንዴ ከማይ ለበጣ (የማኅበረ መነኰሳቱ ሰፊው የአትክልት ቦታ) ናቸው፡፡ ሁለቱ አበው መነኰሳት በፖሊሶቹ ተይዘው ከመወሰዳቸው አስቀድሞ በኣቶቻቸው በፖሊሶቹ ፍተሻ እንደተካሄደበት ተገልጧል፡፡ ከፖሊሶቹ አንዲቱ ከጾታዋ የተነሣ ወደ ዋልድባ ለመግባት የማይፈቀድላት ሴት መኾኗ የወረዳው አስተዳደር ለገዳሙ ትውፊታዊ ሥርዐትና ክብር መጠበቅ ያለውን የወረደ ግንዛቤ የሚያሳይ ነው፡፡

ትናንት ምሽት በገዳሙ ውስጥ ከተካሄደው ፍተሻ ሁለት ቀናት ቀደም ብሎ ዓርብ፣ ሐምሌ 20 ቀን 2004 ዓ.ም፣ ከጠዋት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በዋልድባ ዶንዶሮቃ ገዳም የሚገኙ ከኀምሳ ያላነሱ መነኰሳትና መነኰሳዪያት ቤት ቁልፎች በኀይል እየተሠበሩ ፍተሻ እንደተካሄደበት ተመልክቷል፡፡

ኻያ ስምንት ያህል የገዳሙ ማኅበረ መነኰሳት የሁለቱን አባቶች መወሰድ በመቃወም ወደ ማይ ፀብሪ ተጉዘው አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ወረዳ ከተማው ከሚወስደው ፅርጊያ መንገድ ሲደርሱ በፖሊሶቹ የኀይል ርምጃ መገታቱ ተነግሯል፡፡ የጉዟቸው መገታት ብቻ ሳይኾን ‹‹መመለሳቸውም አሳሳቢ ነው ብለዋል›› ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ የተናገሩ አንድ የገዳሙ መነኰስ፡፡
ያለፈው ሳምንት መጨረሻ መጠነ ሰፊ ፍተሻ እና እስር ምክንያት በተለይ ከቆላ ወገራ የመጡ ናቸው በተባሉ አርሶ አደሮች ድንገተኛ ርምጃ እንዲሁም በጅብ መንጋና በእባብ በፕሮጀክቱ የጥበቃ ኀይል አባላት እና ሠራተኞች የሕይወት እና አካላዊ ደኅንነት ላይ ደርሷል የተባለው ጉዳት ነው፡፡

አስገራሚው ጉዳይ ግን በሽታቸው ይኹን የወቅቱ መገኛቸው አነጋጋሪ ስለኾነው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ጽኑ ሕመም የፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊሶች በመነኰሳቱ ላይ የተናገሩት ቃል ነው - ‹‹እናንተ ምታታሞች [ምትሃተኞች] ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕመም ተጠያቂዎች ናችኹ፡፡››

በተደጋጋሚ በወረዳው ፖሊስ ድብደባ፣ እንግልትና እስር ተጋልጠው ከሚገኙት የዋልድባ አብረንታንት ቤተ ሚናስ መነኰሳት መካከል ‹‹ፕሮጀክቱን እንቃወማለን፤ ለገዳማችን ክብር እና ህልውናም እንሰየፋለን›› በሚል ግልጽ ተቃውሞ ያሳዩ 49 መነኰሳት ስም ዝርዝራቸው ተይዞ በፖሊስ እየተፈለጉ መኾኑን ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል፡፡ ፖሊሶቹ በየጊዜው እየመጡ መነኰሳቱን እየለዩ ለሚያደርሱት እንግልትና እስር ከዋልድባ ቤተ ሚናስ መነኰሳት ጋራ የአስተምህሮ ልዩነት ያላቸው የዋልድባ ቤተ ጣዕማ መነኰሳት ‹‹ተባባሪዎች ናቸው›› ተብሏል፡፡ ሐምሌ 13 ቀን 2004 ዓ.ም ከዋልድባ አብረንታንት ገዳም በማይ ፀብሪ ፖሊስ ተወስደው የታሰሩት መነኮስ አባ ገብረ ሥላሴ ዋለልኝ አሁንም ያልተለቀቁ መኾናቸውን ምንጮቹ ጨምረው አስረድተዋል፡፡

በተለይም ከሰኔ ወር ጀምሮ የወልቃይት ስኳር ልማት ፕሮጀክትና የዛሬማ ወንዝ ግድብ በዋልድባ ገዳም ላይ ከሚያደርሰው ተጨባጭ አደጋ እና ታሳቢ ስጋቶች ጋራ ተያይዞ በፀለምት - ማይ ፀብሪ ፖሊስ በማኅበረ መነኰሳቱ ላይ የሚደርሰው ወከባ፣ እስርና እንግልት ተባብሶ ስለ መቀጠሉ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

የማይ ፀብሪ ፖሊሶች እንደተናገሩት ለገዳማቸው ክብርና ህልውና መጠበቅ የቆሙት ጽኑዐኑ የዋልድባ ማኅበረ መነኮሳት ‹ምታታሞች› ባይኾኑም÷ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ መለስ ዜናዊ የተያዙበትን ጽኑ ሕመም እንደ እግዚአብሔር ተግሣጽ (እንደ መቅሠፍት) የሚቆጥሩ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን ጥቂት እንዳልኾኑ በሕመማቸው ዙሪያ በማኅበራዊ ድረ ገጾች የሚተላለፉ መልእክቶች ያስረዳሉ - ‹‹ደዌ ዘመቅሠፍት›› እንዲሉ፡፡

በርግጥም ሰው ኾኖ መታመም የሚያነጋግር ባይሆንም የታላቁ ገዳም መነኰሳትና ባሕታውያን አባቶች የዘወትር ሐዘንና ልቅሶ÷ በተለይም በዚህ የሱባኤያቸው ወቅት÷ ግዳጁን አይፈጽምም ለማለት አይቻልም፡፡

Re: ወያኔ የዋልድባ መነኮሳትን ማሰር ጀመረ

Postby Berak » 01 Aug 2012, 01:59

The next sign is the demise of the pagan aba paulos. He has a severe mental illness and depends on multiple daily medication. Woyane will go away just like Mengistu and his clique. Then, we will tear down their pagan idols and life stone marking. Live to witness history. Deny the existence of God at your own peril!!!!

Re: ወያኔ የዋልድባ መነኮሳትን ማሰር ጀመረ

Postby revelations » 01 Aug 2012, 10:07

Walta woyane's misinformation center has denied all these reports. No shame in woyane's game!

P.S. The police officer looks like heas one week left lemeqesef

No arrest in connection with Welkait sugar project, police confirm

Image
Addis Ababa, July 31 (WIC) – No one has been arrested in connection with Welkait sugar development project, a police officer of Mezega Wereda disclosed.

“There is no a single person in the police station who is arrested in connection with the sugar development project,” Inspector Mulugeta Gebremeskel, told WIC.

Regarding the allegations of mass arrest in the Wereda by some media, the Inspector said “all the allegations are baseless.” The police and the society are working jointly to bring the project a success.

“Ever since the project started, the activities have been going well without any security breach. Residents of the Woreda have also been working in collaboration with the police,” the Inspector said.

Currently, the federal and the Wereda police, anti-bandit force and the militia are working in partnership with the residents to ensure the successfully realization of the project.

“The Welkait sugar development project is progressing well as the people are the primary guardian of law and order in the area,” he said.

The Wereda police hold frequent discussions with the residents to identify problems (if there are) and bring about community-based lasting solutions for them, he added.

The Inspector finally said the Wereda police will continue working with the people to safeguard the development activities and peace of the area as a whole.

Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: asmarino09, Bing [Bot], Bwendimu, elias, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Halafi Mengedi, kokeb, Macaanto, mee, midwest, New Guy, Tit for Tat, TurnitinBot [Bot]