አዲስ ፓርቲ የማቋቋም ማመልከቻ ለምርጫ ቦርድ ቀረበ

የቅንጅት የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአዲስ ፓርቲ ለመንቀሳቀስ የሚያስችለውን የፊርማ ማሰባሰቢያ ፈቃድ ለማግኘት በዛሬው እለት ለምርጫ ቦርድ ማመልከቻ አቀረበ፡፡

አመራሩ ባለፈው ሳምንት የላእላይ ም/ቤቱን 33 አባላት በማወያየት አዲስ ፓርቲ የመመስረት ሃላፊነቱን እንደተረከበ የሚታወስ ሲሆን በጉዳዩ ላይ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ያሉ ወኪሎቹን የማነጋገሩን ሂደት በም/ሊቀመንበር ብርቱካን ሚደቅሳ አማካይነት በዚህ ሳምንት መጀመርያ ላይ በአዋሳ ከተማ በማድረግ ውጤታማ ውይይት አካሂዷል፡፡

ምርጫ ቦርድ የቀረበውን ማመልከቻ ከመረመረ በኋላ በነገው እለት የፊርማ ማሰባሰቢያ ፈቃዱን ለመስጠት ቀጠሮ እንደሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡