Ethiopian News and Opinion Forum


ኦሮሚያን የሚቸበችበው ማነው?

Postby Aragaw » 17 Aug 2012, 12:35


ዱጋሳ ጀቤሳ
ትውልዴ እዚሁ የአፍሪካ፤
የኢትዮጵያና የኦሮሚያ ዋና ከተማ
በሆነችው አዲስ አበባ ነው፡፡ ገና የ30
ዓመት ጐልማሳ ነኝ፡፡ በዛሬ ዘመን
አገላለጽ ብሄሬ ኦሮሞ፣ ዜግነቴ
ኢትዮጵያዊ ነው፡፡ እዚህ አዲስ
አበባ፣ ኦሮሞዎች እንደሚሉአት
ፍንፊኔ ስለተወለድኩና ስለኖርኩ
ቋንቋዬ አማርኛ ነው፡፡ ሆኖም
አያቶቼ በኦሮምኛ ሲነጋገሩ
ስለነበር አንዳንድ ቃላት
መውረሴ አልቀረም፡፡ ስለሆነም
ኦሮሞዎች አይሰማም ብለው
ሊያሙኝ አይችሉም፡፡ ደሜ እንደ
ጀርመኑም፣ እንደጃፓኑም እንደ
ናይጄሪያውም እንደ አይሁዱም፣
እንደ አረቡም እንደ ሶማሌውም፣
እንደ አማራውም ቀይ ነው፡፡ የደም
ዓይነቴ “ቢ” ነው፡፡ ሆኖም ዛሬ ዘር
ክልል ስለሚባልና አባቴ “ኦሮሞ
ነህ” ስላለኝ ብሄሬን በኦሮሞነት
አስመዝግቤአለሁ፡፡
ወላጆቼ የጉለሌ ኦሮሞዎች
ሲሆኑ ኑሮአችን እዚሁ ኮቶቤ
አካባቢ ነው፡፡ ከኮተቤ ማዶ ጣፎ
የምትባል ጅረት (ለጋ) አለች፡
፡ ከዳዲ ጅረት ጋር ትገናኝና
የመጠጥ ውሃ ግድባችንን ለገዳዲን
ትሞላለች፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ
ለገጣፎና ለገዳዲ የሚባሉ የገጠር
የገበሬ ማህበራት ወይም ቀበሌዎች
ልዩ የከተማ አስተዳደርና ልዩ
ወረዳዎች ሆነዋል፡፡ ምነው ቢባል
የኦሮሚያ ክልል መስተዳደር አዲስ
አበባ ዙሪያ የሚገኙትን ቀበሌዎች
ልዩ የኦሮሚያና የኢትዮጵያ
የልማት ማዕከላት ተምሳሌት
እንዲሆኑ ነው፡
ልማቱስ ምን ይመስላል?
ከአዲስ አበባ ወደ ምዕራብ ሲወጣ
በሆሎታ በኩል ብዙ የአበባ
እርሻዎች ይታያሉ፡፡ በሰበታ በኩል
የእነ አበበ ግርማ (ፕሬዚዳንት)
ሪል ስቴትና ብዙ መጋዝኖች
ይገኛሉ፡፡ በናዝሬት በኩል ገላን
የምትባል የኢንዱስትሪ ማዕከል
ተወልዳለች፡፡
በምስራቅ በኩል የለገጣፎና
የለገዳዲ ልማት ተጧጡፏል፡
፡ ልማቱስ ከምን አኳያ ነው?
ግለሰቦችና የሪል ስቴት ባለሀብቶች
የገበሬውን መሬት እየተቀራመቱት
ነው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡
፡ በምርጫ 97 ጊዜ የኦሮሚያ
አስተዳደር በየዞኑ መ/ቤቶች
ሠራተኞችን በማደራጀት በአዲስ
አበባ ዙሪያ መሬት እንዲወስዱ
አድርጓል፡፡ ለገጣፎና ለገዳዲም
በዚህ ወረራ ሰለባ ሆነዋል፡
፡ የሚገርመው ግን የለገጣፎው
ጉዳይ ነው፡፡ ኮተቤ አካባቢ ሲምሲ
የአርሶ አደሩን መሬት በርካሽ
ዋጋ ወስዶ ለራሱ ሚሊዮኖችን
እንዳተረፈ ሁሉ ለገጣፎ አካባቢም
በእነ “ሲሲሱ” (CCC) የወጣለት
የሪል ስቴት ኩባንያ ተፈጥሯል፡፡
“CCC” የሚባለው የሪል ስቴት
ኩባንያ ሠርቶ የሚሸጣቸው ቤቶች
ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ
ያወጣሉ ይባላል፡፡ የለገዳዲ “CCC”
ቤቶች ባለቤቶች ከሆኑ ሰዎች
መሃከል ቱባ ቱባ የኢህአዴግ
ባለስልጣናትና ዘመዶቻቸው
አሉባቸው ይባላል፡፡
የኢህአዴግ ባለስልጣናትና
ቤተ ዘመዶቻቸው እንደዚህ
የሚንደላቀቁባቸው ቤቶችን ሲያሰሩ
መሬታቸው የተወሰደባቸው አርሶ
አደሮች የት ገቡ ብዬ እጠይቃለሁ፡

እነሱማ ብዙዎች ያገኙአትን
ትንሽ ካሳ ገንዘብ ጠጥተውበት
መሬት አልባና ባዶ ኪስ ሆነው
ከለማኝነት ያልበለጠ ኑሮ
ይኖራሉ፡፡ ይህን ሁሉ የመሬት
ችብቸባና ቅርምት መቆጣጠር
የተሳነው የኦሮሞ ህዝብ ወኪል ነኝ
የሚለው በኦህዴድ የሚመራው
የኦሮሚያ አስተዳደር ነው፡፡ ታዲያ
ኦሮሞነቴ ምኑ ላይ ነው? “መሬት
አይሸጥም አይለወጥም” የሚለው
የመንግሥታችን አቋም ምን

http://www.fnotenetsanet.com/wp-content ... -No-55.pdf



Re: ኦሮሚያን የሚቸበችበው ማነው?

Postby Guest1 » 17 Aug 2012, 17:14


Whoever invests will invest wherever - Gambella, oromia or somalia. There will be no development withoout foreign direct investment.

talking about Oromia land is politicising development. Why do you have to go round in circle instead of telling us oromia is only for oromo people?

People like you are the once who are prolonging misery. shut the hell up!!!



Re: ኦሮሚያን የሚቸበችበው ማነው?

Postby ProudEthiopian » 17 Aug 2012, 18:42


you should talk about Ethiopian land.



Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Beles, Bing [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Johnson, Macaanto, Yahoo [Bot]