Ethiopia: Al Amoudi’s Sheraton Hotel faces bankruptcy

The Reporter in its latest edition reports that Sheraton Addis, which is owned by Ethiopia’s billionaire businessman [and drunkard womanizer] Ato Mohammed Al Amoudi may be put on the auction block to pay for 170 million birr debt that the parent company, Midrock, owes to the Commercial Bank of Ethiopia (CBE).

The Reporter’s editor, Amare Aregawi, who almost died after he was savagely attacked last month by three thugs who were suspected of being hired by Al Amoudi, is going after the billionaire with a vengeance. Both Al Amoudi and Amare are registered and high-profile members of the ruling Tigrean People Liberation Front (Woyanne). So this is nothing more than a feud among a family of thieves.

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ብድሩን ባለመክፈሉ ዋስትናው ሸራተን በሐራጅ አደጋ ላይ ነው

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ወስዶ ባለመመለሱ በዋስትና በተያዘው ንብረት ላይ የሐራጅ ጨረታ ለማውጣት ባንኩ መቸገሩን፣ ችግሩን ለመፍታት የመንግሥት ጣልቃ ገብነት እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ፡፡

ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የባንኩ አንድ የሥራ ኀላፊ ለሪፖርተር ጋዜጣ እንዳረጋገጡት ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ብድሩን ሲወስድ በዋስትና ያስያዘው ሸራተን ሆቴልን ነው፡፡ ሚድሮክ ከባንኩ ወስዶ ያልመለሰው ብድር እስከ ሰኔ 30 ቀን 2000 ዓ.ም ድረስ ከ170 ሚሊዮን ብር በላይ መሆኑን ያረጋገጠው ምንጫችን ስለብድሩ አከፋፈል ጉዳይ በተደጋጋሚ ባንኩ ለሚድሮክ ኮንስትራክሽን ደብዳቤ ቢፅፍም አንድም ጊዜ ምላሽ ማግኘት አልቻለም፡፡ለሌሎች ባለሀብቶች በማይደረግ መልኩ ሚድሮክ ኮንስትራክሽን ብድሩን እንዲከፍል የማስታመም ያህል ባንኩ በተደጋጋሚ ደብዳቤ ቢፅፍም ብድሩ የማይመለስበት ምክንያት እንኳን ተጠቅሶ መልስ ማግኘት አለመቻሉ ትልቁ ችግር መሆኑን ምንጫችን ገልፀዋል፡፡

አንድ ተበዳሪ ብድሩን መመለስ ካልቻለ በሕጉ መሠረት የ30 ቀናት ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ማስከፈል ካልሆነም በዋስትና ያስያዘውን ንብረት በሐራጅ ለጨረታ እንደሚቀርብ ኀላፊው ጠቁመው በሚድሮክ ኮንስትራክሽን ጉዳይ ባንኩ በዋስትና የያዘውን ሸራተን ሆቴል ላይ የሐራጅ ጨረታ አውጥቶ መሸጥ የነበረበት ቢሆንም ይህንን ለመወሰን ድፍረት ማጣቱን ጠቁመዋል፡፡ በመሆኑም መንግሥት በጉዳዩ ጣልቃ ገብቶ አንድ ውሣኔ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሚድሮክ ኮንስትራክሽን 107 ሚሊዮን ብር የሚደርስ የኪራይና የብረት ዋጋ ዕዳ አለመክፈሉን እንዲሁም በአዲስ አበባ ከመገናኛ እስከ ሐያት የወሰደውን የ190 ሚሊዮን ብር የመንገድ ሥራ ፕሮጀክት በወቅቱ ማጠናቀቅ ባመቻሉ ፕሮጀክቱን መነጠቁን በተለያየ ጊዜ መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ሸራተን አዲስ ሆቴል ከሚድሮክ ኮንስትራክሽን በእጥፍ የሚበልጥ ገንዘብ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብድር መውሰዱም የሚታወስ ነው፡፡