የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ

«መበለቶችም ቅሚያቸው እንዲሆኑ፥ ድሀ አደጎችንም ብዝበዛቸው እንዲያደርጉ፥ የድሀውን ፍርድ ያጣምሙ ዘንድ፥ የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ ያጐድሉ ዘንድ የግፍን ትእዛዛት ለሚያዝዙ፥ ክፉንምጽሕፈት ለሚጽፉ ወዮላቸው!»
— ትንቢተ ኢሳያስ 10‹ 1-2

ሰዋስው ስለሺ ዮሐነሰን

ግንቦት 12, 2015

በተለይ እግዚአብሔርን እናውቃለን ብለን፣ ለወገን፣ ለአገር፣ ለሰው ልጅ መከራ እና መብት መሙዋገትን ፖለቲካ ነውና አትንኩት እያልን፣ራሳችንን በአያገባንም ጎራ ውስጥ ከትተን፣ መውጣት ላቃተን ሁሉ እግዚአብሔር መንፈሳችንን ያባንነው ዘንድ ጸሎቴ ነው፡፡ የሕዝባችን መከራ ከምንግዜውም በላይ እጅግ በከፋበት ወቅት በመንፈሳዊ ካባ ራሳችንን ከልለን በዝምታ መቀመጥ እግዚአብሔር ይጸየፈዋልና፡፡
 

ጥያቄው ፖለቲከኛ ሁኑ ማለት አይደለም፣ እኔ እስከሚገባኝ ፖለቲካ ማለት በሐቅ እና በእውነት ላይ የተመሰረተ ሕብረተሰብን የማስተዳደር ጥበብ ይመስለኛል፣ ምናልባትም ለአብዛኞቻችን ይህ ቃል የሚዘገንንን፣ ፖለቲካ ማለት ምን እንደሆነ እንኩዋን ጠንቅቀው በማያውቁ ሰዎች ትውልድ አገራችን መመራትዋና፣ በእነርሱም መሐል ማሰተዋል ያላቸው፣ እውቅትን የተሞሉ፣ ምሁራን እና የፖለቲካው እውቀት ያላቸው አማካሪዎቻቸው፣ በየጊዜው የሚሰጡዋቸውን ምክር ያለመስማት እና ከእኛ በላይ አዋቂ ማንም የለም ባይነት፣ አምባገነንነት፣ ጉልበተኛነት፣ ስልጣንን ያለአግባብ መጠቀም በሕዝባችን ሥነልቦና ላይ ያስከተለው ጠባሳ እና የፖለቲካው መዘዝ ያሳረፈበት ሰቆቃ ይመስለኛል ለቃሉ ከፍተኛ ፍርሐት ያሳደረብን፡፡

___________________________________________________________________________________
ሙሉውን ለማንበብ ከዚህ በታች ይጫኑ

የችግረኛውንም ሕዝቤን ፍርድ

 
 
 
 
 
 

_________________________________________________________________________________________