እነ ኢንጅነር ሀይሉና ዶ /ር ብርሀኑ ዛሬ በፍርድ ቤት መሰከሩ

በዛሬው ጁላይ 31/2007 ኢንጅነር ሀይሉና ሻውልና ዶ /ር ብርሀኑ ነጋን ጨምሮ አንዳንድ የቀድሞው ቅንጅት አመራሮች የአቶ ነፃነት ደምሴና የአቶ ዳንኤል በቀለ መከላከያ ምስክሮች በመሆን ነው በቃሊቲ እስርቤት ባለው ችሎት የመሰከሩት :: የቅንጅት አመራሮቹ ሁለቱ የ “NGO” ሰራተኞች የቅንጅት ለአንድነትና ዲሞክራሲ አባላት እንዳልነበሩ አረጋግጠዋል ::

ታዲያ በዛሬው ቀን ቀደም ሲል Recognition የነሱት ፍርድ ቤት ዛሬ ክቡር ፍርድ ቤት እያሉ በመናገር እያንዳንዳቸው እውቅና ለግሰውታል :: ይህ ማለት በተዘዋዋሪ ተፈርዶባቸው የነበረውን ፍርድ ጭምር “recognize” እንደማድረግ የሚያስቆጥር መሆኑን የህግ አዋቂዎች ያስረዳሉ ::