ቅንጅቱን ለአመራሩ ማስረከብ በጅምር ቀረ

በአየለ ጫሚሶ ቡድን አባላት ፍላጎትና ተነሳሽነት ቅንጅትን በወ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ ለሚመራው የስራ አስፈጻሚ አካል የማስረከብ ሂደት በግላዊ አጀንዳዎችና ፍላጎቶች የተነሳ ተቋረጠ፡፡

ተቀባይነት በማጣትና በደጋፊ ድርቅ የተመቱት የአየለ ጫሚሶ ቡድን አባላት ከህብረተሰቡ እየደረሰባቸው የነበረውን ጫናና የፖለቲካ ሚዛኑን በማስላት ከስራ አስፈጻሚው ወኪሎች ጋር ለመወያየት ጥረት አድርገው የነበረ ቢሆንም በተለይ የአየለ ምክትል የሆነው ለገሰ ቢራቱና ጸሃፊው ሳሳሁልህ ከበደ የተለያዩ መደራደሪያዎችን ለመጠየቅ በመሞከራቸው ጉዳዩ በአጭሩ ቀርቷል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቀጣዩን የትግል እንቅስቃሴ በጽናት ይወጣሉ የተባሉ የቅንጅቱ ነባር አባላት በሁሉም ክፍለ ከተሞች ውስጥ አባላትን የማደራጀትና ህጋዊ ፓርቲ በሚመሰረትበት ወቅት ሊከናወኑ በሚገባቸው ተግባራት ላይ በሰፊው እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙ አንድ የአመራር አባል ለዜና አገልግሎቱ ገልጸዋል፡፡