Memher Zebene, Ethiopia’s Jimmy Swaggart?

Memher (Preacher) Zebene Lema has started out as a charismatic young preacher at the Ethiopian Orthodox Medhani-Alem and St. Mary churches in DC and Maryland. Then he opened his own bible class so that he can keep all the donation from his students. After making loads of money, 2 years ago he went to Ethiopia’s capital Addis Ababa to get married at the Sheraton Hotel — Al Amoudi’s whorehouse. The fake patriarch, Ato Gebremedhin (formerly Aba Paulos), was the guest of honor. (Zebene says he did not invite him.)

Following the wedding, Ato Gebermedhin’s lackeys awarded him Abune Petros’ Cross. It is the cross this great Ethiopian hero and religious father used to compel the people of Ethiopia to resist Fascist Italy’s invasion in 1935. Italians executed Abune Petros. Now Memher Zebene walks around with Abune Petros’ cross in his pocket. He has been advised by Ethiopians inside the country and abroad to return the Cross to the Church, as it is a national treasure. He arrogantly refused.

After returning from his lavish wedding at the Addis Sheraton (a favorite spot for Arab sheiks to molest underage girls), all the money and fame became too much for Memher Zebene to handle. The “servant of God,” became a power-crazed thug who insults the elderly and antagonize senior Orthodox Church priests.

Zebene is currently using his blind young followers to harass and intimidate church leaders in the Ethiopian Community. Any one who criticizes Zebene is labled “pente” (a follower of the Pentecostal denomination) by him and his followers. Ironically, Zebene attends classes at the Howard University School of Divinity in Washington DC, which is run by adherents of the Baptist and Pentecostal denominations.

If Zebene keeps up what he is doing, he will soon become Ethiopia’s Jimmy Swaggart. He is bringing upon himself his own downfall through corruption and hubris.

Zebene just needs to follow what he preaches, and he can save himself. He is indeed a talented preacher. He started out great, particularly attracting young Ethiopians to the Church, but sudden fame and wealth have corrupted him.

The following article about Memher Zebene is sent to Ethiopian Review by a concerned Ethiopian and member of the Orthodox Church in Washington DC.

መምህር ዘበነ፥ መስቀሉን መልስ

ከታሪኩ ይበልጣል (ዋሽንግተን ዲሲ)

“ይህንን ባታደርጉ ትቀሰፋላችሁ፣ ይህንን ብታደርጉ ደግሞ የመንግስተ ሰማያት ቤታችሁ ይሰራላችኋል፤ ቤታችሁ በገነት ይሆናል” እያሉን ነገር ግን እራሳቸው በምድራዊ ቤት የዘቀጡ፣ መቀሰፊያውን የሚፈጽሙ ዓለመኞች፣ ከጎስቋሎች በይሁዳ ኮሮጆ በምጽዋት በፈለጉት መንገድ በተሰበሰበ ገንዘብ ሸራተን ሰርግ የሚሰርጉ፣ ዘመኑ ባፈራው የቅንጦት ዕቃና ተሽከርካሪ የሚንፈላሰሱና ቪላ የሚሰሩ በአንፃሩ ደግሞ ሌላው ግን ዳዋ ለብሶ፣ ድንጋይ ተንተርሶና ጤዛ ልሶ በደበሎ እንደተጠቀለለ ለቀኑ ቆሎ አሮበት ስለ አገሩና ህዝቡ በቁርና በጸሃይ ሳይዝል በጸሎት ተጠምዶ ጉድ የሚታይበት የጉድ ዘመን በኢትዮጵያ ሰፍኗል። “እኔ አውቃለሁ መንፈሳዊ ነኝ” የሚሉ ዳሩ ግን በምዝበራ የደለቡ የዓለም ሰንጋዎች፣ ግን መንፈሳዊ ተብየዎች በተናቀ ሥራቸው እውነተኛ ካህናቶችን አሰዳቢዎች ክርስቶስ መስቀሉን የተሸከመው ለመላው የሰው ዘር መሆኑንን በሆዳቸው የካዱ ጉደኛ ሹመኞችና ነጠላ ያጣፉ ጀሌዎችና ዱልዱሞች ተዋህዶ ተጥለቅልቃለችና መላ ይሻላል። ካህናት ነን እያሉ በካህናት ሥም ዛሬ በቤተክስቲያናትና በልጆቿ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ተንኮልና ደባ ሰይጣን እራሱ ቢጠየቅ “ከእነርሱ ተማርኩበት እንጅ ተንኮላቸውንና ከፋፋይነታቸውን በፍጽም አልደረስኩበትም” የሚል ይመስለኛልና ልብ ያለው ልብ ይበል!

ዘበነ (መምህር) እራሱ በተግባር የማይፈጽመውን አስተምራለሁ የሚል፤ በድህነት ከተነነ ቤተሰብ ውስጥ ወጥቶ ግን በሙዳይ በተቀፈፈ የምዕመናንና የመበለቶች ገንዘብ ሰርግ ሸራተን ያደረገ ዓለመኛ ሳባኪ በማይፈጽመው ግን የእምነት ንጉስ ነኝ ባይ ጮሌ እንደ እኩዮች ዓለም በዘረጋቻቸው የዕውቀት ዘፎች ሁሉ አውቃለሁ የሚል እውነት የሚናገሩትን ያለስማቸው ስም የሚሰጥና የሚፈርጅ ቤተክርስቲያንዋ በታሪክ ያላየቻቸውንና የማታዋቃቸውን ‘የቡድሃ’ አይሉ ‘የኒንጃ’ ወይንም የኦሎምፒክ መወዳደሪያ ወይም ሌላ ቀለም ባፅሸበረቁ የጳጳስ፣ የቆሞስ፣ የመነኩሴ፣ የቄስ ወይንም የዲያቆን አሊያም የምዕመን አይሉት የሌላ የሥልጣን ተዋረድ ያልጠበቀ ልብስ አጥላቂ “ምንቸት ጋን ነኝ” ያለበት የመለያየትና የስድብ ፊታውራሪ ፍቅርን ሳያውቀው ስለፍቅር፤ አንድነትን እየናደ ስለአንድነት፤ የውንድማማችነትን መንፈስ እየገደለ ስለወንድማማችነት መምህር ነኝ የሚል፤ አዛውንት አባቶች ወደ ኋላ እንዲቀመጡ ተደርጎ እሱ አሳራጊ፤ ይህች ከንቱ ዓለም እንኳን የቅደም ተከተል ተዋረዷን ታውቃለች ይገርማል! ግን ይህንን አያስተውለውም።

በጣም የሚገርመው የማይለው ስለሌለ “ሁለት ሶስተኛውን እልፍ ሲልም ሶስት አራተኛውን የኢትዮጵያ ሕዝብና የሰሜን አሜሪካን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን አድርጌያለሁ” ያለ ደፋር፤ ለመሆኑ ይህንን አድርጌያለሁ ካለ አመዛኙ የኢትዮጵያ ሕህብ እምነት ምን ይሆን የነበረው? አይን አውጣነት ወይንስ ሌላ? ከዚህ ቀደም እስከ አሁን የሚያንገበግበን በኢትዮጵያ የነጻነት ተጋድሎ ለዓለ ህብረተሰብ በዓለም አደባባዮች ለኢትዮጵያ እንዳንጮህ ለአገር የመጮህን ተስፋ ለማመንመን ያደረጋቸው መሰሪና አደናጋሪ ሰበካዎችና በማር የተለወሱ መርዛማ እንቅስቃሴዎች ታሪክ ይቅር የምይለው በደል ነው። አንድ ነገር ግን እናረጋግጣለን የኢትዮጵያ ትንሳዔም ቅርብ ነው!!! ይህንን ለጊዜ ፍርድ እንተወዋለን ያኔ ማጣፊያው ያጥራል።

ግለሰቡ ተመክሮ የማይሰማ ነው። ከዚህ ቀደም በቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከእየሩሳሌም በመጡ የዕድሜ ባለጸጋ መንፈሳዊ አባት “አባቶችን አትዳፈር፣ ትህትና ይኑርህ” ብለው በእማኝ ፊት ያሉትን ባለመቀበል እነሆ ዛሬ ተመክሮ የማይሰማ ትዕቢተኛ፣ ቀናተኛ የሆነና ያለአግባብ ሰዎችን በመዝለፍ አባቶችንና እናቶችን በማዋረድና በመዘርጠጥ በሚከፍተው አፍ ጭንቅላቱ የሚታይ እራሱ የቆብ፣ የልብስና የአፍ ምሩቅ መሆኑን ማወቅ ለማንም አያዳግትም። የቤተክርስቲያንዋ መከፋፈል በውግዘት መለያየት ተጠቃሚዎች እርሱና መሰሎቹ ሆነዋልና። የኢ.ኦ.ተ. ቤ/ክር አንድ ከሆነች ሊቅውንተ ቤ/ክር ስለሚሰባሰቡና ፍቅር ሁሉን ስለሚገዛ ተራራ ነኝ ያለው ኩይሳም ስለማይሆን ጠላት ዲያብሎስም ስለሚያፍርና ጥቅም ስለሚቀር የቤተክርስቲያንዋን አንድነት አይወዱትም። ያልሆነ ስም ልጠፋና ስድብ ግን ይቀናቸዋል። ስድብ ባዶነት ነው። ስድብ ከዲያብሎስ ጋር ሕብረት መፍጠር ነውና ልታቆም ይገባሃል! አደራችን የጌታችን የመድሃኒታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል እንጂ የመከፋፈልና የስድብ፣ የጩኽትና የልፍለፋ የመሳለቂያ የሥጋ ገበያ ሊሆን አይገባም እንልሃልን።

ኃይላችን ስለሆነው መስቀል ስናነሳ ጌታችን፣ መድኅኒታችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ መከራን በመቀበል በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደም ሰላምን እንዳወጀልን ሁሉ አባታችን ኢትዮጵያዊ ሰማዕቱ ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስም የእምነት የተዋህዶ አርበኛ ስለ እምነቱና ስለውድ ሃገሩ ኢትዮጵያ፣ ከአምላኩ እንዳየው መስቀሉን እንደጨበጠ ጠላትን በመገሰፅና በማውገዝ በባንዳዎች ትብብር በጨካኞች እጅ ተረሽኗል። ጌታችን በመስቀሉ ዲያብሎስን እንደገደለና እንዳሸነፈ ሰማዕቱ ኢትዮጵያዊ ጴጥሮስም በመስቀሉ ፋሽስትን ገደለና አሸነፈ። የእዛ የእምነት ፅናት የተዋህዶ አርበኝነት ምልክት ቅርስ መሆኑ ተዘንግቶ “በእከከኝ ልከክልህ” የስጋ ገበያ ለከንቱ ውዳሴ በአባ ቀውስጦስ አማካይነት ለዘበነ (መምህር) በመሰጠቱን ከዚህ በፊት እንዲመለስ በየጊዜው በኢንተርኔት ከአገሪቱ ዜጎች መጠየቁን እኛም እንደ ኢትዮጵያዊ ዜግነታችን የሃገር ቅርስ በመሆኑ ያንገበግበናልና በአስቸኳይ ያለቅድመ ሁኔታ መመለስ አልበት። ግልሰቡ አልወሰደም እንዳይባል አፍ ሲያመልጥ እንዲሉ “ለሰርጌ መመረቂያ ከአባ ቆውስጦስ ተሰጥቶኛል” በማለት በደብረ ገነት መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ሲመጻደቅ የተናገረውን ማውጣት ይቻላል። የአባ ቆውስጦስ ስጦታ ቤተክርስቲያኒቱን ለሶስተኛ ሲኖዶስ አሳልፎ ለመስጠት የተደረገ ውስጣዊ ደባ ነው ሲሉ አንዳንድ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት በጊዜው ሲናገሩ ተደመጠዋል። ታዲያ እንግዲህ ታላላቅ አባቶችን ሳያፍሩ “ሆዳሞች” ያሉና ያዋረዱ፣ ከሆዳሞች ያገኙትን ማረጋገጫ ያልቀረበበትን አለኝ የሚሉትን ክህነት እንዴት እንቀበለው? ስሊዚህ የኢትዮጵያ ቤ/ክር በቀደሙ አባቶች አማካይነት ተዋህዶ በቤዛነት ለሃገሯና ለዜጎቿ ለመላ የዓለም ክርስቲያን የተከፈለ የመስዋዕትነት ቋሚ ምስክር ነውና ዘበነ (መምህር) የመመለስ ኃላፊነትም ግዴታም አለብህ።

የተዋህዶ አርበኛ ሰማዕቱ አባታችን ቅዱስ ጴጥሮስ በምላስ፣ በልብስና በዘር ከፋፋይነት ሳይሆን የተመካው በጌታችን በመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ማለትም እንደቃሉ እኔስ ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር በሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ (ገላ 6-14) ብሎ በዛች በመጨረሻዋ የጭንቅና ፈታኝ ሰዓት የክርስቶስን ዓርማ መስቀሉን መንፈሳዊ ክብሩን በቀኝ እጁ እንደጨበጠ ጽናትን እስከሞት ታላቅ ምስክርነቱን ስለኢትዮጵያ ስለህዝቡና ስለእምነቱ ደሙን በማፍሰስ ፍቅሩን የእግዚያብሔር ጽናቱን የገለጠበት የተሰዋውን የዛን የተዋህዶ አንበሳ መስቀል ለግል መውሰድና በማስኮብለል ከሀገር በማስወጣት ወደ ኪስ መክተት የመጨረሻ ነውርና ወደ ታች መዝቀጥ ነው። መመለሱ ግዴታ ነው። “ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ” ካልሆነ በስተቀር አንተና መሰሎችህ በመጀመሪያ ገዝታችሁ ያንጠለጠላችሁትን መስቀል በቅጡ ያዙ! የሰማዕቱን ፈለግ ተከተሉና ከከንቱ ውዳሴ ይልቅ እውነቱን የቤተክርስቲያን አንድነት ጩሁ። መጀመሪያ በዓለም ካለ ህይወት እንደ ሸራተን ከመሰለው ውጡ። አባታችን የተገኘው በመስቀሉ ስር ከቤተክርስቲያን እንጅ ሸራተን በሳንቲም መልቀሚያ ጉባዔ አልነበረም።

ስለአባ እከሌ መኖር ይብቃችሁ። ነገሩ የእናንተ አባእገሌ ሆዳችሁ ጥቅማችሁ ነው።እስኪ የእውነት ሰው ሁኑና ስለ አገር የማይነገርበትና ከእውነት ከራቀው አደንቋሪ ጩኸት ውጡና ሰማዕቱ ጴጥሮስን ልትሆኑት ባትችሉም መሰሉት። ይህ መስቀል እንዲመለስ ሕግም ያስገድዳል። ቅርስን መዝረፍና ለግል ማድረግ የማየገባውን ማድረግ ወንጀል ነውና!!! ምን ይታወቃል አሊያም አንድ ቀን እንደ ድንቅነሽ (ሉሲ) ታከራዩትና ገንዘብ ትሸቅጡበት ይሆናል። ሕዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ፊሊጶ 3-10 በመልዕክቱ “የእነሱ መጨረሻ ጥፋት ነው፣ ሆዳቸው አምላካቸው ነው። ክብራቸው በነውራቸው ነው፣ አሳባቸው ምድራዊ ነው” እንዳለን መጨረሻቸው ጥፋት የሆነ የስም ክርስቲያኖች ፊሊጵ 3-10 ታንኩንና የመርዝ ጭሱን እየባረኩ በመላክ በባንዳዎች ትብብር ኢትዮጵያ ሀገራችንና ህዝቧን በወረሩበት በዛ የመከራ ቀን ብዙ ተጎድተናል፤ ከጉዳታችም አንዱ የአቡነ ጴጥሮስ በባንዳዎች ትብብር መረሸን ነው። መስቀሉ የዚህ ምስክር ነው። ቫቲካንም ይቅርታ ልትጠይቅበት ይገባል። እውነተኛ አባቶቻችንም ይህንን ጥያቄ እንድትጠይቁ ጩኽታችን ይድረሳችሁ።

አባታችን ካህን አሮንና ልጆቹ የእስራኤልን ልጆች እንደባረካቸው፣ ያዕቆብም በሸመገለ ጊዜ ኤፍሬምንና ምናሴን እንደባረካቸው አባታችን ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስም የኢትዮጵያን ልጆችና ምድሯን ሁሉ ስለእውነትና ነጻነት የባረከበት የኢትዮጵያ ሕዝብ ሀብትና ቅርስ የሆነው ያ ታሪካዊ መስቀልም ትናንትም ዛሬም ወደፊትም የማይሸጥ፣ የማይለውጥና የሀገርና የህዝብ ሀብት ነው። ይህ መስቀል አቡነ ጴጥሮስ የነፍሳችን መዳኛ እንዲሆን እንድናስተውል ለኢትዮጵያ አለኝታ እንዲሆነን ትቶልን ያለፈ የእውነት ቅርስ ነውና ዘበነ (መምህር) መልስ! በሀገርና በዓለም ዙሪያ የምትገኙ ኢትዮጵያውን ይህ መስቀል እንዲመለስ የበኩላችሁን ጥረት ታደርጉ ዘንድ ጥሪ ይድረሳችሁ። በተለይም የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ፣ የጀርመን ድምፅ ሬዲዮ፣ ነፃነት ለኢትዮጵያ ሬዲዮ፣ የህብረት ሬድዮ፣ አዲስ ድምፅ ሬዲዮ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ድምፅ ሬዲዮ፣ የኢትዮጵያዊነት ሬዲዮ፣ የሀገር ፍቅር ሬዲዮ፣የኢትዮጵያ የዘውድ ምክር ቤትና እንዲሁም ሌሎችም የህዝብ መገናኛ አውታሮችና ድረ ገጾች የሀገርን ቅርስ ከማስመለስና የሀገርን ታሪክ ለተተኪው ትውልድ ከማቆየት አኳያ በጉዳዩ ላይ ጥሪ አድርገንላችኋለንና ምላሻችሁን እንጠብቃለን። ስለሁሉም ነገር ልዑል እግዚያብሔር ይመስገን።