Ethiopian Proverbs


Ethiopian Proverbs ( ምሳሌዎች)

ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
ከወፈሩ ሰው አይፈሩ
ሲስሟት ቀርቶ ሲስቧት
ቀድሞ ማን ቢስምሽ ታሞጠሙጫለሽ
እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ወፍራም ይቀድማል
ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል
በቦሃ ላይ ቆረቆር
የቸገረው እርጉዝ ያገባል፣ የባሰበት እመጫት
የአህያ ስጋ አልጋ ሲሉት መሬት
ልጅ ያቦካው ለራት አይበቃም
የደላው ሙቅ ያኝካል
የፈሪ ዱላው ረጅም ነው
የፈሪ በትር ሆድ ይቀትር
ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ ንጣት ይገለው ነበር
ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
ተንጋለው ቢተፉ ተመልሶ ካፉ
ሰዶ ማሳድድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ
ዞሮ ዞሮ ወደቤት ኖሮ ኖሮ ወደ መሬት
ራሴን ሲበላኝ እግሬን ቢያኩኝ አይገባኝም
የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም
ከዕባብ እንቁላል እርግብ አይፈለፈልም
አንቺው ታመጪው አንቺው ታሮጪው
ጨው ለራስህ ብለህ ጣፍጥ
በአንድ ራስ ሁለት ምላስ
ብላ ባለኝ እንዳባቴ በቆመጠኝ
የድሀ ቅንጡ እንጀራ ሲሰጡት ይላል ድልህ አምጡ
ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል
ወረቀትና ሞኝ የያዘውን አይለቅም
አይመጣምን ትተሽ ይመጣልን ባሰብሽ
ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
ዘመደ ብዙ ጠላው ቀጭን ነው
ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል
ከድሀ ከመበደር ከባለጸጋ መስረቅ ይቀላል
ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አያስታውቅም
የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
አስቀድሞ ነበር መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ይሰራል ድስት ድጦ ማልቀስ
ጉልቻ ቢቀያየር ወጥ አያጣፍጥም
ጭብጥ ቆሎ ይዘህ ወደ አሻሮ ተጠጋ
ውሀ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው
የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ
ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
ልጅን ሲወዱ እስከነ ንፍጡ ነው
መልካም ስም ከመልካም ሽቶ ይበልጣል
ሰውና እንጨት ተሰባሪ ነው
ጌታዋን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች
ሰው ጥራ ቢሉት ራሱ መጣ
ምንም ብቀጥን ጠጅ ነኝ
በቅሎን አባትሽ ማነው ቢሏት እናቴ ፈረስ ነች አለች
ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ
የአዝማሪ ሚስት አልቅሰው ካልነገሯት አይገባትም
ምነው እናቴ እንቁላል ስሰርቅ በቀጣችኝ
ዶሮ ብታልም ጥሬዋን
ዶሮ ጭራ ጭራ መታረጃዋን ታወጣለች
አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል
የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር
ወሬ ቢበዛ በአህያ አይጫንም
ገንዘብ ካለ በሰማይ መንገድ አለ
የማያውቁት አገር አይናፍቅም
ዳሩ ሲወረር መሀሉ ዳር ይሆናል
መካሪ የሌለው ንጉስ አንድ አመት አይነግስ
ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ
የአገሩን መሬት በአገሩ በሬ
ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ
ለጌታም ጌታ አለው
ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ
ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ
ሰውን ማመን ቀብሮ አለች ቀበሮ
ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም
ባለቤቱ ያቀለለውን አሞሌ ባለእዳ አይቀበለውም
ከሞመት መሰንበት
የወደቀ ግንድ ምሳር ይበዛበታል
አያ ጅቦ ሳታመካኝ ብላኝ
እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ


Leave a Reply

Your email address will not be published.