Aba GebreMedhin denounces Woyanne!!

ADDIS ABABA, ETHIOPIA – The fake patriarch of Ethiopia’s Orthodox Tewahdo Church, Ato GebreMedhin (formerly Aba Paulos), for the first time since he was appointed by Meles Zenawi as the puppet head of the Church, spoke out against the Woyanne dictatorship through his synod.

The legitimate patriarch of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church, Abune Merkorios, is currently in exile.

Aba GebreMedhin’s synod on Saturday denounced Woyanne minister of Federal Affairs, Ato Abay Tsehay, who is also a member of the Woyanne politburo, for falsely accusing the Ethiopian Orthodox Church of promoting religious extremism.

More details by Awramba Times reporter (in Amharic):

‹የአገሪቱን ህልውና የሚፈታተን ስጋት ተደቅኗል› – ሲኖዶስ
መንግስትና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተወዛገቡ


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በምንም አይነት የጥፋት መንገድ ላይ ባልተገኘችበት ሁኔታ ቤተክርስትያኒቷንና ተከታዮቿን የሚጎዳ መግለጫ በመንግስት መሰጠቱ እንዳሳዘናት ገለጸች፡፡

ባለፈው ረቡዕ በአባይ ጸሀይ የሚመራው የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ጽ/ቤት ‹አንዱ በሌላው የእምነት ስፍራዎች …ተገቢ ያልሆኑ ተግባራትን መፈጸም› በሚል ርዕስ ኦርቶዶክስና እስልምና በሚል ዘይቤ በማጫፈር በመገናኛ ብዙኃን ላይ ያስተላለፈው መግለጫ ቤተክርስቲያኒቷን እጅግ አሳዝኗል ብሏል፡፡

ሲኖዶስ ከትናንት በስቲያ ባወጣው መግለጫ የህገ ወጦች እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና እየከፋ መጥቶ የባሰ አደጋ ከማስከተሉ በፊት አስቸኳይ የመፍትሄ እርምጃ ይወሰድ ብላለች፡፡ በማያያዝም ከህገመንግስታዊ ድንጋጌና ከኃይማኖታዊ ስነምግባር ውጪ በመንቀሳቀስ አንዳንድ ጸረ ቤተክርስቲያን አክራሪዎች እየፈጸሙት ያለው ተንኮልና ደባ እንዲሁም በሀይማኖት ሽፋን እየተደረገ ያለው ህገወጥ እንቅስቃሴ እያደገ ሲሄድ ቤተክርስቲያኗን ብቻ ሳይሆን የአገሪቱንም ህልውና እስከመፈታተን ደረጃ ሊደርስ የሚችል ስጋት እንደተደቀነ የቤተክርስቲያኗ ሲኖዶስ ስጋቱን ገልጻል፡፡

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች እንዳሉት የኢትዮጵያ ህዝብ በረጅም ጊዜ ታሪኩ ጎሳ ሀይማኖት ሳይል ተቻችሎ የኖረውን ዛሬ ዘመን አመጣሽ ከፋፋዮች ጥላቻና ልዩነትን እየሰበኩ ወደ እልቂት እንዲያመራ እያደረጉት ነው ብለዋል፡፡