የ «ሉሲ» የድብቅ ጉዞ

 የቅድመ ሰው ቅሪተ አካል « ሉሲ» ወይም  ድንቅነሽ ለዓለም አቀፍ ትርዒት ወደ ዩኤስ አሜሪካ ተወሰደች። እንዳትፈራርስ በጥንቃቄ ልትያዝ ድንቅነሽ ይህንኑ አከራካሪ ጉዞዋን የጀመረችው ትናንት መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ የታሪክ ቤተ መዘክር ሰራተኞች አስታውቀዋል። ድንቅነሽ በዚህ ወር ወደ ዩኤስ አሜሪካ እንደምትጓዝ ቀደም ብሎ ብትታወቅም፣ የትናንቱ ጉዞዋ  ይፋ ሳይደረግ የተከናወነበት ድርጊት ብዙዎችን አስገርሞዋል፤ አጠያይቆዋልም።

Source: DW