Ethiopian News and Opinion Forum


'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby ምዕራፍ » 14 Sep 2012, 19:51


በጣም የሚወዱትን መዝሙር ይንገሩኝ?

አቶ ኃ/ማርያም፡- ‹‹እኔም እንደ ዳዊት ጨርቄን ልጣልልህ›› የሚለውን

ጉባዔ ገብተው ሲያመልኩ ግን እንደ ባለሥልጣን የፕሮቶኮል ነገር አለ፡፡ የጥበቃ ጉዳይ አለ፡፡ ሌላም ሌላም፡፡ ይሄን ሁሉ ረስተው በነጻነት ለማምለክ አይቸገሩም?

አቶ ኃ/ማርያም፡ ምንም አልቸገርም፡፡ ጉባዔ ውስጥ ካለሁ እኔ ስለ ራሴ ጨርሶ አላስብም፡፡ እነ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ጨርቃቸውን ጥለው ያመልኩ ነበር፡፡ እኔስ የማመልከው እግዚአብሔር ፊት እንደሆንኩ እንጂ የማስበው ሌላ ነገር አላስብም ማልቀስ ካለብኝ አለቅሳለሁ፣ መንበርከክ ካለብኝ እንበረከካለሁ፡፡ ጌታ ሁን ያለኝን ሁሉ ለመሆን ዝግጁ ሆኜ ነው የማመልከው፡፡

ልጆችዎ በቤተክርስቲያን ውስጥ የመክሊት (የአገልግሎት) ሥራ ውስጥ ሲሳተፉ ይታያል፡፡ የእከሌ ልጅ ነኝ እኮ ብለው ሳይኩራሩ ወንድሞችና እህቶች የጠጡባቸውን የሻይ ብርጭቆዎች እየዞሩ ሲለቅሙ እንዳየ ወንድሜ ፍጹም ነግሮኛል፡፡ በቤት ውስጥ ምን ብለው ቢያስተምሯቸው ነው?

አቶ ኃ/ማርያም፡- እኔም ባለቤቴም ቤት ውስጥ ሁሉም የምንነግራቸው ነገር እኛ ጋር ምንም እንደሌለ እኛ ምንም እንዳልሆንን ሀብታችን ኢየሱስ እንደሆነ የማወርሳቸውም አምላኬን እግዚአብሔርን ብቻ እንደሆነ ነው የምንነግራቸው፡፡ አንተ የራስህ መኪና እንኳን የለህም፡፡ ቤት የለህም፣ አሁን እናንተ አንድ ነገር ብትሆኑ እኛ ምን አለን? ሲሉኝ እንኳን የምመልስላቸው መልስ የለንም ግን መኪና አጥተን እናውቃለን ወይ? ቤትስ አጥተን ማደሪያ አጥተን እናውቃለን ወይ? መኪና ብገዛም ቤት ቢኖረንም የእኛ አይደለም፡፡ ሁሉንም ትተነው ነው የምናልፈው፡፡ ሀብታችን ጌታ ብቻ ነው እላቸዋለሁ፡፡ በአገልግሎት እንዲበረቱም እንመክራቸዋለን፡፡

ለአገልግሎትና የክርስቶስን አካል ለማነጽ ልዩ ልዩ ጸጋ ይሰጣል፡፡ ለእርሶ የተሰጦት የጸጋ ዓይነት ምንድነው?

አቶ ኃ/ማርያም፡ እንግዲህ ጥሪ የተለያየ ነው፡፡ ሁላችንም መሰዊያ ላይ ቆመን አንሰብክም፡፡ እኔን ደግሞ የሰጠኝ የሚመስለኝ ጸጋ ሕዝብን እና አገርን በመልካም አስተዳደር ማገልገል ነው፡፡ ስለዚህ ለእኔ ሥራዬ ስራ ብቻ ሳይሆን አገልግሎትም ጭምር ነው ብዬ የተቀበልኩት፡፡

አቶ ኃ/ማርያም ጠዋት ከመኝታዎ ስንት ሰዓት ይነሳሉ?

አቶ ኃ/ማርያም፡/ሳቅ ብለው/ መመለስ አለብኝ እኔ ሁልጊዜ ከእንቅልፌ ምነሳው ከለሊቱ 11 ሰዓት ነው፡፡ ጉዞ፣ እንደዚህ አይነቱ ነገር ካልረበሸኝ በስተቀር 11 ሰዓት እነሳለሁ፡፡ ከ11 ሰዓት እስከ 12 ድረስ የፀሎት ጊዜዬ ነው፡፡ ከ12 እስከ 12፡30 ትንሽ ‹‹ኤክሰርሳይስ›› (ስፖርት እሰራለሁ፡፡ በቀሪው ጊዜ የዕለቱን የቢሮ ስራ አዘጋጅቼ 1፡30 አካባቢ ወደ ቢሮዬ እሄዳለሁ፡፡

አዘውትረው የሚጸልዩባቸው ጉዳዮች አሉ ካሉ ቢያስታውቁን?

አቶ ኃ/ማርያም፡እኔ ዘወትር በአራት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እጸልያለሁ፡፡ አንደኛ ሰላምና በረከት ለዚህች አገር እንዲበዛ እጸልያሁ፡፡ ለመሪዎቿ፣ ለመንግሥት፣ ባለሥልጣናት ጥበብና ማስተዋልን እንዲሰጥ እጸልያሁ፡፡ ሁሉም ሃይማኖቶች ያለ አድልዎ እና ልዩነት በእኩልነት እና በመቻቻል እንዲኖሩ እመኛለሁ፡፡ ሁለተኛ የእግዚአብሔር ቃል ‹‹ሰው ሁሉ ወደ መዳን እንዲመጣ›› ይላል፡፡ ስለዚህ ሰው ሁሉ እንዲድን እጸልያለሁ፡፡ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ ነውና፡፡ ሶስተኛ እናቴ አልዳነችምና ለወላጅ እናቴ በተለይ እጸልያለሁ፡፡ አራተኛ ለልጆቼና ለቤተሰቤ ዘወትር እጸልያለሁ፡፡

እንደው በግልጽ ለመጠየቅ ያህል ወደ ሥልጣን ሲመጡ አብረው የሚመጡና ለመሥራትም የሚመቹ የኃጢአት ፈተናዎች ይኖራሉ፡፡ እርስዎ እስካሁን ድረስ የገጠምዎትን ፈተና በምን መንገድ አልፈውታል?

አቶ ኃ/ማርያም፡ የእውነት ለመናገር እስካሁን እግዚአብሔር ረድቶኛል፡፡ በፈተናዎቹ አልፌአለሁ እላለሁ፡፡ ይሄን ከልቤ ነው የምልህ፡፡ ንጉሥ ዳዊት የተከበረ በእግዚአብሔር ዘንድም የተወደደ በብዙ ነገር በጣም የተመሰገነ ንጉሥ ነበር፡፡ እስራኤልን የሚመስል ትልቅ ሕዝብ መግዛት የቻለ ዳዊት ግን ራሱን መግዛት አልቻለም ነበር፡፡ ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ ከተማን ከመግዛት ይልቅ ራስን መግዛት ይበልጣል ያለው፡፡ ነገር ግን መጽሐፉ የሚመክረው ራስን ቤተሰብን መግዛት እንድንችል ነው፡፡ አለ አይደል ከተማን በመግዛትህ ሁሉን እገዛለሁ አትበል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ውስጣዊ ሰብዓዊ ውድቀት ሊኖርብህ እንደሚችል አስበህ ጥንቃቄ አድርግ፡፡ ጥንቃቄ ይጠብቅሃል አይደል የሚለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዝሙት ሊያታልህ ይችላል፡፡ ዝሙት እንዳይጥልህ ጥንቃቄ አድርግ፡፡ የሥጋ ምኞት፣ ገንዘብ ፍቅርና የዓይን አምሮት የሚባሉት አይደሉም ሰውን የሚጥሉት፡፡ ስለዚህ ከተማን የገዛ ሰው፣ በተለይ እነዚህ ሶስት ነገሮች ላይ መጠንቀቅ አለበት፡፡ እኛ ኢህአዴጎች ስኳር ነው የምንለው፡፡ ስኳሩ እንዳያታልልህ ጥንቃቄ መደረግ አለበት ነው ሀሳቡ፡፡ ፓርቲዬን በጣም የምወድበት ትልቁ ምክንያት ሙስናን፣ ያለ አግባብ፣ ጥቅም ለማግኘት የሚደረግን ጥረት ፓርቲዬ የኪራይ ሰብሳቢ አመለካከት የሚላቸው በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተወገዙ ናቸው፡፡ እነዚህ መሰረታዊ መርሆች ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮት ጋር ይጣጣሙልኛል፡፡ አይቃረኑም፡፡ ስለዚህ ሙስና፣ አላስፈላጊ ጥቅማጥቅሞች፣ ውሸት ውስጥ ሳትገባ ሕዝብን ማገልገል አለብህ ስለሚል የኔ ፓርቲ እነዚህን መርሆዎች ስለሚያራምድ ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ በጣም ደስ ብሎኝ ነው የምሰራው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንተ ራስህ ከእግዚአብሔር ጋር ንስሐ በመግባት የምትፈታው ነገር ከተገኘ ተገምግመህ እንድትስተካከል ይሆናል ወይም ደግሞ ልትባረርም ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ፓርቲዬ በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም በጣም ጠንካራ አቋም አለው፡፡ እና በዚህ ዓይነት ነው፡፡

የሚጸጸቱበትን ውሳኔ አስተላልፈው ያውቃሉ?

አቶ ኃ/ማርያም፡- የሚገርምህ ነገር ሆን ብዬ ሰውን ለመጉዳት የሰራሁበት ጊዜ የለም፡፡ በጣም እፈራለሁ፡፡ አንድ ጥፋት ሰው ላይ ከሚደርስ ብዙ ጊዜ ራሴን ብጎዳ እመርጣለሁ ግን እኔ የማላውቅቃቸው የተፈጸሙ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እኔም አላውቃቸውም፡፡ ሰዎች በኔ ተጎዳን የሚሉ ይኖሩ ይሆናል አላውቅም፡፡ እስካሁን ድረስ ጎድተኸኛል ብሎ የተናገረኝ ሰው የለም፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ወንድም ህከራስ እንዲሻል በትህትና ቁጠር›› ይላል በፖለቲካ ውስጥ ደግሞ ከሩቅም ቢሆን ያየሁት ግጭትና ክርክር እኔ እሻላለሁ ባይነት ይበዛል፡፡ በተለይ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ከማጣጣል አንጻር፡፡ ከዚህ አኳያ እርስዎ ይህንን ጥቅስ እንዴት እየተገበሩት ነው የሚኖሩት?

አቶ ኃ/ማርያም፡-አዎ መጽሐፍ የሚለው ወንድም ህከአንተ እንደሚሻል ቁጠር ነው፡፡ እንደ ፖለቲከኛ ግን ግለሰቦች ላይ አትኩሬ አንተ እንዲህ ነህ አንተ እንዲያ ነህ የምለው የለም፡፡ አቋሞችን ግን ከፓርቲዬ አቋም አንጻር ማብጠልጠል እችላለሁ፡፡ አንተን አከብራለሁ፡፡ ነገር ግን የያዝከው አቋም ለኢትዮጵያ ሕዝብ አይጠቅመውም እለዋለሁ፡፡ የማይረባ አቋምን ሳልዘልፍና የማይረባ ነው ሳልል አላልፍም፡፡ ይህ ሲሆን ግን በሰለጠነና በሰከነ መንገድ አደርጋለሁ፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ‹‹ተቆጡ በቁጣችው ላይ ግን ጸሐይ አይግባ›› ይላል፡፡

ከመጽሐፍ ቅዱስ ደስ የሚሎት ቃል የቱ ነው?

አቶ ኃ/ማርያም፡- መጽሐፍ ቅዱስን እወደዋለሁ፡፡ የዮሴፍ፣ የዳዊት፣ የሙሴ፣ ሕይወት በጣም ይለውጡኛል፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን ሕይወት በጣም ያንጹኛል፡፡ ዳንኤልም በጣም ጠቢብ ነው፡፡ ስለዚህ እንደርሱም መሆን መልካም አንደሆነ አስባለሁ፡፡

ምንጭ፡- ምዕራፍ መጽሔት፣ ጥር 2003 ዓ.ም.



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Bertu » 14 Sep 2012, 22:00


There goes the most heretic interview I ever heard trying to defend the indefensible. This man could be more dangerous than what we have seen so far as he wraps himself in the scripture to explain the most sadistic, genocidal ethnic dictatorship Ethiopia ever faced. Behold my country men and women of what's to become of this man, who is yet to disavow the atheists among his own party to unleash their unfinished mission on Ethiopia in the name of God.

May God Save Ethiopia, Amen !
Bertu



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby berheg » 14 Sep 2012, 22:03


let GOD be with you brother ,LORD has started his work and hoping he will help you and better be like mandela than meles ,pray and be aman of GOD as usual and show the love of ALMIGHTY for both extrimists tplf and the oppositions ,GOD be with you again ,love wins not hater ,we love you ,peace,prosperity and freedom to the poor .thank you .



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Conformist » 14 Sep 2012, 23:14


ጉባዔ ውስጥ ካለሁ እኔ ስለ ራሴ ጨርሶ አላስብም፡፡ እነ ንጉሥ ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ጨርቃቸውን ጥለው ያመልኩ ነበር፡፡


H/M forgets that in David's time they didn't have underwear, in his exuberance David exposed his genitals while dancing. Does H/M want to expose his genitals in the Pente church likewise?

ሁሉም ሃይማኖቶች ያለ አድልዎ እና ልዩነት በእኩልነት እና በመቻቻል እንዲኖሩ እመኛለሁ፡፡ ሁለተኛ የእግዚአብሔር ቃል ‹‹ሰው ሁሉ ወደ መዳን እንዲመጣ›› ይላል፡፡ ስለዚህ ሰው ሁሉ እንዲድን እጸልያለሁ፡፡


How can he talk about respecting all religions in one breath, and then pray for their conversion to his religion in the next?

ጥንቃቄ ይጠብቅሃል አይደል የሚለው መጽሐፍ ቅዱስ፣ ዝሙት ሊያታልህ ይችላል፡፡ ዝሙት እንዳይጥልህ ጥንቃቄ አድርግ፡፡


H/M claims to be happily married, so why is he publicly accusing his wife of neglecting her conjugal obligations?

ስለዚህ ሙስና፣ አላስፈላጊ ጥቅማጥቅሞች፣ ውሸት ውስጥ ሳትገባ ሕዝብን ማገልገል አለብህ ስለሚል የኔ ፓርቲ እነዚህን መርሆዎች ስለሚያራምድ ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስለሆነ በጣም ደስ ብሎኝ ነው የምሰራው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንተ ራስህ ከእግዚአብሔር ጋር ንስሐ በመግባት የምትፈታው ነገር ከተገኘ ተገምግመህ እንድትስተካከል ይሆናል ወይም ደግሞ ልትባረርም ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ፓርቲዬ በዚህ ጉዳይ ላይ በጣም በጣም ጠንካራ አቋም አለው፡፡ እና በዚህ ዓይነት ነው፡፡


Goddamn liar! The entire Woyane superstructure is bulit on the plunder of the public treasury.

ዳንኤልም በጣም ጠቢብ ነው፡፡ ስለዚህ እንደርሱም መሆን መልካም አንደሆነ አስባለሁ፡፡


Does Hailemariam know that Daniel was a castrated eunch? That was the price of entering the palace of the king of Persia in those days. Does he really want to be a eunch like Daniel?



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Conformist » 14 Sep 2012, 23:18


berheg wrote:let GOD be with you brother ,LORD has started his work and hoping he will help you and better be like mandela than meles ,pray and be aman of GOD as usual and show the love of ALMIGHTY for both extrimists tplf and the oppositions ,GOD be with you again ,love wins not hater ,we love you ,peace,prosperity and freedom to the poor .thank you .


Don't you Pentes use your brains for a change, why in the hell are you involving yourselves in the mess created by communists in the last 38 years. Are you that power hungry to take the blame for the crimes of the Derg and the Marxists-Leninist League of Tigray?



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Guest » 14 Sep 2012, 23:24


be civil. David threw his kingly rob, not his under wear. When a fool opens his mouth without knowledge his ignorance is exposed. Let us appreciate the fact that he prays and recognizes a superior power. He is not a vicious dictator. What are you looking for my country men.



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Genet » 14 Sep 2012, 23:33


ከዘረኛው ወያኔ ጋር በመሆንዎ በርቀት ስለማውቅዎት በጣም እጠላዎት ነበር። ይህን ቃለ ምልልስ ካነበብኩ በኋላ ግን እንባዬን አፈሰስኩ። እኔ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ነኝ:: ባገራችን ታረክ ዬግዚአብሄርን ስም የሚጠራ መሪ ስላላየሁ እርስዎ የአምላክን ስም ስለጠሩና ራስዎን ዝቅ አርገው ለፈጣሪ ስለተገዙ የእሥራኤል አምላክ ይረድዎታል። ኢትዮጵያን እግዚአብሄር በርስዎ በኩል ሊታደጋት ይሆናል። አቦ ይባረኩ። ይህ ቃለ ምልልስ ያስነበብከን ኤሊያስ ተባረክ። እግዚአብሄር በቃሉ ለሙሴ ስሜን አውቀሃልና የረገጥከውን መሬት አወርስሃለሁ ያለው አምላክ ወደፊት ለሚጠብቅዎ አስቸጋሪ የሥልጣን ዘመንዎ በጌታ ሞገስ በድል እንዲወጡ ጸሎቴ ነው። ተቃዋሚውንም ደጋፊውንም በጌታ ፍቅር አስማምተው ኢትዮጵያችን ያንን ስቆቃ የምትረሳበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፈትበትም ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይባርካት።



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Guest » 14 Sep 2012, 23:38


God is good! My prayer is God will give us leaders who fear HIM and lead the people with integrity. May God bless Deputy PM Hailemariam Desalegn!!

Pas. Tilahun Sida.



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Temelkach » 15 Sep 2012, 00:35


I do not know how Hailemariam Dessalegn evaluating Ethiopians. Is he running after Meles' position or Abune Paulos'. From this interview I could not guess. If Hailemariam is afraid to hurt people, then he is not in the right place. If he wants to be a Pente preacher, he can find a place in church with his rhetoric he found in the bible. We Ethiopians, whether we are labourers, farmers, secretaries, construction workers, etc., are smart enough to know what is good for us. The vast majority of us have low income, we are now unable to afford the food in the market. Hailemariam, please listen, the cost of teff, oil, vegetables, shiro, etc, are beyond our means. We are hungry people, with no money, controlled to speak or give our opinions, have no political rights, our children are dying in the seas around us trying to get a job and work like other human beings. If you look around the world, there are few places in the world where you do not see Ethiopians trying to survive. Our daughters are sold to Arabs as maids and they are so mistreated, at times they are not paid for their labours, are burnt or thrown from balconies by their masters to die. You are working hands and feet with Woyanes, a group of gangs that are torturing and bleeding Ethiopians to death and you tell us that you have not hurt anyone knowingly. Are you a Zombie that does not know what is going on. Wake up, you are a man with no power, and like a puppet, you are there to serve Woyanes, the puppet masters. Among them you are a joke.



Re: 'አገርን በማገልገል የጸጋ ስጦታ ተሰጥቶኛል' - ሃይለማርያም ደሳለኝ

Postby Haile Mikael » 15 Sep 2012, 01:48


Being a faith charlatan in the service of Lucifer, Hailemariam is more like Saul than David. In being a loyal accomplice of Ato Meles, Hailemariam, if he was not in league, has shown that he places expediency above principle, demonstrating that he unethically takes advantage of circumstance for his personal benefit. If he was fully in league with Ato Meles, then his claim of fear of God becomes all the more a fraudulent claim. His interview also vividly projects his opportunist attributes. His hidden grievance for lack of a personal car speaks it all.

TPLF was constructed for the destruction of Ethiopia. As is well known, foreign hands took part in nurturing it. It is a no-brainer that the same alien hands partook in dumping a junk pile of denominations in Ethiopia for the purpose of dismantling the Ethiopian Orthodox Church for it was clear to them that the Orthodox Church was the solid bond that allowed Ethiopians to stick together, A self-seeker that he is, Hailemariam joined one of these cultish junkies whose eventual aim is to put Ethiopia in harms way. Clearly, the TPLF does deserve Hailemariam, but, by God, Ethiopia doesn’t.

Here is an advice to Hailemariam and to other non-believing (those who are not Orthodox Tewahdo) seekers of power. Ato Meles and the Patriarch were removed by the hands of God. There is fire at the throne now. It is God’s. To seek it you have to convert to the Orthodox faith from the heart and pledge to restore it to its full height and to walk with God. If not, be warned that you will be walking right into the fire and that you will burn. Beware.

Next Page


Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Abdelaziz, Beles, Bing [Bot], ethiopianunity, Exabot [Bot], Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Harboy II, jainhost, midwest, molover, MSNbot Media