የቅንጅት ስራ አስፈጻሚ አዲሱን የፓርቲ ስያሜ ነገ ያወጣል

የመስራች አባላት የፊርማ ማሰባሰቢያ ቅጽ ሰነድ እንዲሰጣቸው ምርጫ ቦርድን ቢጠይቁም የምርጫ ቦርድ አዋጁ ከሚያዘው በተለየ መንገድ በቅድሚያ ስያሜውን ይዘው እንዲቀርቡ የታዘዙት የቅንጅት ስራ አስፈጻሚ አባላት በነገው እለት በመሰባሰብ አዲሱን ስያሜ እንደሚወስኑ አንድ የአመራር አባል ለዜና አገልግሎቱ ገለጹ፡፡ ብዙዎች አመራሩ ፈቃዱን ለማግኘት ፈታኝ እንደሚሆንበት ያላቸውን ስጋት በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

ከነገው ውሳኔ በኋላም በወሪ/ት ብርቱካን ሚደቅሳ የሚመራ የልኡካን ቡድን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚያደርገውን አባላቱንና ደጋፊዎቹን የማነጋገር (የማወያት)ሂደት በመቀጠል በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ጎንደርና ሌሎች ክልሎች እንደሚጓዝ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡