የምርጫ ቦርድ ጨዋታ ዛሬም ቀጥሏል

የቀድሞው ቅንጅት አመራሮች አዲስ የፓርቲ ስያሜ በመያዝ የመስራች አባላት ማሰባሰቢያ ፈቃድ ለማኘት ለዛሬ የተቀጠሩ ቢሆንም የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ሰራተኞች ጉዳዩ የሚወሰነው የቦርድ አባላት ተሰብስበው በሚያሳልፉት ውሳኔ ብቻ ነው የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው ተወክለው የሄዱት የአንድነት ፓርቲ ሃላፊዎች ለዜና አገልግሎቱ ገለጹ፡፡

በህጉ መሰረት የፓርቲ ፈቃድ ለመጠየቅ ምርጫ ቦርድ መሄድ የሚያስፈልገው የ1500 መስራች አባላት ፊርማ ከተሰባሰበ፤ ጠቅላላ ጉባኤ ከተጠራ፤ አመራር ከተመረጠና የፓርቲው ፕሮገራምና መተዳደርያ ተያይዞ ለቦርዱ ከቀረበ በኋላ ቢሆንም ፈጽሞ ከህግና ስርአት ውጭ ነገሮች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የቅንጅትን ስያሜ በፍርድ ቤት እናስመልሳለን የሚለው የአቶ አባይነህ ቡድን አጠቃላይ ጉባኤ ለመጥራት የሚያስችለውን ዝግጅት ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል፡፡