እነ አቶ አባይነህ በመኢአድ ሰርተፍኬት እየተንቀሳቀሱ ነው

የቅንጅት ከፍተና አመራሮችን አግደናል በማለት ከህገ ደንብ ውጭ የሆኑ አፍራሽ እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂዱ የቆዩት እነ አቶ አባይነህ የመኢአድን ሰርተፍኬት በማደስ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለዜና አገልግሎቱ ገለጹ፡፡ ስራ አስፈጻሚው መታገድ ዋንኛ አላማም ይህ ምስጢራዊ አጀንዳ እንደነበር ታውቋል፡፡

የሚቀርቧቸው ሰዎች እርምጃው አደገኛ አይሆንም ወይ በማለት ጠይቀዋቸው አሁንም እየሰራን ያለነው የቅንጅቱን ስራ ነው፤ ይሁንና በህጋዊ መንገድ ገንዘብ ለማንቀሳቀስና ህገ-ወጥ ናችሁ የሚለውን ክስ ለመከላከል ነው የሚል ምላሽ በአቶ አባይነህ ተሰጥቷል፡፡

ራሳቸውን ህጋዊ ካባ አልብሰው ለመንቀሳቀስ የመጀመርያው እንቅፋት የነበረው የታገደው አመራር በመሆኑ በአሁኑ ሰአት ያለምንም ተጽእኖ በመንቀሳቀስ ላይ ይገናሉ፡፡ በገዢው ፓርቲ በኩል አንዳችም እንቅፋት እንዳይገጥማቸውና ለሁለት ተከፍለው እስከተጓዙ እንዲቆራቆሱ በሚል በወያኔ ካድሬዎች ጉዳዩ በቸልታ እንዲታይ መደረጉን ሁኔታው አመልክቷል፡፡