Ethiopian News and Opinion Forum


አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ሆስፒታል ገብተዋል

Postby Beli » 15 Aug 2012, 20:56


Aug 15, 2012 (ESAT) -- አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ሆስፒታል መግባታቸውን በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ን ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ዜናዎችን በቅርበት በመዘገብ የሚታወቀው ደጀ ሰላም ድረ-ገጽ ዘገበ። ከፓርያሪክ ረዳቶች አንዱ የሆኑትን አባ እንቁ ባህርይ ግን፤ “የለም አልታመሙም እሳቸው ቤት ነው ያሉት” ብለዋል።

አባ ጳውሎስ ትናንት ምሽት በጠና ታመው ባፋጣኝ ደጃዝማች ባልቻ ሆስፒታል እንደተወሰዱ የሚያትተው ይኸው ዜና ዘገባ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ራሳቸውን ችለው መራመድ አቅቷቸው መኪናቸው ውስጥ ሲገቡና ሲወጡ እንኳን ከግራና ከቀኝ ሌሎች ሰዎች እየደገፏቸው እንደነበር አብራርቷል።

የተያዘውን የፍልሰታ-ለማሪያም ጾም በመንበር ፓትርያርክ ቅድሰተ ቅዱሳን ማሪያም ገዳም ጸሎተ ቅዳሴ ላይ እንደነበሩ የተናገሩት እነዚሁ የደጀ-ሰላም ምንጮች፤ ምንም እንኳን የአባ ጳውሎስን አጣዳፊ ህመም ምንነት ለይተው ባይገልጹም የጤንነታቸው ሁኔታ አስጊ በመሆኑ በሆስፒታሉ ሃኪሞች ከፍተኛ ክትትል ስር መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

አባ ጳውሎስ የጤናቸው ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን በተለይም ከጉልበታቸው በታች የሚገኘው የእግራቸው ክፍል መጎዳቱን ዘግቦ የነበረው ይኸው ድረ-ገጽ፤ በዚህም የተነሳ ጤናቸውን ለመከታተል የሚያደርጉት ሳምንታዊ ወጪ ከስድሳ ሺህ ብር በላይ ማሻቀቡን ጠቁሟል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢሳት ያነጋገራቸው ከአባ ጳውሎስ ረዳቶች አንዱ አባ እንቁ ባህርይ ባልቻ ሆስፒታል ሰው ሊጠይቁ መሄዳቸውን፤ እሳቸው ግን አለመታመማቸውን ገልጸዋል።

አባ ጳውሎስ በቅርቡ 20ኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸውን መጀመሪያ በቤተ ክህነት በማስከተል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት በተጋበዙበት በሸራተን አዲስ ሆቴል፤ እንዲሁም ለሶስተኛ ጊዜ በክራውን ሆቴል በወኪሎቻቸው አማካኝነት ከፍተኛ ገንዘብ ፈሰስ በማድረግ ድል ያለ ድግስ አዘጋጅተው ግብር ማብላታቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ቤተክርስቲያኗ፤ በተለይም የዋልድባ ጥንታዊ ገዳም እና በውስጡ የሚገኙት መነኮሳት ህልውና እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ በደረሰበት ባሁኑ ወቅት፤ እርሳቸው እንደ ቤተክርስቲያኗ አባትነታቸው ከመነኮሳቱና ከምእመናኑ ጎን በመቆም፤ ይህንን መቃወም ሲጠበቅባቸው በተቃራኒው የመንግስትን አቋም በግልጽ ያራምዳሉ በሚል፤ የሚወቅሱዋቸው ቁጥራቸው እየበዛ ነው።

አቡነ ጳውሎስ ለማነጋገር እንችል ዘንድ ስልካቸውን ከረዳታቸው አባ እንቁ ባህርይ ለመቀበል ያቀረብነው ጥያቄ ባለመሳካቱ፤ ባልቻ ሆስፒታል ወይንም ቤታቸው እንዳሉ ለማረጋገጥ አልቻልንም።

ሆኖም የኢሳትም ሌሎች ምንጮችም አቡነ ጳውሎስ መታመማቸውን አረጋግጠዋል።





Re: አቡነ ጳውሎስ በጠና ታመው ሆስፒታል ገብተዋል

Postby Mott Lefiyyelu » 16 Aug 2012, 00:47


I knew this man in Derg's prison, Arategna Kifletor. He did not pray while other bishops did and did not show interest behaving like a religious leader. He was a rather unpleasant and curt mannered person. I was so surprised how this person who neither had a devout leaning nor an agreeable character shoud be the archbishop! Yes, We saw strange things happen. we heard things in disbelief. When would this be over?



Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Bwendimu, elias, expert, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Halyeyga, horn fighter, kebede kebe, MatiT, royal, WediKeren, Zack