የሚያዝያው ምርጫ መመዝገቢያ ወቅት ለአንድ ወር ተራዘመ

በምርጫ ታሪክ በጣም ቀዝቃዛውና በተመዝጋቢ ድርቀት አስተባባሪዎቹን ያሸማቀቀው የሚያዝያው ምርጫ የተመዝጋቢዎች የጊዜ ሰሌዳ ዛሬ የሚጠናቀቅ ቢሆንም እስከ ቀጣዩ ወር መጀመርያ ድረስ እንዲራዘም በምርጫ ቦርድ ተወስኗል፡፡

ይህ ገዢው ፓርቲ ከራሱ ጋር የሚወዳደርበት የመሰለ የምርጫ ሂደት ለወያኔ ያለው ፋይዳ ያን ያህል ባይሆንም እንደተቃዋሚ የሚቆጠሩትን በጣት የሚቆጠሩ ፓርቲ እጩዎች ከማሰር ጀምሮ የተለያዩ ጫናዎች እያደረሰባቸው መሆኑን መሪዎቹ በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡