Dagmawi Arbegnoch Movement (ዳ አ ን) Press Release

et-flag-arbegnoch2

“የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዲሞክራሲ ዘብ” የስም ለዉጥ ስለማድረጉ የተሰጠ መግለጫ..

አዲሱ መጠሪያ ስማችን፣ “ዳግማዊ አርበኞች ንቅናቄ” (ዳ.አ.ን) እንደሚባል እናስታዉቃለን

መስከረም 8 2008/ ኦክቶበር 19፣ 2016

ዘረኛዉ የወያኔ ቡድን ከጥንስሡ ጀምሮ የብዙ ብሄረሰቦች መኖሪያ የሆነችዉ ሀገራችን ኢትዮጵያን ለመበታተን መጀመሪያ አማራን ማጥፋት በሚል ሰነድ ላይ በሰፈረ አላማ ይዞ ትግል መጀመሩ ይታወቃል። በሰነድ ማስፈር ብቻም ሳይሆን በመገናኛ አዉታሮቹም ጭምር አስነግሯል:: የጥፋት ስራዉንም በተግባር ላይ ማዋል የጀመረዉም የወልቃይት አማራዎችን በመግደልና በማፈናቀል ነበር።

የደርግ ስርአት ገጥሞት በነበረዉ የራሱ የዉስጥ ችግር ምክንያት በተፈጠረዉ ክፍተት ሳቢያ ያንን በመጠቀም እራሳቸዉን በመንግስትነት የሚጠሩት የዛሬዎቹ ከሃዲ ወያኔ ፋሺስቶች አብዛኛዉንም የሰሜኑን ክፍል ድብቅ ሴራዉን ባልተረዱ በአማራ ታጣቂ አርሶ አደሮች እርዳታ በቁጥጥራቸዉ ስር አዋሉት፤ በመቀጠልም ሙሉ ሀገራችንን በወረራ ተቆጣጠሯት፣

የወያኔ መራሹ ቡድን ስልጣን ላይ ከወጣ ጀምሮ በሃገራችን ብሄር ብሄረሰቦች ላይ ከመጠን ያለፈ ወንጀል ፈጽሟል በመፈጸም ላይም ይገኛል፣ በሲዳማ፣ በአማራ፤ በኦሮሞ፤ በጋምቤላ በኦጋዴን እንዲሁም በሌሎች ኢትዮጵያዉያን ላይ ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት ድርጊት ፈጽሟል።

በተለይ በአማራዉ ህዝብ ላይ የተደረገዉና እየተደረገ ያለዉ ጥፋት ከሌሎቹ ሁሉ ለየት የሚያደርገዉ ሌሎች ብሄረሰቦች ተጨቆን ፍትህ አጣን መብታችን ተነካ ብለዉ ሲጠይቁ ይገደላሉ ይታሰራሉ፤ በአማራዉ ህዝብ ላይ ግን ዝም ብሎ አርፎ ቢቀመጥም በተለያዩ ዘዴዎች የዘር ማጥፋት ተግባር እየተፈጸመበት ነዉ፣ መሬቱ እየተቀማ ከወያኔ መስፋፊያነት አልፎ ለባእዳን ወዳጅ ማፍሪያ ችሮታ ይሰጣል፣ በኢኮኖሚ በትምህርት እና በማህበራዊ ሁኔታ እንዳይጠነክር ከሌሎች በተለየ ተጽኖ ይደረግበታል፤ የአማራዉ ህዝብ ከሌላዉ ብሄረሰቦች ጋር በመከባበር በፍቅርና በመዋለድ በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች እንደጨዉ ተበትኖ ይኖራል፣ ይህንኑ ህዝብ ወያኔ እራሱ በቀጥታ ጥቃት በመፈጸም እንዲገደልና በወረራ የመጣ ነዉ በማለት ጥሮ ግሮ ያፈራዉን ሀብት ንብረቱን ነጥቆ ከመኖሪያዉ ቀየዉ እንዲፈናቀል ተደርጓል። ለዚህም ከጉራፈርዳና ቤንሻንጉል የተባረሩት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸዉ፤ የአማራን ህዝብ እወክላለሁ የሚለዉ ብሄር ዓማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) የዚህ ሁሉ ወንጀል ዋና ተባባሪ ነዉ። በተጨማሪም በአማራ ህዝብ ላይ ካለዉ ስር የሰደደ ጥላቻ እና ደባ ገደብ በማጣቱ የተነሳ እየተዋለደ አገር ተረካቢ ትዉልድ እንዳይተካ የአማራን ልጃገረዶች የማምከኛ መርፌ እየወጋ እንዳይወልዱ በማድረግ ከፍተኛ ወንጀል ፈጽሟል።

ስለዚህ የአማራዉ ጠላቶች ተወግደዉ ችግሮቹ የሚፈቱት እራሱን አድኖና አስከብሮ በኢትዮጵያዊነቱ ሲኖር እንደሆነ በማመን፣ በተጠና ስልት ከአስር አመታት በፊት በአገር ዉስጥ በአማራነት በመደራጀት “የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዴሞክራሲ ዘብ” የሚል ድርጅት መስርተን ምንም እንኳ ሳይሳኩ ቢቀሩም አመርቂ የሆነ ያደረጃጀት ስልትና ሌሎችንም ጥሩ ዉጤት ማስገኘቱ ይታወቃል። አሁንም ወያኔ ሰራሽ የሆኑ የአማራ ችግሮች ከግዜ ግዜ እየበዙ በመምጣታቸዉ በእኩልነት የምንኖርባት ኢትዮጵያ ጥያቄ ዉስጥ ሳትገባ ይህን ወያኔን ለማስወገድ አሁንም በአማራነት መደራጀት መቀጠል እንዳለብን ጽኑ እምነት ስላለን የድሮዉ ስማችን “የኢትዮጵያ ብሄራዊ ዴሞክራሲያዊ ዘብ” የነበረዉ ቀርቶ “ዳግማዊ አርበኞች ንቅናቄ” (ዳ.አ.ን) በሚል መቀየሩን እናስታዉቃለን።

ይህን አዲሱን ስማችን የመረጥንበት ምክንያትም፣ወቅቱ የሚጠይቀዉ የትግል ስልታችን በትክክል ስለሚገልጽ ነዉ፣ እንዲሚታወቀዉ በጣልያን ወረራ ጌዜ አባቶቻችንና እናቶቻችን ከባድ እና ወጤታማ የሆነ ያርበኝነት ተጋድሎ አድርገዉ  ጣልያንን ድል አድርገው አገራቸዉን ነጻ አዉጥታዋል።

ያ የአባቶቻችን ያርበኝነት ተጋድሎ የዲሞክራሲ የስልጣንና የፖለቲካ ጥያቄ ሳይሆን አገርን፣ ሀይማኖትን፣ ማንነትን ለማዳን የተደረገ የአርበኝነት ትግል ነበር ። ጣልያን ኢትዮጵያን ሊወር ሲል ከአማራ ጋር አትስሩ፣ አትኑሩ፣ ለብቻችሁ ሁኑ፣ተበታተኑ እያለ ለመከፋፈል ሞክሮ ነበር። ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ ግን ያንን ትቶ ፤ እኛን ሳይከፋፍለን ባንድላይ ነበር አገሪቱን ያስተዳደራት። ጣልያን በሐይል ተባሮ ሲወጣም ኢትዮጵያን አፈራርሸ ልሂድ አላለም አልሞከረም።  አሳፋሪዉ ወያኔ ግን ከመነሻዉ ትግራይን እገነጥላለሁ ፤ አማራን አጠፋለሁ የሚል አለም አቀፍ ወንጀል  እየተናገረ መጣ ፣ ኢትዮጵያን እንደተቆጣጠረ አማራን የማጥፋት ተግባሩን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲፈጽም ኖሯል፣ አሁንም በማናለብኝነት እየፈጸመ ነው። ከኢትዮጵያ ህዝብ ጠንከር ያለ ተቃዉሞ ሲነሳ ኢትዮጵያን እበታትናለሁ እያለ ባደባባይ ግልጽ የወንጀል ዛቻ ይዝታል ህብረብሄር ድርጅቶች ሲጠነክሩበት ሰበብ አድርጎ አማራን ይጨፈጭፋል። እኛ ካልገዛን ኢትዮጵያ እንደ እንደ ሀገር መቀጠል አትችልም እያሉ ደጋግመዉ ነግረዉናል፡ ስለዚህ አባቶቻችን በፍትሕዊ ጀግንነት ፣ እርስ በርስ በመተማመን የመጀመሪያዉን ያርበኝነት ተጋድሎ ፈጽመው አገራቸዉንና ሀይማኖታቸዉን አድነዋል። ዛሬ ደግሞ አገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ ከድሮዉ የከፋ ስለሆነ ሁለተኛዉን ወይም ዳግማዊ ያርበኝነት ትግል ማካሄድ ያስፈልገናል። ለዚህም ነዉ የድርጅታችን ስም “ዳግማዊ አርበኞች ንቅናቄ” ወደሚል  መጠሪያ የተቀየረዉ።

            የተከበርከዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ሆይ! 

እራሱን እንደመንግስት የሚጠራዉ ይህ እኩይ ሀይል የረጅም ግዜ ግቡ አማራ የሚባል ህዝብን ማጥፋት እንደሆነና እንዲሁም ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በከፍተኛ ግፍ እየጨፈጭፈ መሆኑን ድርጅታችን ዳግማዊ አርበኞች ንቅናቄ (ዳ አ ን) ተገንዝበን ይህ ከሀዲ ቡድን መወገድ እንዳለበት አምነን ትግል ከጀመን እነሆ ከአስር አመት በላይ ሆኖናል፣

ይህ ዘረኛ ቡድን የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት በመዝረፍ የራሱን ጎሳና ቤተሰብ ከመጥቀምና ከማበልጸግ እንዲሁም ለነሱ ያጎበደዱ ባንዳ ግለሰቦችን ባንድ ጀንበር ባለሀብት ከማድረግ ዉጭ ለህብረተሰቡ ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል አያደርጉም፤ በኦሮሚያና በሌሎች ያገራችን ክፍሎች ያለዉን የተፈጥሮ ሀብት በመዝረፍ የራሱን ጎሳና ቤተሰብ ከመጥቀምና ከማበልጸግ የላቀ ይህ ነዉ የሚባል የመሰረተ ልማት አዉታር እንኳን ስላልተዘረጋ ዛሬም በኦሮሚያና በሁሉም ያገሪቱ ክፍሎች እናቶች በወሊድ ይሞታሉ፣ ይህም የብልጣብልጥነት የዘር ማጥፋት ተግባር እንደሆነ መረዳት አያዳግትም።

ድርጅታችን ዳግማዊ አርበኞች ንቅናቄ (ዳ አ ን) ላለፉት አስር አመታት ያደረገዉን የትግል ጉዞ በመገምገምና ቀጣዩን ትግል በስኬት ለማካሄድ መጠነኛ የአደረጃጀትና የትግል ስልት ለዉጥ አድርጓል፤ ለዚህም በተለያዩ የትግል መድረኮች ልምድ ያላቸዉ የቁርጥ ቀን ዜጎችን አሰባስቦ በሁለገብ የትግል ስልት ይህን ከሃዲ ቡድን ለማስወገድ ትግሉን እንደቀጠለ ነዉ፤ በተጨማሪም ተመሳሳይ አላማ ካላቸዉ ሀይሎች ጋር እንቅስቃሴ መጀመራችንን እያበሰርን በዚህ ጉዳይ ላይ ስምምነት ካላቸዉ ከማንኛዉም ሀይሎች ጋር በመተባበር ሊያስማሙን በሚችሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ሁልግዜ በራችን ክፍት መሆኑን እናስታዉቃለን።

ድል ለሰፊዉ ህዝብ!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር.

Email: dagmawiarbegnoch@gmail.com

Leave a Reply

Your email address will not be published.