Ethiopian News and Opinion Forum


ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby ተስፋዬ ገብረአብ » 16 Sep 2012, 12:50


ከተስፋዬ ገብረአብ

የኢህአዴግ ምክርቤት ጉባኤ ተጠናቆአል። ምክርቤቱ ሃይለማርያምና ደመቀን ዋና እና ምክትል አድርጎ መርጦአል። በዚህ ምርጫ አነጋጋሪ የሆነው፣ ከምርጫው በፊት፣ “ታጋይ የነበረ ለምርጫ አይቀርብም” በሚል ማሳሰቢያ ከበረሃ የገቡ ታጋዮች ሁሉ ራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸው አንዱ ነበር። በጥቆማው ወቅት ከህወሃት እጩ ሆኖ ለውድድር የቀረበ አለመኖሩ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ሆኖአል። ሶስት ሰዎች ተጠቆሙና ሁለቱ ተመረጡ።

ሶስተኛው ተወዳዳሪ ሶፊያን አህመድ ነበር። ሶፊያን አህመድን የጠቆመችው አዜብ ነበረች። እንዲመረጥላትም አስቸግራ ነበር። ችላ ሲሏት ተወችው። በረከት ስምኦን መግለጫ ሲሰጥ የሶፊያን አህመድን ስም ለምን መጥራት እንዳልፈለገ ግን አልገባኝም።

“ሶስተኛውን ተወዳዳሪ ስም መጥቀስ አያስፈልግም” ሲል ዘለለው።

መቼም እነዚህ ሰዎች ምስጢር ሲወዱ ጉድ ነው። እነሱ ቢደብቁት እኛ ምን ስራ አለን? እንገሸልጠዋለን። የእኛ የጋዜጠኞች ጆሮ እንኳን ሰምቶ፣ ሳይሰማም ቀዥቃዣ ነው። የሆነው ሆኖ፣ “ከበረሃ የመጡት ታጋይ ባለስልጣናት ከእንግዲህ ወደስልጣን አይመለሱም” ተብሎአል። እያማከሩ ቆይተው በዚያው ወደ ጡረታ ይሸኛሉ። ይህ ዜና መቼም “እፎይ” አሰኝቶኛል። እንዲህ ማሰብ መጀመራቸው ራሱ አንድ ፀጋ ነው። ህይወት ከንቱ መሆኗን ከመለስ ህይወት ተምረዋል። እንዲህ እንደጀመሩት፣ በነካ እጃቸው እስረኛ ቢፈቱ፣ በአካባቢያችን ላይም ሰላም እንዲሰፍን አንዳንድ እርምጃ ቢወስዱ፣ ነፍሳቸው ገነት ትገባለች።

ከትናንቱ ምርጫ ጋር በተያያዘ መልከ ብዙ አስተያየቶች እየጎረፉ ነው። የህወሃት ሰዎች አካባቢ መደናገጥ ይታያል። በአንፃሩ በተቃዋሚዎች በኩል ግራ መጋባት ሰፍኖአል። “የምር ህወሃት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ አካባቢ ተሰናበተ?” ገና ግልፅ አይደለም። “በጎ ምክር ለጓዶች” በሚል ርእስ ባቀረብኩት ፅሁፍ ላይ፣ (www.tgindex.blogspot.com) ስዩም መስፍን አማካሪ ሆኖ ሃይለማርያምን እንዲመራ አሳብ አቅርቤ ነበር። ያደርጉታል ብዬ እገምታለሁ።

በርግጥ ስዩም መስፍን ታሞአል። ቢሾሙትም በርትቶ ሊሰራ አይችልም። ስዩም ጤና የለውም። በጣም ታሞአል። ለነገሩ ማን ያልታመመ አለ? ስኳሩ፣ ደምግፊቱ፣ ሪህ፣ እንትን፣ ስምአይጠሬ፣ ኩላሊት፣ ጉበት፣ ልብ፣ ሳምባ፣ ካንሰር፣ ወፈፌነት፣ ምኑ ቅጡ… የኢህአዴግ አመራር ውስጥ የሚሰማው የበሽታ አይነት ሲመዘን፣ ሁሉንም የበሽታ ተዋፅኦ የጠበቀ ይመስላል። መቀለዴ አይደለም። በበሽታ ምን ምን ይቀለዳል? 40 አመት ያለፈው አበሻ አንድ በሽታ አያጣውም። እኔ ራሴ ቮድካ ስቀምስ ልቤን ይከዳኝ ጀምሮአል።

የሆነው ሆኖ “የህወሃት ዘመን አበቃለት” የሚሉ ወሬዎች አሉ። መቸኮል እንኳ አያስፈልግም። “ህወሃቶች ከጀርባ ሆነው አገር መምራታቸው አይቀርም” የሚሉትንም ማድመጥ ያስፈልጋል። ሁኔታዎች የተደበላለቁ ቢመስሉም በአንድ ነገር ግን መግባባት ይቻላል። የህወሃት ሰዎች አማራጭ ስላጡ ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስቱ ተገፍትረው ወጥተዋል። ተስፋ የሚያደርጉት ደህንነት እና መከላከያን በመያዛቸው ነው። ይሄ ግን ከንግዲህ አያስኬድም። ሃይለማርያምን እንዲዋሽ ማስገደድ ያስቸግራቸዋል። ሰውየው ጥብቅ ሃይማኖተኛ እንደመሆኑ፣ መግደልና መዋሸት ውስጥ ለመግባት ይቸገራል። ደህንነቱ ሰው ቢገድል የሚጠየቀው ሃይለማርያም እንደመሆኑ፣ ስራውን መልቀቅ ወይም ስለተፈፀመው ድርጊት ማብራራት ይኖርበታል። በመሆኑም ህወሃት ደህንነቱን ስለያዘ ሃገሪቱን ሙሉ በሙሉ ያሽከረክራል ማለት ላይሆን ይችላል። እና መቸኮል አይገባም። ነገም ሌላ ሰንበት አለ።

የሃይለማርያም ሹመት በፓርላማ ከፀደቀ በሁዋላ፣ የራሱን አዲስ ካቢኔ እንደሚመሰርት ይጠበቃል። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለኦህዴድ የታሰበ ቢሆንም፣ የህወሃት ሰዎች “ብርሃነ ገብረክርስቶስ መሆን አለበት” ሲሉ ቸክለዋል። ወርሃ ጥቅምት ላይ የሚሆነውን እናያለን። በአዲሱ ካቢኔ ደህንነት እና መከላከያ ያለምንም ጥያቄ በህወሃት እጅ የሚቆዩ ሲሆን፣ የሌሎች የሚኒስትር መስሪያ ቤት ስልጣናት እጣ ፈንታ ገና አልታወቀም።

አዲስ አበቤ መቸም ቀልድ ይወዳል።

ማምሻውን ቢራ ላይ ቀልዶች ፈልተው ነበር አሉ። ከተፈጠሩት ቀልዶች አንዱ፣ “የህወሃት ሰዎች መለስን ከላይ አስቀምጠናል በሚል እምነት፣ ገንዘብ ሲያሳድዱ ተተኪ ባለማዘጋጀታቸው ስልጣኑ ከእጃቸው አመለጠ።” የሚለው ፉገራ አንዱ ነው።

የህወሃት ሰዎች በበኩላቸው፣ “የዚህ ሁሉ ተንኮል ጠንሳሽ በረከት ስምኦን ነው” በሚል ጥርስ ነክሰውበታል። ይሄ ሰውዬ ምን ይሻለዋል? ጠላቱ በዛ። ጀግና ነው ግን። ታንክ የመሰለ ግንባሩን ደቅኖ ሁሉን ተቋቁሞ እዚህ ደርሶአል። በረከት - የስምኦን ልጅ።

መለስና ጳጳሱ የተቃጠሩ ይመስል ተከታትለው ሄደው፣ ባልተጠበቀ ፍጥነት የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የኢህአዴግ ከፍተኛ ስልጣናት ከህወሃት እጅ መሹለካቸውን፣ “የእግዚአብሄር ተአምር” በሚል የሚገልፁም ተደምጠዋል። የፈረደበት እግዚአብሄር ያለፍላጎቱና ያለግብሩ ፖለቲካ ውስጥ እየተነከረ መከራውን ያያል። እግዜር ይርዳው!



Re: ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby Maleda » 16 Sep 2012, 17:17


TG, you don't think it is a miracle because you are an atheist.




Re: ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby Getch » 16 Sep 2012, 17:41


Unboubtedly a master piece...Tesfaye, you have that rare touch of delivering sparkling literarry beauti out of a messy and confusing termoil...thanks a lot..a very good and enlightning read.. i laughed a lot too



Re: ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby revolutions » 16 Sep 2012, 18:04


“ህወሃቶች ከጀርባ ሆነው አገር መምራታቸው አይቀርም” ....
ሃይለማርያምን እንዲዋሽ ማስገደድ ያስቸግራቸዋል። ሰውየው ጥብቅ ሃይማኖተኛ እንደመሆኑ፣ መግደልና መዋሸት ውስጥ ለመግባት ይቸገራል። ደህንነቱ ሰው ቢገድል የሚጠየቀው ሃይለማርያም እንደመሆኑ፣ ስራውን መልቀቅ ወይም ስለተፈፀመው ድርጊት ማብራራት ይኖርበታል።


Now it makes sense why Eden was losing her mind over the new leadership structure that could deprive the world renowned liars like herself of the means to deceive themselves and others. It's as though Meles Zenawi, through his timely death, demolished the TPLF house of cards and took the scraps along with him as he descended into hell.



Re: ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby BelayWmariam » 16 Sep 2012, 19:19


Nonsense ; Tesfaye Gebrab stop the same BS as Berket Siomon's campaign of "Line of Argument/ Yemesmer Leyunet that Shabia used to divide and kill us and Woyane still uses to divide and rule us. It does not work any longer, because we have learned from our past. "Never Again!"
We know the truth is that the "Hawlet" are still in arat killo palace. Hailemariam Desalene is alone at "Cross-Road."
We still straggling for unity and democracy...for last 40 years....



Peace

Postby Tsegenet » 16 Sep 2012, 19:39


Does it mean Azeb mesfin "Crazy lady" will be kicked out of the Minilik Palace and soon she and those who collaborating crime will be striped of the money they stole and will senteced to prison. That would be Hallelujah God, Who knows God works in misterious ways.

Oh the tplf securities...will be kicked out thank God those butchers! I hope our countries streets will be cleaned from those horrible kgb like mass murderers and our childrens, brother and sister will walk in a free Ethiopia!

God is definitly with Ethiopia that means we can go back home and contribute and build mama Ethiopia!



Re: ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby Tej » 16 Sep 2012, 19:39


የመከላከያውንና የደህንነቱን የስልጣን ርካብ ከቀድሞው ይልቅ ቆንጥጦ ለመያዝ እየተረባረበ ያለው ህወሓት በግልጽ ከሚታየው የፖለቲካ አመራር ወንበሩ ተነሳ። ለ21 ዓመታት የድርጅት፣ የጠ/ሚኒስትርነትና ቁልፍ የስልጣን መደቦችን ተቆጣጥሮ የኖረው ህወሓት ሁለቱን ግዙፍ ወንበሮች ለማስጠበቅ በድርጅትና በጎንዮሽ ትስስር ያካሄደው ዘመቻ አልተሳካለትም።

ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አቶ መለስን የሚተካ መሪ መሰየም አለመቻሉን አቶ በረከት ስምኦን ያሳበቁበት ህወሓት በቀጣዩ ምርጫም ወንበሩን እንደማያገኘው አቶ በረከት በግልጽ ተናግረዋል። ኢህአዴግ ቀጣዩን ምርጫ ካሸነፈ ሁለቱ አዲስ ተሿሚዎች በስልጣናቸው እንደሚቀጥሉ በይፋ ተናግረዋል።

የኢህአዴግን የአመራር ወንበር ላለማጣት ያደረገው ሙከራ በየድርጅቶቹ በተካሄደ የተናጠል ስብሰባ ተሞክሮ ሊሳካ እንዳልቻለ ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። በስም ተጠቅሰው ኢህአዴግን እንዲመሩ የቀረቡትን የህወሃት ሰዎች አንቀበልም ያሉት አባል ድርጅቶች በተቃራኒ በቀጣዩ የኢህአዴግ ጠቅላላ ጉባኤ መተካካቱ በተዋጽዖ የተመጣጠነ እንዲሆን የሚያሳስብ ጥያቄ ማንሳታቸውን የጎልጉል ምንጮች ጠቁመዋል። ከአቻ ድርጅቶቹ በተጨማሪ አሜሪካ ያስተላለፈችው መመሪያም ተጽዕኖ መፍጠሩ ተገምቷል።

ለዚህ ይመስላል አቶ በረከትና አቶ ሬድዋን ሁሴን በሂልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ላይ “አቶ ኃይለማርያም የራሳቸውን ካቢኔ የመመስረት ሙሉ መብት አላቸው” በማለት አቶ በረከት የቀድሞው ካቢኔ ሊፈርስ ወይም ማስተካከያ ሊደረግበት እንደሚችል አመላክተዋል።

የህወሓት/ኢህአዴግን አካሄድ በመገመትና በመተንተን የሚታወቁት ረዳት ፕሮፌሰር መድኔ ታደሰ ሴፕቴምበር 14 ለአሜሪካ ሬድዮ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል በሰጡት ማብራሪያ አሁን ተፈጠረው አጋጣሚ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ለውጥ ማስከተሉ አይቀሬ መሆኑን አስረድተዋል። አያይዘውም መለስ በሌሉበት ሁኔታ የቁጥጥር አስተዳደር ማራመድ እንማይቻልም አመልክተዋል። ከቁጥጥር ይልቅ ወደ መመካከርና አብዛኞችን ወደሚያሳትፍ አመራር እንደሚለወጥ ተናግረዋል።

ተተኪ ሊቀመንበር ለመሰየም ሲሳብና ሲጎተት የከረመው ኢህአዴግ ራሱ ካወጀው የአቶ መለስ ህልፈት ከሃያ ስድስት ቀናት በኋላ አስቀድሞ በስፋት የተተነበየውን ሹመት ይፋ አድርጓል። በዚሁ መሰረት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝና የትምህርት ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን የኢህአዴግ ሊቀመንበርና ምክትል አድርጎ ሰይሟል። አቶ ኃይለማርያም “ምደባው የመስዋዕትነት ነው” ሲሉ ለመንበራቸው ያላቸውን ቁርጠኛነት ለጓዶቻቸው አረጋግጠዋል። ህወሓትን ወክለው አቶ ስዩም መስፍን ለምርጫ ቢወዳደሩም ድምጽ በማጣታቸው ሳይመረጡ ቀርተዋል።

ብቸኛው የመረጃ ምንጭ ኢቲቪ መስከረም 4 ቀን 2005 ዓ ም በምሽቱ ሶስት ሰዓት የዜና እወጃው ቀንጭቦ ባቀረበው ምስል አቶ ኃይለማርያምና ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንን በኢህአዴግ ምክር ቤት የአመራር ወንበራቸው ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠው ታይተዋል።

አቶ ኃይለማርያም ይህን ጊዜ ነበር “ምድባው ለመስዋዐትነት ነው፤ ምደባው ህዝብ ከኢህአዴግ የሚጠብቀውን በሙሉ ለመፈጸም ነው፤ ምደባው በሙሉ በኢህአዴግ ምክር ቤት አባላትና በናንተ ሙሉ ምክር ከኋላና ከፊት በምታደርጉት ጥረት የተደረገ ነው …” በማለት በተሳሰረ አንደበት የተናገሩት።

ሙሉ የኢህአዴግ ምክር ቤትን ያመሰገኑት አቶ ኃይለማርያምና አቶ ደመቀ ለደንብ ያህል ቃለ መሃላ መፈጸም ብቻ የሚቀራቸው ጠ/ ሚኒስትር ም/ጠቅላይ ሚኒስትር መሆናቸውን አቶ በረከት ከጉባኤው መጠናቀቅ በሁዋላ በግልጽ ተናግረዋል። በዚሁ መሰረት በወስከረም ሶስተኛ ሳምንት አቶ ሃይለማርያምና አቶ ደመቀ የአዲሱን በትረ ሹመት ስርዓተ ፓርላማ ያከናውናሉ። የአቶ ሃይለማርያም ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋዬም ቀዳማዊት እመቤት ሆነው አራት ኪሎ ከነቤተሰቦቻቸው ይዘልቃሉ።

ህወሓት አቶ ስዩምን አቅርቦ መሸነፉን ኢቲቪ አሳብቋል። 180 አባላት ያለው የኢህአዴግ ምክር ቤት ያካሄደውን ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ቅዳሜ ምሽት በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተላለፈው ኢቲቪ ድምጽ ቆጠራውን ሲያሳይ የአቶ ስዩም መስፍን ስም በድንገት ታይቷል። የጎልጉል ዘጋቢ ከአዲስ አበባ እንዳረጋገጠው ኢቲቪ የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት ለውጪ አገር ዜጎችና ዲፕሎማቶች ለማሳየት ባሳየው ፊልም ላይ የታው የድምጽ መስጫ ወረቀት ሶስት ስሞች ያሉበት ነው። የአቶ ስዩም ስም በሶስተኛ ደረጃ ላይ ታይቷል። አቶ በረከት ስም አይጥቀሱ እንጂ ሶስት እጩዎች ለውድድር ቀርበው እንደነበር ማረጋገጣቸውን አገር የሰማውን ወሬ “ሰበር ዜና” ሲል ያጋጋለው ሪፖርተር አስታውቋል።

ለጊዜ ማግኛ የአቶ መለስ ህልፈት ምስጢር ተደርጎ በድርጅት ውስጥ ለውስጥ የነበረው ሽኩቻ ከረገበ በኋላ በጋራ የተያዘውን አቋም ሲያንከባልል የቆየው የኢህአዴግ ምክር ቤት ህብረተሰቡንና የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን የሚማጸን መልዕክት አስተላልፏል። “በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ለምትንቀሳቀሱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች” በማለት ኢህአዴግ በመግለጫው ያልተለመደ ውዳሴ አቅርቧል። “በጽሁፍና በአካል በመገኘት በሃዘናችን ስላጽናናችሁን እናመሰግናለን” ያለው መግለጫው በማያያዝ ስለ ምርጫና ስለ አብሮ መስራትም ጠቁሞ አልፏል።

“…አብረን እንሰራለን። በሚያለያዩን ጉዳዮች ላይ በሰለጠነ መንገድ ለመወያየት ዝግጅታችንን እንገልጻለን” ሲል ቃል የገባው ኢህአዴግ ተቋማዊ ለውጥ ስለመደረጉ የሰጠው ፍንጭ ግን የለም። አሁን በስራ ላይ ያለውን ምርጫ ቦርድ ይዞ ኢህአዴግ ስለ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ መናገር አይችልም። የመድረክ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ገብሩ አስራት ህወሓት/ኢህአዴግ በትግራይ ተቃዋሚዎችን ከነድራሹ ለማጥፋት እየሰራ መሆኑን በተለይም ህወሓት ይህንኑ በተደጋጋሚ በይፋ መግለጹን ባለፈው አርብ ለአሜሪካ ሬድዮ ተናግረዋል። በዚህ መነሻ የኢህአዴግ የእንተባበር ጥሪ የተለመደ ማደናገር እንደሆነ ተደርጎ ተወስዶበታል።

የፖለቲካውን ወንበር የተነጠቀው ህወሓት የጦር ሃይሉን፣ ፖሊስንና ደህንነቱን ቆንጥጦ መያዙ አገሪቱን ወደ ወታደራዊ አስተዳደር እንዳያመራት ስጋት የገባቸው ክፍሎች አቶ ኃይለማርያም የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥነት ይስሙላ ሊሆን እንደሚችል ከወዲሁ ግምታቸውን አስቀምጠዋል። ጎልጉል የአዲስ አበባ ምንጮቹን ጠቅሶ ከምርጫው ሶስት ቀን አስቀድሞ ህወሓት በፖለቲካው የአመራር ሰጪነቱ ሚና እንዳከተመበት በመረዳቱ የጦር ኃይሉና ደህንነቱ ላይ ያለውን አቅምና ኃይል ለማጠናከር ትኩረት መስጠቱን መዘገባችን ይታወሳል። ከተሿሚዎቹም መካከል የመጀመሪያዋን ሴት ጄኔራል (አስካለ ብርሃኔ ተድላ) ከአቶ መለስ ትውልድ ቦታ አድዋ ማድረጉ ለአብነት የሚጠቀስ ነው፡፡

በተመሳሳይ ዜና በስፋት ሲወራ ስለሰነበተው የሶስት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ጉዳይ አቶ በረከት ምላሽ መስጠታቸው ታውቋል። አቶ በረከት ቅዳሜ ምሽት በሒልተን ሆቴል በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በቀጣይ ይሾማሉ ስለተባሉት ሶስት ጠቅላይ ሚኒስትሮች የተጠየቁት ከጋዜጠኞች ነበር። ለጥያቄው መልስ የሰጡት አቶ በረከት “ሶስት ምክትል ጠ/ሚኒስትር የለም። የሚወራው ሁሉ ወሬ ነው። ኢህአዴግ ደግሞ በወሬ አይመራም” በማለት ትንበያውን አጣጥለውታል። አቶ በረከት ይህን ይበሉ ጉዳዩ እንደ አቶ መለስ ሞት ሰነባብቶ ይፋ ላለመሆኑ ማረጋገጫ የለም።

Source: http://goolgule.server312.com/%E1%8A%A8 ... %E1%88%B0/



Re: ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby TED1 » 16 Sep 2012, 20:10


Most comments seems to believe that Bereket simon has everything to do with what has happened, I would like to differ all those assertions .Because I strongly believe that foreign intelligences has a big share of all the decisions made at arat kilo these days.if that is not the case, I don't have the slightest doubt that all these stonehead generals and B/generals of TPLF will bow for this "no body simon."
I believe they are ordered by these foreign intelligences(their bosses) to back off or do it differently this time around for face-saving as their crime is too much to cover up from the world.
Mind you, foreign intelligences know far more better than any Ethiopians claim to know about the crime of woyanes a against their people. For bereket, he might be some at the right place at the right time.



Re: ህወሃቶች ባልጠበቁት ፍጥነት ከቤተመንግስት ተገፍትረው ወጡ

Postby getch » 16 Sep 2012, 22:35


h....please write some more and often times..I am adicted to your satire style ...."qum neger yazelle qeld"....it is brilliant and sweet...thanks s lot and "my hat's tip"

Next Page


Return to News & Opinion

Who is online

Registered users: Bing [Bot], Degnet, East, Edenabera, Google [Bot], Google Adsense [Bot], Google Feedfetcher, Macaanto, Somali-Ethio, Tekatkemaywedew, Zack