Mistreatment of Ethiopian Airlines hostesses

የኢትዮጵያ አየር መንገድና አስተናጋጆቹ


ከአዲስ አበባ ወደ ለንደን በኢትዮጵያ አየር መንገድ እገዝ ነበር፡፡ ያ ጉዞ ነው ታዲያ ለዚህ ጽሑፍ መነሾ የሆነኝ፡፡

በዚያ ጉዞ ላይ እንደአጋጣሚ ሆኖ ለመጸዳዳት አስቤ ክፍሉ ስለተያዘብኝ እዚያው በሩ አጠገብ ቆም ብዬ ተራ ስጠብቅ የአስተናጋጆቹ ኃላፊ የነበረችው ወይዘሮ (ስማን ባውቀውም ከመጥቀሱ ተቆጥቤአለሁ) አንዳን አስተናጋጅ ዝቅ ባለ ድምጽ በጣም በሚዘገንን አነጋገር ስትቆጣት ሰምቼ በጣም አዘንኩ፡፡ አስተናጋጃ ካጠፋች ቁጣው ተገቢ ነው ሆኖም ለቁጣው ቦታም ጊዜም ያስፈልገዋል ባይ ነኝ፡፡ ወጣተ አስተናጋጅ ከፍርሃት ይሁን ከአክብሮት የተነሳ ምንም ዓይነት መልስ አትሰጥም ነበር፡፡ የቀጠለውን ሁኔታ ሳልገነዘብ መጸዳጃው በመለቀቁ ወደዚያው አመራሁ፡፡

ሁኔታው በአንጎሌ ውስጥ ተቀርጾ የቀረ ስለነበር ልረሳው አልቻልኩም፡፡ ከለንደን ስመለስና ከዚያም አንዴ ወደ ባንግጎንግ ቀጥሎም ወደ ሮም ስገዝ አጋጣሚዎችን በመጠቀም አስተናጋጆችን በዘዴ ለማነጋገር ሞክሬ ያተረፍኩትን በአጭሩ ላወጋችሁ ፈለግሁ፡፡

በመሠረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአስተናጋጆች አያያዝ በውጭ እንደሚወራለት ሳይሆን ወደ አሳፋሪነቱ እየተገዘ ነው፡፡

በአጠቃላይ ባይሆንም አስተናጋጆቹን የሚመሩት ኃላፊዎች ጸባይ ፈጽሞ የማይመችና በማንአለብኝነት የሚወረውሩት ቃላት አጥንት የሚሰብር እንደሆነ አብዛኛዎቹ አስተናጋጆች ይስማሙበታል፡፡ ተደፍረው የማይነኩ ወንዶቹ አስተናጋጆች ብቻ ናቸው፡፡ አልፎ አልፎ ሥራውን የሚለቁ ሴት አስተናጋጆች ቢኖሩ አብዛኛውን ጊዜ በነዚሁ ጸባይ በተነፈጋቸው ሃላፊዎች ወከባ ምክንያት መሆኑ ይነገራል፡፡

እላይ የተጠቀሰውን ሁኔታ ለማወቅ ጥረት ሳደርግ ያገኘሁትን ልጨምር፡፡ ከዚህ በላይ የተዘረዘረው በበረራ ላይ የሚያጋጥመው ሲሆን በአስተናጋጆቹ የበረራ ፕሮግራም ላይም የሚያማርሩና የሚያበሳጩ ሁኔታዎችም እንዳሉ በሰፊው ይወሳል፡፡ ለምሳሌ ለእያንዳንዱ አስተናጋጅ ለተወሰኑ ጊዜያት የሚገለግሉ የበረራ ፕሮግራሞች ይበተናሉ፡፡ ይህም የሚሆነው አስተናጋጆቹ የሚሄዱበትን አገርና የሚቆዩበትን ጊዜ በቅድሚያ አውቀውት እንዲዘጋጁ ይረዳቸዋል ተብሎ ስለተገመተ ነው፡፡ አሠራሩ ፍጹም ትክክለኛ ቢሆንም ነገር ግን ፕሮግራሙን የሚያቀነባብሩት የቢሮ ሠራተኞች የሚፈጽሙት የአሠራር በደል ብዙዎችን አስተናጋጆች ያማረረ ነው፡፡ ለምሳሌ ፕሮግራሙን ከሚያቀነባብሩት አንዳንዶቹ የሚያውቀት አስተናጋጅ በውሎ አበል ክፍያ እንደትጠቀምና ስትመለስም ምናምን ይዛ እንድትመጣ ከፈለጉ ብዙ ቀናቶች ውጭ የሚያቆየውን የበረራ ፕሮግራም ለሚፈልገት በመስጠት ለዚያ ጉዞ የተመደበችውን አስተናጋጅ በደርሶ መልስ ጉዞ ላይ በመቀየር ያለጊዜያቸውና ያለፕሮግራማቸው እንዲበሩ የወጣውን ፕሮግራም በማፋለስ አግባብ ያልሆነ ሁኔታን እንደሚፈጥሩ ይነገራል፡፡ እንዲሁም በአስቸካይና በሚስጥር የሚመጣላቸው ነገር ካለም የሚያውቀትንና የሚያምነትን አስተናጋጅ

እንድትበር ፕሮግራሞችን በመለዋወጥ አስተናጋጆችን እንደሚበድሉም በሰፊው ይወራል፡፡

ሁንታው ከአሰተናጋጆች በአቤቱታ መልክ ለሚመለከተው ክፍል ሲቀርብም በአብዛኛው ተቀባይነት የለውም፡፡ እየተከሰሱ ቢሮ ተጠርተው በሚሄዱበት ጊዜ እዚያ የሚደርስባቸውም ወረፋ በጣመወ የሚያሳዝን እንደሆነም ይናገራሉ፡፡
በአጠቃላይ ነገሮች ሲስተዋሉ ግን ከአየር መንገዱ የአስተዳደር ቸልተኝነት ጋር ተያይዞ የሚያዘግም ድክመት መሆኑ እንዳልቀረ ይገመታል፡፡

ከዚህ በፊት የነበረውና አየር መንገዱ ስሙ በመልካም የሚነሳበት ለአስተናጋጆቹ የሚሰጠው እንክብካቤና አክብሮት እየቀለለ በመምጣቱ አየረ መንገዱን እየለቀቁ የሚሄዱት ብዛት ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመሩ አልቀረም፡፡

አሁን በቅርቡ ደግሞ የአስተናጋጆች የበረራ ሰዓት ከ13 ወደ 15 ሰዓት ከፍ እንዲል ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ መሆኑ ይነገራል፡፡ በመሠረቱ የዓለም አቀፍ የበረራ ሕግ በተከታታይ የበረራ ጊዜው ከ13 ሰዓት እንዳይበልጥ ይደነግጋል፡፡ አየር መንገዱ በ15 ሰዓቶች ውስጥ ሄዶ ሊመለስባቸው የሚችሉ አገሮች በዛ ያሉ ሆነው በመገኘታቸው ሄደው ቢያድሩ ለሠራተኞች የሚከፈለውን የውሎ አበል ለመቀነስ የበረራ ጊዜውን ወደ 15 ሰዓት ከፍ ለማድረግ ሲታሰብ የአስተናጋጆችን ከፍተኛ ድካም ሳያገናዝቡ አብራሪዎችን ብቻ የደሞዝ ጭማሪ እናደርግላችሃለን በሚል ለማሳመን እየተሞከረ ሲሆን አብዛኛዎቹ ካለው ሃላፊነት ጋር ሲታይ ከድካም ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለው ከፍተኛ ችግር በገንዘብ ሊተመን ስለማይችል የበረራው ጊዜ ከ13 ሰዓት እንዳይበልጥ እንቢተኛነታቸውን ሲገልጹ ጥቂቶቹ ደግሞ ገንዘብ ተጨምሮልን እንሥራ በማለት በመከፋፈላቸው ጉዳዩ በእንጥልጥል ላይ ይገኛል፡፡ የአብዛኞቹ አስተናጋጆች ስጋት ግን በጣም ከፍተኛ ነው፡፡ ምክንያቱም በአንድ በረራ ስንካ የአገር ውስጥ ካልሆነ በስተቀር አሥር በማይበልጡ አስተናጋጆች ቢያንስ እስከ 250 መንገደኞችን በቁርስና ምሳ ወይንም በምሳና በእራት ማስተናገድ የተለመደ ሲሆን ድካሙ ምን ያህል እንደሆነ ሲገመት አሁን የበረራውን ጊዜ ወደ 15 ሰዓት በማራዘም የደርሶ መልስ ጉዞ ከተመደበ እስከ 500 ሊደርሱ የሚችሉትን መንገደኞች ማስተናገድ ድካሙ ከእንቅልፍ ማጣት ጋር ተደርቦ ፈጽሞ ለመሸከም እንደማይቻል በእርግጠኝነት ይናገራሉ፡፡ ይህ አካሄድ ሲታይ አየር መንገዱ ጥቂት ለማትረፍ ብሎ አብራሪዎችንና አስተናጋጆችን በበረራ ሰዓቶች መራዘም እያዳከመ ሊከሰት የሚችለውን ችግር ማስተዋል እንዴት እንደተሳነው ለመገመት ያስቸግራል፡፡

ከዚህ በፊት አየር መንገዱ ብዙ ልምድ ያላቸውን ቴክኒሺያኖቹን ከአስተዳደር ጉድለት የተነሳ እየኮበለሉበት መሆኑ በሰፊው ተወርተል፡፡ ታዲያ እነዚህም በትህትናና በቅልጥፍና የተሞሉ አስተናጋጆቹን አሰልጥኖና ለብዙ ልምድ አብቅቶ ከአሠራር ጉድለት የተነሳ ቀስ በቀስ እነዳያጣቸው አለ ለሚባለው ጉድለት እርምት ቢደርግ ምኞታችን ነው፡፡ ካልሆነ ግን የውጭ አገር ተወላጆች ቴክኒሺያኖች እያፈላለግን እንደሆነ ሁሉ አየር መንገዳችን በአገር ልጅ ማስተናገዱን ጥሎ በውጭ አገር ተወላጆች እንዳያስተናግደን ሰጋታችን መሆኑን ሳንገልጽ አናልፍም፡፡

ከጌታብቻ አንተነህ
አዲስ አበባ