የቅንጅት የላእላይ ም/ቤት ወሳኝ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል

በወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራው የቅንጅት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ቀጣዩን የትግል ሂደት በሚወስኑ ወሳኝ አጀንዳዎች ላይ የላእላይ ም/ቤት ስብሰባውን በአሁኑ ሰአት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በማሟያው የላእላይ ም/ቤት የተካተቱትን የነአቶ ተመስገንን 12 አባላት ጨምሮ 33 የላእላይ ም/ቤት አባላት በወሳኙ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ጉባኤው በቀጣይ የትግል እንቅስቃሴዎች ላይ መወሰድ ያለባቸውን እርምጃዎች አስመልክቶ ከፍተኛ ውሳኔዎችንእንደሚያሳልፍ የሚጠበቅ ሲሆን ከህዝቡ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በመፍጠርና በማስተባበር መከናወን ባለባቸው ድርጅታዊ ስራዎች ላይ እንዲሁም በአዲስ የፓርቲ ስያሜ መንቀሳቀስን አስመልክቶ አቋም እንደሚይዝ ጉባኤው ሊጀመር ሲል በተለይ ለዜና አገልግሎቱ አስተያየታቸውን የሰጡን አንድ የስራ አስፈጻሚ አባል ጠቁመዋል፡፡