በኢንቨስትመንት ስም የመሬት ነጠቃ

በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ የካናዳ የፓርላማ አባላትና እውቅ ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት በኦታዋ ተደረገ

Ottawa, Canada

February 25, 2014

Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ  በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም  የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል።

Canada parliamentarians and scholars discuss controversial land grab in Afrtica

Canada parliamentarians and scholars discuss controversial land grab in Afrtica

በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ካናዳውያን እንዲሁም ከበርካታ አፍሪካ ሀገራት የመጡና  በአህጉሪቱ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ይመለከተናል የሚሉ ትውልደ አፍሪካ ምሁራንን ጭምር ያካተተ ነው። በዚህ ድርጅት ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም የሚሳተፉበት ሲሆን ከመስራች አባላት አንዱ ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ናቸው።

ሉውን ሪፖርት ለማንበብ ታች ይጫኑ

Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa