በኮለምበስ ኦሃዮና አካባቢው ለምትገኙ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን በሙሉ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በድሃው የኢትዮጵያ ሕዝብ ኑሮ ጠኔ የሚቀልደው የወያኔ አገዛዝ ኢኮኖሚያችን አድጎ ተትረፍርፏል፤ ለጎረቤቶቻችን መትረፍ እንችላለን፤ ከፍተኛ ልማት እያካሄድን ነው እያለ የተለመደውን አፍዝዝ አደንግዝና አሰልች ፕሮፓጋንዳውን በመንዛት ላይ ይገኛል።

የቅርብ ጊዜ ትዝታ የሚሆነን፣ ፀረ-ኢትዮጵያው ወያኔ ትላንት በአደባባይ ያደረጋቸውን ፀረ-ኢትዮጵያ ቅስቀሳዎችና ንግግሮች ወደ ጎን በማስቀመጥ፤ የሕዝን ቀልብ ለመሳብ ብሔራዊ ስሜት ያለው ለመምሰል፤ የአባይን ወንዝ ገድበን በአግባቡ እንዳንጠቀም ግብጽ እንቅፋት ሆናብናለች በሚል ስበብ በማር የተቀባ መርዝ መፈክሩን ያነገቡ ካድሬዎቹን አደራጅቶ በኮለምበስ ኦሃዮና አካባቢው እንዲሁም በሌሎች አሜሪካ ክፍለ-ግዛቶች (ስቴትስ) የሚኖሩትን የዋህ ዜጎቻችንን በማወናበድና በማሳሳት የትራንስፖርትና ሆቴል ወጭዎቻቸውን ከኢትዮጵያ ሕዝብ በተዘረፈው ሃብት በመሸፈን በዋሽንግተን ዲሲ አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጡ ሲያደርግ፤ የግብጽ ተቃውሞ ጉዳይ ደብዛው ጠፍቶ በምትኩ የጠቅላይ ሚኒስትራችንን አመራር እንቀበላለን፤ የ2002 ምርጫ ተክክለኛና ሃቀኛ ነው፤ የዓለም-አቀፍ ሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት (Human Rights Watch) በኢትዮጵያ ላይ የሚያወጣቸውን መግለጫዎች እናወግዛለን በሚሉ መፈክሮች ተተክተው ነበር። ሰሞኑን ደግሞ፤ ከቀረጥ ነፃ የሆኑ ትራክተሮችን፣ የጭነት መኪናዎችንና የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሶችን ታስገባላችሁ በሚሉ ትናንሽ ጥቅማ ጥቅሞች መደለል ይዘዋል። ርሃብ፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግርና ማሕበራዊ ቀውስ በሰፈነባት አገራችን በተጻራሪው “የእድገትና ትራንስፎርሜሽ እቅድ” የሚል አዲስ መፈክር ያነገቡ ክፍተኛ የወያኔ ካድሬዎች ሕዝብን ለሚቀጥለው አምስት ዓመት በአዲስ ስሌትና መልክ ለማደንዘዝ፣ ለማታለልና ለማሳሳት እንዲያችላቸው በኮለምበስ ከተማ ለApril 9, 2011 ከቅኑ 1:00pm በHyatt Regency Hotel, 350 North High Street, Columbus, OH 43215 ስብሰባ ጠርተዋ።

የወቅቱ አካባቢያችን ሁኔታ እንደምናየው፤ የአንባገነኖች የጭቆናና የግፍ አገዛዝ ያንገፈገፈውና ለነፃነትና ለዲሞከራሲያዊ ሥርዓት ለመታገል ቆርጦ የተነሳው የስሜን አፍሪካና የመካከለኛው ምሥራቅ አረብ ሕዝብ ያቀጣጠለው መሬት አንቀጥቅጥ ሕዝባዊ አመጽ አንባገነኖችን እያሽቀነጠረ አውርዶ የታሪክ ትቢያ እያደረጋቸው በአለበት ሰዓት፤ ይኸው ሕዝባዊ አመጽ በቅርብ ቀናት ውስጥ ኢትዮጵያን ማጥለቅለቁ ያማይቀሬ ነው። በዚሁ ምክንያት ፀረ-ኢትዮጵያው ወያኔ የውድቀት ቀናቱን በመቁጠር ላይ ነው። ስለዚህ ከታሪክ ሠሪው ሕዝባችን ጎን ቁመን፤ ታሪክ እንስራ። የወያኔን ከፋፋይ ተልዕኮ በማጋለጥ ሕዝባዊ ቁጣችንን እንግለጽ።

በቅርብ ቀናት የምናወጣውን መግለጫ ተከታተሉ።

ኢትዮጵያ በአንድነቷ ለዘላለም ትኑር!
በኮለምበስ ኦሃዮና አካባቢው የምንገኝ አገር-ወዳድ ኢትዮጵያውያን