Ethiopia: UDJ prevented from printing flyer

Ethiopia Zare reports that the Unity for Democracy and Justice Party (UDJ) has been prevented from printing fliers that announce a public meeting scheduled to be held in Addis Ababa on December 6.

UDJ is a party that is daydreaming about being able to operate as a genuine opposition party in Ethiopia under the rule of the fascist regime of Tigrean People’s Liberation Front (Woyanne).

While UDJ is prevented to print a flier in Ethiopia that announces a simple meeting, its chairperson, Birtukan Mideksa, is currently visiting European countries to talk about (misinform) how it is possible to conduct peaceful political activity in the country. Birtukan’s party also condemns those Ethiopians who try to defend themselves by picking up guns as ‘primitives’ and ‘chauvinists’.

More in Amharic by Ethiopia Zare

(ዓርብ ኅዳር 19 ቀን 2001 ዓ.ም. November 28, 2008)፦ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በራሪ ወረቀቶችን ለማሣተም ገንዘብ ከፍሎ ውጤቱን ሲጠባበቅ ማተሚያ ቤቱ ጽሑፉን ማተም ስለማይችል፤ ገንዘቡን እንዲወስድ መጠየቁን አስታወቀ።

የፓርቲው ም/ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ኃይሉ አርኣያ፤ እንደገለጹት በራሪ ወረቀቱን ለማተም ከፈቃጅ አካል ማኅተም አስደርገው እንዲመጡ መጠየቃቸውንና “ቅድመ ምርመራ (ሳንሱር) በሕግ በተከለከለበት ሀገር በሕጋዊ መንገድ ፍቃድ አውጥተን የምንቀሳቀስ ፓርቲ ማተሚያ ቤቱ ከማናውቀው አካል ማኅተም አስደርገን እንድንመጣ ጠይቆናል” ብለዋል።

ፓርቲው ቅዳሜ ኅዳር 27 ቀን 2001 ዓ.ም. ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ “ሠላማዊ ትግል” የሚል በራሪ ወረቀት ለማሣተም “ርኾቦት አሣታሚዎች ኃ/የተ/የግል ማኅበር” ለተባለ ማተሚያ ቤት ረቡዕ ኅዳር 17 ቀን 2001 ዓ.ም. የሚያስፈልገውን የሕትመት ዋጋ ከፍለው፣ የሚታተመውን ጽሑፍ አስረክበው ከሄዱ በኋላ፣ በዚያው ዕለት ማምሻውን ተደውሎ ጽሑፉን ማተም ስለማይችሉ ገንዘባቸውን እንዲወስዱ እንደተነገራቸው አስረድተዋል።

ማተሚያ ቤቱ ለማተም ፍቃደኛ ያልሆነበትን ምክነንያት ሲጠይቁ፤ ጹሑፉ ላይ ከፈቃጁ አካል ማኅተም ማስደረግ እንዳለባቸው ከመግለጽ ውጭ ፈቃጁ አካል ማን እንደሆነ፣ ማተሚያ ቤቱ በቃል ወይም በጹሑፍ የደረሰው ነገር እንዳለ ጠይቀው ምላሽ አለማግኘታቸውን አስረድተዋል።