የአቶ ክንፈ /መድህን ገዳይ በሞት መቀጣት

የቀድሞውን የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ሚንስትር አቶ ክንፈ ገብረመድህንን በጥይት የገደሉት ሻለቃ ጸሀየ ወልደስላሴ በጠቅላይ ፍርድ የተበየነባቸው የሞት ቅጣት ዛሬ መፈጸሙን የኢትዮጵያ ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር አስታወቀ። ሻለቃ ጸሀየ ወልደስላሴ  የሞቱ ቅጣት እንዴት እንደተፈጸመባቸው ግን አስተዳደሩ አእገለጸም። የቀድሞውን የኢትዮጵያ የሀገር ውስጥ ሚንስትር የተገደሉት የኢትዮጵያ ዋነኛ ገዢ የፖለቲካ ፓርቲ ሕዝባዊ ሀርነት ትግራይ ህወሀት አመራር በተከፋፈለበት ወቅት ከስድስት ዓመታት በፊት ነበር።