በሚያዝያው ምርጫ ወያኔ ኮሮጆ መገልበጥ አያስፈልገውም

ከሁለት ወር በኋላ ለሚደረገው የአከባቢና የማሟያ ምርጫ ወያኔ ካድሬዎች በአዲስ አበባ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች እስከአምስት የሚደርሱ መታወቂያዎችን በመጠቀም ምርጫውን ሂደት ስለሚያዛቡት ኮሮጆ በመገልበጥ የማጭበርበር ድርጊት መፈጸም እንደማያስፈልጋቸው ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ ምንጮቻችን ገለጹ፡፡

ከተለያዩ ክልሎች በመምጣት የአዲስ አበባን መታወቂያ እንዲያገኙ የሚደረጉት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ካድሬዎች ጉዳይ በአንዳንድ የቀበሌ ሃላፊዎች ተቃውሞ ሲገጥማቸው በልዩ ትእዛዝ እንዲያገኙ ስለሚደረግ የምርጫው ውጤት ካሁኑ ታውቋል በማለት ምንጮቻችን ሁኔታውን ይገልጹታል፡፡

ምርጫ ቦርድ ከፍተኛ ህዝባዊ ተሳትፎ ከታየበት ከምርጫ 97 ጋር የሚቀራረብ አሃዝ ያለው ህዝብ መመዝገቡን ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ አስፈላጊ ምርመራዎችን ማድረግ የሚችል አካል ቢኖር ይህን የውንብድና ተግባር ለማጋለጥ ሁኔታዎቹ በግልጽ እንደሚደረስባቸው ጠቁመዋል፡፡