ኢትዮጵያ፣ በህዳርና በ… ሁልጊዜ አስታውሳለሁ!!

ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገ/ማርያም
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ

Eth massacre victims

 

 

 

 

 

 

 

 

 

የህዳር ወር በኢትዮጵያውያን በአሰቃቂነቱ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል፡፡
እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2013 ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ ሰቆቃ የተፈጸመበት ወር ነው፡፡ ላለፉት ጥቂት ዓመታት በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ፣ በሚሰሩና የፖለቲካ ጥገኝነት ለመጠየቅ ጥረት በማድረግ ላይ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን/ት ላይ ስልታዊ የሆነ ጥቃት ሲሰነዘር ቆይቷል፡፡ እንዲያውም በግል በሚኖሩበት ቤት እምነታቸውን በማራመዳቸው ብቻ ኢትዮጵያውያኑ/ቱ ዜጎች ላይ የወንጀል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ እንዲጋዙም ተደርጓል፡፡

እ.ኤ.አ 2011 የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ (Human Rights Watch) ዘገባ የሳውዲ አረቢያ ፖሊስ “ህገወጥ ስብሰባ በሚል ሰበብ 35 የክርስትና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያወያንን/ትን“ “በአንድ ኢትዮጵያዊ የክርስትና እምነት ተከታይ የግል መኖሪያ ቤት በእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ዋዜማ ተሰባስበው ጸሎት በማድረግ ላይ እንዳሉ” በፖሊስ ቀጥጥር ስር ውለዋል” ይላል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በሳውዲ አረቢያ ጥገኝነት በሚፈልጉ እና ሌሎች ስደተኛ ኢትዮጵያውያት የቤት ሰራተኖች ላይ በሚደረገው ሰብአዊ መብት ረገጣ ምክንያት ምንጊዜም የማያቋርጥ ትችት እየተደረገ መሆኑን መግለጽ ማጋነን አይሆንም፡፡ በዚህ ወር በዕየለቱ በሚባል መልኩ የሳውዲ አረቢያ ፖሊሶች፣ የደህንነት ኃላፊዎችና ተራ የሳውዲ ዜጎች በየመንገዱ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎችን ያድናሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሰቃያሉ፣ አንዳንድ ጊዜም ይገድላሉ፡፡ የሳውዲ ፖሊሶች ኢትዮጵያውያንን ሲያሰቃዩ የሚያሳየው የቪዲዮ ቅርፅ ለህሊና የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ የሳውዲዎች ኢትዮጵያውያንን በየመንገዱ የማባረር ሁከት፣ ጥቃት የመሰንዘርና የመግደል ድርጊት ምንም ዓይነት ማብራሪያ አያስፈልገውም፡፡ በአሁኑ ጊዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን/ት ላይ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ የሚያሳየው የፎቶግራፍ ምስል አስደንጋጭና ከሰለጠነ የሰው ልጅ አስተሳሰብ በእጅጉ የዘለለ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያለው ገዥ አስተዳደር 200 ሺ እና ከዚያ በላይ የሚሆኑትን በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያን/ት ለማገዝ ምን እያደረገ ነው? ምንም!!! እራሱ አምኖ በተቀበለው መሰረት ገዥው አስተዳደር ምን ያህል ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ እንደሚኖሩ እንኩዋን አያውቅም፣ ሆኖም ግን ተጨባጭነት በሌለው መልኩ ኢትዮጵያውያንን/ትን ከሳውዲ አረቢያ ሙሉ በሙሉ በተቻለ መጠን ወደ ኢትዮጵያ እመልሳለለሁ የሚል ቃል ገብቷል፡፡

የወባ ተመራማሪው “የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር”፣ ቴዎድሮስ አድሃኖም የሳውዲ መንግስት በግዛቱ በሚገኙት ስደተኛ ኢትዮጵያውያን/ት ሰራተኞች ላይ የፈጸመውን አረመኒያዊ የኃይል እርምጃ “መንግስቱ አውግዘዋል፡፡ ይኸ በፍጹም ተቀባይነት የለውም፡፡ ይህን ጉዳዩ የሳውዲ መንግስት እንዲያጣራ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ እዚያ በነበሩበት ጊዜ በክብር መያዝ የነበረባቸውን ዜጎቻችንን ወደ ሀገራቸው ለመመለስም ደስተኞች ነን፡፡ ተቀባይነት የለውም” የሚለውን አባባል ገዥው አስተዳደር እንደ አስፈሪ የጭካኔ ድርጊቶች፣ ያለመሰልጠንነትና ዘግናኝ ጨካኝነትና ወንጀለኛነት የሚሉትን ቃላት ለመግለጽ የሚጠቀምበት የውግዘት ቃል ነው፡፡ አልጄዚራ እንደዘገበው ከሆነ በተፈጸመው ድርጊት ተበሳጭተው የነበሩ ኢትዮጵያውያን/ት አዲስ አበባ በሚገኘው የሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት ሰላማዊ ተቃውሟቸውን ለማሰማት በሄዱበት ጊዜ የገዥው አስተዳደር ፖሊስ በቁጥጥር በማዋል ድብደባ ፍጽሞባቸዋል፡፡ “ፖሊሶች ከመጡ በኋላ ደብድበውናል፣ እና በአሁኑ ጊዜ ከ100 በላይ የሚሆኑ ሰዎች በእስር ቤት ይገኛሉ” በማለት የተቃዋሚው የሰማያዊ ፓርቲ ነባር አባል ጌትነት ባልቻ ገልጿል፡፡ ጌትነት በመቀጠልም “የፓርቲው ሊቀ መንበርና ምክትል ሊቀመንበር ከታሰሩት ውስጥ ይገኙበታል” በማለት ሀሳቡን አጠቃሏል፡፡

ሆኖም ግን ኢትዮጵያውያን/ት በሀዳር ወር መጎዳትና መጎሳቀል ለምን ይደንቀን? እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 ያለው የገዢ አስተዳደር ለመናገር በሚዘገንን መልኩ የጭካኔ ድርጊት በአትዮጵያኖች ላይ ፈፅሞአል:: በዚያው ዓመት የፓርላማውን ምርጫ ተከትሎ በግንቦት ወር በጠራራ ፀሐይ የተዘረፈውን የህዝብ ድምጽ በመቀወም ድምጻቸውን ባሰሙ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች እራሱ መለስ ዜናዊ ያቋቋመው አጣሪ ኮሚሽን 193 ያልታጠቁ ወንዶች፣ ሴቶች እና ልጆች በአዲስ አበባ መንገዶች በሰላማዊ መንገድ ተቃውሟቸውን በመግለጻቸውና እና ሌሎች በከፍተኛ ደህንነት በእስር ቤት የሚገኙ እስረኞችን ሆን ተብሎ በጥይት ደብድበዋል፣ ሌሎች 763 የሚሆኑት በጽኑ ቆስለዋል፡፡

እ.ኤ.አ ከ2007 ጀምሮ በየጊዜው በህዳር ወር እ.ኤ.አ የ2005 ምርጫን ተከትሎ በመቶዎች የሚቆጠሩ ጨዋና ያልታጠቁ ሰልፈኞች ተኩስ በመክፈት ገደሏቸው፣ አካለ ጎደሎ አደረጓቸው፡፡ እኔም ያንን ጊዜ ለማስታወሰ ስል መጻፌን ቀጥየ ነበር፡፡

በመጀመሪያው የማሰታወስ ጽሁፌ እ.ኤ.አ በኖቬምበር 2005 እና በጁን 2005 የተከፈለው መስዕዋትነት ለዘላለም ይታወሳል! ለአንባቢ ዎቼም ሳስታዉስ በህይወት ላሉትና ለሞቱት ምስክርነት መስጠት እንዳለባችሁ የሞራል ግዴታ ተጥሎባችኋል ብዬ ነበር፡፡ ኤሊ ዌይሰል የዕልቂቱ ተራፊና የኖቬል ተሸላሚ በክብር እንዳስቀመጠው “ማስታዋስ አለብን ምክንያቱም የጋራ ትውስታችን የሆኑትን ያለፉ ድርጊቶች የወደፊቱን ትውልድ መብት መከልከል ስለማንችል ነው መርሳት መጥፎ ነገር ብቻ አይደለም ነገር ግን ስድብም ነው፡፡ የሞቱትን መርሳት ሁለተኛ ከመግደል እኩል ነው፡፡”

በ2005 ያለቁትን መርሳት ማለት በእነርሱ ላይ የተፈጸሙትን ግፎች መርሳት እንዲህም ያሉትን አረመኔአዊ ወንጀል መርሳትማለት ነው፡፡ እልቂቱን መርሳት ማለት ወንጀለኞች ተጠያቂ እንዳይሆኑ የልብ ልብ መስጠት ማለት ነው፣ ምክንያቱም ወንጀሎቹ ተረስተዋል፡፡ በመጨረሻም መርሳት ማለት በስልጣን ላይ ያሉ ወንጀለኞች እንደገና እና እንደገና የወንጀል ደረጃውን ከፍ በማድረግና ተጠያቂነት የሌለበትን ሁኔታ በመፍጠር ወንጀል እንዲሰሩ ማበረታታት ማለት ነው፡፡

አስታውሳለሁ! በምንም አይነት አልረሳምም፣ በፍጹም!!!

አስታውሳለሁ ምክንያቱም እኔ ካላስታወስኩ ማን ያስታዉሳል? አስታውሳለሁ ምክንያቱም የምረሳ ከሆነ ወንጀሎችና ወንጀለኞች ይረሳሉ፡፡ የምረሳ ከሆነ ታሪክ እንዴት ሊያስታውስ ይችላል? ታሪክ ሊያስታውስ የሚችለው ሌላ ሊያስታውስ የሚችል ሰው ሲኖር ነው:: በህዳር፣ በታህሳስ፣ በጥር፣ በየካቲት፣ መጋቢት፣ ሚያዝያ… ዛሬ ለኢትዮጵያ ወጣቶችና ነገ ለሚወለዱ ህጻናት አስታውሳለሁ፡፡

የእኔን ስራ በማድነቅና ለበርካታ ዓመታት ሲደግፉ ሲቆዩ ሌሎች ደግሞ ሲተቹ ሲቃወሙ የሚኖሩ አሉ። እኔ በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ ነው ይሉኛል:: በኢትዮጵያውያን ሰበአዊ መብቶች ችኮ መሆን ለኔ ታላቅ ክበር ነው::

የ2005 ዕልቂትን አስታውሳሁ፡፡ እያንዳንዱን በግፍ የተገደሉትን አስታዉሳለሁ፡፡ አስታውሳለሁ ወጣት ሴቶች ወደፊት እናት ላይሆኑ፣ ወጣት ወንዶችን የአራዊቱን ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም ወደፊት አባት ላይሆኑ፣ ወላጅ የሌላቸውን ወላጆቻቸው የተገደሉባቸውን አስታውሳለሁ፡፡ ልጆቻቸው የተገደሉባቸውን እናቶችንና አባቶችን አስታውሳለሁ::

ወንጀለኞችን አልረሳም፣ ተንኮል የሰሩትን 237ቱን የፖሊስ አባላት አስታውሳለሁ፣ የወንጀለኞችን ቁንጮና መሪ የነበረዉን አራዊትን አልረሳም:: የአራዊቱን ጭፍረኞች ገዳዮችን አልረሳም::

አስታውሳሁ፣ መቼ ረሳለሁ: ሁልጊዜ ህዳርን፣ ታህሳስን፣ ጥርን፣ የካቲትን፣ መጋቢትን፣ ሚያዝያን…. አልረሳም፡፡

ተ.ቁ ስም ጾታ እድሜ ስራ
መግለጫ
1 ሬቡማ ኢርጋታ ወ 34 ግንበኛ
2 መለሳቸው አለምነው ወ 16 ተማሪ
3 ሀድራ ኦስማን ወ 22 አይታወቅም

4 ጃፋር ኢብራሂመ ወ 28 ቢዝነስ
5 መኮንን ወ 17 አይታወቅም
6 ወልደሰማያት ወ 17
7 ባህሩ ደምለው ወ አይታወቅም
8 ፈቀደ ነጋሽ ወ 25 መካኒክ
9 አብርሀምይልማ ወ 17 ታከሲ ነጂ
10 ያሬድ እሸቴ ወ 23 ቢዝነስ
11 ከበደ ገ/ህይወት ወ 17 ተማሪ
12 ማቴዎስ ፍልፍሉ ወ 14 ተማሪ
13 ጌትንት ወዳጆ ወ 48 ቢዝነስ
14 ቃሰም ራሽድ ወ 21 መካኒክ
15 ሸውሞሊ ወ 22 ቢዝነስ
16 አሊየ ኢሳ ወ 20 የቀን ስራ
17 ሣምሶን ያዕቆብ ወ 23 የህዝብ ማመላ
18 አለባለው አበበ ወ 18 ተማሪ
19 በልዩ ዛ ወ 18 ትራንስ. ረዳት
20 ዩሱፍ ጀማል ወ 23 ተማሪ
21 አብርሃም አገኘሁ ወ 23 ትራንስ.ረዳት
22 መሀመድ በቃ ወ 45 አርሶ አደር
23 ረዴላ አወል ወ 19 የታክሲ ረዳት
24 ሀብታሙ ኡርጋ ወ 30 ቢዝነስ
25 ዳዊት ፀጋዬ ወ 19 መካኒክ
26 ገዛኸኝ ገረመው ወ 15 ተማሪ
27 ዮናስ አበራ ወ 24 አይታወቅም
28 ግርማ ወልዴ ወ 38 ሾፌር
29 ደስታ ብሩ ሴ 37 ቢዝነስ
30 ለገሰ ፈይሳ ወ 60 ቢዝነስ
31 ተስፋዬ ቡሽራ ወ 19 ጫማ ጠጋኝ
32 ቢንያም ደገፋ ወ 18 ስራ አጥ
33 ሚሊዮን ሮቢ ወ 32 ትራንስ.ረዳት
34 ደረጀ ደኔ ወ 24 ተማሪ
35 ነብዩ ሃይሌ ወ 16 ተማሪ
36 ምትኩ ምዋለንዳ ወ 24 ዶመስቲክ ሰራተኛ
37 አንዋር ሱሩር ወ 22 ቢዝነስ
38 ንጉሴ ዋብግነ ወ 36 ዶመስቲክ ሰራተኛ
39 ዙልፋ ሀሰን ወ 50 የቤት እመቤት
40 ዋስይሁን ከበደ ወ 16 ተማሪ
41 ኤርሚያስ ከበደ ወ 20 ተማሪ
42 00428 ወ 25 አይታወቅም
43 00429 26 አይታወቅም
44 00430 30 አይታወቅም
45 አዲሱ በላቸው ወ 25 አይታወቅም
46 ደመቀ አበበ ወ አይታወቅም
47 00432 22 አይታወቅም
48 00450 20 አይታወቅም
49 13903 25 አይታወቅም
50 00435 30 አይታወቅም
51 13906 25 አይታወቅም
52 ተማም ሙክታር ወ 25
53 በየነ በዛ ወ 25 አይታወቅም
54 ወሰን አሰፋ ወ 25 አይታወቅም
55 አበበ አንተነህ ወ 30 አይታወቅም
56 ፈቃዱ ኃይሌ ወ 25 አይታወቅም
57 ኤሊያስ ጎልቴ ወ አይታወቅም
58 ብርሃኑ ዋርካ ወ
59 አሸብር መኩሪያ ወ አይታወቅም
60 ዳዊት ሰማ ወ አይታወቅም
61 መርሀጽድቅ ሲራክ ወ አይታወቅም
62 በለጠ ጋሻውጠና ወ አይታወቅም
63 ብኃይሉ ተስፋዬ ወ 20 አይታወቅም
64 21760 18 አይታወቅም
65 21523 25 አይታወቅም
66 11657 24 አይታወቅም
67 21520 21 አይታወቅም
68 21781 60 አይታወቅም
69 ጌታቸው አዘዘ ወ 45 አይታወቅም
70 21762 75 አይታወቅም
71 11662 45 አይታወቅም
72 21763 25 አይታወቅም
73 13087 30 አይታወቅም
74 21571 25 አይታወቅም
75 21761 21 አይታወቅም
76 21569 25 አይታወቅም
77 13088 30 አይታወቅም
78 እንዳልካቸው ገብርኤል ወ 27 አይታወቅም
79 ኃይለማርያም አምባዬ ወ 20 አይታወቅም
80 መብራቱ ዘውዱ ወ 27 አይታወቅም
81 ስንታየሁ በየነ ወ 14 አይታወቅም
82 ታምሩ ኃይለሚካኤል ወ አይታወቅም
83 አድማሱ አበበ ወ 45 አይታወቅም
84 እቴነሽ ይማም ወ 50 አይታወቅም
85 ወርቄ አበበ ወ 19 አይታወቅም
86 ፈቃዱ ደግፌ ወ 27 አይታወቅም
87 ሸምሱ ካሊድ ወ 25 አይታወቅም
88 አብዱዋሂደ አህመዲን ወ 30 አይታወቅም
89 ታከለ ደበሌ ወ 20 አይታወቅም
90 ታደሰ ፌይሳ ወ 38 አይታወቅም
91 ሶሎሞን ተስፋዬ ወ 25 አይታወቅም
92 ቅጣው ወርቁ ወ 25 አይታወቅም
93 ደስታ ነጋሽ ወ 30 አይታወቅም
94 ይለፍ ነጋ ወ 15 አይታወቅም
95 ዮሀንስ ኃይሌ ወ 20 አይታወቅም
96 በኃይሉ ብርሀኑ ወ 30 አይታወቅም
97 ሙሉ ሶሬሳ ወ 50 አይታወቅም
98 የቤት እመቤት አይታወቅም
99 ቴዎድሮስ ወ 23 አይታወቅም
100 ጫማ ሰሪ ወ ጫማ ሰሪ
101 በኃይሉ ብርሃኔ ወ 30 አይታወቅም
102 ሙሉ ሶሬሳ ወ 50 የቤት እመቤት
103 ቴዎድሮስ ኃይሌ ወ 23 ጫማ ሻጭ
104 ደጄኔ ይልማ ወ 18 መጋዝን ጠባቂ
105 ኡጋሁን ወልደገብርኤል ወ 18 ተማሪ
106 ደረጀ ማሞ ወ 27 አናጺ
107 ረጋሳ ፈይሳ ወ 55 ላውንድሪ ሰራተኛ
108 ቴዎድሮስ ገብረዎልድ ወ 28 የግል ንግድ
109 መኮንን ገ/እግዚአብሄር ወ 20 መካኒክ
110 ኤሊያስ ገ/ጊዮርጊስ ወ 23 ተማሪ
110 አብርሀም መኮንን ወ 21 የቀን ሰራተኛ
111 ጥሩወርቅ ገ/ጻድቅ ሴ 41 የቤት እመቤት
112 ሄኖክ መኮንን ወ 28 አይታወቅም
113 ጌቱ ምሀትተ ወ 24 አይታወቅም
114 ክብነሽ ታደሰ ሴ 52 አይታወቅም
115 መሳይ ስጦታው ወ 29 የግል ንግድ
116 ሙሉአለም ወይሳ ሴ 15 አይታወቅም
117 አያልሰው ማሞ ወ 23 አይታወቅም
118 ስንታየሁ መለሰ ወ 24 የቀን ሰራተኛ
119 ጸዳለ ቢራ ሴ 50 የቤት እመቤት
120 አባይነህ ሰራሴድ ወ 35 ልብስ ሰፊ
121 ፍቅረማርያም ተሊላ ወ 18 ሾፌር
122 አለማየሁ ገርባ ወ 26 አይታወቅም
124 ጆርጅ አበበ ወ 36 የግል ትራንስፖርት
125 ሀብታሙ ዘገየ ወ 16 ተማሪ
126 ምትኩ ገ/ስላሴ ወ 24 ተማሪ
127 ትዕዛዙ መኩሪያ ወ 24 የግል ንግድ
128 ፈቃዱ ዳልጌ ወ 36 ልብስ ሰፊ
129 ሸዋጋ ወ/ጊዮርጊስ ወ 38 የቀን ሰራተኛ
130 አለማየሁ ዘውዴ ወ 32 የቴክስታይል ሰራተኛ
131 ዘላለም ገ/ጻድቅ ወ 31 የታክሲ ሾፌር
132 መቆያ ታደሰ ሴ 19 ተማሪ
133 ሀይልየ ሁሴን ወ 19 ተማሪ
134 ፍስሀ ገ/ጻድቅ ሴ 23 የፖሊስ ተቀጣሪ
135 ወጋየሁ አርጋው ወ 26 ስራ ፈላጊ
136 መላኩ ከበደ ወ 19 አይታወቅም
137 አባይነህ ኦራ ወ 25 ልብስ ሰፊ
138 አበበች ሆለቱ ሴ 50 የቤት እመቤት
139 ደመቀ ጀንበሬ ወ 30 አርሶ አደር
140 ክንዴ ወረሱ ወ 22 ስራ ፈላጊ 141
141 እንዳለ ገ/መድህን ወ 23 የግል ንግድ
142 አለማየሁ ወልዴ ወ 24 መምህር
143 ብስራት ደምሴ ወ 24 መኪና አስመጭ
144 መስፍን ጊዮርጊስ ወ 23 የግል ንግድ
145 ወሎ ዳሪ ወ 18 የግል ንግድ
146 በሀይሉ ገ/መድህን ወ 20 የግል ንግድ
147 ሲራጂ ኑሩ ሰይድ ወ 18 ተማሪ
148 እዮብ ገ/መድህን ወ 25 ተማሪ
149 ዳንኤል ሙሉጌታ ወ 25 የቀን ሰራተኛ
150 ቴዎድሮስ ደገፋ ወ 25 የጫማ ፋብሪካ ሰራተኛ
151 ጋሻው ሙሉጌታ ወ 24 ተማሪ
152 ከበደ ኦርቄ ወ 22 ተማሪ
153 ለሊሳ ፋጤሳ ወ 21 ተማሪ
154 ጃገማ ባሻ ወ 20 ተማሪ
155 ደበላ ጉታ ወ 15 ተማሪ
156 መላኩ ፈይሳ ወ 16 ተማሪ
157 እልፍነሽ ተክሌ ሰ 45 አይታወቅም
158 ሀሰን ዱላ ወ 64 አይታወቅም
159 ሁሴን ሀሰን ዱላ ወ 25 አይታወቅም
160 ደጀኔ ደምሴ ወ 15 አይታወቅም
161 ዘመድኩን አግደው ወ 18 አይታወቅም
162 ጌታቸው ተረፈ ወ 16 አይታወቅም
163 ደለለኝ አለሙ ወ 20 አይታወቅም
164 ዩሱፍ ኡመር ወ 20 አይታወቅም
165 መኩሪያ ተበጀ ወ 22 አይታወቅም
166 ባድሜ ተሻማሁ ወ 20 አይታወቅም
167 አምባው ጌታሁን ወ 38 አይታወቅም
168 ተሾመ ኪዳኔ ወ 65 የጤና ባለሙያ
169 ዮሴፍ ረጋሳ ወ አይታወቅም
170 አብዩ ንጉሴ ወ አይታወቅም
171 ታደለ በሀጋ ወ አይታወቅም
172 ኤፍሬም ሻፊ ወ አይታወቅም
173 አበበ ሀማ ወ አይታወቅም
174 ገብሬ ሞላ ወ አይታወቅም
175 ሰይዴ ኑረዲን ወ አይታወቅም
176 እንየው ጸጋዬ ወ 32 እረዳት ትራንስፖርት
177 አብዱራህማን ፈረጅ ወ 32 የእንጨት ስራ ባለሙያ
178 አምባው ብጡል ወ 60 የቆዳ ፋብሪካ ሰራተኛ
179 አብዱልመናን ሁሴን ወ 28 የግል ንግድ
180 ጅግሳ ሰጠኝ ወ 18 ተማሪ
181 አሰፋ ነጋሳ ወ 33 አናጺ
182 ከተማ ኡንኮ ወ 23 ልብስ ሰፊ
183 ክብረት እልፍነህ ወ 48 የጥበቃ ሰራተኛ
184 እዮብ ዘመድኩን ወ 24 የግል ንግድ
185 ተስፋዬ መንገሻ ወ 15 የግል ንግድ
186 ካፒቴን ደበሳ ቶሎሳ ወ 58 የግል ንግድ
187 ትንሳኤ ዘገየ ወ 14 ልብስ ሰፊ
188 ኪዳና ሹክሩ ወ 25 የቀን ሰራተኛ
189 አንዷለም ሺበለው ወ 16 ተማሪ
190 አዲሱ ተስፋሁን ወ 19 የግል ንግድ
191 ካሳ በየነ ወ 28 ልብስ ሽያጭ
192 ይታገሱ ሲሳይ ወ 22 አይታወቅም

የጸጥታ ኃይሎች እርስ በእርስ ባደረጉት የተኩስ ልውውጥ በጥይት የተገደሉ ሰዎች፣

193 ነጋ ገብሬ ወ
194 ጀበና ደሳለኝ ወ
195 ሙሊታ ኢርኮ ወ
196 የሃንስ ሶሎሞን ወ
197 አሸናፊ ደሳለኝ ወ
198 ፈይሳ ገ/መንፈስ ወ
በመቶዎቹ የሚቆጠሩትን የግድያ ሰለባዎች፣ አካለ ጎደሎዎች፣ ቁስለኞች፣ በኃይል የተመቱትንና ሰውነታቸው በጥይት የተበሳሱትን ሁሉ አስታውሳለሁ፡፡

እ.ኤ.አ ኖቬምበር 2/2005 ከቃሊቲ እስር ቤት ለማምለጥ ሲሞክሩ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ በጥይት ተደብድበው ያለቁ ሰዎች ስም ዝርዝር፣
ተ.ቁ ስም ጾታ የተከሰሱበት ጥፋት፣
1 ጠይብ ሸምሱ መሀመድ ወ ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
2 ሳሊ ከበደ ወ ምንም ዓይነት ክስ አልተጠቀሰም
3 ሰፊው እንድሪስ ታፈሰ ወ በአስገድዶ መድፈር
4 ዘገዬ ተንኮሉ በላይ ወ በዝርፊያ ወንጀል
5 ቢያድግልኝ ታመነ ወ የተወነጀሉበት ያልታወቀ
6 ገብሬ መስፍን ዳኘ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
7 በቀለ አብርሃም ታዬ ወ በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
8 ጉታ ሞላ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
9 ኩርፋ መልካ ተሊላ ወ በማስፈራራት ወንጀል
10 በጋሻው ተረፈ ጉደታ ወ የህዝብን ሰላም በማደፍረስ ወንጀል
12 አብደልወሃብ አህመዲን ወ በዘርፊያ ወንጀል
13 ተስፋዬ አብይ ሙሉጌታ ወ ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
14 አዳነ ቢረዳ ወ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል
15 ይርዳው ከርሴማ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
16 ባልቻ አለሙ ረጋሳ ወ በዝርፊያ ወንጀል
17 አቡሽ በለው ወዳጆ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
18 ዋለልኝ ታምሬ በላይ ወ በአስገድዶ መድፈር
19 ቸርነት ኃይሌ ቶላ ወ በዝርፊያ ወንጀል
20 ተማም ሸምሱ ጎሌ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
21 ገብየሁ በቀለ አለነ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
22 ዳንኤል ታዬ ለኩ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
23 መሀመድ ቱጂ ቀኔ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
24 አብዱ ነጂብ ኑር ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
25 የማታው ሰርቤሎ ወ በአስገድዶ መድፈር
26 ፍቅሩ ናትናኤል ሰውነህ ወ በማስፈራራት ወንጀል
27 ሙኒር ከሊል አደም ወ በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
28 ኃይማኖት በድሉ ተሸመ ወ ጽንፈኝትን በማራመድ
29 ተስፋዬ ክብሮም ተኬ ወ በዥርፊያ ወንጀል
30 ወርቅነህ ተፈራ ሁንዴ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
31 ሲሳይ ምትኩ ሁነኛ ወ በማጭበርበር ወንጀል
32 ሙሉነህ አይናለም ማሞ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
33 ታደሰ ሩፌ የኔነህ ወ በማስፈራራት ወንጀል
34 አንተነህ በየቻ ቁበታ ወ ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
35 ዘሪሁን መርሳ ወ በንብረት ላይ ጉዳት በማድረስ ወንወጀል
36 ወጋየሁ ዘሪሁን አስፋው ወ በዝርፊያ ወንጀል
37 በከልካይ ታምሩ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
38 የራስወርቅ አንተነህ ወ በማጭበርበር ወንጀል
39 ባዝዘው ብርሀኑ ወ ግብረሰዶም በመፈጸም ድርጊት
40 ሶሎሞን እዮብ ጉታ ወ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
41 አሳዩ ምትኩ አራጌ ወ በማስፈራራት ወንወጀል
42 ጋሜ ኃይሉ ዘገዬ ወ በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
43 ማሩ እናውጋው ድንበሬ ወ በአስገድዶ መድፈር ወንጀል
44 እጂጉ ምናለ ወ በግድያ ሙከራ ወንጀል
45 ኃይሉ ቦስኔ ሀቢብ ወ የተቀደሰን ቦታ በማራከስ
46 ጥላሁን መሰረት ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
47 ንጉሴ በላይነህ ወ በዝርፊያ ወንጀል
48 አሸናፊ አበባው ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
49 ፈለቀ ድንቄ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
50 ጀንበሬ ድንቅነህ ቢለው ወ በህዝብ ላይ ሁከት በመፍጠር
51 ቶሎሳ ወርቁ ደበበ ወ የዝርፊያ ወንጀል
52 መካሻ በላይነህ ታምሩ ወ የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
53 ይፍሩ አደራው ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
54 ፋንታሁን ዳኘ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
55 ጥበቤ ዋቀኔ ቱፋ ወ ለትጥቅ አመጽ በማነሳሳት
56 ሶሎሞን ገብረአምላክ ወ የህዝብን ሰላም በማደፍረስ
57 ባንጃው ቹቹ ካሳሁን ወ በዝርፊያ ወንጀል
58 ደመቀ አበጀ ወ በግድያ ሙከራ ወንጀል
59 እንዳለ እውነቴ መንግስቴ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ
60 አለማየሁ ጋርባ ወ እ.ኤ.አ በ2004 ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች አመጽ ጋር በተያያዘ መልኩ በቁጥጥር የዋሉ
61 ሞርቆታ ኢዶሳ ወ የተወነጀሉበት ምክንያት ያልታወቀ

ለምዘገባ፣ በዚህ እልቂት ላይ ተዋንያን የነበሩ 237 የተረጋገጠ የፖሊስ እና የደህንነት አባላት ዝርዝርን የያዘ ሰነድ ተቀምጧል፡፡

Yenesew Gebreየኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ!

እ.ኤ.አ በ11/11/11 የኔሰው ገብሬ የተባለ የ29 ዓመት መምህር እና የሰብአዊ መብት ተሟጋች በደቡብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ዞን በተርጫ ከተማ ከህዝብ መሰብሰቢያ ዳራሽ ፊት ለፊት እሳት በመለኮስ እራሱን በእሳት አያይዟል፡፡ ለሶስት ቀናት ቆስሎ ከቆየ በኋላ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ እራሱን በእሳት ከማያያዙ በፊት የኔሰው ከህዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውጭ ለተሰበሰበ ህዝብ እንዲህ የሚል ንግግር አሰምቶ ነበር፣ “በእኩልነት ላይ ባልተመሰረተ አስተዳደር እና ፍትህ በሌለበት እንዲሁም የሰብአዊ መብት በማይከበርበት አገር ውስጥ እራሴን ለመስዋዕትነት አቀርባለሁ፣ ይህንንም በማድረጌ ወጣቱ ትውልድ ነጻ ይወጣል፡፡” የአትዮጵያ ጀግናዉ የእኔሰው ገብሬን አስታውሳለሁ…

“ገዳዮችን አስታውሳለሁ፣ የግድያ ሰለባዎችንም አስታውሳለሁ፣ ለትግሌ የሚያግዙ አንድ ሺ እና ከዚያ በላይ ያሉ አሳማኝ ምክንያቶች እና ተስፋ ቢኖረኝም፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ተስፋየ ይሟጠጣል፣ ያንን ድርጊት ባስታውስኩ ቁጥር ደግሞ ተስፋቢስነቴን የማስወገድ ኃላፊነት እንዳለብኝ እገነዘበላሁ፣ ተስፋ ከተስፋቢስነት በላይ ነው፡፡“ ይላል ኤሊ ዊሴል!

**ለጥቃቱ ሰለባዎች ተጨማሪ መረጃ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ያሬድ ኃ/ማርያም እ.ኤ.አ ሜይ 15/2006 “በሰው ልጆች ላይ የተፈጸመ ወንጀል በኢትዮጵያ፣ የጁንና ኖቬምበር 2005 የአዲስ አበባው ዕልቂት“ በሚል ርዕስ ለአውሮፓ ህብረት ፓርላሜንት ለልማትና ውጭ ጉዳዮች እና ለሰብአዊ መብቶች ንዑስ ኮሚቴ አስቸኳይ ጥምር ጉባኤ የቃረቡትን ምስክርነት ይመለከቷል፡፡

***የመርማሪ ኮሚሽኑ ሪፖርት ሙሉ በሙሉ የጥቃቱ ሰለባዎችን ነጻ ሲያወጣ አጠቃላይ ኃላፊነቱን ግን በፖሊስና ታጣቂ ኃይሎች ላይ ደፍድፎታል፡፡ መርማሪ ኮሚሽኑ አስተያየቱን በመቀጠል እንደሚከተለው አጠቃሎታል፣ “በተቃዋሚዎቹ የተጎዳ ንብረት የለም፣ በመንግስት በሞኖፖል በተያዘው መገናኛ ብዙሀን እንደተለፈፈው ጥቂት ተቃዋሚዎች የእጅ ቦንቦችንና ጠመንጃዎችን ታጥቀዋል እንደሚለው ሳይሆን በተቃራኒው የእጅ ቦንብ እና ጠብመንጃ የታጠቀ አንድም የተቀዋሚ አባል የለም፣ በመንግስት ታጣቂ ኃይሎች የተከፈተው ተኩስ ሰላማዊ ሰልፈኞችን ለመበተን ሳይሆን በተቃራኒው የሰልፈኞችን ጭንቅላትና ደረት ለመበርቀስ ዒላማ ያደረገ ነበር፡፡” የመርማሪ ኮሚሽኑ የ193 የእልቂቱ ሰለባዎችን ስም ዝርዝር የያዘ ሰነድ የሚያካትተው እ.ኤ.አ ከጁን 6 – 8 እና ከኖቬምበር 1- 4/2005 በዚህ ጊዜ ብቻ ያለውን ድርጊት እንዲያጣራ ለአጣሪ ኮሚሽኑ የተሰጠው ስልጣን ነበር፡፡ አጣሪ ኮሚሽኑ ግን በፓርላማው ከተሰጠው የጊዜ ገደብ ውጭ ከህግ ውጭ በመንግስት የፖሊስና የደህንነት ኃይሎች የተፈጸሙ ግድያዎችን ስም ዝዝዝር ያገኘ ቢሆንም እነዚህ ግድያዎች ኮሚሽኑ እንዲያጣራ ተለይቶ ከተሰጠው ጊዜ ውጭ በመሆናቸ ለህዝብ ይፋ ሳያደርገው ቀርቷል፡፡

==

FORUM | AMHARIC